ኮሎኔል ደመቀን ወደ ማእከላዊ ሊወስዷቸው መሆኑን ተከትሎ ተቃውሞ ተካሄደ ።

ኮሎኔል ደመቀን ወደ ማእከላዊ ሊወስዷቸው መሆኑን ተከትሎ ተቃውሞ ተካሄደ ። #MinilikSalsawi
በጎንደር አሁንም ህዝቡ መንገድ በመዝጋት ላይ ሲሆን የፊደራል ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን መሳሪያ በመተኮስ ላይ ናቸው። ጎንደር የቶክስ እሩምታ ላይ ነች ፒያሳ ሚባለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ መንገዱ ተዘግቷል። ኮሎኔል ደመቀን ወደ ማእከላዊ ሊወስዷቸው መሆኑን ተከትሎ ነው ይህ ተቃውሞ ተካሄደ ።
በጎንደር የወያኔ ጦርና በዐማራ ገበሬዎች መካከል የጦፈ ጦርነት ተጀምሯል ። ዐማሮች ወገኖቻቸውን እንዲደርሱላቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ መንገዶች ተዘግተዋል፡፡ የዐማራ ገበሬዎች እና በወያኔ ሠራዊት መካከል የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ከቦታው ያነጋገርናቸው የዐማራ ተጋዮች በቅርብ እርቀት የሚገኙ የአርማጭሆ፣ የቋራ፣ የደምቢያ፣ እና የጎጃም አካባቢ የታጠቁ ገበሬዎች በአስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጧቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡



