ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!!
የዐማራ ተጋድሎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው!! የዐማራ ተጋድሎ ታቦር ተራራ አናት ላይ ሆኖ ደብረ ታቦርን እየጠራ ነው፤ ውዶ አሞራገደል፣ አፈረዋናት፣ እብናትና በለሳን፣ ከምከም ቃሮዳን እስከ መልዛ ድረስ ተነስ! ተራመድ እያለ ነው፡፡ አቤት ቅዳሜ የቴዎድሮስ አደባባይን ያየ ሰው?! ጋዜጠኞች ኢየሱስ ተራራ አናት ላይ ሆናችሁ ቅዳሜ ደብረ ታርቦርን ተመልከቱ!!

በአጅባር ሜዳ፣ በቴዎድሮስ አደበባይ የፋርጣ ፈረሶች ጌቶቻቸውን ይዘው ተሸልመው ደምቀው ይውላሉ፡፡ ዐማራነት ይዘከራል! የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል፡፡ጨጪኾ አምባ ላይ ሆኖ ‹‹አምበሳው ጋይንት ኧረ ምነው ዝም አልክ?›› ሲል የዐማራ ተጋድሎ ድምጽ እስከ ተከዜ ወንዝ በርሀ፣ እስከ ጉና ተራራ አናት፣ ወገዳ፣ ሦስቻምና ሙጃ፣ አርብ ገበያ ቤተልሔም ድረስ ተሰምቷል፡፡ ክምር ድንጋይና ጋሳይማ የሐሙስ ወንዝን ገበሬ ይዘው ከመከሩ ከርመዋል፡፡ ሞክሸዎችን ማን ብሏቸው ለዚህማ!!

እስቴ ዴንሳ ተራራ ሥር ያለችው መካነየሱስ ከተማ ጥሪዋን ለእሁድ ካስተላለፈች ሰንብታለች፡፡ ሰባራ ድልድይ ድረስ ከተሰማ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ የባየ ግራር ሜዳ እንዴት እንደናፈቀኝ እኮ!! መቄት ዋድላ ደላንታ ይቀጥላል፤ መርጦ ኢየሱስ ላይ የሚሆን ሰው የዋድላና ደላንታ፣ የየጁን ባላባቶች ድምጽ ከመቻሬ ሜዳ ይሰማል፡፡ ራያ ራዩማ፣ ወሎን በፍቅር ለሚይዘው እንጅ በማንነቱ የሚመጣውንማ መቼም ታግሶ አያውቅም! በወልድያ ሰርጥ አልፎ ቆቦ ማዶ ራያ ይደርሳል! ድምጻችን የወያኔን ዙፋን ያርበደብዳል!

ያች ምድር ያች፤ መርሳ አባ ጌትየን አልፋ ያለችው አዎ ውጫሌ ጣሊያን እንደሸወደኝ ለወያኔማ አልሸወድም እንዳለች ሰምቻለው፡፡ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ የዐማራ ተጋድሎ እየተጣራ ነው፤ ኧረ ሞረሽ እያለ ነው!? ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ ኮምቦልቻ ብትል ሀይቅ፣ ተንታ ብትል አምባሰል ከየትኛውም ቦታ ሁሉ ጥሪያችን ከእኛ አገር ኔት ወርክ ቀድሞ ይነሳል፡፡

(የደብረ ታቦርንና የእስቴን ሰልፍ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ይዤ እቀርባለሁ)
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

ይህ ሁሉ ግን የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

11 Comments on “ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል”

  1. Atnekakachewu atstachewu tene welkayit tewosdo tgrayim layikena. Arif mereja eyederesen new ketlbet wollo ;shewa ………

  2. This is the best calling to strive againest Tplf juntas. “We need freedom more than food” as said Abebe Gelaw

  3. oh ! ! ! you wretched of the earth ! ! ! ! Let me see what you are going to do when the ሱናሜ hits you hard.You have been all silent all these years.

  4. ቀጥሉበት በርቱ አንዲያዉም ግልግል ነው ኢትዮጵያ አንመራለን ብላቹ ግን ኣታስቡ ኢትዮጵያ የምትባል ኣገር ከኣለም ካርታ
    አስወጥዋት አራት ነጥብ
    ኣሁን መሳደብ ትችላላቹ

  5. Biru be 5´000000 Tigre

    95´000000 Ethiopiawi yemetefa yemeslihal ??

    Agases Agame

    GO tigray mekele dedebet !!

    ye Tirgay weyane is cancer for Ethiopia !

  6. እባካችሁ የዘር ፀብ ይቅር አንሰዳደብ አጥፊውን ለይተን እንወቅ ክርክሩ የምሁራኖች ይሁን መሰዳደብ ነውር ነው

  7. hello the people every thing must be done peace fully peace must be our motto. polis, military , federals are selected from us they are our brother’s don’t through stone & such like things .

  8. መቐለ ኸ? ዓድዋ ኸ ? መንደፈራ ኸ? ኣስመራ ኸ? ምጽዋዕ ኸ? ኣማራ ይሆን?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*