ከለፈው ስህተት ተምረን የሞተውን ወያኔን ቀብሩን እናፋጥን!!

አሚናት ኢብራሂም፣ ከኖርዌ

(ይህንን መነበብ ያለበት በሳልና ወቅታዊ መጣጥፍ በፒ.ዲ.ኤፍ.ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ከለፈው ስህተት ተምረን የሞተውን ወያኔን ቀብሩን እናፋጥን!!)

ህወሃት ወያኔ ኢትዮጵያን ከመቆጣጠሩ በፊትና ስልጣንም ይዞ በቆየበት ዘመን እስከ 1990 ዓ ም ድረስ ከኤርትራ መንግስት ሻዕቢያ ጋር እጅና ጏንት እንደሆኑ በአንደበታቸው ሳይቀር እየተኩራሩ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ግን እነርሱ እንዳወሩት ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት ወደ ተለያዩ ግጭቶች በመግባት ሰላማዊውን ዜጋ ባልሆነ ተልካሻ ምክንያት ሲያስጨርሱት ከርመዋል። በኤርትራም ይሁን በኢትዮጵያ በኩል ያሉ ህዝቦች እውነተኛ የሆነውን የግጭት መንስኤ አያውቁም። በተለመደ መልኩ በሁለቱም በኩል ያሉት አምባገነን መሪዎች ተመሳሳይ የሆኑ ምክንያቶችን በማቅረብ ህዝብን ሲያደናግሩ ይስተዋላሉ። ወያኔ ካስፈለገው ድንገተኛ ወረራ በሻዕቢያ እንደደረሰበት አድርጎ ያቀርባል። ሻዕቢያም በተራው ወያኔ ጥቃት ሰንዝራብኛለች በማለት ሲከስና ሲካሰሱ ይደመጣሉ።

እነዚህ ሁለት አምባገነን ገዢዎች በሀገራቸው ውስጥ በዜጎች የሚነሱ ማንኛውንም አይነት ጥያቄዎችን የሚመልሱት ጠያቂውን ክፍል የሚገደለውን ገለው የሚታሰረውን አስረው በቃ ለነሱ የህዝብ ጥያቄ የሚመለሰው እንደዚህ ነው። በሁለንተና ባህሪያቸው አንድ ከሚያደርጋቸው ነገር ህዝብን በልተው ሳይጨርሱ መወገድ አለባቸው። ስልጣናቸው ጣኦት የሆነባቸው እነሱ ከተቀመጡበት ወንበር ላለመነሳት ሲሉ የሁለት ሀገር ህዝቦችን በስደት በርሀብ በጦርነት እርስ በርስ በማጋጨት ዛሬም ድረስ እየገዙ አሉ።

ወያኔ አሁን በሀገር ውስጥ ያለውን ትግል እንዳስፈራው የሚያሳየው ከየአቅጣጫው የሚወስደው እርምጃ ትግሉን መጠናከሩን እንጂ ወደሗላ መመለሱን አያሳይም ለዚህም ነው ወያኔ ትግሉ አስፈርቶት በሁሉ ስፍራ አውሬነቱን እያሳየ ያለው ኢትዮጵያዊውም በዚህ ሰአት በሁሉ አቅጣጫ ትግሉን እያፋፋመው መስዋእት እየከፈለ የወያኔን ግብአተ መሬት መድረሱን ተረድቶ እየታገለ ይገኛል ።

