ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም!

በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ ትግል ለማገዝና ለመምራት በእውነተኛ የለውጥ ፈላጊ አመራሮችና አባላቶች በተከፈለና ወደፊትም በሚከፈል መሰዋዕትነት የቆመ ፓርቲ ነው።ይህ ሁሉ የሚሆነው የህዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ ነው። ይህም በመሆኑ በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በአገዛዙ ሥርዓት ላይ የተነሣው ህዝባዊ ተቃውሞ “የእኔ ነው ፣የእኔ” ዓይነት ለአምባገነኑ አገዛዙ የሚመች፣ የለውጥ ፈላጊው አንድ ስንዝር የማያራምድ ባለህበት እርገጥ፣ አሰልቺ ፓለቲካ የእኔን ትውልድ የማይመጥን ፤ከምንም በላይ ደግሞ የአገራችንን ነበራዊ ሁኔት እንደ-መርሳት የሚቆጠር ጭምር ነው። ሰማያዊ ፓርቲ በውስጣዊ ችግሮቹ ለላፋቱ ወራት ታች-ላይ ማላቱ ለማንም ግልፅ ነው።

አሁን ላይ ችግሮቹን ለይቶ ህዝባዊ ትግሉን ለማገዝና ለመምራት ሥራዎቹን እያጠናቀቀ ይገኛል።ከችግሮቹ ወጥቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የፓርቲው ከፍተኛ አመራርና አባላት ያደረጉት በጎ አሰተዋአዖኦ ወደፊት በፓርቲያችን ታሪክ እንደ ማሳያ የሚጠቀስ ነው። በፓርቲያችን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ሲያስጨንቃቸው እና ሲያሳስባቸው የነበረ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ስለ ፓርቲያችን መልካም ዜና የሚሰሙበት ቀን እሩቅ አይደለም ። ከላይ ለገለጽኩት ለመልካሙ ዜና እና ለበጎ ምኞቴ የአመራሩና የአባላቱ ጥረት ታሳቢ በማድረግ ብቻና፣ ብቻ! ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ተነሳውበት ሃሳብ ስመለስ፣ ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም! የሚለው የጽሑፊ መግቢያ፣ ለሰማያዊ ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የሚያገለግል ነው።

ፓርቲያችንም የአገዛዙ ሥርዓት ከምስረታው ጀምሮ ከህዝብ ጎን በመቆም ሲታግልና ሲያትግል እንጂ ለደቂቃም ቢሆን ያደናቀፈበት የትኛው ዓይነት አጋጣሚ የለም፣ወደፊትም አይኖርም። በዚህም መሰረት በአገራችን የሚካሄደው ህዝባዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ፓርቲያችን እንደ-አግባቡ እና አስፈላጊናቱ እውቅና በመስጠት ፣ ህዝብ በራስ ተነሳሽነት የጀመረውን ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ለእራሱ ለባለቤቱ (ለህዝብ) ቅድሚያ መሰጠት አለበት ብዬ አምናለሁ ።ምክንያቱም ጥቅሙ ብዙ ስለሆነ። ፓርቲ ህዝብን እንጂ፣ እንዴት ህዝብ ፓርቲን ይመራል፤ ከሚባለው ሃስተሳሰብ ይሄኛው መንገድ በብዙ መልኩ ይለያል። መንገዱ አይለይም ቢባል እንኳን አሁን ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ታሣቢ መደረገ አለበት። በዚህም መሰረት ፓርቲያችን የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል፣ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ፣ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ፓርቲው በራሱ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ እንደ-ማመላከቻ ሊወስዳቸው ይገባል የሚል (የግል) ምልከታ አለኝ። ምልክታዬን ለሚጋራኝ ይሄን ለማድረግ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ! የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባላት ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ እና የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአግባቡ መርምረው ፤በፓርቲያችን ላይ የተፈጠረውን ብዥታ በማከም ፣ በአገራችን በሁሉም አካባቢ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከፓርቲያችን ፕሮግራም ጋር በተጣጠመ መልኩ የሚያግዝ እና አቅጣጫ የሚያሲዝ ውሳኔ በአስቸኳይ እንደሚያሳልፉ ተስፋ አደርጋለሁ ። የኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

