በአዲስ አበባ ሁለት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ህይወታቸውን አጡ

በአዲስ አበባ ሁለት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ህይወታቸውን አጡ ተባለ፡፡ባሳለፍነው ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ኮልፌ ቀራኒዬ ወረዳ 14 አስኮ አዲሱ ሰፈር ከሚገኘው ወንዝ ውስጥ የአንድ የ60 አመት ሰውዬ አስክሬን ተገኝቶ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል፡፡

በዚያው ባሳለፍነወ ቅዳሜ ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ወረዳ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ጀርባ ካለ ወንዝ ውስጥ አንድ የ45 ዓመት ሰውዬ ሞተው ተገኝተዋል፡፡

ዘንድሮ ክረምት ከገባ በጐርፍ አደጋ ብቻ ሰባት ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