እንዲያውም ትግሉ ውጤት ማምጣት ስለጀመረ የሚከፈለውም የመስዋእትነት ዋጋ ይበልጥ እየጨመረ ሄዱዋል። ወያኔም በተጋለጠ ቁጥር ትግሉም በተሻለ ልምድ ባላቸው የትግል ተሞክሮዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊጠቅም በሚችል በሳል አመራሮች ሲመራ ውጤቱ ያማረ ይሆናል። ታዲያ ከእስከዛሬው በተሻለ ኢትዮጵያዊነታችንንና አንድነታችንን በማጠናከር ለትግሉ በቆራጥነት የተዘጋጀን መሆናችንን ማሳየት ይጠበቅብናል። አንድነታችን ምንም አይነት ድንበር ሳይገድበው ማሳየት አለብን። ከዚህም በሁዋላ ወያኔ ለሚያደርስብን ችግሮች እንቅፋት ፈጣን ምላሽ እየሰጠን እንቀጥል እምቢ ለሀገሬ ብለን በድል ጎዳና እንጉዋዝ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት ለነገሰው ወያኔ ህልውናውን የሚፈታተኑት አስከፊ ተግባሮችን እንዲያቆም ስልጣኑንም ለቆ ለፍርድ ለማቅረብ ጊዜው መድረሱን የሚያሳዩ ምልክቶች በዝተዋል። ወያኔ ምርጫ በሚባል ቋንቋ እንደማይወገድ ካወቀ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ነው በሁለገብ ትግል ወያኔን አሽቀንጥሮ ለመጣል የተነሳው። ዘረኞቹ ወያኔዎች ሀገር አውዳሚነታቸው ትውልድ ገዳይነታቸው ሉአላዊነትን አሳልፈው ሰጪነታቸው ህዝቡ ይሄን ጨካኝ ባህሪያቸውን በምርጫ ካርድ እንደማይቆም ከተገነዘበ አመታት አልፈዋል።
ታዲያ ለነፃነታችን እንዲሁም ለሀገራችን ለህዝባችን ካለፈው ትውልድ ጀምሮ አዎ ብዙዎች ታስረዋል እየታሰሩ ነው ግፍና መከራን ተቀብለዋል አሁንም እየተቀበሉ ነው ነገም ለነፃነታቸው እንደሚቀበሉ ይታወቃል። ኢትዮጵያዊው ዛሬ በሀገሩ ላይ ስራ ለመስራት የወያኔ ካድሬ መሆን የግድ እንደሆነ እየተነገረ አለ። ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ አይጠቅምም ስራም ከተቀጠሩ በሁዋላ ወሬ ማቀበልና ማነፍነፍ አለበት። ዘረኛው ወያኔ በዘር ፖለቲካ የተለከፈ በመሆኑ በብሄር ማንነት እንደ አንድ መስፈርት ነው የሚቆጥረው።

ኢትዮጵያዊ ወጣት እንደዚህ በሀገሩ የሚሰደድበት ምክንያት ከምንም በላይ ምክንያቱ ወያኔ ነው። የወያኔ የዘር ፖለቲካ ወጣቱን አማሮታል። ወያኔ ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በመግፈፍ ህዝብን ረግጦ እየገዛ በመሆኑ ህዝቡ በተለይ ወጣቱ ሀገሩን እየጣለ መሰደዱን ተያይዞታል ስደት ግን መፍትሄ ሊሆን አይችልም ስለተሰደድን ወያኔ የሚያደርስብን ግፍና በደል አይቆምም። ወያኔን አሽቀንጥረን በመጣል መገላገል ነው ያለብን ለይስሙላ ሳይሆን ከልባችን ተደራጅተን ወያኔን ማስወገድ አለብን።

ወያኔ ከአንድ ጎሳ የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ቀጥሮ በነፃ ጋዜጣ ስም ራሱ በተቆጣጠረው ሚድያ ሀሰትን እውነት እያስባለ ያስለፈልፋል። ፀረ ወያኔ ሀይሎችን በህዝብ ዘንድ ጥላቻ እንዲኖር ለማድረግ የቁራ ጩኸቱን ይጮሀል። ለብቻው እንደፈለገ የተቆጣጠረውን ሚዲያ ህዝብን ከፋፍሎ ለማዳከም ይጠቀምበታል። ወያኔ በሱ አስተሳሰብ ሀቅና ታሪክ ተዳፍኖ የሚጠፋ ይመስለዋል። ታሪካችንን አስረስቶ ውሸትንም ሀቅ አድርጎ ለማቅረብ ሁሌም ይተጋል ሆኖም ግን ይህንን የወያኔ ሴራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተረዳ ቆይቱዋል የማህበረሰባችንን ውስብስብ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ችግርን ይበልጥ እያወሳሰበ ስልጣኑን ለማራዘም በውሸት ህዝብን ሲያደናብርና ሲያደናግር ግራ ሲያጋባ የነበረው ወያኔ ዛሬ ላይ ግን ኢትዮጵያውያን በእንደዚህ አይነት ቀላል በሆነ ተረት ተረት ማለፍ የሚቻልበት ጊዜ አይደለም። የሀገራችን ዜጋ በታሪኩ ከግፍና ከጭቆና ጋር አብሮ የኖረ ነው ታዲያ ይህ ሆኖ ዛሬ መንፈሰ ጠንካራ ነው ጠላቱን ወያኔን ለመጣል ቆርጥዋል። በኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ፈተናዎችም ከባድና ብዙ ስለሆኑ በሌላ አለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያኖች እገዛ ይፈልጋል።
እናቸንፋለን!