Yidinekachew kebede

4 Comments on “ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም!”

  1. ወንድሚ ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ፓርቲ ኢትዮፒያ ከሚያስፈልጋት ፓርቲዎች አንዱ እንደሆነ ጥርጥር የለውም ለምን ? ብትለኝ ኢትዮፒያን እንደ አገር የተቀበለ ድርጅት ነው ብዪ ስለማምን ኢትዮፒያን እንደ አንድ አገር አድርጎ የተቀበለ ድርጅት ደግሞ የጎጥ የዘረኝነት አስተሳሰብ የለውም :: የሚተማመነው በኢትዮፒያ ህዝብ ነው በጎጥ የሚደራጁ ዘረኞች ከዘራቸው ውጭ ሊላ ነገር አይታያቸውም አገራቸውና ዘራቸውን መለየት አልቻሉም ስለዚህ የሚተማመኑት በባእዳን ሃይል ለዘሮቻቸው ህልውና ማስከበር ብቻ ስለሚሰሩ የሚታማመኑትም በዘር ብቻና ከባእዳን በኢትዮፒያ ስም በሚጎርፍላቸው እርዳታ የሚያስቡት ለዘላለም ዘር እያጠፉ ኢትዮፒያን አጥፍተው የራሳቸውን አገርና መንግስት በወረራ መመስረት ነው ይህ ደግሞ ዛሪ ህወሃት በአምሃራ እና በኦርቶዶክስ የጀመረውን ሃይሉን እያጠናከረ የጎጥ ፖለቲከኞችን እየፐወዘ እየተጠቀመባቸው የነሱንም መቅበሪያ በገዛ እጃቸው እያጠናከረ ከማጥፋት ወደሃላ አይልም:: ምክንያቱም የጎጠኞች ፖለቲካ የሚወሰነው በጎጠኞች ስር ስለሆነ የትግሪ ጎተኛ ፖለቲካ በትግሪ ብቻነው የሚወሰነው የኦሮሞው እንደዛው …….ስለዚህ ትግሪ ትግሪን እንጂ ኢትዮፒያን አይወክልም :: ኢትዮፒያን ከሆነ የምንፈልገው በኢትዮፒያዊነት ተማምነው አንድ ላይ የሚሰሩ በኢትዮፒያዊነታቸው ላይ ብዥታ የሊለባቸው መሆን አለበት ስለዚህ ሰማያዊ አንዱ ሲሆን እንደ ሰማያዊ ደግሞ በኢትዮፒያዊነት ላይ ብዥታ የሊለባቸው ግን የኛ ሃሳብ ኢትዮፒያችንን በዚህ መልኩ እንድታድግ እንፈልጋለን የሚሉ የሃሳብ ልዩነት ያላቸው ጠንካራ ፓርቲዎች ቢኖሩ ሰማያዊም መቀበል አለበት እንደዚህ አይነት ድርጅቶች ሲፈጠሩ በጋራ ከባእዳን ጋር የሚያደርጉትን የፖለቲካ ግንኙነት በአንድ ድምጽ ይወስናሉ ምክንያቱም በአገራቸው ጉዳይ ላይ አንድ ስለሆኑ ከባእዳን ጋር የሚሰራው ፖለቲካ ላይ ግን ሁሉም አንድ ናቸው ለኢትዮፒያ እንደዚህ ነው የሚያስፈልጋት የኢትዮፒያን ህዝቦች ህልውና ለማስጠበቅ የሚሰራው ፖለቲካ ከጎጥ ውጭ መሆን አለበት ጎጠኛና የጎጠኞች ስብስብ መውደም አለበት ሃላ ቀሮች ናቸው :: ወያኒ ሲጀመር በግልጽ የትግሪ ነጻ አውጭ ብሎነው ጫካ የወጣው ስለዚህ የትግሪን ህልውና ለማስከበር ጎጠኞች እንዲደግፉት እሃድግ ብሎ በኢትዮፒያ ስም ያቆመው ለመገንጠል በጋራ ለመስራት ነው በኢትዮፒያ በጣም የሚገርመው ነገር ኢትዮፒያን ለመገነጣጠል የውጭውን ፖለቲካ በአንድ ዘር ውስጥ ጠቅልሎ ሰቶ የትግሪ ነጻ አውጭ ለህልውናው ሲል በኢትዮፒያ ስም የሚደረገውውን ሁሉ ለራሱ ይጠቀምበታል ለዚህ ነው ሊላው ነገድ አገሩን በትግሪ ወራሪ እየተወረረ ኢትዮፒያዊነቱንም ሆነ ማንነቱንም ያጣው ጎጠኞች መሰረት የላቸውም እንደ እንሥሣ ህዝብን እያሰቡ በህዝብ እልቂት የሚነግሱ ናቸው ያ ደግሞ ፖለቲካ አይደለም ፖለቲካ ከጎጥ አልፎ በአገር ደረጃ ህዝብን ለህዝብ በጋራ እንዲሰራ ሃሳብ እንዲካፈል ማድረግ ነው ::

  2. le Telat adrew le shabya yagonebesu-

    1/ ye Ethiopian Hizb aywekilum !!

    2/ Amara yemebal zer yelem yalew prof
    Amaran yeqirta yeteyek !

    3/ye shabyaw wedaj Dr prof kk,,
    weyanen enaswegid sil Amara entekabet ,, malete aydelem !! Amara,,3000 zemen aqrartobinal –

  3. Senu,

    You don’t qualify to be fully referred as human!

    You must be one of the human like beings to be found only in Ethiopia, agents of the killing machine called TPLF.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*