ባለፈው ታሪክ ብቻ የሚኖር ፤ በወደፊቱ ላይ ማተኮር ይሳነዋል ! (መነበብ ያለበት በፍኖተ ሬድዮ የተነበበ )
መነበብ ያለበት በፍኖተ ሬድዮ የተነበበ
ባለፈው ታሪክ ብቻ የሚኖር ፤
በወደፊቱ ላይ ማተኮር ይሳነዋል !
ኢትዮጵያ፤ እንደማነኛውም ሀገር፤ የራሷ መጥፎም ሆነ መልካም ታሪክ ነበራት/ አላት። የጥቃትና የድል፤ የጥጋብና ረሀብ፤ የስፋትና የመጨራመት፤ የመከራና ሀሴት ዘመናት ሁሉ ተፈራርቀውባታል ። የተለያዩ ሥርዓተ- ማኅበራትንና ገዥዎችን ሁሉ አሳልፋለች። ድንበሯ ያልተደፈረ ፤ ታሪኳ የተከበረ ፤ ሉዓላዊነቷ ያልተገሰሰ ፤ የንግድ መናሃርያዋ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተዘረጋ፤ ኃያል ሀገር ነበረች ። የጦርና የንግድ መርከቦቿም በውቅያኖሶችና ታላላቅ ወደቦች ይንሳፈፉ ነበር። ያ ሁሉ ዛሬ፤ ነበር ሆኖ አልፏል ! ” የነበር ሲያወሩት ይመስላል ያልነበር፤ የኢትዮጵያ ጠረፍ ውቅያኖስ ነበር ! ” እያሉ መናገር፤ የዕለት -ተዕለት ቁዘማ ሆኖ ቀርቷል ! ታሪካዊና ነባራዊ ሀቆች ግን እነኝኽ ናቸው !
ዜጎቿም በነኝህ ተፈራራቂ ሥርዓተ- ማኅበራትና ስልተ-ምርቶች ሂደት ተጉዘዋል። ያም ሁሉ ሆኖ እስካሁን ደረስ፤ የራሳቸው ዕድል ባለቤቶችና ወሳኞች አልሆኑም። በዚህ በያዝነው 21ኛው ክፍለ-ዘመን እንኳ፤ የዴሞክራሲ ጭላንጭልን ሊጎናጸፉ አልቻሉም ። የነፃነትና ፍትኅ-ርትዕ ዕጦት አሉባቸው። የጉስቁልና ኑሮ የህይውታቸው መቆያ፤ ረሀብና ስደት፤ የማንነታቸው መለያ መሆኑን ድፍን ዓለም አውቆላቸዋል ። እነርሱ ግን ወዴት እንደሚሄዱ ብቻ ሳይሆን፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንኳን የተገነዘቡት አይመስልም።
ርሃብን በስደት፤ ጭቆናን በሽሽት፤ ድኅነትን በምፅዋዕት፤ ቁጭትን በብስጭት፤ እያፈራረቁ ማስተናገድ፤ ዘላቂ መፍትሄ አላመጣልንም ። ለችግራችን ሁሉ ማስወገጃ የሚሆን መድሃኒት ለማምጣት፤ ቆራጥ ውሳኔ ለመውሰድ ፤ እስካሁን አልተሳካልንም ። ሌላው ዓለም ፤ የየራሱ ችግር ስለአለበት፤ ከችግሩ ለመውጣት ይፍጨረጨራል እንጅ፤ ስለ እኛው ችግር ለማስብ፤ ጊዜውም፤ ደንታውም፤ ፍላጎቱም የለውም ። ማነኛውም ሀገር፤ ለሌላ ችግር ቅድሚያ አይሰጥም ። ለራሱ እንጅ !
