ተቃዋሚዎች፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች አሳሳቢ ሆነዋል አሉ

· ኢዴፓ የብሄራዊ እርቅ መድረክ እንዲፈጠር ጠየቀ

የአገሪቱን ወቅታዊ ችግሮች በመጥቀስ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንዳለበት የገለፁት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ችግሮቹ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ሲሉ አስጠነቀቁ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ለፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በፃፈው ደብዳቤ፤ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን ጠቅሶ፤ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲ በማስፈን፣ ለህዝቡ የተረጋጋ ህይወት ማስፈን አልቻለም ብሏል፡፡
በኦሮሚያ የተፈጠረው ግጭትና ተቃውሞ፣ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ላደረሰው ጥፋት እስካሁን ዘላቂ መፍትሄ አለመቀመጡን የጠቀሰው ፓርቲው፤ በአማራ ክልልም በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መነሻነት የተፈጠረው ግጭት በተመሳሳይ መልኩ ለሰው ህይወት መጥፋትና ለብረት መውደም ምክንያት መሆኑ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክ/ከተሞች ህገ ወጥ እየተባሉ ቤቶች በመፍረሳቸው፣ ዜጎች ያለ መጠለያ መቅረታቸውን ያወገዘው መኢአድ፤ ለእነዚህ ወቅታዊ ችግሮች መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ለፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤዎችም ደብዳቤውን እንደላከ ገልጿል፡፡  ፓርቲው እነዚህን በመሳሰሉ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ሲፅፍ መቆየቱን አስታውሶ፤ ለሚፅፋቸው ደብዳቤዎች አንድም ጊዜ ምላሽ እንዳልተሰጠው ይገልፃል፡፡ የአሁኑን ደብዳቤ ለመጨረሻ ጊዜ ለ4ቱ የመንግስት አካላት መላኩን የጠቆመው መኢአድ፤ “ለዚህ ደብዳቤ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፣ በሌላ መንገድ ጥያቄውን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብሏል፤ ለአዲስ አድማስ በሰጠው መግለጫ፡፡
የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮችና ግጭቶች በእጅጉ እያሳሰበኝ ነው ያለው ኢዴፓ በበኩሉ፤ በአስቸኳይ የብሄራዊ እርቅ መድረክ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቧል፡፡
“ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ብሄራዊ እርቅ ወሳኝ ነው” ያለው ኢዴፓ፤ መንግስት ለተቃውሞዎች የሃይል እርምጃ መጠቀሙ ተገቢ እንዳልሆነ ገልፆ፣ ህዝቡም ሀገርን ከሚያፈርስ እንቅስቃሴ እንዲቆጠብና ልዩነቶች በሰላም እንዲንፀባረቁ ጠይቋል፡፡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚተላለፉ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያዎች ልዩነትን ከማራገብ ተቆጥበው፣ ሰላምን ለማምጣት ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም ፓርቲው ጠይቋል፡፡
ቀደም ሲል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ሲያወጣ መቆየቱን የጠቆመው ፓርቲው፤ መንግስት መግለጫዎቹን ቸል በማለቱና የእርምት እርምጃዎች ባለመውሰዱ በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች፣ የሰው ህይወት ከማለፉም ባሻገር ሀገሪቱን ወደ አስከፊ ሁኔታ እየመራት ነው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በበኩሉ፤ መንግስት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ ያላቸውን ቤቶች ያለ አማራጭ ማፍረሱና በክረምት ዜጎችን ለብርድና ለእንግልት መዳረጉ ኢ-ሰብዓዊ እርምጃ ነው በማለት እንደሚያወግዘው አስታውቋል፡፡
በጎንደር የተፈጠረው ችግር ለህዝብ ጥያቄዎች በህገ መንግስቱ አግባብ ፈጥኖ መልስ አለመስጠት ያስከተለው መሆኑን በመግለጫው ጠቅሶ፤ መንግስት ይህን ለመሳሰሉ የህዝብ ጥያቄዎች ፈጥኖ ምላሽ እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡ በክልሉ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት በእጅጉ ማዘኑን የገለፀው መድረክ፤ ነዋሪነታቸው በጎንደር ደባርቅ ከተማ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው ንብረታቸው እንዲወድም መደረጉንም አጥብቆ ኮንኗል፡፡
በተመሳሳይ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፤ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉት ግጭቶች እንደሚያሳስበው የገለፀ ሲሆን የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይም በሰላም እንዲፈታ በአፅንኦት ጠይቋል። በመዲናዋ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች ጉዳይም እንደሚያሳስበውና መንግስት የመጠለያ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚገባ መዐሕድ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

12 Comments on “ተቃዋሚዎች፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች አሳሳቢ ሆነዋል አሉ”

  1. EDPA !!!!! YEMIN ERQ NEW ?????????

    kefelek ante rasih ke weyane Gar temodamod !!

    ante tareq

    ye Ethiopia Hizb beqagn bilowal !!

    ARAT NETIB ::

  2. ገና ዛሬ ነው የሐገሪቱ ጉዳይ ያሳሰባቸው ተቃዋሚዎቹን!!