15 Comments on “ከለፈው ስህተት ተምረን የሞተውን ወያኔን ቀብሩን እናፋጥን!!”

  1. አይ የኔ እህት ክማክበር ሰላምታ ጋር ትልቁን ችግር ስተሽዋል።ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት እያለ አዲስ ባንዲራ ይዞ አንገቴን እና ብልቴን በሜጫ ሊቆርጠኝ እየተዘጋጀ ያለ ቡድን ከወያኔ በምን እንደሚለይ ግልጽ አይደለም።ስለዝህም እኔ ወያኔ እኛን ሲቀብር ነው የሚታይኝ። ለማነኛውም Good Luck! ! ! ! !

  2. WARNING ! This guy is either shabia/CIA agent Tesfaye Gebreab or a TPLF cadre using scare tactic ========> ” አፈንዲ ሙተቂ says : July 25, 2016 at 11:47 am

    አይ የኔ እህት ክማክበር ሰላምታ ጋር ትልቁን ችግር ስተሽዋል።ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት እያለ አዲስ ባንዲራ ይዞ አንገቴን እና ብልቴን በሜጫ ሊቆርጠኝ እየተዘጋጀ ያለ ቡድን ከወያኔ በምን እንደሚለይ ግልጽ አይደለም።ስለዝህም እኔ ወያኔ እኛን ሲቀብር ነው የሚታይኝ። ለማነኛውም Good Luck! ! ! ! ! “

  3. The only solution to vanish woyanes from our motherland Ethiopia is unity. Be stand together and let speeded up the death of TPLF. I hope with in two months, TPLF will go to the grave.

  4. የወያኔን ውድቀት ለማፋጠን
    ህዝብን ከትግል የሚያዘናጋ ተጨባጭ ያልሆነ ፕሮፖጋንዳ ከማሰራጨት መቆጠብ።
    ሁሉንም ብሄረሰቦች ያቀፈና በአንድ ወቅት ሁሉም ሰፍራ የሚካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ አመፆችን ማካሄድ
    በወያኔና ቡችሎቹ ተቋማትና ተጠሪዎቻቸው ላይ መዘመትና ማዘመት።
    በተገኘው ሀገራዊና አለማቀፋዊ መድረኮች ላይ የወያኔን ኢዲሞክራሲያዊነት ያለመታከት ማጋለጥ።
    ትግሬዎች እንደቀድሞ ኢትዮዽያዊነታቸውን ከኢትዮዽያ ህዝብ ጋር መቆማቸውን በተቃውሞ ማሰመስከር ወይም በዘር ሀረግ ብቻ ጥቂት ፋሽስቶችን መደገፍ።
    ተጋሩ ፐለቲካ ያረጀባቸውን ሰታንሊስት መሪዎቻቸውን በአስቸኯይ ማሳፈርና ማውረድ።

  5. አማራን እናጥፋ ብለው ሲነሱ፧ አማራ ስላልሆንኩኝ ዝም አልኩኝ፤ ኦሮሞን እናጥፋ ብለው ሲነሱ፧ ኦሮሞ ስላልሆንኩኝ ዝም አልኩኝ፤ ጋምቤላን እናጥፋ ብለው ሲነሱ፧ ጋምቤላ ስላልሆንኩኝ ዝም አልኩኝ፤ አኙዋክን እናጥፋ ብለው ሲነሱ፧ አኙዋክ ስላልሆንኩ ዝም አልኩኝ፤ ኢትዮ ሱማሌን እናጥፋ ብለው ሲነሱ፧ ኢትዮ ሱማሌ ስላልሆንኩኝ ዝም አልኩኝ፤ ሁሉንም በየተራ ካጠፉ በኃላ፡ እኔን ሊያጠፉ ወደ እኔ ሲመጡ ማንም አልነበረም፡፡ ኢግዚአብኄር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተዋሉን ይስጠን። አንገታችንን ቀና የምናደርግበት ቀን እየደረሰ ነው።