እኛው በኛው፤ ለእኛው መፍትሄ ካላገኘን፤ ስለኛ ሆኖ ለኛ አስቦ፤ የኛን ችግር የሚፈታልን ሌላ ማንም እንደሌለ አውቀን፤ ቆርጠን መነሳት አለብን ። ዕድሜያችን ሲደርስ፤ የናታችንን ጡት መጥባት ቆርጠን እንዳቆምነው ሁሉ፤ በውጭ ርዳታ፤ ችግራችን ይቆረጣል የሚለውን ምኞት ቆርጠን መጣል አለብን! የራሳችንን ችግር ራሳችን ፈችዎች መሆናችንን ካስመስከርን፤ ዓለም ሁሉ ያከብረናል ። በየጊዜው ከ 10 እስከ 20 ሚሊዮን ረሃብተኛ ሕዝብ እያመረትን፤ ምፅዋዕት ጠያቂዎች መሆናችን ግን ያስንቀናል እንጅ አያስከብረንም ። ከ 1966 ዓም ጀምሮ፤ እስከ ዛሬ 2008 ዓም ድርስ ያለው ዘመን ታሪካችን፤ የረሃብተኛ ዜጋ ፈጣሪዎች እንጅ፤ የኢንዱስትሪ ውጤት አምራች አላደረገንም ። አሁንም ይህ ችግራችን እንደቀጠለ ነው። በውቅቱ ያለው ዘረኛ አገዛዝም፤ ተግባራዊ ፖሊሲዎቹ እንደሚያመላክቱት የችግሩ ምንጭና አባባሽ እንጅ፤ የመፍትሄ አካል ሊሆን አይችልም።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ፤ ወዳጆቿን እያጣች፤ ጀግኖቿን እያጠፋች፤ አጥፊዎቿን እያነገሰች ፤ ዐርበኞቿን እየቀበረች፤ ቀባሪዎቿን እያቀፈች፤ ልጆቿን አስከፍታ እያሰደደች ፤ ራሷ ግን፤ ቀስ በቀስ፤ በሂደት የምትጠፋ ሀገር ሆናለች ! እስከ መቼ ?
ኢትዮጵያ፤ በራሷ ዜጎች ፍላጎትና ውሳኔ ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊ ሥርዓተ- መንግሥት እስካላገኘች ድረስ፤ ሁልጊዜ ሕዝቦቿ፤ በዕርጎ ባኅር እየዋኙ ከመኖር በቀር ሌላ ተስፋ አይኖራቸውም። ኢትዮጵያዊ መንግሥት ማለት፤ በትውልድና በዜግነት ብቻ ኢትዮጵያውያን የሆኑ መሬዎች የሚመሩት መንግሥት ማለት ሳይሆን፤ መሪዎቿ፤ የሀገርንና የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጥቅም ጠብቀው የሚያስጠብቁ ፤ የሀገርን ክብር አክብረው የሚያስከብሩ፤ ለሀገራቸው ነፃነትና ሉዐላዊነት የሚሰዉ ማለት ነው ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈራረቁ ” መሪዎች ” ፤ ይህን መስፈርት አሟልተው አልተገኙም ። ” መወለድ ቋንቋ ነው ። ” እንደሚባለው ፤ ዜግነት ብቻውን፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥትን ለመምራት ብቁ አያደርግም ። በሰው ልጆች ታሪክ ሂደት፤ በሕዝቦች ላይ በተለያዩ ስሞች ብዙ ግፎች ተፈፅመዋል ። በሥልጣኔ ስም ፤ በሀይማኖት ስም፤ በሶሻሊዝም ስም፤ በብሄር ነፃ አውጭ ስም ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍና በደል፤ በሕዝቦች ላይ ተፈፅሟል። ኢትዮጵያም በልዩ ልዩ ስሞች ብዙ ፍዳ ተቀብላለች ። ኅልውናዋ አደጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ አያሌ ፈተናዎችን አልፋለች ። ዛሬም ከዚህ አደጋ አልወጣችም።
