ቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል የሕመምተኞችን ኩላሊት በመስረቅ ተከሰሰ፤4,590,000 የጉዳት ካሳ ተጠይቋል
የገጠማቸውን ሕመም ለማወቅ ባደረጉት ምርመራ በግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር መኖሩ የተነገራቸው የ37 ዓመት ሴት፣ ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ለማስወገድ በቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የተኙ ቢሆንም፣ ሕክምናው ተደርጎላቸው በሰላም ከተጠናቀቀ ከአራት ዓመታት በኋላ ባደረጉት የአልትራ ሳውንድ ምርመራ የግራ ኩላሊታቸው ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ መውጣቱን በማወቃቸው የፍትሐ ብሔር ክስ መሠረቱ፡፡
ያለፈቃዳቸውና ያለዕውቀታቸው የግራ ኩላሊታቸው መውጣቱን ካረጋገጡ በኋላ ክስ የመሠረቱት የ37 ዓመቷ ወጣት ወ/ሪት ወርቅነሽ ደበላ የሚባሉ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ክሱን የመሠረቱት በቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታልና ቀዶ ጥገናውን አድርገዋል በተባሉት እንግሊዛዊው ሐኪም ፕሮፌሰር ጎርደን ዊሊያም ላይ መሆኑን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጥተኛ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ያቀረቡት የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡ ተጎጂዋ በጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ጓንጉል አማካይነት ያቀረቡት የፍትሐ ብሔር ክስ እንደሚያብራራው፣ በሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. በሚሠሩበት ተቋም ክሊኒክ ተመርምረው፣ በሪፈራል ወደ ቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ተልከዋል፡፡
በሆስፒታሉ የላብራቶሪና የአልትራሳውንድ ምርመራ ታዞላቸው ውጤቱ በሌላ አካላቸው ላይ ውኃ መኖሩንና በግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር እንደሚታይ ተገልጾላቸዋል፡፡ ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ካስወጡ በኦቫሪ ላይ የታየው ውኃ እንደሚጠፋ ተነግሯቸው ወደ ፕሮፌሰሩ መላካቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ፕሮፌሰሩ ድጋሚ ምርመራ አድርገው ጠጠር መኖሩን ካረጋገጡ በኋላ፣ ግለሰቧ አልጋ እንዲይዙ አድርገው ጠጠሩን ለማስወገድ ሌሎች አማራጮች እንዳሉ ሳይገለጹላቸው፣ የኩላሊት ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና አውጥተው ለከሳሿም እንዳሳዩዋቸው ክሱ ይገልጻል፡፡ የስድስት ሳምንታት እረፍትና የተኝቶ ታካሚዎች የምስክር ወረቀት ፈርመው ሰጥዋቸው፣ ታካሚዋ ሐምሌ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሆስፒታሉ እንደወጡም ያክላል፡፡ የሕክምና ተቋሙ ከመሥሪያ ቤታቸው ጋር ባለው የሕክምና ስምምነት መሠረት ከሳሿ በሆስፒታሉ ለተለያዩ ሕክምናዎች ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ ለሌሎች ሕመሞች የሚታዘዙላቸው መድኃኒቶች አልስማማ እንዳላቸው ክሱ ይገልጻል፡፡
በሌላ አካል ላይ ታይቷል የተባለው ውኃ መጥፋት አለመጥፋቱን ለማረጋገጥ ከሦስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም. አልትራሳውንድ ሲነሱ፣ የግራ ኩላሊታቸው እንደማይታይ ባለሙያዎች እንደነገሯቸው ክሱ ይጠቁማል፡፡ ግለሰቧ በባለሙያ የተነገራቸውን ባለማመንና በመደናገጥ ክትትል ወደ ሚያደርጉላቸው የቤተል ሆስፒታል ሠራተኛ ዶክተር ሄደው የተነገራቸውን ሲያስረዷቸው፣ ቀደም ብለው የቀዶ ሕክምና ባደረጉበት ወቅት የነበራቸውን የሕክምና ማስረጃ እንዲያገኙ ነግረዋቸው፣ በብዙ ውጣ ውረድ ማስረጃቸውን ማግኘታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ኩላሊታቸው መኖር አለመኖሩን በድጋሚ በቤተዛታ ሆስፒታል ባደረጉት ምርመራ፣ የግራ ኩላሊታቸው እንደማይታይ ማረጋገጣቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
ነገር ግን ቀደም ብለው በቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ባደረጉት ምርመራ፣ ሁለቱም ኩላሊታቸው እንደነበር በሰነድ መረጋገጡን ክሱ ጠቁሞ፣ በሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ካደረጉ በኋላ ኩላሊታቸው እንዴት ላይታይ እንዳልቻለ ተጎጂ ማብራርያ ጠይቀው፣ ፕሮፌሰሩ ማብራርያ መስጠታቸውንም ክሱ አካቷል፡፡ ፕሮፌሰሩ በሰጡት ማብራርያ ግለሰቧ የቀኝ ኩላሊታቸው ጤነኛ እንደነበርና የግራ ኩላሊታቸው ግን ጠጠር እንደነበረበት መናገራቸው በክሱ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም የግራ ኩላሊታቸው መኮማተሩንና ሌሎችም ምርመራ አክለው ከቀዶ ሕክምና በፊት የታካሚዋ ኩላሊት መወገድ እንዳለበት በመወሰን ማስወገዳቸውን፣ በጽሑፍ ማብራርያ መስጠታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ፕሮፌሰሩ የራሳቸውን ውሳኔ ለታካሚዋ የማሳወቅና የማስፈረም ግዴታ ቢኖርባቸውም አለማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡
ፕሮፌሰሩ ለታካሚዋ በሰጡት የሕክምና ሰርተፊኬት ላይ የጠቀሱት የኩላሊት ጠጠር ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን እንጂ፣ ስለኩላሊቱ መወገድ የጠቀሱት ነገር እንደሌለም ያብራራል፡፡ ፕሮፌሰሩ ማብራርያ ሲሰጡ ከግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር እንዳወጡ የገለጹ ቢሆንም፣ ተኝተው ታክመው ሲወጡ በሰጡት ሰርተፍኬት ላይ ግን ከቀኝ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠሩ እንደወጣ መግለጻቸውንና ይህም የተለያየ መረጃ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡ ግለሰቧ በመጀመርያ ሕክምና ሲያደርጉ ምንም ዓይነት የኩላሊት ሕምም እንደሌለባቸውና ጤነኛ መሆናቸውን የሚያስረዳው ክሱ፣ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸው ከሦስት ዓመታት በላይ ሌላ ሕክምና ሲከታተሉ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና ፕሮፌሰሩ በራሳቸው ውሳኔ አካላቸውን ከሚያሳጧቸው ሊያማክሯቸው፣ ሊስማሙና ሊፈርሙ ይገባ እንደነበር ያክላል፡፡
በአንድ ኩላሊት ሲኖሩ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸው እንደበርም ሊገለጽላቸውና ሙያዊ ምክር ሊደረግላቸው ይገባ እንደነበርም ግለሰቧ በክሱ ገልጸዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በእንግሊዝ በመምህርነትና በሆስፒታል አስተዳዳሪነት መሥራታቸውን፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ፕሮግራሞችን በተለያዩየ የአፍሪካ፣ አውሮፓና ሌሎች አገሮች የጀመሩት እሳቸው መሆናቸው በክሱ ተዘርዝሯል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የእንግሊዝ መንግሥት በሚያስተዳድረው ብሪትሽ ካውንስል አማካይነት መሆኑን ጠቁመው፣ ከፍ ያለ የሥራ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር የተጎጂን ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባቸው ይጠፋቸዋል የሚል ግምት እንደሌላቸው በክሱ ገልጸዋል፡፡
የግራ ኩላሊታቸውን ያወጡትም ሆን ብለው ነው የሚል ግምት እንዳላቸውም አክለዋል፡፡ በመሆኑም ፕሮፌሰሩ የተጎጂን የግራ ኩላሊት ያለፈቃዳቸው በማውጣታቸው ላደረሱት ጉዳት ኃላፊነት እንዳለባቸው በክሱ ገልጸዋል፡፡ ተጎጂዋ የኩላሊታቸው መውጣትን ካወቁ ጀምሮ ከፍተኛ የሥነ ልቦና ችግር እንዳጋጠማቸውም በክሱ አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ቀጥተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት 4,590,000 ብር ተከሳሾች የጉዳት ካሳ እንዲከፍሏቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ግለሰቡ የዳኝነት መክፈል እንደማይችሉ ለፍርድ ቤቱ በማመልከት በደሃ ደንብ እንዲታይላቸው ጠይቀዋል፡፡ ክሱ መታየት ያለበት በደሃ ደንብ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ለመወሰን ቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል መልሱን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ለሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ መጥሪያ ልኮለታል፡፡
No excuse for those heuman. eater the court’s should have justes for that innocent person.they have to get lesson money is not enough.
Oh my God !!
What is the meaning of EDUCATION ??
Where is Professional Value ??
Where is ethical Code for high level educated Professional people ??
Where is human being responsibility ??
I wish all best for Lady ????
Oh my God !!
What is the meaning of EDUCATION ??
Where is Professional Value ??
Where is ethical Code for high level educated Professional people ??
Where is a human being responsibility ??
I wish all the best for Lady ????
ይህ ሆስፒታል ነው ወይስ የዘራፊዎች ስብስብ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ንግድ ከዚህ የበለጠ ምን ሊመጣ ነው?
ከውጭም ሆነ ከውስጥ ሃገር ዜጎች ጋር ተባብር የሰውን ብልት የሚበልቱ ሃኪሞች አይደሉም ሊሆኑም በኢትዮጵያ ሃኪም ማለት ምን ማለት ነው? ሰውን ገድለው ነው ገንዘብ የሚሰበስቡት፣የሚያካብቱት በዚህ ሃገር ውስጥ የዜጎችን ሕይወት የሚነጥቁና የሚያስነጥቁ እስከ አሁን ድረስ ሰንት ሰው ተገደለ የተፋ ሰው ሁሉ መረጃዎችን በጥንቃቄ መሰብስብ አሁን የግድ ይለናል!
