ከአውሬ ጋር ትግል

ነፃነት ዘለቀ

(“ኢትዮጵያ ዛሬ”ድረ ገጽ)

ትግል ከሰው ጋር እንጂ ከዐውሬ ጋር ከሆነ አደገኛ ነው። ህወሓት ከጥንስሱ ጀምሮ መቼም ቢሆን በሰዎች ተመርቶ አያውቅም። ይህ ድርጅት ከመነሻው በሰው መሰል አራዊት እንደሚመራ የታወቀ ሆኖ ሳለ ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ ይፈለፈል ይመስል ከዚህ ቡድን መልካም ነገርን የሚጠብቁ ሞኛ ሞኝ ፍጡራን ሲስተዋሉ የሚገርም ነው። እነዚህ የህወሓት ሰዎች የራሳቸው ጠባብ የአስተሳሰብ አድማስ ከፈጠረላቸው የትግሬ ዘር ውጪ ሌላውን ሰው በሰውነት ሊቀበሉ አይፈልጉም።

ከትግሬ ዘር እንኳን ከነሱ ጎጠኛ አመለካከት ባለፈ ሰው ልሁን ብለው የሚፍጨረጨሩ ትግራውያንን ሳይቀር ከማሰርና ከማሰቃየት ብሎም ከመግደል እንደማይመለሱ በቅርብ ከረሸኑት የአረና አባል መረዳት ይቻላል። ይህ ሰሞኑን የገደሉት ኢትዮጵያዊ ትግሬ ለድርጅቱ አራተኛ መስዋዕት ሲሆን አብርሃ ደስታም በእሥር የሚማቅቅ ፀረ-ህወሓት የሆነ ትግራይ በቀል ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። ኢትዮጵያዊነታቸውን ክደው ለጥቅምና ለዘረኝነት ያልተምበረከኩ፣ ከነፃነት ትግሉም ጎን የተሠለፉ ብዙ ተጋሩ መኖራቸውን ማወቅ አለብን። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው።

በዚህች ማለዳ የሰማነው አሳዛኝ ዜና አለ። ይሄውም ሀብታሙ አያሌው ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንዳይሄድ በወያኔው ፍርድ ቤት መጓተቱን ተመርኩዞ ባለቤቱ በድንጋጤ ራሷን ስታ መውደቋ ነው። ይህን ግፍ እግዚአብሔር እየመዘገበው ነው። “ዳኛው አልተገኙም” ብሎ ጣር ላይ በሚገኝ ዜጋ ላይ መቀለድ ከሰው ቢቀር ከፈጣሪ ምን መቅሰፍት ሊያመጣ እንደሚችል እነዚህ ደናቁርት የወያኔ ባለሥልጣናት አልገባቸውም ማለት ነው። በጥይት መግደል – ምክንያት ኖረውም አልኖረውም – “ጀግንነት”ና ለሰውም የመራራት ያህል ነው። በራስ የወደፊት ዕድል ላይም አለመጨከን ማለት ነው። በገዛ የወደፊት ትውልድ ላይም መጥፎ ጠባሳ አለማሰቀመጥ ማለት ነው – በጥቅሉ በእጃችን ውስጥ በሚገኙ ምሥኪን ዜጎች ላይ መጨከንና አለመጨከን በራስ ሕይወት ላይ ሣይቀር ብዙ አንድምታ አለው። እነዚህ የሰይጣን ልጆች ግን በእግዚአብሔር ፍጡር እንዴት እንደሚጫወቱ በአግራሞት እያየን ነው። የነዚህን አጋንንት መጨረሻ የሚያይ የታደለ ነው – በፈጣሪ ፍርድ ብዙ ይማርበታልና። ሬሣቸውን ውሻና ጅብ ሲጫወትበት ይታየኛል። በጣም ክፉዎችና የክፉ ክፉዎች እንደመሆናቸው የፈጣሪ ቅጣት ከዚህ መልስ የሚባል አይሆንም። ከነሱ የበለጠ ዐረመኔ ልኮ ኢትዮጵያን የወረሳትን የጠነባና የከረፋ የማፊያና የአፓርታይድ ሥርዓት እንደሚያጸዳ አለአንዳች ጥርጥር አምናለሁ።

