ሰበር ዜና ጎንደር ምሽቱን ውጥረት ውስጥ ናት፤ሕዝቡና የህወሓት ደኅንነቶች ተፋጠዋል

ጎንደር ምሽቱን ውጥረት ውስጥ ናት። ሕዝቡና የህወሓት ደኅንነቶች ተፋጠዋል። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የሕዝብ ተወካይና የኮሚቴ አባል የሆኑትን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን በምሽት አፈኖ ለመውሰድ የትግራይ ክልል ደኅንነቶች አንገረብ እስር ቤትን ከበውታል። ሕዝቡ ኮለኔሉ ተላልፈው የሚሰጡት በሬሳችን ላይ ይሆናል እያለ ነው። በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች የተኩስ ድምጽ ይሰማል።