    ድንቄም ተቃዋሚዎች!!

    ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ቡድን ጋር እየተሞዳሞዳችሁ የወር ደሞዛችሁን ለጥልጡ!! ሆዳችሁን ሙሉ!!

    ለመሆኑ በላፍቶ፣ ሐና ማርያም፣ ወዘተ ከሀምሣ ሺህ በላይ ህዝብ፣ (ህፃናት፣ ነፍሰጡሮች፣ ገና የወለዱ ትኩስ አራሶች፣ የደከሙ አዛውንቶች፣ በአልጋ ላይ ያሉ ሕመምተኞች፣ ወዘተ) በላያቸው ላይ በተደራጁ ፀረ ህዝብ አፍራሽ ቡድኖች በግሬደር ከነዕቃዎቻቸው ጋር በቤታቸው ውስጥ ሲጨፈላለቁ በዚህ ፅሁፋችሁ እንኳን የረሳችኋቸው!!

    እንዴት ለወያኔ ተላላኪ ካድሬዎች በህዝብ ቁጣ ለጠፋ ንብረታቸው እጅግ ተቆርቋሪነታችሁን በግልፅ ደረታችሁን ነፍታችሁ፣ ወገባችሁን ቀስራችሁ ጠንከር ባለ ሁኔታ በፅሁፋችሁ አስመልክታችሁ እንዲህ ስትጠይቁ የሞራላችሁ ዝቅጠት ከጫማ በታች ወርዶ እየተረጋገጠ የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን አጥብቀን እንነግራችኋለን!!

    ለነገሩ መስሚያ ጆሮዎቻችሁ በወያኔ ተቀቅለው ተበልተዋል እና ዕውነትን መስማትም ሆነ ማየት አትፈልጉም!!

    ማፈሪያዎች ናችሁ አርፋችሁ ሆዳችሁን ሙሉ!!

    ድንቄም ተቃዋሚዎች!!

    የተጋጋለውን የህዝብ ትግል ቀልባሾች፣ የወያኔ ምሶሶዎች ናችሁ !!!!

    ኢትዮጵያ አምርረው ለነፃነቷ በሚታገሉላት የተባበሩት ልጆቿ አኩሪ ድልን ትጎናፀፋለች!!

  3. ድንቄም ተቃዋሚዎች!!
    የወያኔ ምሰሶዎች!!
    የተጋጋለውን የህዝብ ትግል ቀልባሾች!!
    ነፃነት የጠማውን ህብረተሰብ አፋኞች!!
    በሆድ ፍቅር የተለከፋችሁ ስግብግቦች !!
    የማትጠግቡ ወያኔ በጥቅም ሸብቦ የሚጋልባችሁ መጋጆች!!

    የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅትን (የዕባቦች ድርጅትን) እንደምሰሶ አቅፈው ደግፈው አጠንክረው እስከአሁን የያዙት በኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ሐገር ያሉ ከርሣም ሆድ አደሮች (የወያኔ የጥቅም ተካፋዮች) ብቻ ናቸው!!

    እነዚህ ባይኖሩ ወያኔ የለም !!

    ፋሺስት ሞሶሎኒ በሐገር በቀል ባንዳዎች(የወያኔ አባቶች/አያቶች) እየተመራ ነው ሃገራችንና ሕዝባችንን ለአምስት አመታት የጨፈጨው!!

    ሐገር በቀል ባንዶች ባይኖሩ ኖሮ ፋሽስት ኢጣሊያን ዕውር ነው!!
    ካለመሪ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር !!

    ውድ እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኖራለች !!!!

  4. የሐያ አምስት አመት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖር እንዴት ከሕብረተሰቡ ጋር እንኳን የተቀራረበ ግንኙነት አይኖራቸውም!!

    እንዴት በእስር ላይ ላሉት እንኳን ተስፋ ለመሆን ጥሏቸው ወደፊት ከቀደማቸው የተቆጣው ሕብረተሰብ ጋር እንኳን መቀራረብና መደባለቅ ትተው ከሕዝብ ሳይገናኙ ብቻቸውን መግለጫ ብቻ በየጊዜው ሲደረደሩ እንሰማለን !!

    እምቢ አሻፈረኝ ነው እያለ ያለው ሕዝቡ !!
    ወያኔን ከዚህ በሁዋላ ለሰላማዊ ሠልፍ ፈቃድ መለመን፣ ለሰላማዊ ድርድር ወያኔን በማመልከቻ መጠየቅ፣ ወዘተ የሚለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ በምንም ተአምር ከወያኔ ጋር አይቻልም !!

    ሕዝብ የጀመረውን ተገቢ የሆነውን ትግል ተቀላቀሉ !! ግንባርቀደም ሁናችሁ ሀሞታችሁን እንደሕዝቡ ኮስተር አድርጋችሁ ቀበቶአችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ እምቢ ለወያኔ በሉና ሕዝቡን ተቀላቀሉት !!

    የመረረ ትግል ነው ለወያኔ የሚያስፈልገው!!

