የወልቃይትን ጥያቄና የወያኔ የጋዜጠኝነት ካርታ

Welkeit map

በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ስር ያለ ጋዜጠኝነት ሁሌም በገዥው መንግስት ሸክም ላይ ነው።ተሸካሚው እንደፈለገ ይመራዋል።ጋዜጠኛው እንዳሻው ቢሰራም መሪው ያለው በተሸካሚው ስር ሰለሆነ የትም አይንቀሳቀስም።ወያኔም ልማታውነትን ጋዜጠኝነት አመጣው ሲለን በዚህ ምህንድስና ነው።በተቀየሰልህ ትሮጣለህ፣ከእዛ ውጪ ብትወጣ መንገድ የለም ፤ አትፅፍም ፣አትናገር እንደው ዝም ነው ጫወታው።

  • በአንባገነን ስርዓት የወልቃይት ጥያቄ ከጋዜጠኛው ጋር ይጣላል? መልሱ አዎ ነው።እንዴት ካላችሁኝ መናገሩ ቀላል ነው። በወያኔ የጋዜጠኛ ካርታ ላይ በደማቅ የተፃፈው ልማታው ጋዜጠኝነት ጋር የወልቃይት ጥያቄ ይጋጫል።የጋዜጠኛ ካርታ መንግስት የወደደውን ነው የሚወደው።መንግስት የማይፈልገው የትኛውን ነገር በዚህ ካርታ ሸፋን የለውም።ማለትም የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ ወያኔ አይቀበልም የልማታው ካርታም አይቀበልም።ለዚህም ነው የመንግስት ሚዲያዎች ሰሞኑን ባልሰማ ያለፍት።እንደው ትንሽ ከተቀመጠላቸው ካርታ ወጣ ብለው ከሰሩ ዜናው እንዲ ነው የሚሆነው።
    በጎንደር የተነሳው አመፅ የህዝቡ ጥያቄ ሳይሆን የአሸባሪዎች ተላላኪዎች ትርፍ ሊያገኙ ነው።
  • የቅማንት ብሄረሰቦች ሰሞኑን የተከሰተው ረብሻ እኛን አይወክልም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነው።
  • አንዳንዶቹም ባልሰማ የራሳቸውን ትተው«በአሜሪካ ምና ምን ግዛት ህዝባው ተቃውሞ ተባብሷል ይሉናል»
    እንደው ከዚህ ጭራሹን ባይሰራስ።
    ስለ ልማታው ጋዜጠኝነት ስማር የህዝብ አጀንዳ ይዘለላል የሚል————————

ስለ ልማታው ጋዜጠኝነት ሰማር የሟቾች ቁጥር ይቀነሳል :: ልማታዊነት ጋዜጠኝነት ሰማር የህዝብ ጥያቄ ከሸብርተኘነት ጋር ይያያዛል የሚል እኔ አላስታውስም።አብራችሁኝ የተማራቹ ከረሳው አስተሰውሱኝ።

እኔ ረስቼ ሳይሆን ይህ የተጻፈው የወያኔ ካርታ ላይ ነው።በወያኔ የጋዜጠኝነት ካርታ ላይ «የትኛውም ዜና ከኢህአዴግ አይበልጥም» በሚል በቀይ የተፃፈ ህግ ነው ይሄ።

ኢህአዴግ ወልቃይት የትግራይ ነው ብሎ ያምናል።ልማታው ጋዜጠኛም ይህን ህግ ጠብቆ ይሰራል።ወያኔ ሀሳቡ እስካልቀየረ ድረስ ይህ ህግ ነው።እንደ ማንኛውም ህግ የማይጣስ ህግ ነው።

ታዲያ ይህ ምን ያስከትላል?

ጋዜጠኛው ስለ ወልቃይት የህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ስለ መንግስት ምን አለ ያሰጨንቀዋል።የሚናገረ እና የሚፅፈው ወፈር ያሉትን እና ንጉሳንን ከወንበር የሚያስነሳ ታሪክ እንዲሆን ያደርገዋል።

በእሱ እጅ ወያኔ ይፅፍለታል!
በእሱ አንደበት ወያኔ ያወራል!
ይህ የካርታው ንድፍ ነው።

ልማታዊ ካርታው ስንት ነው?
በትልቁ ካርታ የመንግስት እና የግል ፕሬስ አለ።ሁለቱም የተወሰነ ቦታ ድረስ አብረው ይራመዳሉ።በካርታው ላይ ሁሉን የሚያካልለው የመንግስቱ ነው።የግሉ እዚህ ጋር ይኮረከማል።የመንግስቱ ለዙፋኑ ቀድሞ ሰለሚያስብለት ከፈለገ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መተኛት ይችላል።መጠኘና ነጳነት ለግሉ እንዳለው ካርታው ላይ ያሳየሰል።ስለ ፍቅር ፣ሰለ ጤና ፣ስለ ፋሸን ፣ስለ ቢዝነስ እንደፈለገ እንዲናገር ተፈቅዳል ካርታው ላይ።በደማቁ ለግሉ በቀይ የኖረው «ፖለቲካ ጭቃ» ነው የሚለው።የወልቃይትም ጉዳይ ጭቃ ነው ለወያኔ።

በልማታዊ ጋዜጠኝነት ካርታ ሸብርተኛ ማን ነው?

ጭቃውን የረገጠ ነው።ኦባማ አዲስ አበባ ገባ ማለት ትችላለህ።ኦባማ ለምን ኬንያ ሳይገባ እኛ ጋር ገባ ማለት አትችልም።ይህን ካል በወያኔ መነፅር ዜናውን አልሰራህምና ተብለህ ሸብርተኛ ትባላለህ።ስለ ወልቃይት ዜና መስራት ትችላለህ።ዜማው ግን መነፅሩ የልማት ነው መሆን አለበት ይህ ካልሆን ውሻው ይናከሳል።

ካርታው ለምን አስፈለገ?
ካርታው ብቻ ለማውራት ነው።እኔ ያልኩትን ሰማ ነው።ኢትዮጰያ አደገች ለማለት ነው።ድህነት አጥፍተናል ለማለት ነው።በቀን አምስቴ ያውም ፓዛ ጀምረናል ልንባል ነው።ከጭለማ ወደ ብርሃን ሄድ ነው።ምርጫ ፍጱም ፍትሃዊ ነው ለማለት ነው።መኪና ማምረት ጀምረናል ለማለት ነው።ለአንድ ሰው አንድ ላዳ ለማለትም ነው።ኢትዮጵያ በአለም በዲሞክረሲን ማሰፈን ቀዳሚ ሆነች ለማለት።
ተመረቀ
ተከፈተ
ተገለፀ
ያለበት ሁኔታ ነው———————— ተብለን ልንሰበክ።

ሰለቸን !!!
በቶማስ ሰብሰቤ