  6. ዎያኒ ሲሞት ለመግዛት የአለም ዙሪያ ታዋኪ ሃብታሞች ቸኩለው ባሉበት ጊዚ የወያኒ የገዛ ትዳር አጋሮቻቸው ያላወኩት ሰፍ ዲፖሲት ቦክስ ዳይመንድ ሞልቶታል::

    “ወደ አውሮፓ አማሪካን ቻይና ጅቡቲ እና ማላይሲያ የተላከው የዎያኒ ሃብት በዳይመንድ የተዘረፈ ገንዘብ ኢትዮፕያ ያላትን መሪት በሙሉ ቢያንስ ቢያንስ 5 ጊዚ ደጋግሞ መግዛት የሚችል ሆንዋል ዎያኒ ምን ገዶዋቸው ቢተሩዋቸው የማይሰሙይት ዳይመንዱን እየተማመኑ ነው” ሲሉ ሲፍ ዲፖዚት ቦክስ ያለው ዳይመንድን ውስት አዋኪዎች ተናገሩ::

  7. @Abay
    Pls tell me after that.the neftena time.do not dream no more ethiopia.ethiopia is walk dead.finaly i say RIP and RIP your ethiopia.RIP 10000000 times

  8. ወያኔ ለሌብነቱ፣ ለዘረፋው፣ አምባገነንነቱ፣ አገር ሻጭነቱ፣ ሎሌ ሆኖ እየሰራ እንድመጣና አሁንም እየሰራ እንደሆነ፣ ወዘተ… ሌላ ምስክርና ያልሆነ የውሸት ድሪቶ ሳናክልበት ታውቆ ያደረ በመሆኑ አንዳንዶቻችን ዳያመንዱን ይሁን ሌላው ዘረፋ ላይ አብረን የነበርን እስሚመስል ድረስ እንቶ ፈንቶውን ስንተርክ መዋሉ የሚረባ አይደለም።
    አሁን የሚያስፈልገው እንዴት አድርገን ነው አገራችንንና ህዝቧን በማይጎዳ መልኩ ይህንን ፋሽስታዊ አገዛዝ የምናስወግደው በሚለው ላይ መሥራት ያለብን ይመስለኛል።
    አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን በቻሉት መንገድ ሁሉ ያቅማቸውን እየታገሉ እንደሆነ የምንስተው አይደለም። እኛስ ቢያንስ ከአገዛዙ ራቅ ብለን ሰላምና ዲሞክራሲ በሰፈነበት ቦታ ሆነን እያለ ምነው ከሌላው የበለጠ መሥራት አይጠበቅንም ወይ? ምንድን ነው ያስፈራን? ነገ አገር ቤት ሄጄ መሬት ይሰጡኛልና ይቅርብኝ ነው? ወይስ ሥራ በዝቶብን ማድረግ አልቻልንም ነው?
    ብቻ የምክንያቶች ብዛት እንዳሉ ግልጽ ነው፣ ቢሆንም ታዲያ ሰው በሚችለው ነው ማድረግ የሚጠበቅበት። ቅድሚያ መሰጠት ያለበት የሚመስለኝ መደራጀት ነው፣ ከሚስማማችሁ ድርጅት ይሁን ቡድን ጋር ስብስብ፣ ጉድኝት ፍጠሩ። ከዚያ በኋላ ልትሰሩ በምትችሉበት መስክ የሥራ ድርሻ መቀበልና ትግሉን ማጠናከርና ማጎልበት ነው የሚሻለው።
    በየድረ ገጹ እንደምናደርገው ጦርነት በተግባር አድርገንው ቢሆን እኮ፣ ወያኔ እስካሁን ይህን ያህል ዕድሜ ኖሮት ሊቆይ ባልቻለ ነበር።
    ያም ሆነ ይህ፣ ወጣቱ የነብር ጣቱ እንደሚባለው የነገ አገር ተረካቢዎቹ እናንተ እንደመሆናችሁ መጠን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ላቅ ያለ ድርሻ ይኖራችኋል ባይ ነኝ። ቢያንስ ካለፈው ትውልድ ጥሩ ጥሩ የሞራልና የትግል ቀስሞችን በመውሰድ፣ የጠብና ቁርሾ ፖለቲካውን ወደዚያ አድርጋችሁ እስኪ ለየት ያለ የትግል ስልት በመከተል አገራችሁን አድኑ።
    ይህን ስል እኛም የበኩላችንን ከማድረግ ወደኋላ እንደማንል በማረጋገጥ ነው። ስለ ወያኔ መጥፎነት እየዘረዘርን መዋል ለቀባሪው ማርዳት ነውና የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ የሚያውቀው፣ ዓለም ያወቀው ጨካኝና ጠገብኩ የማይል ድርጅት መሆኑ ሁሉም ያውቀዋል። ባዕዳኖች እንኳን ሊያደርጉት የማይችሉትን ነው በራሳችን ሰዎች እየተፈጸመብን ያለው። ታሪክ ሁሉንም መዝግቦታል።
    አሁን የሚያስፈልገው የጠላትህን ግምት አሳንሰህ መናገር ስህተት ነው። ምክንያቱም አንዳንዶች ወያኔ ሞቷልና እንቅበረው ብለው የጻፉ ተመልክቻለሁ፤ ከሞተ ለመቅበሩ ችግር የለውም። እንደኔ ዕምነት ግን ለመሞት እያጣጣረ ያለ አደገኛ አውሬ ስለሆነ፣ ከመሞቱ በፊት ቆስሎ እንደሚወራጭ አውሬ ግራ ቀኙን ያገኘውን እየጠረገ እንዳያጠፈ ምን ማድረግ ይገባናል ነው ጥያቄው።
    ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በዘር አጥር ተከልለን እርስ በርሳችን ከመናከስ በመቆጠብ በዋናው ጠላታችን ወያኔ አገዛዝ ላይ የኅብረት ክንዳችንን አንስተን በማያዳግም ወደ መጨረሻ ትቢያ መወርወር ይገባናል። ሁላችንም አንዳንድ ድንጋይ መወርወር አለብን።