ምድሪቱን በዘረኝነት አረንቋ ስላጨቀዩዋት የእግዚአብሔር ቁጣ ከአፎቱ ሲወጣ በሚፈጠረው መብረቃዊ መቅሰፍት አንድም ወያኔ ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ አይመስለኝም – አያያዛቸው ወደዚህ ዓይነቱ አርማጌዴዎናዊ ኹነት የሚያመራ ነው፤ ምሕረትን ለማያውቅ ፈርዖን የሚታዘዘው ተኩሶ የማይስት ሳዖል ወይም በአህያ መንጋጋ ድባቅ የሚመታ ሦምሶን ነው። ነገረ ሥራቸው ሁሉ “ፈጣሪ ሆይ! አባታችን ዲያብሎስን ለማስደሰት የምንሠራው ግፍና በደል ሁሉ ቋቱን አልሞላ ብሎ ይሆን ወይ እስከዚህ ጨክነህ ዕድሜያችንን በማንዘላዘል አሣራችንን የምታበዛው? ለምን ከዚህ የእሳት ወንበር በቶሎ አንስተህ አትገላግለንም? ለምን ወንጀላችንን ታበዛህ?” እያሉ እግዜር ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት እንዲያስወጣቸው የሚለምኑ ይመስላሉ። እንጂ በነሱው ምክንያት የአልጋ ቁራኛ የሆነን ዜጋ ለህክምና ከሀገር አትወጣም ብሎ መጨከን ቢቻል በምድር ያ ቢቀር በሰማይ የሚያስጠይቅ መሆኑን አጥተውት አይደለም። ዛሬ ባይሆን ነገ፣ ነገም ባይሆን ከነገ ወዲያ እነሱም በተፈጥሮ ወይም በአደጋ ወይም በጦርነት እንደሚሞቱ ማወቅ ነበረባቸው። ሞት ለማንም የማይቀር ርስት ነው። እንደ አጠቃላይ ሕግ ሞትን ማታለልና ማዘግየት ወይም ከነጭራሹ ማስቀረት አይቻልም። ትልቁ ጸሎት መሆን ያለበት አሟሟትን እንዲያሣምርልን ፈጣሪን መለመን ነው – እንደወያኔ ለይቶልን ካልታወርን።

ሰዎች ከሰዎች ጋር ቢታገሉና ቢሸናነፉ ያለ ነው። ኃይለኛው ደካማውን ያሸንፋል። ደካማውም ልባም ከሆነ አሸናፊውን ኃይል በማክበር መሸነፉን አምኖ ይገዛል። ኃይለኛው አሸነፍኩ ብሎ ግፍና በደል ቢፈጽም ለራሱ ዕዳ እያስቀመጠ ነውና ከዚህ መጥፎ ድርጊት መታቀብ ይኖርበታል። ማሸነፍ ብርቁ የሚሆንበት አሸናፊ ኃይል ወደማማው ከወጣ ግን ተሸናፊው መፈጠሩን እስኪራገም የግፍ ጽዋን ይጨልጣል።

በሀገራችን አሁን የምናየው አሸናፊ ማሸነፍ ብርቁ የሆነ ፈሪ ኃይል ነው። ለምን ቢባል የጀግና አሸናፊ ቢሆን ኖሮ ፍቅርና ትዕግስት ተፈጥሯዊ ባሕርያቱ ይሆኑና ታጋሽና በፍቅር የሚያስተዳድር ኃይል ይሆን ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ግን ይህ ኃይል ማሸነፉን እንኳን ለማመን 25 ዓመታት ያልበቁት ገና ጦርነቱን ያልጀመረ ያህል የሚሰማው እጅግ ቦቅቧቃና ጥላውን ሣይቀር የሚጠራጠር ፈሪ ኃይል ሆነና ተቸገርን። እኛ መሸነፋችንን ለመግለጥና ሆዱን ለማራራት ብንሰግድለትም አላምነን አለና ባጎነበስንበት ጦሩን በጀርባችን ይወደውድብን ገባ። ሽንፈታችንን ለማሳመን ምን እናድርግ? የፈሪ አሸናፊ ለጠላትም አይስጥ። መከራ ነው።

ይህን ዓይነቱን ጠላት ለመርታት ልዩ ሥልት መቀየስ ሲገባ በሰላማዊ መንገድ ታግዬ እጥለዋለሁ የሚሉትን የጅሎች ፈሊጥ መከተል ተራ በተራ ግን በሂደት ሁሉንም ታጋይ ለሽንፈትና ለሥልታዊ ዕልቂት የሚዳርግ ነው። ይህንን እውነት ደግሞ ባለፉት ከ40 የማያንሱ ዓመታት ውስጥ በተግባር አረጋግጠናል።

በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚመከርና በሁሉም ረገድ የሚታገዝ ወያኔን የመሰለ ኃይል እንዴትና እነማንን ማጥፋት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህም ሰዎችን ብቻ ሣይሆን ተቋማትንና ተስፋን ራሱን ጭምር ድምጥማጣቸውን ማጥፋት ዋና ዓላማው ነው። የኢትዮጵያ አንድነት አንዱ ምሰሶ የነበረውን የዐማራን ብሔር ከመነሻው ጀምሮ እንደሚያጠፋው በፕሮግራም ቀርፆ ለመሰሎቹ ሲሰብክላቸውና ሲታገል የነበረው፣ ለተግባራዊነቱም ላለፉት 40 ዓመታት ሲታክት የቆየው በተጨማሪም የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ድራሹን ለማጥፋት በካህን መሣይ ጳጳሣትና ኤጲስ ቆጶሣት ተጋዳላዮቹ ቤተ አምልኮውን ወርሮ ኦና ማስቀረቱ፣ ምዕመናኑንም ለቀበሮና ለተኩላዎች ማስረከቡ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ትልቁ ግብ አካል እንደነበር ተደጋግሞ የተነገረ ነው – የገባውና የነቃ አካል ተገኝቶ ይህን ሸውራራ ጉዞ ለመግታት ባይቻልም ሃቁ ይሄው ነው።

