ከትግራይ ተወላጆች የበሰሉና ታሪክ የሚያወቁ ምን ይላሉ – ግርማ ካሳ

Tigray

ሕወሃቶች የተለያዩ ሰልፎችን እያደረጉ (ካድሬዎቻቸዉን በባስ በመሰብሰብ) ወልቃይት ጠገዴ የትርጋይ ክልል ነው፣ ወልቃይቴው እና ጠገዴውም “ትግሬ” ነው እያሉ ለዘመናት ትግሬ፣ አማራ..ሳይባባል በሰላም እና በፍቅር የሚኖረውን ሕዝብ እየከፋፈሉት ነው።

የወላይት ጠገዴ ህዝብ የፍቅር ተምሳሌት የሆነ ህዝብ ነው። ትግሪኛ ይናገራል. አማርኛ ይናገራል፤ ሲያሻው ሽሬ ፣ ሲያሻው ጎንደር ሄዶ ይነግዳል። በዘር ተለፋፍሎ አያውቅም። ሆኖም እነዚህ ዘረኞች መጡና ሊያበጣብጡት እየሞከሩ ነው።

እስቲ ከትግራይ ወገኖቻችን መካከል የተከበሩና ታሪክ የሚያውቁ ምን ይላሉ

፨ “ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲገባ የተደረገው ወደ ሱዳን መውጫ ለማግኘት ነው”(ዶ.ር አረጋዊ በርኸ)
፨ “የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው” (ልዑል ራሥ መንገሻ ሥዮም)
፨ “የጎንደርና ትግራይ ግዛቶች የሚያዋስነው ተከዜ ወንዝ ነው”(አሰገደ ገ.ስላሴ)
፨ “ወልቃይት ወደ ትግራይ ሲካለል ከሱዳን ጋር ለመገናኘት ስለነበር የህዝብ ፍላጎት አልጠበቀም።በመሆኑም የህዝብ ምርጫ ሊከበር ይገባል”(ግደይ ዘርዓጽዮን)
፨ “የወልቃይት ህዝብ የዘር ማጥፋትና የግዛት ማካለል የተጀመረው በ1970ዎቹ ነው።ህወሓት ወልቃይቶችን ወደ ትግራይ ልትጠቃለሉ ነው ሲሏቸው ህዝቡ እምቢ በማለቱ ከዚያን ግዜ ጀምሮ የኃይል ርምጃ እየተወሰደ ህዝቡም በግድ ትግራዋይ ሆነ”(ገብረ መድህን አርዓያ)
እኛም ብለናል ተጋሩ ውስጥ የህወሓትን የትምክህት ተስፋፊነት የሚኮንኑ ኤሊቶች አሉ።አስተቃቃፊ ህዝባዊ አጀንዳ መቅረጽ የቻልን ቀን ደግሞ ለእውነት የታመኑ ተጋሩዎችን ከጎናችን ማሰለፍ እንችላለን።እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው….ተሰናባች የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች ኳስ በመሬት አድርጉ።ከስሜት ይልቅ ስሌት ይቅደም።