የኦቶማን ኢምፓየር፤ በግዛት ማስፋፋት ሰበብ፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሞክሯል። ግብፅና ሱዳን ተባብረው በዐባይ ወንዝ ምክንያት ፤ የሀገራችንን ኅልውና ተፈታትነዋል። ያ፤ ጠንቅ አሁንም አልጠፋም። ምዕራባውያን በበኩላቸው፤ ( እንግሊዝ፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን) ኮሎኒያሊስቶች ተባብረው፤ ኢትዮጵያን፤ በመቀራመት ከአፍሪካ ካርታ /ገፅ ለማጥፋት ከፍተኛ ጥርት አድርገዋል። ደርግ በሶሻሊዝም ስም በሀገርና በህዝብ ላይ የፈፀመውን ወንጀል ለመዘርዘር የዚህ ሐታታ መነሻ አይደልምና በዚያ ላይ አናተኩርምም ። ወያኔ እንኳ በዐቅሟ፤ በብሄር ነፃ አውጭ ስም ፤ የቱን ያኅል ብሄራዊ ጥፋት አያደረገች እንደሆነ ለመዘርዘር አይሞከርም ። ውቅያኖስን በጭልፋ ይሆናልና! ሁሉንም ፤ ለታሪክ መዝጋቢዎችና ለዜና መዋዕል ፀሀፊዎች ትተነዋል ።
በዚህ አንቀጽ የተዘረዘረው፤ ለጥቅሻ ያኅል የሀገራችን ታሪክ አካል መሆኑን ጠቅሰን ማለፍን መርጠናል ። ሌላው ቢቀር፤ለአሁኑ ትውልዱ ግንዛቤ ይረዳል ብለን እንገምታለን። ይኽ ሀቅ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን፤ በከፉም ሆነ በደግ ገፅታው፤ባለፈ ታሪክ ላይ ብቻ ትኩረት እያሰጡ መኖር ፋይዳ ቢስ ነው ። ባለፈ ታሪክ ብቻ፤ መኖር፤ መቀጠል፤ መራመድ ፤ መበልፀግ፤ ማደግ፤ መከበር፤ መገስገስ አልቻልንም። በታሪክ እሳቤ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ፤ ያሁኑን ሁኔታ ከመጨው ጋር እያጣቀስን መራመድ ያዋጣናል ።
ለዘመናችን ታሪክ መመዝገብ ያለብን፤ በዚህ ዘመን የምንኖር ዜጎችና ትውልድ ብቻ ነን ። በቀደምት፤ ጀግኖች፤ ዐርበኞች፤ ሠማዕታት፤ ደራሲያን፤ መዘምራን፤ ወዘተ.. ታሪክ ሰሪነት ብቻ እየተኩራራን ከቀጠልን፤ አዲስ ጀግና፤ መሪ፤ ማውጣት የሚቸግረን ይመስለናል። በዘመናችን አዳዲስ ጀግኖች ለማውጣት ግን ቀደምት ጀግኖቻችንን ማክበርና ማወድስ ተገቢ ነው ። ቀደምቶችን ካለከበርን ደግሞ፤ አዳዲስ ጀግኖች ማውጣት ይቸግረናል ። “ኢትዮጵያ፤ አንድ መቶ ዓመት ታሪክ የሌላት ሀገር ነች ” የሚሉ ገለሰቦች፤ ከሚገዟት ሀገር የሚያድግ ትውልድ፤ እንዴትስ ብሎ አዳዲስ ጀግኖች ማውጣት ይቻላል ? አዲስ ጀግና ለማውጣት፤ የቆየ ኣርዓያን ማግኘት ይጠይቃል ።
