ብዙ የትግራይ ተወላጆች የወልቃይትን ጉዳይ በአንድ ክልልየመካለል ፣ ካርታ ላይ መስመር እንደ ማስመር ቀላል ነገርአድርገው ያቀርቡታል
ብዙ የትግራይ ተወላጆች የወልቃይትን ጉዳይ በአንድ ክልል የመካለል ፣ ካርታ ላይ መስመር እንደ ማስመር ቀላል ነገርአድርገውት ያቀርባሉ :: ነገሩ እንደሱ አይደልም እነሱም ልያቀሉት የፈለጉበት ምክንያት ኢትዮጵያ አንድ ነች ወዴትም ቢካለል ችግር የለውም ከሚል ህሳቤ አይደለም ነገሩ ቅኔ ነው።እኛ ግን ወልቃይት አማራ ነው፣ የአማራም ድንበር ተከዜ ነው የምንለው የወያኔን የብሔር ፖለቲካ ለማራገብ ፈልገን አይደለም። ነገር ግን ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲካለል ለምን እንደተፈለገ ጠንቅቀን ሰልምናውቅ ፣ ላለፉት 40 አመታት በዚያ እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ ላይ ምን ደባ ሲካሄድ እንደነበር ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ በአንድ ክልል ከመካለል በላይ በወልቃይት ተወላጆች ላይ በስነ- ልቦናም ፣ በኢኮኖሚም ፣ በማንነትም ላይ ምን እየተደረግ እንዳለ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ለዘመናት በአከባቢው ላይ የሚኖሩ የወልቃይት ተወላጆችን በማፈናቅል ፣ በመግድል ፣ በማሰር ከትግራ ብዙ ሺ ስዎችን በማምጣት በማስፈር የአከባቢውን (ዲሞግራፊ፣ ማለትም የህዝብ አሰፋፈርና አኗኗር) ለመቀየር ጥረት እየተደረ መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናውቀው ፣ በማንኛውም ሰብአው ፍጥሩ ላይ ልደረግ የማይገባው ዜጎች ያለፍላጎታቸው ባልፈለጉት ቋንቋ ባህል እንዲጠቀሙ እየተገደዱ መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ የወልቃይት ሕዝብ በታሪክ የትግራ ክልል (አመራር ስር) ሆኖ እንደማያቅ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው ::
እኛም እንጠይቅ (ይህ ጥያቄ የህወሓት ካድሬዎችን ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት አምናለው ለምትሉ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነው) እናንተስ በኢትዮጵያ አንድነት የምታምኑ ከሆነ አንድ ሕዝብ በፈለገው ክልል የመካለል ፣ የፈለገውን ባህል ለመተግበር፣ ከፈለገውን ቋንቋ መጠቀም ድሞክራሳዊ መብቱ ከሆነ የወልቃይት ሕዝብ የአማራነት ጥያቄ ሲያነሳ ስለምን ይከፋችሁል ፣ ስለምን የህዝቦችን ጥያቄ ለማድበስበስ ትሞክራላችሁ ፣ ስለምን በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥያቄ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ ፣ ስለምን በወልቃይት ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ አታወግዙም ስለምን??? …..
#አቤል