ሌላው የወያኔ ጥቃት ሰለባ ደግሞ ተስፋ ነው። ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው። አንድ ሰው ተስፋ ሲያጣ ነው መሞት የሚጀምረው። ፈረንጆች The last thing to lose is hope የሚሉት ወደው አይደለም። ልትሞት ደቂቃዎች ቀርተው በጠና ታመህ ሳለ በተስፋ ድነህ ያጣሃውን ነገር ሁሉ ስታገኝ የምታየው በተስፋ ነው። ቤሣ ቤስቲን አጥተህ በመደህየትህ የማዘጋጃ ቤት ቱቦ ሥር እያደርክ ሳለ ነገ ከብረህ ቪታራና ቪ8 መኪና ይዘህ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ስትዘማነን የምታየው በተስፋ ነው። ልጅ የማትወልጅ መካን መሆንሽ በሀኪሞች ተነግሮሽ ሳለ አንድ ቀን እግዜር ብሎልሽ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ አድርገሽ ስሜቱ የጎፈነነውን ባልሽን አስደስተሸ በአዲስ መልክ ከባልሽ ጋር የፍቅር ቄጤማ እንደምትቀነጥሽ የምታልሚው በተስፋ ነው። ተስፋ ብዙ ነገር ነው። ከመኖር ወዳለመኖር የሚመልስ ዋና የሕይወት ቅመም ነው። ለዚህም ነው ሰው ተስፋ ካጣ ሁሉንም ነገረ እንዳጣ የሚቆጠረው። ለዚህም ነው ሰው ተስፋ ሲያጣ መሰቀያ ገመዱን ይዞ ወደሚቀርበው ዛፍ በመሮጥ የሚንጠለጠለው ወይም ወዳንዱ ፎቅ ወጥቶ የሚፈጠፈጠው ወይም ብልቃጥ መርዙን ጨልጦ ባዶነት ከወረሰው የቀቢፀ ተስፋ ዓለም የሚገላገለው። የተስፋ ወርድና ቁመት በሦስት ሆሄያት ይወሰን እንጂ ትርጓሜው ጥልቅና የዓለማችን ኑባሬ ዓይነተኛው ግብኣት ነው። ካለ ተስፋ ቢዋል አይታደርም ወይም ቢታደር አይዋልም። እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር የሕይወት ቋሚ ምሰሦና ወጋግራ መሆናቸው የሚነገረውም ለዚህ ነው።

ወያኔዎችና ላኪዎቻቻው ይህንን እውነት በደንብ ይረዳሉ። የገጠመን ጠላት ቀላል አይደለም። ያለህን ማናቸውንም ነገር ቀምቶ ባዶ የሚያስቀር ከባድ ጠላት ነው ከጥልቁ የእሳት ባሕር ወደምድራችን የተላከብን፤ ግን አላወቅነውም። ሁሉን ነገር ተቀምተን ከተስፋ ጋር እንኳን እንዳንኖር እያደረጉን ነው። ታች አምና አንዳርጋቸውን ለመጥለፍ ያን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈሉት – ያው የኛው ሀብትና ንብረት ቢሆንም – አንድን የሕዝብ ተስፋ ለማንጠፍ ነው። ሀብታሙን የሚያጠፉት ተስፋችንን ለማጥፋት ነው። ፕሮፌሰር ዐሥራትንና ሌሎች ዕንቁ ዜጎቻችንን የገደሉብን ተስፋችንን ለማጨለም ነው፤ እሥር ቤቶችን በተስፋዎቻችን የሞሉት ተስፋችንን ለማደብዘዝና በሂደትም ለመግደል ነው። ይህን አባባል ልብ በል፡- “ከጓደኞቿ ወጣ ያለች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ”። አዎ፣ ሁላችንም በግ ሆነን “ባባእ” እያልን እነሱ እንዳደረጉን ከሆን ለተወሰነ ጊዜ ይታገሱን ይሆናል፤ “አይ፣ አገዛዛችሁን በቅጡ አድርጉት፤ ለሰሚ ሣይቀር የሚሰቀጥጠውን ግፍና በደል መፈጸማችሁን አቁማችሁ በወጉ አስተዳድሩን። ግዴለም በለስ ቀንቷችኋልና የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ባህል ኖሮን ባንመርጣችሁም መግዛቱን ግዙ – ግን ሁለመናችሁን አሳውራችሁ የለየላችሁ ዘረኞችና ነፍሰ በላዎች አትሁኑ። ሀገሪቱ የሁላችንም ናት፤ ደግሞም ጠባይ ካለን ለሁላችንም ትበቃናለች….” ብለህ ሃሳብና ምክር የምትሰጥ ከሆነ ከጓደኞችህ በልጠህ ነቅተሃልና ለወፍ ወይ ለወንጭፍ ትዳረጋለሁ። ስለዚህ አንተም በዚህ አባባልህ የወደፊት የሕዝብ አለኝታና የነገ ተስፋ ነህና የሕዝብን ተስፋ ለማቀጨጭ ሲባል ጭዳ ትሆናለህ። ደናቁርቱ ወያኔዎች ያልገባቸውና የማይገባቸው ትልቅ ነገር ደግሞ በሠይፍ የሰው አንገት የሚቀነጥሱ የነሱም አንገት በሠይፍ የሚቀነጠስ መሆኑን ነው – “የሰው በልቶ አያድሩም ተኝቶ” ይባላል።