አሁን ያለው ትውልድ፤ ያልተማረውን ዕውነተኛ ታሪክ ፤ ከየት አምጥቶ፤ ሊያውቅ ይችላል ? ጀግናን፤ በአርዓያነት ሊጠቅስ ካልቻለ፤ እንዴት አድርጎ ነው የራሱን ጀግና የሚያወጣ ? የራሱን መሪ ፈጥሮ – አውጥቶ ካልመረጠ ፤ መሪ ማን ሊሰጠው ይችላል? ” ሀገሬ ኢትዮጵያ ፤ የደጋጎች ምድር ነበረች ” የሚል የሕዝብ ዕምነት ቢኖርም፤ ዛሬ ደጋጎቹ ስለሌሉ ፤ ኢትዮጵያዊ ሙሴን በመሪነት የሚሰጣቸው አላገኙም። ኢትዮጵያውያን ፤ ያላቸው ምርጫ፤ የሚሆነው አንድ ብቻ ነው ። እራሳቸው ተስማምተው፤ የራሳቸውን ኢትዮጵያዊ መሪ ማውጣት ብቻ ይሆናል ። ይኽንን ጥረት ግን እስካሁን አልሞከሩትም። ይኽንን ሞክረው ውጤት ካስመዘገቡ ግን የችግራቸው መወገጃ ፤ የመፍትሄያቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ፤ ይሆንላቸዋል ።
አዲሱን ምዕራፍ ለመክፈት ፤ አንድ የተጋረደባቸውን ደንቃራ መስበር አለባቸው ። እርስ በእርስ መነታረካቸውን ማቆም አለባቸው። አንዱ በሌላው ላይ ማሳበብ መፍትሄ አላልስገኘም እስካሁን ! ጎይቶም በጌታቸው፤ በለጠ በጭላ፤ ጫልቱ፤ በማሚቱ እያመካኙ አብሮ መኖር አይቻልም ። የጋራ መሪ ለማውጣት፤ አስቀድሞ የጋራ ችግርን በጋራ የማስወገድ ችሎታ እንዲኖር ግድ ነው።
ይኽንን በቅጡ ከተገነዘብን ፤ ጀኔቫ ሂዶ ሰልፍ መውጣት ፤ ኒውዮርክ መጥቶ አቤቱታ ማቅረብ፤ የዕልፍ አዕላፍ ፊርማዎችን ሰብስቦ ፔቲሽን ማስፈረም ፤ ቅንጣት ያኽል መፍትተሄ አያመጣም ። “የጨነቀው ነፍስ-ጡር ያገባል። ” እንደሚባለው፤ የሚይዙት የሚጨብጡት በማጣታቸው ምክንያት፤ ሻዐቢያ ነፃ ያወጣናል የሚሉ ክፍሎች መኖራቸውን ታዝቦ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ ” ይህንን ሊያሰማኝ ነው እንዴ ፤ ሲቃዠኝ ያደረው ? ” ብሎ አሹፎባቸዋል ።
” በተመሳሳይ ሁኔታና የጊዜ አጋጣሚ፤ ታሪክ ራሱን ይደግማል። ” እንደሚባለው፤ ፤ ቤኒቶ ሙሶሊኒ፤ ኢትዮጵያን ለመውረር ምክንያት ካደረጋቸው ማጠየቂያዎች አንዱ፤ ” አቢሲኒያን ከባርነት ነፃ ለማውጣት ነው ። ” የሚል ዲስኩር / ፕሮፓጋንዳ ነበር ። ከ70 ዓመታት በኋላም ዛሬ፤ ” ሻዕቢያ ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃ ያወጣል ” የሚሉ ፕሮፓጋንዲስቶች ተፈጥረዋል። ዕድሜ ዘልዛላ ነው ፤ የማያሰማው ጉድ የለም ! እስቲ እናያለን፤ ሻዐብያ ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ ነፃ ሲያወጣት !
ያም ሆኖ፤ ግን በአለፈው አኩሪ ታሪካችን ብቻ እየተፅናናን መኖርን መርጠናል ። ” የኋለኞቹ ወደፊት ፤ የፊተኞቹ ወደ ኋላ ” እንደሚባለው፤ በኋላቸው የነበሩ ሀገራትና ሕዝቦች እየቀደሟቸው ሲራመዱ ፤ እነርሱ ግን ባሉበት መርገጣቸውን ብቻ ሳይሆን፤ ወደ ኋላ መቅረታቸውን እንኳን አልተገነዘቡትም ። ይህ አልበቃ ብሏቸው፤ ዛሬማ ፤ ይባስ ተብሎ፤ በማንነትና በኅልውና ጥያቄ መካከል የሚኖሩ ሰዎች ሆነዋል ። ኢትዮጵያውያን/ ያት!
