ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል

ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል

Addis Admass:   የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን ጨምሮ ዋና ዋና የከተማዋ ባለስልጣናት፤ በተለያዩ አካባቢዎች ከሳምንት ባላይ ሳይነሱ ለቆዩት የደረቅ ቆሻሻ ክምችቶች መፍትሄ ለማግኘት በስብሰባ ተወጥረው መሰንበታቸው ተገለፀ፡፡
በጉዳዩ ላይ የአስተዳደሩን ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ከንቲባው ቢሮ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም፤ “ኃላፊዎቹ ከቢሮ ውጪ በኦሮሚያ ክልል በስብሰባ ላይ ናቸው” በሚል ሙከራችን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰንደፋ ከተማ አካባቢ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ የአዲስ አበባ ቆሻሻ እንዳይጣል በአካባቢው አርሶአደሮች መከልከሉን ተከትሎ ከሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋን ቆሻሻ ወደ ስፍራው ወስዶ መጣል አልተቻለም። ይሄን ተከትሎ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች (ዋና ዋና ጎዳናዎችና አደባባዮችን ጨምሮ) የቆሻሻ ክምር ተቆልሎ ሰንብቷል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የከተማዋ አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይትና ድርድር ሳይሳካ መቅረቱ የተገለፀ ቢሆንም ባለስልጣናቱ ትላንት ድረስ በዚሁ ጉዳይ በስብሰባ ላይ እንደነበሩ ከንቲባው ፀሃፊ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከሳምንት በላይ በየአካባቢው ተጠራቅሞ የቆየው የደረቅ ቆሻሻ፤ ነዋሪውን ለከፍተኛ የጤና ችግር እየዳረገው መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በፒያሳ፣ በመርካቶ፣ በአትክልት ተራ፣ በካዛንቺስና ሳሪስ አካባቢዎች ተዘዋውረን ለመመልከት እንደቻልነው፤ የደረቅ ቆሻሻ ክምሩ በየአስፋልቱና በየ ጥጋጥጉ ከመጠን በላይ ተቆልሏል፡፡
ወቅቱ የክረምት ጊዜ በመሆኑም የቆሻሻው እጣቢ በፍሳሽ መልክ በየጎዳናው ሲፈስ ያስተዋልን ሲሆን ይሄም በከተማዋ ከተከሰተው የአተት በሽታ ጋር ተያይዞ ነዋሪውን ለከፍተኛ ስጋት እንደዳረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡
‹‹የአገሪቱ ዋና ከተማና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እየተባለች የምትሞካሸው አዲስ አበባ፤ የቆሻሻ ማከማቻ ሆና መሰንበቷ አስደንጋጭ ነው” ያሉ አንድ ነዋሪ፤ ሁኔታው እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዲስፋፉ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች የተዘጉበትና ህፃናት በየሰፈሩ የሚጫወቱበት ወቅት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል ያሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ፤ በዚህ ከቀጠለ የህፃናቱ ህይወት ለአደጋ መጋለጡ አይቀርም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

9 Comments on “ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል”

  1. ‹‹የአገሪቱ ዋና ከተማና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እየተባለች የምትሞካሸው አዲስ አበባ፤ የቆሻሻ ማከማቻ ሆና መሰንበቷ አስደንጋጭ ነው”

    So, do you believe that Oromos should be your የቆሻሻ ማከማቻ?

  2. SO WHAT? IF THE ADDIS ABEBA CITY ADMINISTRATION BLINDLY CONTINUES SHIPPING THIS TRASH ON OUR LAND; THE COUNTER-ATTACK IS DIFFICULT

  3. እኮ ኣ.ኣበባ ውያኔን የምያክል ቆሻሻ ችላለች
    ሰለዝህ ቅድምያ መሰጠት ያለበት የወያኔ መጣያ ጉርጋድ መሆን ኣለበት።

  4. ይህ እኮ 11% እድገት ነው ምን ትንጫጫላችሁ በሚቀጥለው ደብል ድጂት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም

  5. ታዲያ ሰንዳፋ አከባቢ ያሉ አርሶአደሮች ቆሻሻ ማጣያ ነቸው ያለ ማነው እነሱስ ልጆች የላቸውም? እንዳውም እኔ እንደ አንድ ሰው ለክልሉ አስተዳደር ለማለት የምፈልገው አድስ አበባ እራሷን ትቻል ኦሮሚያ የአድስ አበባን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ልትሆን አይገባም። በአድስ አበባ ቆሻሻ ምክንያት ለምን የአከበቢው አርሶ አደርና ልጆቹ ጤናቸውን ያጣሉ?

  6. የአዲስ አበባ ቆሻሻ ከቤት የሚወጣው ጥራጊ አይደለም ያቆሸሻት የወያኔ የገማ ጭንቅላት ነው ያቆሸሻት አዲሰ አበባ ንፁህ ለማድረግ ለወያኔዎች መቀበሪያ እዚያው አዲሰ አበባ ውስጥ አንዲት ስንዝር ወደ ኦሮምያ ሣይጠጋ መቆፈርና መቅበር ከዚህም አ አበባ ትፀዳለች

  7. የሰንዳፋ የቆሻሻ መጣያ ቦታ የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ውስጥ ተጠቃሎ የነበረ ሲሆን ማስተር ፕላኑ ሳይጸድቅ የአዲስ አበባ መስተዳድር አስቀድሞ 337 ሚሊዮን ብር አውጥቶ ይህንን የቆሻሻ መጣያ ቦታ መገንባቱ የሚገርም ነው::

    ማስተር ፕላኑን ትተናል ካሉ ድርድሩ ለምን አስፈለገ? ማስተር ፕላኑ የሰንዳፋውን ቆሻሻ መጣያ ቦታ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የቆሻሻ መጣያ ቦታዎች በውስጡ አሉት:: የሰንዳፋው ቆሻሻ መጣያ መሰራቱ ጥሩ ነው:: የወያኔ መጣያና መቀበሪያ እናደርገዋለን:: ወያኔ ቆሻሻ ነውና::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*