ነገር ግን ይህን ልብ በል! መግደል መቼም ቢሆን መፍትሔ አምጥቶ አያውቅም። ለተወሰነ ጊዜ እውነተኛ ሰላም የሌለበት እፎይታ ያመጣ እንደሆነ እንጂ መግደል ዘላቂ ሰላምን ያመጣበት ሁኔታ እስካሁን የለም – መግደል መግደልን ይተካልና። ፍቅርና መተዛዘን ግን የሚተካው ሌላ ፍቅርንና መተዛዘንን ስለሆነ የዘላቂ መፍትሔ ዋና መሠረት መሆኑ አይካድም።

ወያኔዎች ግን ሥጋና ጅማታቸው ከምን ተበጅቶ ይሆን እንዲህ በግድያ የሚደሰቱት? የአንጎላቸው ሥሪት ከምን ይሆን? እርግጥ ነው እነዚህን መሰል ወንጀለኞች የኤክስና ዋይ ክሮሞሶሞቻቸው ተፈጥሯዊ ስብጥርና ውህደት በተገቢው መንገድ ያልተሰደረና ባሕርያቸው ለወንጀለኝነት የቀረበ እንደሆነ አንብቤያለሁ፤ የሚገርመኝ ግን ይህ ሁሉ የወያኔ ጀሌ እንዴት አንድ ዓይነት ተፈጥሯዊ ግድፈት (ደፊሸንሲ) ሊኖርበትና ግም ለግም ተያይዞ ሊያዘግም እንደቻለ መረዳት ያቃተኝ መሆኔ ነው። በአመራርም በተመሪም ቦታ የሚገኙ ብዙዎቹ ወያኔዎች ከሕጻንነት ጀምሮ የተሰበኩበትና አእምሯቸውን ያንሻፈፉበት አንዳች ጠማማ ስብከት እንዳለ አምናለሁ። ግን ያ መርዘኛ ስብከትና ሥነ ልቦናዊ ጥመት በማኅበራዊ ተራክቦና በጊዜ ሂደት ሊሰክን ያልቻለው ለምን ይሆን? ብዬ ብዙውን ጊዜ እጨነቅላቸዋለሁ። ለተበዳይ ብቻ ሣይሆን ለበዳይም መጨነቅ ይገባል – እርሱም ከተበዳዩ ባልተናነሰ ያሳዝናልና፤ ሰው መቼም ወዶ አይደለም ሰውን ከመሬት ተነስቶ የሚገድለው ወይም የሚያሰቃየው። በሌላ በኩል ደግሞ ጥቂት የማይባሉ ትግሬ ወንድምና እህቶቻችን ይህን ያህል የለወጣቸው ቀደም ሲል ሌሎቻችን ምን በደልና ጥፋት አድርሰን ይሆን? ብዬም አስባለሁ። በርግጥ ይህን ያህል ሊያስቀይማቸውና በኛ ላይ ክፉ እንዲሆኑ ያስቻለ በደል ፈጽመን ከሆነ እናስታውስና ይቅርታ እንጠይቅ፤ ከዚያም ይቅር ተባብለን ይህን አስጠሊታ ታሪክ እንለውጠው። ይቻላልም። በዚህ ጉዞ ግን የትም አንደርም።

ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት ተስፋም ይገደላል፤ ተስፋም ይሞታል። ተስፋ ሲገደል ሕዝብ አንገቱን ይደፋል። ተስፋ ሲያንሠራራ ሕዝብ አንገቱን ቀና ያደርጋል። አንገቱን ቀና ያደረገ ሕዝብ ለአገዛዝ አይመችም። ለአገዛዝ የማያመች ሕዝብ ውስጡ ተስፋ ያረገዘ እንደሆነ መገመት አይከብድም። የሕዝብ እውነተኛ ተስፋ መሆን ደግሞ ብፁዕነት ነው። ከብዙ ትንንሽ ተስፋዎች ደግሞ አንድ ትልቅ ተስፋ የተሻለ ነው። በብዙ ትንንሽ ተስፋዎች ውስጥ ብዙ ሣንካዎች ሊኖሩና ተስፋን ወደ ቀቢፀ ተስፋነት ሊለውጡ እንደሚችሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። የብዙ ተስፋዎች የጋራ ሕልም በብዙ የተናጠል ምኞቶችና የማይቀራረቡ ፍላጎቶች ምክንያት ሊጨነግፍ እንደሚችልም መረዳት ብልህነት ነው። ስለዚህ ተስፋን ከተስፋነት ወደ እውንነት ለማሸጋገር ብዙ ትግል አለ። በዋናነት ግን ብዙ ተስፋዎችን ወደአንድ የተማከለ ተስፋነት መለወጥ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆን ይርበታል። በብዙ ኩይሣዎች ሥር ብዙ የምሥጥ ነገሥታት አሉ። በብዙ ተስፋ ፈንጣቂ ንቅናቄዎችና ማኅበራዊ ስብስቦች ውስጥም ብዙ ፕሬዝደንቶች አሉ።… ችግር ነው። …