” ነኝ፤ ወደ ነበርኩ፤ እየተለወጠ ብቻ ሳይሆን፤ አለሁ፤ የሚለውም ወደ አልቦነት እየተለወጠ በመሄድ ላይ ነው። ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል ።” ሆኖ ነው መስል፤ የጃርት ሥርዓት አራማጆች፤ እንደ ጃርት እየቆረጠሟቸው ይገኛሉ። አንገቷ የተቆረጠባትን ሀገር ብቻ ይዘው፤ መተንፈሻ -መናፈሻ ያጡ ዜጎች ከሆኑ ጥቂት ዓመታትን አሳልፈዋል ። ” መቃበር፤ ከለመዱት ይሞቃል። ” እንደሚባለው፤ ችግርና መከራን ተለማምደው የሚኖሩ ሁነዋል። በዚህ ምክንያት ይመስላል፤ ያለፈ ታሪካቸውን እንደ መጽናኛ እየተጠቀሙ ኑሯቸውን መግፋት መርጠው ተቀምጠዋል ።
የሀገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች፤ ባቆዩት ገናና ታሪክና አኩሪ ሥራ ብቻ እየተኩራሩ መኖር፤ ለሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ነዋሪ የሚያመጣው ፍይዳ አለመኖርን አውቆ፤ የራስን አኩሪ ታሪክ እያስመዘገቡ፤ ለዘመኑ የሚጠቅም ሥራ ካልሰሩ ፤ ወደፊት መራመድ የሚቻል አይደለም። የራስን ታሪክ እየሰሩና በራስ ጥረት ላይ የተመሰረተን ውጤት እያስመዘገቡ መሄድ ከተቻለ ግን ፤ የወደፊቱን ራዕይ ለመቀየስም ዕድል ይኖራል ። ያለፈን ታሪክ ስንቅ እያደረጉ መኖርንም ሊያስቀር ይችላል ።
ይኽ የወቅቱ ትውልድ፤ ያለፈውን መጥፎም ይሁን መልካም ታሪክ ፤ እንደ አግባቡ ለትምህርት ግንዛቤ እየተጠቀመ ፤ ያለበትን ወቅታዊ /ነባራዊ ሁኔታ እየገመገመ ፤ በራሱ ጊዜ እየተጠቀመ፤ የራሱን ታሪክ እየሰራ/ እያስመዘገበ መቀጠል አለበት። የወደፊት ዕድሉን ለመወሰን የሚችለው፤ የራሱ ተገዥ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ የራስ ተገዥ ለመሆን ደግሞ፤ በራስ መተማመንን ይጠይቃል። በራሱ የሚተማመን ዜጋ ማፍረት የምትችል ሀገር፤ የራሷን መሪዎች መፍጠር ትችላለች። የራሷን መሪ መፍጠር ከቻለች፤ ብዙዎቹ ችግሮቿ ሊቃለሉላት ይችላሉ ። በሂደት !