ከኢትዮጵያዊያን ጋር የሚተባበሩ የውጭ ሃገር ዜጎች አንዳንዶቹን ለመጥቀስ
1- እስራኤል
2- እንግሊዝ
3- ደቡብ አፍሪካ
4- ግብጽ
5- አሜሪካን
6- ጀርመን
7- ጣሊያን
8- ፈረንሳይ
ፈይሳ
ይህ ሆስፒታል ነው ወይስ የዘራፊዎች ስብስብ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ንግድ ከዚህ የበለጠ ምን ሊመጣ ነው?
ከውጭም ሆነ ከውስጥ ሃገር ዜጎች ጋር ተባብረው የሰውን ብልት የሚበልቱ ሃኪሞች አይደሉም ሊሆኑም አይችሉም በኢትዮጵያ ሃኪም ማለት ምን ማለት ነው? ሰውን ገድለው ነው ገንዘብ የሚሰበስቡት፣የሚያካብቱትን በዚህች ሃገር ውስጥ የዜጎችን ሕይወት የሚነጥቁና የሚያስነጥቁ እስከ አሁን ድረስ ሰንት ሰው ተገደለ የጠፋው ሰው ሁሉ መረጃዎችን በጥንቃቄ መሰብስብ አሁን የግድ ይለናል!
ከኢትዮጵያዊያን ጋር የሚተባበሩ የውጭ ሃገር ዜጎች አንዳንዶቹን ለመጥቀስ
1- እስራኤል
2- እንግሊዝ
3- ደቡብ አፍሪካ
4- ግብጽ
5- አሜሪካን
6- ጀርመን
7- ጣሊያን
8- ፈረንሳይ
ፈይሳ
ወንድሜ ፈይሣ!!
እጅግ በጣም በሚሰቀጥጥ እና በሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ ነው ወገኖቻችን እየኖሩ ያሉት በዛች የሰው በላ ሥርአት በነገሠባት ሃገራችን!!
በትክክል አገላለፅ አስቀምጠህዋል ወንድሜ ፈይሣ!!
እግዚአብሔር ፍርዱን በቶሎ ያውርድላት ለሃገራችን!!
fuck u bitch. u sick motherfucker
I’m gone tear ur ass. dog shit!!!!
and I know ur insulting me right now so I should say the same to you Mr. fuck .
hah see I’m one step further than u
AND I have to answer a math question to post my comment , you primitive fucks u have long way to go before reaching the comparative blog to the developed world . u black asses . dush bag, cock suckers , pussy lick ….
I have been there five years ago. To handle the so called yekulalit teter on my left kidney. The thing (teter) have 0.2 inch size. My beloved doctor nameley dr. Needs told me to drink so much water and it can be washed out with my urine. I have observed some days after I began taking so much water, I observed a crystal thing when I am pissing.thanks to the Almaihty GOD.i have been cured since that time. but after a months I have gone to That Hospital for checkup. And I have taken an ultrasound examination. The examination report says” there is no any sign of nephrolith”. While I am waiting my turn I read the report and googled it on internet with my mobile phone.after some minute the doctor (I think his name is dr. Beniyam)told me I can have a surger if I can pay the deposit from 5000 to 6000. At that time I argued the doctor that the report states there is no any sign of kidney stones. And I have left the hospital(Bethel). The meaning of the name Bethel is house of GOD. But their work is devel’s.
I have been there five years ago. To handle the so called yekulalit teter on my left kidney. The thing (teter) have 0.2 inch size. My beloved doctor nameley dr. Bee’de (በዕደ) told me to drink so much water and it can be washed out with my urine. I have observed some days after I began taking so much water, I observed a crystal thing when I am pissing.thanks to the Almaihty GOD.i have been cured since that time. but after a months I have gone to That Hospital for checkup. And I have taken an ultrasound examination. The examination report says” there is no any sign of nephrolith”. While I am waiting my turn I read the report and googled it on internet with my mobile phone.after some minute the doctor (I think his name is dr. Beniyam)told me I can have a surger if I can pay the deposit from 5000 to 6000. At that time I argued the doctor that the report states there is no any sign of kidney stones. And I have left the hospital(Bethel). The meaning of the name Bethel is house of GOD. But their work is devel’s.
This stupid why do this stupid things this is not dokte this dog
ይህ ሆስፒታል ነፍሰ ገዳይ ነው….የኔዋን ምስኪን ፍቅሬን ያሳጣኝ፣ ልጄን ያለ እናት ያስቀረ ያውም በወለደች በ 3 ወሯ የነጠቀኝ ነፍሰ በላ ሆስፒታል ነው፡፡ ገና የንጹሀን ደም ይፋረደዋል፡፡