ለመሆኑ በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሕዝብ ተስፋ ልትሆኑ የምትችሉ ሻማ ልጆቻችን ወዴት አላችሁ? ተስፋነታችሁስ እስከመቼ ነው? ልብ አድርጉ፣ ተስፋ እንደማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር ይጸነሳል፤ ይወለዳል፤ ያድጋል፤ እንደየሁኔታውም ታሞ ወይም በድንገተኛ አደጋ ይሞታል። የጫጫ ተስፋን ለማዳን ከባድ የመሆኑን ያህል የተወለደ ተስፋን ተንከባክቦ በማሳደግ ለፍሬ ማብቃትም አስቸጋሪ ነው። ሁሉ ነገር ለጊዜ ተገዢ መሆኑን ልብ ማለትም ተገቢ ነው። ሕዝብ ባህር ነው፤ ሕዝብ ሁሉን ያውቃል። ሕዝብን ዝም ማሰኘት እንጂ እንዳያስብና እንዳያውቅ ማድረግ ግን አይቻልም። ሕዝብ ሆን ብሎ ይታለላል እንጂ ባለማወቅ ተጭበርብሮ አያውቅም። ሕዝብ ዕድሉን ካገኘ አገርን አፍርሶ መገንባት የሚያስችል እምቅ ኃይል አለው። ሕዝብን ንቆ መጓዝ የት እንደሚያደርስ ለማወቅ ቀ.ኃ.ሥንና ደርግን ማስታወስ ብቻ ይበቃል።

በነገራችን ላይ የአቶ አሰፋ ጫቦን “ትቼው ረስቼው” ክፍል አንድ መጣጥፍ ካነበብኩ ወዲህ እነፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ነፍሴ ተፀየፈቻቸውና እንዴት ሊያስጠሉኝ እንደጀመሩ አትጠይቁኝ። የሥልጣን ሱስና ፍቅር እንዲህ ያደርጋል? በስማም!!!! ሀገራችን እንዴቱን ያህል ተረግማለች እባካችሁን?

10 Comments on “ከአውሬ ጋር ትግል”

  1. በተለይ ዬጎንደር ኣማራና ትግራይ ምን ልዩነት ኣሎው ብላችሁ ነው። ያው ሁሉም ኣንድ ይሓበሻ ዘር ነው። ታሪክን መለስ ብሎ ማንበብ ነው። 80% ኣሁን ኣማርኛ የሚናገረው ዬጎንደር ህዝብ እኮ ትግርኛ ተናጋሪ ነበር። ዬታሪክ ሰዎች በደምብ ያውቁታል። የትናንት የቅርብ ታሪክ ስለሆነ። ታሪክን ማንበብ ክዚህ ከድንቁርና ኣካሄድ ያድናል። እንዲሁ ዝም ብሎ የህዝብና ዬሃገር ንብረት ማውደምና የሰው ህይወት ማጥፋት ዬትም ኣያደርስም ዬኋላ ቀርነት መግልጫ ካልሆነ በስትቀር።
    ግን እንደምትሉት የኣማራ ነጻነት ወይም ምንጥሲ ከፈልጋችሁ በረሃ ሂዱና ረሃቡም፣ እንግልቱን መከራውን ሞትንም ችላችሁ ታግላችሁ “ነጻ” እውጡት። በጣም ያሳዝናል ብ21 ክፍለ ዘመን ይህ ኣስትሳሰብ። ኣዬ ዬናንተ ነገር። ኣፍና ተግባር ዬተለያዬ ነው። እስቲ ጎንደርን ጨምሮ ዬኢትዮጵያ ከተሞችን እይዋቸው። ከ25 ዓመት በፊት እንዴት ነበሩ ኣሁን ዬት ደረሱ? ህልና ያለው ሰው ይመሰክራል። ይሄ የመሳፍንታዊ የሰነፎች ባህል መቼ እንደሚተው እኔ እንጃ?
    እመካብታለሁ ዬምትሉት ዬምድረ ሓበሻ የጀግንነት ታሪክ ባለቤቱ ማን እንደሆነ ማወቁ ኣይከፋም። ከጀግኖች፣ ከደፋሮች፣ ከታሪክ ሰሪዎች፣ ከብልሆች፣ ከኣይብገሬዎችና መማር። እንዲሁ ለማስታውስ፣ ስልጣኔ የጀመረው ክሰሜን ወደ ደቡብ ነው ወይም ከቀይ ባሕር ጀምሮ ነውና። ትክክልኛው ታሪክ ይሄ ነው። ትክክለኛ ኣካሄዱን እዬያዝ ነው።

  2. Awrien megdel awrie hunonew yilal bihilu.
    Le lieba lieba hunubet, le zereña zereña hunubet, le geday geday hunubet, zerafin zrefut, moralyeleshn moralalba hunubet.

  3. Iski jeginan jegna
    bilo metrat lemin yasafral yanin ke
    Sub Sharan ( The
    best army in Africa ) yetbalwun anberkeko lezmenat
    Inde barriya angetun yedefa Biher Behersb Netsa
    Yaweta wend tekul
    Suri yelbse hulu wend aydelm.