ብዙኅነትን በአግባቡ የምታስተናግድ ሀገር ትሆናለች። የዘውግ ፖለቲካን ማስተናገድ አትመኝም ፡፡ አይሆንላትምም። የዘውግ ፖለቲካ አጥፊ / ከፋፋይ እንጅ አልሚ ሊሆን አይችልም ። ለአንድነት ጠንቅ ነው። ይኽ ፖለቲካ ፤ በወያኔ አገዛዝ የታየ ሀቅ ነው። በምትኩ ግን ፤ የዴሞክራሲ ሥርዓተ- መንግሥት መገንባት አማራጭ አይኖረውም። በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስር ፤ በሀገረ- መንግሥት (State Power) እና በፓርቲ መካከል በህግ የተገደበ ልዩነት ይኖራል። ይህ ልዩነት ከሌለ ግን እውር ድንብሱን እንደሚሄድ መልኅቅ- አልባ ጀልባ መሆን ነው ። ይህ ከሆነ ደግሞ መንግሥቱም ሆነ ፓርቲው በባኅር ውስጥ ጠፍተው ይቀራሉ። የደርግን መንግስትና ኢሠፓን መጥፋት ያጤኗል! የሚቀጥለው ተራም፤ የወያኔ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው።
በመጨረሻም፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መኖሯ ሊያከትም የሚችልበት ዕድል ሰፊ የማይሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም። የወያኔ መሪዎች ዛሬ የሚፈልጉትም ይኽንኑ ነው። ይህንን ሕዝቡ እየተከታተለ እንዳይቃወማቸው፤ በፕሮፓጋንዳ ሊያደነዝዙት ይጥራሉ ። ወያኔን፤ የዴሞክራሲነት ፀዳል ለማልበስ የሞከሩ ባዕዳንም በመጨረሻ የሚያፍሩበት ቀን ይመጣል ። ትርጉም በሌላቸው ተግታልታይ ቃላት መጠቀም እንኳንስ ለወያኔ፤ የፕሮፓጋንዳ ጠቢብ ለነበረው ለናዚ ጀርመኑ ፕሮፓጋንዲስት፤ ለጆሴፍ ጎብልም አልፈየደ። ናዚዎቹ በመጨረሻ እራሳቸው ጠፍተው፤ አገራቸውን ጀርመንንም እንዳልነበረች አድርገዋት ሄዱ ።
የሀገራችንም ዕድል በዚህ አቅጣጫ እያመራ ይገኛል ። ይኽ እንዳይሆን፤ የውቅቱ ትውልድ የራሱን ታሪክ እየሰራ፤ ሀገሩን ማዳን ይጠበቅበታል ። ሀገሩን ማዳን ከቻለ ደግሞ፤ የራሱን ኅልውና ማረጋገጥ ይችላል ። ባለፈ ታሪክ ማፈርም ሆነ መኩራራት፤ ማዘንም ሆነ መደሰት ብቻውን መፍትሄ አልሆነልንም። የራስ ታሪክ እየሰሩ ማለፍ፤ ለሀገር ኅልውና ዋስትና ሊሰጥ ይችላል ።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !
This article is completly nonsense may be orchetrated by woyane also the so called eprp you better stay from peoples struggle you been tested for the last fotty years but you fail
Finote democracy- what a non-sense article is at all,and a smelling wound of woyane. We never and ever forget what Eprp has mischieved the generation sending to hell by the name of democracy.So please we formely cheated by Eprp are saying stay away from our patriots and our freedom fightes:
Ehapa!is a collection of ye qeyi ahibir nechi shibir tirafil.yihe endeweyira yetenekerew astesasebi ende Abe To kichaw qeldi,wazana qumnegeri ……
TPLF = EPRP
I am trying to figure out what the author is trying to say. But the author sounds like a USA-socialized person or like a USA mental slave. We know a lot of his views from USA mental slave Ethiopians, and those views are disgusting. No self-respecting and mentally free Ethiopian has that kind of views and thoughts about Ethiopia.
In the quote below the author “forgot” to mention the biggest criminal in recent Ethiopian history, satanic USA, it is not hard to guess why. 😉
The times are getting harder for USA-lover Ethiopians as the USA is increasingly exposed and universally viewed as the Great Satan.
” የኦቶማን ኢምፓየር፤ በግዛት ማስፋፋት ሰበብ፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሞክሯል። ግብፅና ሱዳን ተባብረው በዐባይ ወንዝ ምክንያት ፤ የሀገራችንን ኅልውና ተፈታትነዋል። ያ፤ ጠንቅ አሁንም አልጠፋም። ምዕራባውያን በበኩላቸው፤ ( እንግሊዝ፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን) ኮሎኒያሊስቶች ተባብረው፤ ኢትዮጵያን፤ በመቀራመት ከአፍሪካ ካርታ /ገፅ ለማጥፋት ከፍተኛ ጥርት አድርገዋል። ደርግ በሶሻሊዝም ስም በሀገርና በህዝብ ላይ የፈፀመውን ወንጀል ለመዘርዘር የዚህ ሐታታ መነሻ አይደልምና በዚያ ላይ አናተኩርምም ። ወያኔ እንኳ በዐቅሟ፤ በብሄር ነፃ አውጭ ስም ፤ የቱን ያኅል ብሄራዊ ጥፋት አያደረገች እንደሆነ ለመዘርዘር አይሞከርም ። ውቅያኖስን በጭልፋ ይሆናልና! ”
Great Satan USA/CIA were behind:
1. the so-called Ethiopian Students Movement,
2. overthrow of Haile Selassie,
3. overthrow of Derg,
4. separation of Eritrea,
5. landlocking of Ethiopia,
6. introduction of tribalism and killils in Ethiopia as initial steps to dismantle Ethiopia,
7. the failure of the Qinijit revolution in relation to the 2005 elections.
