አንድ ህዝብ አንድ ሀገር! (አብርሃ ደስታ)

አንድ ህዝብ አንድ ሀገር! -አብርሃ ደስታ
=================

ሰው ነፃነት ይፈልጋል። ነፃነት ላለመፈለግ ራሱ ነፃነት ይጠይቃል። ስለዚህ ነፃነቱን የሚቃወም አይኖርም። ምክንያቱም ነፃነትን በራስ መቃወም በራሱ ነፃነት ነው። ሰው ነፃ ለመሆንም ላለመሆንም ነፃ መሆን አለበት። ሰው ነፃ ላለመሆን የመወሰን ነፃነት አለው። ዋናው ጉዳይ ዉሳኔው የራስ መሆን አለበት፤ የሌላ አካል ጣልቃ ገብነት ሊኖረው አይገባም።

ነፃነት የሰው ነው፤ የራሳችን ሃብት ነው። በሌሎች ጣልቃ ገብነት ሊገደብ ግን ይችላል። ስለዚህ ነፃነታትችን ከፈለግን መጠበቅ ይኖርብናል። ነፃነታችንን ለመጠበቅ ፈፃሚ ተቋም ያስፈልጋል። ፈፃሚ ተቋም ወይ ስርዓት የሚኖረው መንግስት ሲኖር ነው። መንግስት የሚኖረው ሀገር ሲኖር ነው። ሀገር የሚኖረው ህዝብ ሲኖር ነው።

የምንፈልገው ነፃ ህዝብ ነው። ነፃ ህዝብ የሚኖረው ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖር ነው። ዴሞክራሲያዊ መንግስት የሚኖረው የዴሞክራሲ ግንዛቤ ያለው ህዝብ ሲኖር ነው። ግንዛቤ ያለው ህዝብ መብቱ ያውቃል፤ መንግስት አገልጋይ እንጂ ጌታ አለመሆኑ ይረዳል።

ባጠቃላይ ህዝብ የስልጣን ባለቤት ሲሆን ዴሞክራሲያዊ መንግስት ይኖራል። እናም ነፃነቱን ያረጋግጣል። ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆነው መንግስትን መቆጣጠር ሲችል ነው። መንግስትን መቆጣጠር ስልጣን መስጠትንና መንጠቅን ይጨምራል።

ህዝብ መንግስትን መቆጣጠር የሚያስችል ዓቅም የሚፈጥረው አንድነት ሲኖረው ነው። ሰለማዊ ህዝብ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በአከባቢ ወዘተ ሳይከፋፈል በአንድነት ሲቆም መንግስትን ይቆጣጠራል። በአንድነት መቆም ማለት የግድ አንድ ዓይነት የፖለቲካ ኣቋም መያዝ አይደለም። የራሱ የመሰለውን አመለካከት ይኖረዋል። የሚወሰነውም በአብዛሃ (አብላጫ) ድምፅ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ነፃ ነው።

ስለዚህ ነፃ ህዝብ እንዲኖረን ነፃ መንግስት ያስፈልጋል። ነፃ መንግስት እንዲኖረን የህዝቦች አንድነት ያስፈልገናል። የህዝቦች አንድነት እንዲኖር የሀገር አንድነት መኖር አለበት። ምክንያቱም የሀገር አንድነት ከሌለ የህዝብ አንድነት አይኖርም። የህዝብ አንድነት ከሌለ የህዝብ ስልጣን አይኖርም። የህዝብ ስልጣን ከሌለ ዴሞክራሲ አይኖርም። ዴሞክራሲ ከሌለ ነፃነት አይኖርም። ነፃነት ከሌለ እኩልነት አይኖርም። እኩልነት ከሌለ ፍትሕ አይኖርም። ፍትሕ ከሌለ የህዝቦች አንድነት አይኖርም። የህዝቦች አንድነት ከሌለ የእርስበርስ ችግር ይኖራል። የእርስበርስ ችግር ሀገርን ያፈርሳል። ሀገር ከፈረሰ ምንም አይኖርም።