  4. 1. ፋሲለደስ says:
    July 15, 2016 at 6:36 am
    ሳሚ እኔና አንተ ትንሽ ትንሽ መሞት ስንጀምር አንዱ ሲታገል ሌላው ተመልካች ካልሆነ ከጎሳና ከጎጥ አመለካከት ወደ አንድ ሀገራዊነ ሁሉን ብሄር አቀፍ አመለካከት ራሳችንን ስንቀይር ውጤት ማምጣት ይቻላል። በተቀረ የኦሮሞ መሬት የወልቃይት መሬት እያልን ትልቁን ሀገራዊ ጭቆናና ግፍ ካኮሰስነው ማን ማንን ሊረዳ ይወጣል ከንፈር መምጠጥ ብቻ ሆኖ ይቀራል የሚታዩት ትግሎች መነሻችን እንጂ ግባችን ሊሆኑ አይገባምና በዚህ ረክተን የትግል ሁሉ ቁንጮ ነን ብለን ባንመፃደቅ መልካም ነው ማፈርም አለና።
    [Reply]
    Reply
    2. ንጉሡ ሞቱማ says:
    July 15, 2016 at 7:19 am
    የመጨረሻው ሠዐት የዳግም አድዎ ዘመቻ ጥሪ ፣ ቁጥር 19 አሰቸኳይ አገር አድን አዋጅ፣ ጎንደር ፍሸካው ተነፈቷል በየቦታው ተነስ በተኛህበት በግሬደር ከመናድ ታሪክ ስራ አዎ አባቶቻችን በቁመና ሳይሆን በጀግንነት ነው የሞቱት አዎጅ፣አዎጅ ብለው ነው ሁሉንም ትተው የተገናኙት። አንተስ ? ተንቀሳቀስ ሞት እንደሆነ አይቀር ውጣ መንገድ ዘጋ በቆረጣ ባላህ ሁሉ ተሰለፈ አርበኞች ከኋላህ ከችየ ይላሉ። የመረጃ ትእዛዝ በኢሳት ሬድዮ ይተላለፈል።
    +-+++++++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዋች) ኢትዮጵያን ሳያቋት ለ25 አመታት የእንባ የደም ገንዘብ ዘረፉ።ባንዲራችን ላይ የጋኔን ምልክት አጣብቀወባት የብሔር እኩልነት ነው ብለውን እንደ አህያ እንድናስብ አረጉን። ኢትዮጵያ ከአለም በፊት 41 ጊዜ በላይ በመጽሐፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበሯትን እነዚህ የሰው ባህሪይ የሌላቸው ጋኔኖች ኢትዮጵያን በዘር ሰለከፈፈልን ሰው የላት አሉን። ሰለዚህ እስከ መቼ ይህንን ሰቆቃ እየሰማን በኦሮሚያ፣ በአማራ፣በትግራይ ፣ በሱማሌ፣በደቡብ፣ በጋምቤላ የሚቆመው ? ጥሪው ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሆድ ሲል ለኢሕአዴግ ያልየገዛ ሁሉን ልብ የሚያንኳካ ነው። በትግራይ ሪፑብሊክ ስም አልበሽርን የበላይ ጠባቂ አርገው ግን ሴራቸውን የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ህዝቦችን እንደባሪያ ቀጥቅጠው ለመግዛት ሲሉ በተለያየ ግዜ ለአልበሽር ጉርሻ $42 ሚሊዮን የከፈሉበት ማስረጃ ስንአወጣ ወያኔ የአበደች ውሻ ሆነች። ይህ ዜና ከወጣ በኋላ አልበሸር ኢትዮጵያዊው እና ኤርትራዊውን አሁን በግዛቱ መሰቃየት ጨምሯል።ከ10ኘ ክፍል ተስፋ ቢስ አድርጎ ያባረራቸው 30 ሚሊዬን ወጣቶች በተጠንቀቅ የአገር ማዳን ጥሪ እንድትወጡ እና አገራችንን የተስፋ ምድር ለማድረግ ጥሪውን ተከታተሉ። አርሴናል፣ ማንችስተር፣ የትርጉም ፊልም አያሳየ ኢሕአዴግ የአገር ታረክህንናፍቅር እንዳይኖርህ እያረገ ነው። በግዜ ንቃ ፋትህን አዙር።
    1ኛ፣ አብዛኛው ጦሩ፣ሰለዮች ለኢትዮጵያ ማዳን እየስሩ ነው። የኤፈርት ንብረት በአለም ዙሪያ ያለውን ስንሰለት ከግለሰቦቹ ጋር ከ የኢሕአዴግ አባላት፣ የገራፈዎች ስም፣ በፍርድ ቤት ወገንን የሚያሰቃዪ፣ ባንኮችን አጭበርብራቹ የከበራቹ የኦኀዲግ ደላሎች ሁሉ ዋና መረጃ በእጃችን ገብቷል። እነሱ 5ለ1 እኛ ደግም በራሳቸው ሰላይ 5ለ3 የምላጭ ምላጭ ሆነንባቸው። ከጦሩ ደግም ከ10 ውስጥ 7ቱ ጠመንጃ ወደ ኢሕአዴግ የሚያዞሩ ነው። በዘረፋ የተስማራቹ የትም አገር ብትሄዱ በአገር ክህደት ከነወለዱ ማስረጃው ስላለን በትውልድ ትውልድ ትተፈላቹ።
    2ኛ የ12ኛ ፈተና አሁንም ድጋሚ እንዲደፈኑ ለ መኮንኖች እና ከድሬ እና ልጆቻቸው ሲሉ ማፈያዎች አወጡት።
    3ኛ አልበሽር በአገሩ ላይ ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊያን ማሰቃየት ጨምሯአል። ሥራችን ስለተነቃ አስመራ አትሆድ አሉት። በወያኔ ውስጥ ያልታሰበ ቡድን ታሪክ እንደሰራ እየተደራደርን አረየጨረስን ነው፣ ከተሳካ እዚያ ላይ በቀላሉ ያበቃል። በየወሩ ለአዲሱ ሚዲያ ለማፈን ለቻይና $10ሚሊዬን እየከፈሉ ነው።
    4ኛ አባ ማትያስ ፣ የተሐድሶ አቀንቃኞች፣ ገንዘብ አፍቃሪዎች በዝግ ሰብሰባ ላይ ነበሩ ስለ ሙሴ ፅላት ሽያጭ ላይ ነበሩ። አይ እናንተ ጋኔኖች ስታሳዝኑ ኢትዮጵያን አንድም ቀን ሳታቋት ልትሸኙ ነው! የአክሱም ህዝብ ቀልድ የለም ማንነትህን አሳያቸው።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ከእግዚአብሔር ጋር! ንጉሡ ሞቱማ የኦሮሞ ማ/ር ኮር አዛዥ።
    [Reply]
    Reply
    3. ፋሲለደስ says:
    July 15, 2016 at 7:59 am
    ተባረክ ንጉሱ ሞቱማ የትግሉ አቅጣጫና ጥሪ መሆን የሚገባው ይሄ ነው። ጀግና ተጠራራ በዱር በገደሉ በገጠር በከተማ ተንቀሳቀስ ወየኔ እስትንፋሱ እንደ ክር ቀጥናለች ተባብረን እንበጥሳት።
    4. ገብሩ ግርማይ says:
    July 15, 2016 at 5:26 pm
    ንጉሡ ጀግና ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ኮራንባቹ የኢሐዲግን መረጃ ሁሉ ሰባበራቹ።
    ይህ ግዜ ሁሉም በትእዛዝ ተነሱ ከደ/ር ብርሐኑ ነጋ ፣ ከጀኔራል ከማል ገልቹ ፣ ከትግራይ አውጭዎች ጋር ወደ ፈት!!!!!!
    እነዚህ ሸርሚጦች መቶ አመት ሊኖሩ ሊገዙ ነበር ጀግኖች ኢትዮጵያ አላት ዛሬም ነገም። አፈ የተያዘው ከአደዎ፣ ውቅሮ ውጭ ያለነው የትግራይ ህዝብ ኮራንባቹ እንወዳቸዎለን። አዜብ መስፈን ወልቃይትን አስጨረሰች፣ ገነት ዘውዴ የትምህርት ጥራትን ገደለች መሬታችንን እየተረሰብን ለህንድ ና ለቻይና የማይረቡ ሰዎችን መሬት በነፃ ብለው አስወረሩን። አሁን በቃቹ ፈክሻ ተነፈ የነገ ሁሉም ባላህ ተነስ አበቃ፣ ሆዳሞቹ ብዙ ይናገራሉ፣ የገማ ስድብ ከኢሕአዴጎች ጭንቅላት ያተፈሉ። ለምሳሌ እዪት ቃለ አቀባዮን ጌታቸው ተብዬውን የመጀመሪያ እና ሁለተኛውን ከአስቸኳይ አሩጠው ኮሌጅ ዘርፍ ” እየዋሸህ ለሆድህ ኑር” የሚል ትምህርት ተመረቀ። ሆቢው ደግም ሆድ እና ሴት ማተረማመስ ነው። ቀልድ የለም አሁንም የመጨረሻው ስአት ደርሰናል። በአንድነት ወደፈት ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!!!!!!!
    [Reply]

