የወያኔ መንግስት እስረኞችን ለማሰቃየት በቃሊቲ እስር ቤት 4 የጨለማ ክፍል እንዳሰራ ታወቀ ።

የወያኔ መንግስት እስረኞችን ለማሰቃየት በቃሊቲ እስር ቤት 4 የጨለማ ክፍል እንዳሰራ ታወቀ ።

የወያኔ መንግስት በእስር ቤት ያሉትን የፖለቲካ እስረኞች ለማሰቃየት በቃሊቲ እስርቤት ውስጥ 4 የጨለማ ክፍሎችን እንዳስገነቡ ምንጮቻችን ዘገቡ ።

ከዚህ በፊት በቃሊቲ እስርቤት ውስጥ ጨለማ ክፍል ስድስተኛ ተብሎ በሚጠራው ቦታ አንድ ብቻ የነበረ እና እሱን አፍርሰው በአሁኑ ሳአት 4 ክፍል በመገንባት በእስረኞቹ ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ለማድረስ በቁርጠኝነት መነሳቱ የሚያሳይ ነው ።

አሁን በአዲስ መልክ የተገነባው የጨለማ ክፍል እያንዳዱ 36 ሰዉ እንደሚያዝ ለማወቅ ተችሎዋል ።

በተያያዘ ዜና በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚደረገው ጫና እንደቀጠለ ሲሆን ከትላንት ጀምሮ ከእናት አባት እና ልጅ ውጭ የትኛውም ዘመድም ሆነ ወገን እንዳይጠይቃቸው እንደተከለከሉ ምንጮቻችን ከስፍራው ዘገቡ ።

መላው ማህበረሰብ በጨቁዋኙ በወያኔ መንግስት ላይ በአንድነት በመነሳት ጭቆናን እንዲታገሉ ጥሪ ቀርቦዋል ።