USA / West were behind Derg as we can read below:
USA political activist Lyndon LaRouche writes: On September 12, 1974 Haile Selassie was overthrown in a Pro-American military coup with approval of Henry Kissinger.
http://www.larouchepub.com/eiw/public/1995/eirv22n24-19950609/eirv22n24-19950609_012-horn_of_africa_the_british_setup.pdf
If the above is true, then Haile Selassie (HIM) was overthrown by the USA or the West. And Derg and Mengistu were agents of the USA or ferenjis.
The coup de etat by Germame Neway in December 1960 G.C. and the so-called Ethiopian students movement were covert CIA operations started in the late 1950s G.C. to early 1960s G.C. by Eisenhower.
So, regarding the CIA or western plot against HIM and Ethiopia, there are two camps within Ethiopia,
a. the camp of the patriots and
b. the camp of the traitors.
.
In the camp of the patriots we find,
1. Haile Selassie
2. Ethiopian nationalists
3. the general Ethiopian public
.
In the camp of the traitors we find,
1. Eritreans
2. Leaders of the “Ethiopian Students Movement”
3. EPRP
4. Meison
5. EPLF
6. TPLF
7. Tribalists
8. Derg
9. Likely traitors, among others, Germame Neway, Kassa Kebede, Mengistu Haile Mariam, Walelign Mekonnen, Meles Zenawi, Sebhat Nega and Isayas Afewerki.
If you ask me, Ethiopians based in the USA like the author are now in a very embarrassing and difficult situation because they are USA-lovers, at a time when USA is being exposed as the Great Satan.
I don’t know what the author is trying to say.
He sounds like a USA-socialized or USA- brainwashed or USA mental slave Ethiopian.
His mindset or his views and thoughts about Ethiopia, that we know from USA based Ethiopians, is DISGUSTING and totally unacceptable for self-respecting and mentally free Ethiopians.
The times now are hard for USA-lover Ethiopians like the author when the USA is being exposed around the world and is universally viewed as the Great Satan.
I quote the piece below because the USA-lover author “forgot” to mention the biggest criminal, USA.
” የኦቶማን ኢምፓየር፤ በግዛት ማስፋፋት ሰበብ፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሞክሯል። ግብፅና ሱዳን ተባብረው በዐባይ ወንዝ ምክንያት ፤ የሀገራችንን ኅልውና ተፈታትነዋል። ያ፤ ጠንቅ አሁንም አልጠፋም። ምዕራባውያን በበኩላቸው፤ ( እንግሊዝ፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን) ኮሎኒያሊስቶች ተባብረው፤ ኢትዮጵያን፤ በመቀራመት ከአፍሪካ ካርታ /ገፅ ለማጥፋት ከፍተኛ ጥርት አድርገዋል። ደርግ በሶሻሊዝም ስም በሀገርና በህዝብ ላይ የፈፀመውን ወንጀል ለመዘርዘር የዚህ ሐታታ መነሻ አይደልምና በዚያ ላይ አናተኩርምም ። ወያኔ እንኳ በዐቅሟ፤ በብሄር ነፃ አውጭ ስም ፤ የቱን ያኅል ብሄራዊ ጥፋት አያደረገች እንደሆነ ለመዘርዘር አይሞከርም ። ውቅያኖስን በጭልፋ ይሆናልና! ”
USA/CIA were behind:
1. the so-called Ethiopian Students Movement,
2. overthrow of Haile Selassie,
3. overthrow of Derg,
4. separation of Eritrea,
5. landlocking of Ethiopia,
6. introduction of tribalism and killils in Ethiopia as initial steps to dismantle Ethiopia,
7. the failure of the Qinijit revolution in relation to the 2005 elections.
