“በጎንደር የወደመው ንብረት ዝርዝር ውጤት በአንድ ብሔር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት መኖሩን አያሳይም” አቶ ንጉሱ ጥላሁን

ሐምሌ አምስት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ሶስት ቀናት በጎንደር ከተማ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በጎንደርና በደባርቅ በደረሰው ንብረት ውድመት በተደረገው ማጣራት በአጠቃላይ በጎንደር የ139 በደባርቅ ደግሞ የሦስት ኢትዮጵያውያን ንብረት በተለያየ ደረጃ መውደሙን የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናገሩ። ይህንን ቁጥር ዘርዝረው በማብራራት ወደ አንድ ብሔር ያደላ ጥቃት እንዳልተፈፀመ ተናግረዋል።

ሐምሌ አምስት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ሶስት ቀናት በጎንደር ከተማ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በጎንደርና በደባርቅ የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ በርካታ ሆቴሎችና መጠኑ ለጊዜው ያልታወቀ ንብረት በቃጠሎ መውደሙንና መዘረፉን መዘገቡ ይታወሳል።

ይህንኑ በተመለከተም በወቅቱ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጥያቄ አቅርበንላቸው ሁኔታው በመጣራት ላይ እንደሆነም ገልፀው ነበር።

ድርጊቱ ከተፈፀም ሃያ ቀናትን ያስቆጠረ በመሆኑ ማጣራት የተደረገበት እንደሆነ ጠይቀናቸው፤ በተደረገው ማጣራት በአጠቃላይ የ16 ሰው ሕይወት ማለፉን፣ 16 ሰው መቁሰሉንና በአጠቃላይ የ139 ኢትዮጵያውያን ንብረት በተለያየ ደረጃ መውደሙን ተናግረዋል። ይህ ቁጥር ወደ አንድ ብሔር ያደላ ጥቃት ያሳይ እንደሆነ ተጠይቀው፤ ምንም እንኳን በስም እየጠሩ መዘርዘሩ ተገቢ ባይሆንም መሬት ላይ ያለው ሐቅ መታወቅ ስላለበት ዝርዝሩን ለመናገር እንደሚገደዱ ገልጸው ፤ ከጠፋው ንብረት ውስጥ የአማራ 85፣ የትግራይ 30 ቀሪው ደግሞ የሌሎች ብሔር ተወላጆች ንብረት መሆኑን የኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተሩ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ የኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁንን አነጋግሮ ያጠናከረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን

5 Comments on ““በጎንደር የወደመው ንብረት ዝርዝር ውጤት በአንድ ብሔር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት መኖሩን አያሳይም” አቶ ንጉሱ ጥላሁን”

  1. Mindinew? Yelelaw behers mekatel alebet? Abesha yale rebsha lela selt yelem malet new? Zeraf eyale yadege hulu! Tifat manen yetekmal? Syria tetekemech? TPLF endehone ende Assad eyatefa yekoyal be hayl kehone. Shulek belo ke Addis Ababa yewetal belachehu new TPLF dengay wurewaro ferto?

  2. ትግራይ ውስጥ አንድ አማራ ወይም ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ነግዶ የሚኖር አለ? መልሱ የለም ነው። ታዲያ ትግሬዎች ሌላው ክልል ሄደው የሌላውን ደም የሚመጡት ለምንድን ነው? አሁንማ ደሙን መጠው ጨርሰው አጥንቱን እየጋጡት ነው። ይህንን በቃ ልንለው ይገባል! ንብረት ወደቀበሌ ትግሬ ወደመቀሌ መሆን አለበት የጊዜው መፈክር!!!!!!

  3. ዐሊ አብዶ እውነትም አብደሃል ቀርበታህ ከሞላ ለማንም ለምንም አታስብም ጭገራም ቢጤ ነህ ሌላው አማራ አልተቀላቀለምና አልተበደለም ለማለት ፈልገህ ከሆነ ተሳስተሃል በስህተት መስራት ለናንተ የቀን ተቀን ጉዳያችሁ ነው ሰለዚህ አፈር።ስለ ሌላው አማራ አለመቀላቀል አይጭነቅህ መላው ኢትዮጵያ ሆ!! ብሎ ሲነሳ የት አባክ እንደምትገባ እናያለን።

  4. Amara yetgrie demeña xelat new blonal tgrie woyanie.
    Ke 42 amet befit jemro be amara lay tgriewoch yezer maxfat tegbar eyakahadu new.
    Ye amaran meriet habtna sra tgrie beworera teqoxaxrotal,
    5 milion amarawech be tgrie woyanie tegelewal. Bzu milion amara tefnaqloal. Habt nebret be tgrie woyanie tezerfual.
    Yihn hulu gf eyefexemubn ke ahun behuala be amara ager xelat tgrie linor aychlm.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*