ኢህአዴግ በወልቃይት ጉዳይ ላይ በቅርብ የሚሰራው የማወናበጃ “ዶኩመንተሪ”
በጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ
ኢህአዴግ ሁሌም ከገጠመው ችግር ተነሰቶ ድርሰት ይፅፋል ፣ ያፅፋል።አዲሱ ዶኩመንተሪ ይህ ነው።
ጎንደርን እንደ ፈረንሳይ
(አኬልዳማ ክፍል 10001)
ደራሲ
ወያኔ
ተዋንያን
ምሁራን( ካድሬ)
እሰረኞች
ነዋሪዎች(አባል የሆኑ )
ኤርትራ (መላከኪያ)
አቅራቢዎች
ኢቲቪ
ፋና
ኢ ዜ አ
ጥብቅ ማሳሰቢያ
ፊልሙን ስለምንደጋግመው አመለጠኝ ብለው አይጨነቁ።ልላው መብራት ሃይል ዋ! መብራት ብታጠፋ።
፠ ፠ ፠
ኢህአዴግ ሁሌም በህዝብ ጥያቄ ላይ እራሱን አያይም።በተለይ ጫወታው የፖለቲካ ከሆነማ በቃ እንዴት ብይ ይህን ጥየቄ ላቆሽሸው ነው ሰራው።እኛ ኢትዮጰያዊያን ኢህአዴግ ላይ ብዙ ጊዜያት ያለን ተቃውሞዎች አሰምተናል።አንድም ጊዜ ትክክለኛ ጥያቄ ነው ተብሎ አናውቅም።ለምን መሰላቹ ደራሲው ለራሱ ነው ሁሌም የሚፅፈው።
ምርጫ ተጭበርብሯል ብሎ ለተነሳ ህዝብ ጥይት እና ሞት ምላሹ።
ኦሮሞ መሬቴን አትንኩብኝ ባለ የኦነግ ተላላኪዎች።
ዳኛ ሀቁን ከፈረደ ተልዕኮ አለው ብሎ መገምገም።
ተማሪ በቃኝ ስዓርቱ ሲል ታቤላ መለጠፋ።
ብዕሩን ባነሳ ጋዜጠኛ ላይ ሰለ እኔ ብቻ ፃፍ።እኔ ብቻ አውቅልሃለው።አልያ ዘብጥያ።
ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ ሲመጣ በገንዘብ ማፈራረስ ፤ ወደ ዘብጥያ መላክ።
የማንነት ጥያቄ ላነሳ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት።
ድህነት እና የመንግ ስትን ግፍ ሸሸቶ ለተሰደደ ሰው በጀምላ ሲያልቅ ደላላ ነው ይህን የሰራው ማለት።
ቆይ እኔ የምለው በራስ ጫማ የሰው እግር መለካት አይከብድም?
እኔ ብቻ አውቅልሃለው እስከ መች?
ሂልተን እና ሸራተን የሚመገብ ባለ ሰልጣን ስለ እኛ
በምግብ ራሳችንን መቻል ማውራት ማንን ያሳምናል?
የራሱን ቤተሰብ ብር ላይ አስቀምጦ ስለ ጉረቤቱ መለውጥ ማውራት ማን እንዲያምን ነው?