    ቸር ይግጠመን

  9. woyanene matfat qelal new. Medahnitu ahun bettor tegel lay yaluten begenzeb ena bettor mesariya merdat new. Yetor mesariya mestetu likebd yichilal. Genze makebel gin letewagiwochu sinqena mesariya megzawin yaberakitlachwl. Sinq yemiyasfelgatchew keyebetachew yetefenakelu ena yetemarerum alu. Ensun merdat eko tegelun yatenakeral. Bekiremt, bedeniget letefenakele eko hulum yichelimebetal. Endresilet enji. Betor Tegil lay yalut eko yehen makenaber yichilalu….

    Hulum sew yihen yawqal. Tadiya minew hulum zem bilo lela were yaweral?

    Enberta

  10. የታገሉት ሀብታችንን ዘርፈው ሚሊየነር ለመሆን ከሆነ፤ በወያኔ የተዘረፍነውን ሀብት እኛ የኢትዮጵያ ልጆች ከገቡበት ገብተን ሀብታችንን እናስመልሳለን። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ።

  11. ወያኔዎች ምድራችን ከፈጠረቻቸው ክፉ ፍጡሮቿ የመጨረሻዎቹ አደገኛ የሲዖል ትሎች ናቸው says:

    ለሆድ አደር በሬ ወለደ ጉጅሌ Crazy ass Elias Kifle Ethiopian version of KKK and president of Shengo. Were you son of former Derg colonel as well ? We know your income is going down. Your ER is not making that much since the advent of ESAT. Are you living or surviving ? How is your kiss ass mouth doing? Are you getting some kind of subsidy from woyane now? You have been playing dead for a while and now you are back fabricating news again. People would never forget what you had done before. You better apologize and join the family before it is too late. I think ESAT’s team are gentle. They didn’t pay attention on you at all so far. I hope they will some day. A documentary should be done on you and gangsters like you.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*