ጎንደር ከተማ በሕወሓት ወታደሮች ተወራለች፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል
ጎንደር ከተማ በሕወሓት ወታደሮች ተወራለች!!የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ የሚኒባስ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን በጀልዱ በጊንጪና አከባቢው ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ነግሷል።ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።
የአማራ ክልል ባለስልጣናት ሕዝቡን ትጥቅ እንዲያስፈቱ በሕወሓት ባለስልጣናት ተወጥረው ተይዘዋል።ጎንደር ስብሰባ የተቀመጠው የብአደን አመራር በሕወሓት አመራሮች እየተሽከረከረ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ሕጋዊ አድርገነዋል ያሉትን የአማራውን ሕዝብ ትጥቅ እንዲፈታ ለማድረግ እየመከሩ እየዘከሩ ይገኛሉ።አማራው ትጥቅ እንደማይፈታ ከወዲሁ እየተናገረ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ አልሳካ ብሎ ትጥቆችን ወደ ሕጋዊነት ማዘዋውር ይሻላል በሚል የአማራው ክልል የሕዝቡን ትጥቅ በሕጋዊነት መዝግቧል።ሕወሓት በአሁን ወቅት የአማራው ሕዝብ የማይታኘክ ስጋ ስለሆነበት እጅግ ድንጋጤ ውስጥ በመግባቱ የአማራ ክልልን በሰራዊቱ ወሮ ይገኛል።ሕዝቡም ጥርሱን እንደነከሰ ነው።
(ለፎቶው ጥራት መጓደል ይቅርታ እንጠይቃለን)