ስለዚህ ነፃነት ከፈለግን ሀገር ያስፈልገናል። ሀገር ከፈለግን አንድ ህዝብ (የሚተባበር ህዝብ) ያስፈልገናል። አንድ ህዝብ ከፈለግን ነፃነት ያለው መሆን አለበት። ነፃነት የሌለው ህዝብ ወይ ሀገር አይቆምም። ስለዚህ ሀገር እንዲቆም ነፃነት ያስፈልጋል። ነፃነት እንዲከበር አንድ ሀገር፣ አንድ ህዝብ አስፈላጊ ነው።

ጨቋኝ ገዢዎች ግን የህዝቦችን አንድነት አይፈልጉም። ምክንያቱም ህዝብ አንድ ከሆነ፣ ከተባበረ ከስልጣን ያስወግዳቸዋል። ለዚህም ነው ብዙ ግዜ “የከፋፍለህ ግዛ” ስትራተጂ የሚጠቀሙ። ስለዚህ ነፃነት ፈላጊዎች እንዲያሸንፉና የህዝብና የሀገር አንድነት እንዲጠብቁ የህዝቦችን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር አንስራ። መከፋፈል ለገዢዎች ይጠቅማል።
አዎ! አንድ ህዝብ አንድ ሀገር ለነፃነት።

It is so!!!

9 Comments on “አንድ ህዝብ አንድ ሀገር! (አብርሃ ደስታ)”

  1. One country one people was the slogan of the Derg in general and of Mengistu in particular. Abreha the slogan of the defeated is buried until heaven comes.

  2. አብረሀ ደስታ በመጀመሪያ እንካን በሠላም ለቤተኵ ዐበቃሕ በመቀጠል ይህን ፅሁፍ በትግርኛም ብታቀርበዉ የበለጠ ዐፅንዕትና መልዕክት ለትግራዊ ህዝብም ጥሩና ገላጭም ይሆናል

  3. አንድ ህዝብ አንድ ሀገር! ቅን አስተሳሰብ ውድ እንቁ አብርሃ ደስታ ትክክል እንደ አንተ አይነት ሁለት ሰው ብናገኝ ከጎሳ በሽታ እንፈወስ ነበር አይዞህ በረታ ፈጣሪም ከኢትዮጵያና ከአንተ ጋር ይሁን!

    በላይ

  4. Commenter “Degol” you’re so stupid and dumb; how can you try to associate Mengistu to Abreha Desta? Youre angry TPLF hitmam who is treatned by Gonder Amharas. You’re hiding your ugly face behind Mengistu to discredit and attack Abreha Desra.

  5. ደጎል፡ አህያው አብርሃ ምን ያህል የተማረና በኢትዮያዊነቱ እንደሚኮራ ኣሳየህ አንተ ግን እንደ ጋሪ ፈረስ ወያኔን ብቻ ነው የምታመልከው። ተረጋጋና አደብ ግዛ አገርህን እወቅ።

  6. በላይ says: “… ከጎሳ በሽታ እንፈወስ ነበር …” Ethnicity is natural! it is not a disease my dude! The disease is only in your head. That is why your types are going always in a circle. One people, one language, one culture, one country is the slogan of Mengistu, which could not work in a multi-ethnic country like Ethiopia. Abraha Desta may not have meant that. But if you want that take “Bete-Amhara” and build a wall around you!

  7. For those of you who opposes the articles of Abraha…One country…one people. So what do you need? Tell us how many countries and people you want to establush? Do you know exactly the meaning of country and people? Would you pkease brief us properly instead of saying Derg…Mengistu…what your dumb bosses told yoy? Let us not be parrots friends instead ask and find more information to get knowledge before non sense comments

  8. From Fithawi.
    Look at the greater good. Peace,equality and justice lasts longer and allows everyone to sleep peaceful night for those who rob their neighbors and fellow countries sweat are waken up night with horrible dreams because of the harm they do/did to others. If we care for our family and country we will take the advice of Abraham Festa for the good of all of us and fear of God.

    God bless Ethiopia.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*