  5. Awo ye Behieroch
    Ikulent yeiger isat
    neaw yehonbachiu
    Yemetemgnoat ye Bandawoch Ethiopia
    Kingdih yemtmetaw
    over the dead body of EPRDF neaw

  6. It has been said long a go woyane get it’s name unknown species. It is crazy to say that the people of Tigay are the first vtimes by those 3rd grader rulers.The question is How do we fight this unknown animal? Keep in mind woyane is depending on agazen arm forces , agazen is very trusted army woyane believed agazen will fight until one agazen drop dead and they also believe they will protected for long time to come that ‘s why they always have plan a head of time for 10,30, even for 56 years to RULE Ethiopia.Lets look back who is agazen ? Where are they come from? Who are they? The name of agazen was given back in 1970-74-75 when TPLF was losing the fight with EHPA,Dreg,EDU and some other fighter in the area.In that time they lost so many fighters so they came up with new idea to set up a camp or hiden cave andthey started to bringing little girls women’s by forces from any where in the area Like wokaite, telement and around Tigray regean and they forced rap them and they told them to have childern as many as they could and that is where agazen was born and raised in hiden cave.this kids only learned to speak one language that is tigraygna and also they learned to shot and kill to their enemy And they are really Godless forces. So how do you fight agazen forces? Well The peace lover Ethiopian’s need to have more than fighter and be come together creat qunick unite,if the people of Ethiopia supporting each other I ‘m sure they can put agazen forces to his knees and crash them down to the earth!!! Death to woyane and power to United Ethiopia.