So, regarding the CIA or western plot against Haile Selassie (HIM) and Ethiopia, there are two camps within Ethiopia,
a. the camp of the patriots and
b. the camp of the traitors.
.
In the camp of the patriots we find,
1. Haile Selassie
2. Ethiopian nationalists
3. the general Ethiopian public
.
In the camp of the traitors we find,
1. Eritreans
2. Leaders of the “Ethiopian Students Movement”
3. EPRP
4. Meison
5. EPLF
6. TPLF
7. Tribalists
8. Derg
9. Likely traitors, among others, Germame Neway, Kassa Kebede, Mengistu Haile Mariam, Walelign Mekonnen, Meles Zenawi, Sebhat Nega and Isayas Afewerki.
You know what, we are now finding out that in the past we were told lies by Ethiopian intellectuals, journalists and activists regarding what happened since the 1960s G.C..
We are finding out that all that was a covert CIA operation and many of the activists then were CIA agents and traitors, even including Mengistu. We can read above that Derg came to power with USA permission, that means Mengistu was a CIA agent. Of course the same is true about Germame Neway, about the so-called Ethiopian students movement and the many leftist organizations.
The narrative has to change, and we should start talking about a western plot against HIM.
Regarding the landlocked status of the country we should start talking about a “WARNING EXAMPLE”
The USA and ferenjis landlocked Ethiopia to make the country a WARNING EXAMPLE for other countries !
Regarding the “WARNING EXAMPLE” matter, a short glance at the Ethiopian map suffices for other countries to get the “message”.
Map of Ethiopia
http://www.mapsofworld.com/ethiopia/maps/ethiopia-map.jpg
Despite conventional views this landlocking was done by ferenjis, and it is one area that shows the ill-will the ferenjis harbour towards Ethiopia.
A short glance at the world map (look at Jordan, Iraq, countries in West Africa and of course DR Congo) suffices to recognize the ill-will of ferenjis towards Ethiopia.
As we can see on the map of DR Congo, the common practice in international law is to always ensure access to the sea when countries are formed, even by cutting corridors through other countries.
We can see on the DR Congo map where a corridor was cut through Angolan territory, creating the Cabinda province north of the DR Congo at the Atlantic coast which is separated from the rest of Angola.
Watch the map carefully, the mainland of DR Congo is hundreds of Kilometers away from the Atlantic Coast, still a corridor was cut through Angola to connect DR Congo to the sea.
And then look at the map of Ethiopia, it lies so near to the coast, not even 100 km away from the coast, still the ferenjis, particularly the USA, decided to make Ethiopia landlocked because of ill-will !
Here you can compare on the map.
http://www.operationworld.org/files/ow/maps/lginset/conz-LMAP-md.png
Ethiopians need to be armed with this kind of info about the ferenjis.
Here you have a better map of the DR Congo.
http://www.nationsonline.org/maps/dr_congo_map.jpg
In Africa USA not only imposes puppet regimes like TPLF on Africans and protects them and fights legitimate opposition forces like G7, the USA trains, arms, finances and commands also terrorist groups like Al Shabaab, Boko Haram, ISIS, AKIM and Al Qaeda in order to wreak havoc in Africa like in Nigeria, Somalia, Kenya and Libya, and in order to destroy and make it difficult for foreign investors like Chinese to operate there.
” IN AFRICA, THE U.S. MILITARY SEES ENEMIES EVERYWHERE”
“FROM EAST TO WEST across Africa, 1,700 Navy SEALs, Army Green Berets, and other military personnel are carrying out 78 distinct “mission sets” in more than 20 nations, according to documents obtained by The Intercept via the Freedom of Information Act.”
https://theintercept.com/2016/07/11/in-africa-u-s-military-sees-enemies-everywhere/