    ሐያ አምስት አመት በላይ የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ ታይቷል እና በቃ !!

    ኢትዮጵያ በተባበሩት ቆራጥ ልጆቿ ትግል ነፃ ትወጣለች !!!!

  5. የሐያ አምስት አመት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖር እንዴት ከሕብረተሰቡ ጋር እንኳን የተቀራረበ ግንኙነት አይኖራቸውም!!

    እንዴት በእስር ላይ ላሉት እንኳን ተስፋ ለመሆን ጥሏቸው ወደፊት ከቀደማቸው የተቆጣው ሕብረተሰብ ጋር እንኳን መቀራረብና መደባለቅ ትተው ከሕዝብ ሳይገናኙ ብቻቸውን መግለጫ ብቻ በየጊዜው ሲደረደሩ እንሰማለን !!

    መላዋ አገራችን ኢትዮጵያ እኮ ጠቅላላ ማሕበረሰቧ የታሰረባት ትልቅ እሥር ቤት ናት!!

    በቃሊቲ፣ ቂሊንጦ፣ ማዕከላዊ፣ ወዘተ ያሉት ወገኖቻችን እኮ የሰቆቃ ጥሪ አያደረጉልን ናቸው ያሉት !!

    በቃኝ ብሎ የተቆጣውና እየተንቀሳቀሰ ያለው ሕዝብ እኮ የወገኖቹ ሰቆቃ በጠባቦቹ እሥር ቤቶች ውስጥ እየሰቀጠጠው እና እረፍት እየነሳው ነው !!

    ሕዝቡ እኮ በታላቋ ሀገሩ በኢትየጵያ ውስጥ በእሥር ላይ እንዳለ ከተቃዋሚዎቹ በተሻለ መንገድ ተረድቶታል !!

    እምቢ አሻፈረኝ ነው እያለ ያለው ሕዝቡ !!

    ወያኔን ከዚህ በሁዋላ ለሰላማዊ ሠልፍ ፈቃድ መለመን፣ ለሰላማዊ ድርድር ወያኔን በማመልከቻ መጠየቅ፣ ወዘተ የሚለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ በምንም ተአምር ከወያኔ ጋር አይቻልም !!

    ሕዝብ የጀመረውን ተገቢ የሆነውን ትግል ተቀላቀሉ !! ግንባርቀደም ሁናችሁ ሀሞታችሁን እንደሕዝቡ ኮስተር አድርጋችሁ ቀበቶአችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ እምቢ ለወያኔ በሉና ሕዝቡን ተቀላቀሉት !!

    የመረረ ትግል ነው ለወያኔ የሚያስፈልገው!!

    ሐያ አምስት አመት በላይ የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ ታይቷል እና በቃ !!

    ኢትዮጵያ በተባበሩት ቆራጥ ልጆቿ ትግል ነፃ ትወጣለች !!!!

  6. ተቃዋሚዎች አሉ እንደ!!ድንቄም ተቃዋሚ !የኢህአዴግ አጋር ድረጅቶች ናቸው !!!”

  7. እወነት ነው እውነተኛ ተቃዋሚዎች ቢኖሩማ የወያኔ የሀያ አምስት አመት ሰይጣናዊ የተግባር ውጤት ያንገፈገፈውን የተቆጣ ሰፊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን ከማቀዝቀዝ ይልቅ ተደባልቀው ይመሩት ነበር!!

    የሕዝብ ቁጣ የሚመራው የተቃዋሚ ፓርቲ በጣም የሚያሳፍር መሰለኝ!!

    ሕዝብን የሚያንቀሳቅስ ፓርቲ እንጂ ሕዝብ ከዕንቅልፉ የሚቀሰቅሰው ፓርቲ በኢትዮጵያችን ብቻ ነው ተከሥቶ ያለው!!

    ለነገሩ ያለፈው የወያኔ ምርጫ 100% የተጠናቀቀ ጊዜ ነው የአለም ሕዝብ ተወዳዳሪ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደሌለ ተገንዝቦ የሰሣቀብን የተሣለቀብን!!

    ወያኔዎችም አጋር ድርጅቶች / ፓርቲዎች አሉ ከእኛ ጋር ተወዳድረዋል ግን እኛኑ መልሰው መርጠውናል ሐሣባቸው ከእኛ ገር አንድ ነው ብለው ወዲ ቴዎድሮስ በአደባባይ ለተጠየቀው ጥያቄ የዘመኑ አስገራሚ እና አስቂኝ መልስ ሰጥቷል!!

    አመሰግናለሁ አሸብር!!

    ኢትዮጵያ በተባበሩት ቆራጥ ታጋይ ልጆቿ ነፃ ትወጣለች!!!!

  8. የክል የሚል ነዉ እየበጠበጠን ያለዉ።ክልል ካልቀር ችግር አለ።

  9. Ye Ethiopia Hizb Be TPLF yetekefafelewn kilil eeyebetatenew ena andnetun eyatenakere new yalew !!

    Kilil malet betigrewoch sibisib bezerenanet lay temerkuzo yetwaqere yeseytan sira new !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*