የ እስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ከሚያደርጉት ጉዞ እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ ።

የ እስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ በተለይም ወደ ጎንደር እንዲሁም ኦሮሚያ ብሎም ወደ አዲስ አበባ ከሚያደርጉት ጉዞ እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ ። Minilik Salsawi

ሰሞኑን በጎንደር በነበረው ግጭት ሰዎች በመሞታቸውና እንዲሁም በቀጣይ ተከታታይ ቀናት ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዳሉ የሚል መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ማንኛውም የ እስራኤል ዜጋ ወደ ቦታው በተለይም ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ሚካሂድበት አካባቢ እንዳይቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አስጠንቅቋል

በተጨማሪም በኢትዮጵያና ኤርትራ እንዲሁም ኢትዮጵያና ሱዳን ፣ ኬኒያ – ኢትዮጵያ ፣ደቡብ ሱዳን በሚያዋስኑት ደንበሮች አካባቢ 10 ኪሎ ሜትር ወደ ቦታው ማንኛውም የ እስራኤል ዜጋ እንዳይቀረብ መክረዋል። ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎችና ስፍራዎች አካባቢ ማንኛውም እስራኤላዊ ዜጋ ቢገኝ በራሱ ሃላፊነት እንደሆነ የ እስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስተር አስጠንቅቋል።