በፖለቲካ ተጠቃቅሞ ፣በዘር ዳማ ተጫውቆ ፣ዲሞክራሲን በወረቀት ላይ አስቀምጦ ፣ በአደባባይ ላይ ሰውን ጨፍጭፎ ፣ዘር ከዘር አበላልጦ ፣ ህዝብ የሰጠውን ድምፅ አሽቀንጥሮ ፣ ከእሱ መሰሎች ውጭ ያሉ ሁሉ አሸባሪ ብሎ ፣ደሃን ከሚኖርበት አፈናቅሎ ፣ መከላከያ ሰራዊቱን የህውሃት አድርጎ እንዴት አንባገነት አይደለውም ይባላል።እንዴት ከደርግ የወጣን ህዝብ ላይ ይበልጥ ደርግ ይኮንበታል።
አሁን በወልቃይት ላይ የሚሰራው ዶክመንተሪ የዚሁ ውጤት ነው።ኢህአዴግ የጎንደር ህዝብ በአንድ ላይ መውጣት የሱ ሰራ መሆኑን አያምንም።ይህ ካመነ ፖለቲካው ዳማ ወደቀ።ሰለዚህ ታፔላይ ሰቶታል።ወልቃይት የአማራ ነው ያሉ ከህፃን እስከ ሸማግሌ ያሉ ሁሉ የሻቢያ ቅጥረኛ ናችው።
ሰለዚህም ዶክመንተሪው የወልቃይት ጥያቄ ያነሱት ህዝቡ ሳይሆን የሻቢያ ተላኪዎች ናቸው የሚል ነው።ዶክመንተሪው አሳማኝ እንዲሆን ደራሲው ብልሃት ተጠቅሟል።ታዲያ ይህን የሰራው የሻቢያ ቅጥረኞች ከሆኑ እንዴት ህዝብ ተከተላቸው ለሚል ሰው መልስም አለው።ህዝብ በጎንደር ከተማ ሆ ብሎ የወጣው የተሳሳተ መረጃ እነዚሁ ሰዎች አናዝተው ነው የሚሉ የወያኔ ምስክሮች ይናገራሉ።ሻቢያ ለምን ጎንደሬን መጠቀም እንደፈለገም ብዙ ያወሩልናል።እኔ አውቅላቸዋለው የሚሉ የበአዴን አባል እና አመራሩም ጎንደርን የሸብር ቀጠና ሊያረጉብን ነበር ይላሉ።ይህ ወያኔ የሚመካበት ሰራው ነው።ህዝብን በውሸት ማሳመን።
በተለይ አማራውን ለማሳመን ሰሞኑን ያዝኳቸው ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች ቃሊቲ ድረስ ሆዶ ምስካሪ ያደርጋቸዋል።አዲሱን ገፀ ባህሪ ይሰጧቸዋል።ኤርትራ እንደ ላካቸው አውሩ ይባላሉ።ደራሲው ፊልሙን እዚህ ጋር ነው የሚያሳምረው።ብልታቸውን ላይ ሃይላንድ አሰረው ፣ በኤሌክትሪክ ቶርች እያደረጉ እንዲ በሉ ያሏቸውን ይነግሩናል ግለሰቦች ከመሞት መሰንበት ብለው ይነግሩናል።100 ቦብ ይሰጧቸዋል ፣መሳሪያ በገፍ ከዚያን አስደንጋጭ ታሪክ።ባንክ ቤቶች ፣የገቢያ ሰፍራዎች ፣ቤተ ክርሰቲያናት ልናቃጥል ነበር በሉ ይባላሉ ይሉታል ሞትን ፈርተው።እዚህ ጋር በእነሱ ማንም አይፈርድም ሰቃዪ ያየው ሰው ብቻ ነው የሚያውቀው።ምን አልባትም አንድ ጎንደሬ ይዘው እንዲህ ቢያደርጉት ሳያውቀው ኦሮምኛ ሊናገር ይችላል ከሰቃዪ የተነሳ።
ፊልሙ ላይ ቡዙ ደሞች ያሳዮናል።ሰላም ባስ እና መሰል የተቃጠሉ ነገሮች ይደጋገማሉ።አበል የተከፈለው አባላት ሁላ አሳቢ መሰሎ በካሜራ ውስጥ እንዲ በሉ ተብለው ይነገሩናል ልክ እንደ ተቆርቌሪ።
1/ይህ ትክክለኛ የወልቃይት ጥያቄ ከሆነ ለምን ንብረት ይቃጠላል―――ምናምን።
2/ሻቢያ የእኛ እድገት ለማስቆም ብሎ የፈጠረው ነው።
3/በዚህ ድርጊት የሚሳተፉትን ከመንግስታችን ጎን ሆነን እንዋጋለን።
4/ድርጊቱ እናወግዛለን የሚሉ ህፃን እና አዋቂ።
5/ይህ የሰሩ ለፍርድ ይቅረቡልን ።
በለው ፊልሙ ጦዘ እዚ ጋር።ቤተ መንግስት ቁጭ ብለው ፊልሙን እያየው ደራሲው።ወይኑን አንስቶ
«ና ግጭ ይለዋል ሃይልሻ ደራሲውን»
በቃ የወልቃይተወን ጉዳይ ዳግመኛ እንዳይነሳ ከሽብርተኝነት ጋር ማላከከ ነው የሚሰራው።ህዝብ ፍርሃት ውስጥ መክተት ።እርስ በእራስ እንዳይተማመን ማድረግ።ይህን ዶኩመንተሪ እየጠበቅ ነው እኛ በአሁኑ ሰዓት አንባቢዎቻችን።
ግን እነዚህን ነጥቦች ፊልሙ ቢመልሳቸው ብይ አነሳለው።
አማራ የሻቢያ ተላላኪ ሆኖ ያውቃል?