  7. እሱ ጌታችን ይቅር ይበለን ሰለ ወያኔዎች ብዙም አያስጨንቀንም ትንሽ ቀን ነው ጽዋው እየሞላ ድምጽን እየሰማን ነው።

  8. Igna indminawqew wond lej bizu
    ayaweram . Muyaw belebu neaw .
    yehunochu demo chirash kedrowochu
    yebasu qedadawoch nachew leka ?

  9. ውድ ወገኖቸ እስኪ ቆም ብለን እናስብ። የወያኔ ስርዓት ምን ስላደረገ ነው በሀገሪቱ ውስጥ ብጥብጥና አመፅ በየቦታው እየተፋፋመ ያለው?
    በመጀመሪያ አስተያየት ሰጭወችም ሆን አንባቢዎች እያንዳንዱን ነገር በሰከነ አእምሮ አስበን ልንናገር እና ለሌሎችም ልንገልፅ ይገባል።
    የብጥብጡ እና የዕልቂት መንስዔ ያልነው በመንግስት በኩል እየተፈፀመ ያለው የጎሳ ፖለቲካን ማስተጋባት ነውነው ካልን እና ድርጊቱን ካወገዝን እኛስ ለምን ጎሳና ዘርን በተመለከተ ግጭትን የሚያባብሱ እና ወደ ግጭት የሚያመሩ ፅሁፎችን ተጠቅመን መልዕክት እናስተላልፋል? የመንግስት አካሄድ ትክክል አይደለም ካልን እና ድርጊቱን ካወገዝን እኛ የተሻልን እና በሰከነ አዕምሮ የምናስብ ልንሆን ግድ ይላል። እስኪ መልዕክታችሁን ደጋግማችሁ አንብቡት ለናንተም ለምትፅፉት ግልፅ የሆነ አይመስለኝም ምክንያቱም እርስ በርሱ የሚጣረስ ሀሳብ ነው የምታቀርቡት። ገዥውን ፓርቲ በሰራው ስህተት እየወነጀልን እኛ በጎን ትግሬውን በለው የትግሬውን ንብረት ዝረፈው አቃጥለው የምንል ከሆነ ከመንግስት የተሻለ አስተሳሰብ ያፈለቅነው ምኑ ጋ ነው? እኛም የጎሳ እና የዘር ፖለቲካን እያራመድን መሆኑን ልብ ብለናል?
    ለመሆኑ በትግራይ ውስጥ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን እንድ ጊዜ እንኳን ጠግቦ ለመብላት የማይችል በወቅቱ የመንግስት ጋዜጠኞች አባባል የድሃ ደሃ የማህበረሰብ ክፍል እንዳለ አታውቁም?
    ታዲያ አንድን ብሄር በጅምላ እንደጥፋተኛ መቁጠር እና በወንጀለኛነት መፈረጅ ጤነኛ አስተሳሰብ ነው ትላላችሁ? ለዚህም ነው ለመናገር ወይም ለመፃፍ አንደበታችንን ከመክፈታችን እና ብዕራችንን ከማንሳታችን በፊት ደጋግመን ማሰብ ያለብን። ምክንያቱም ከብዕራችንም ሆነ ካንደበታችን የሚወጣውን መርዝ ቃል መጠቀም አዋቂ ወይም ለሀገር ተቆርቋሪ ሊያስብለን አይችልም። እንደ ሰው ካሰብን በዚህ ዙሪያ በሚፈጠረው አሳዛኝ ውጤት እያንዳንዱ ድርጊታችን እኛኑ ተመልሶ ይፀፅተናል። ለይተን እንውቀስ ለይተን እንወንጅል በጅምላ ስም እየጠቀስን የማይገባ ነገር አናድርግ አስተዋይነትን እንጨምር። በመንግስት እየተፈፀመ ያለውን የጎሳ ፖለቲካ አካሄድ አግባብ እንዳልሆነ አምነው የሚታገሉ ቁርጠኛ የትግራይ ልጆች እንዳሉ ማወቅ

  10. ወያኔ በለመደው ዘዴ ወልቃይት ጎንደርን መቆጣጠር ችሎ ይሆናል ይህ ማለት አማራውን ሙሉ በሙሉ ከስሩ አስገብቷል ማለት አይደለም። አማራ በቅርንጫፎቹ ወይም እንደ ሞረሽን በመሳሰሉ የእንግዴ ልጆች አይወከልም። እስካሁን ንፁህ አማራ ሲታዘብ ቆይቷል ወያኔ መቀበሪያው አንኮበር ይሆናል።
    ወትሮም ሸዋ ይመከረበት ጉዳይ ተረት ተረት ነወ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*