አማራ ከሻቢያ ጋር ምንም ዝምድና የለውም።ሻቢያን የሚያውቀው ያሰገነጠለው ነው።በአንደበታቸው ሆነ በማንነታቸው ተመሳሳይ የሆኑ።
አማራ በታሪክ ተላላኪ ሆኖስ ያውቃል?
የተላላኪነት ታሪክ የለውም።ህዝቡ ለራሱ እና ለመላው ኢትዮጵያ የኖረ ነው።አማራ ድንገት ተላላኪነት እንኳን ቢለምድ ለሻቢያ አይላላክም።የተላላኪነት ታሪክ ባለቤት የሆነው እራሱን ያውቃል።
ኤርትራ ጎንደር ለሸብር ይመርጣል?
አይመርጥም።ለራሱ ብዙ አጣብቂኝ ውስጥ ነው ያለው።የትኛውም ተቃዋሚ ኢትዮጵያን በሻቢያ ለመቀየር አያሰብም።
ኢህአዴግ ለምን ህዝብ አይሰማም?
ከህዝብ ስህተትን መውሰድ ሽንፈት አድርጎ ሰለሚወስድ ነው።ህዝብ ይንቃል።መሳሪያ መተማመኛው አድርጎል።
ኦህአዴግ እንደ ኤርዶሃን?
ታናሸ እና ታላቅ፤ ከባድ እና ቀላል ናቸው።እንደው አዲስ አበባ እንደ አንካራ አንድ ቀን ብትሆን ብሎ ላሰበ እንደው ይደክምሃል።ኤርዶኽህን ከመፈንቀለ መንግስት ሀገራቸውን ለማትረፍ ምንም ወታደር አላሰፈለጋቸውም።ብቻ ለሚወዳቸው ታላቁ ህዝባቸው አንድ ሚሴጅ ብቻ በቃቸው ።ውጡ ተቃወሙ የሚል።
እንደው ሃይሌማሪያም እየተዝናኑ አዲስ አበባ ላይ መፈንቀለ መንግስት ቢከሰትባቸው ምን ይሆኑ እንደ እኔ።
ገና የሀገሬ ህዝብ ሚሴጁ እንደደረሳቸው ውጡና ተቃወሙ።
እያማጠች ያለች እናት ቆይ አንዴ ብላ
እናቱን እየቀበረ ያለ ልጅ ቆይ አንዴ ብሎ
ባህር ሊሻገር ጣሊያን የደረሰ ኢትዮጵያዊ ፍቱን አዙሮ
ሚሴጁ እንደ ደረሳቸው ኢህአዴግን የገባበት ያሰገቡታል።እንደ ኤርዶሃን ምንም አይነት ነገር ሰርተህም ህዝብ ካልወደደ የድረሱልኝ ጥሪ መጥፊያ ይሆናል።
የዶኩመንተሪ መጨረሻ?
ትግሬን ወደ መቀሌ
ንብረት ወደ ቀበሌ
እንዳሉት ይሆናል።እኛ ግን ከትግሬ ጋር በፍቅር ስንኖር ከወያኔ ጋር ግን በቃን ነው የምንለው።ዶኩመንተሪው እሰክምናቀርብ እነዚህን ዜናዎች እየሰራን ነው ይላል ኢህአዴግ።
ጎንደር ወደ ዕለት ለዕለት እንቅስቃሴዋ ተመለሰች።
አንዳንድ የጎንደር ነዋሪዎች የሰሞኑን እንቅስቃሴ አወገዙ።
የሻቢያ ቅጥረኞችን ላይ መንግስት ተገቢውን እርምዳ ሊወስድ ነው።
ንብረት በማቃጠል ወደ መፍርሄ አይመጣም አሉ አንዳንድ የአዲ ስ አበባ ነዋሪዎች በሰሞኑን የጎንደር ወቅታዊ ሁኔታ።
ወልዋይትን እንደ ጎንደር
ተፈፀመ!
በሌላ የሽብር ጥቃይ እንገናኝ