“ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ሽፈራው ሽጉጤ
ከሰኞ ሐምሌ 4 ቀን የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰረቀ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጨው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን የት/ት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡ 26 የፈተና ወረቀቶች ተሰርቀው መውጣታቸውን አንዳንድ ድረ ገፆች ያስታወቁ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎችም የእንግሊዝኛ ፈተና መሰረቁን የሚያመላክት መረጃዎች ተሰራጭተዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ፈተናው ተሰርቋል የተባለው “ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል ፈተናው ግንቦት 22 ቀን እንዲካሄድ ታስቦ በነበረበት ወቅት የፈተና ወረቀቶች ስለመሰረቃቸው በተለያዩ ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ መንግት መረጃውን እያስተባበለ ቆይቶ፣ በፈተናው መስጫ እለት ነው በድንገተኛ መግለጫ ፈተናው እንዲቋረጥ የወሰነው፡፡


Good news but need to check befor exam days .
Wushet ke hone yehe mindin new?
ፈተናው… ከፈተና በፊት እንደገና ተሰራጨ (መረጃውን ይዘናል)
July 8, 2016 – ታሪካዊ መረጃ እና ፎቶ ግራፍ, አበይት ርዕስ
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በድጋሚ ከፈተናው በፊት መሰራጨት ጀምሯል። ከአንድ ወር በፊት ፈተናው በተመሳሳይ ሁኔታ ወጥቶ በመባዛቱ፤ ተማሪዎች በድጋሚ እንዲፈተኑ በዚህ ሳምንት ቀነ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ከዚህ በፊት ፈተናው ወጥቶ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው የኦሮሚያ ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱ ለፈተናው መሰራጨት ምክንያት የሆነው፤ “ከወራት በፊት በኦሮሚያ በተነሳው ረብሻ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር። በዚህ ምክንያት የኦሮሚያ ተማሪዎች በደንብ አልተዘጋጁም፤ ስለሆነም የፈተናው ግዜ ይራዘምልን።” የሚል ሲሆን፤ መንግስት ጥያቄያቸውን ባለመቀበሉ…. ፈተናው ከመሰጠቱ በፊት፤ እንዲሰራጭ መደረጉ ይታወሳል።
በወቅቱ የትምህርት ሚንስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ፤ “ፈተናው አልተሰረቀም” ሲሉ ቆይትተው፤ ማምሻውን ግን ፈተናው መሰረቁን አምነው፤ ትምህርት ሚንንስቴር ፈተናውን ሙሉ ለሙሉ መሰረዙን ይፋ አድርጎ ነበር። ከዚያ በአፋጣኝ ፈተናውን ለመስጠት ሲጣደፉ፤ “በረመዳን ጾም ወቅት ፈተናውን ብትሰጡ ዋ!” የሚል ማስጠንቀቂያ ከሙስሊም መምህራን አካባቢ በመምጣቱ፤ ፈተናው ከረመዳን ጾም በኋላ እንዲሰጥ ተወሰነ። እንግዲህ ይህ ሁሉ አልፎ ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እያሉ፤ ፈተናው ለሁለተኛ ግዜ ተሰርቆ መውጣቱ በሰፊው እየተነገረ ነው።
በአሁኑ ዙር ፈተናው ወጥቶ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው ደግሞ የገዢው መደብ፤ ኢፍትሃዊ አሠራር መሆኑን አንዳንድ መምህራን እየገለጹ ናቸው። ምክንያቱን ሲዘረዝሩ… “በየአመቱ ፈተናው ሲሰጥ መምህራን በልዩ የአውሎ አበል ክፍያ ይመደባሉ። ይህን የክፍያ ጥቅማጥቅም መምህራኑ አይጠሉትም። ሆኖም በአሁኑ ዙር ፈተናውን እንዲከታተሉ የተደረጉት የኢህአዴግ ደጋፊ ወይም አባል የሆኑ መምህራንን መሆናቸው ቁጣ ቀስቅሷል።” ይላሉ።
ኬዚህ ጋር በማያያዝም፤ “እንዲህ ያለ የፖለቲካ ስራ በትምህርት ሚንስቴር መስሪያ ቤት በኩል በመደረጉ ለአሁኑ ፈተና መውጣት እና መሰራጨት ተጠያቂው ራሱ ኢህአዴግ ነው።” እያሉ ነው መምህራኑ።
እንደ ድረ ገጻችን EMF እምነት ከሆነ፤ ተማሪዎች አመቱን ሙሉ ተዘጋጅተው ሲያበቁ፤ በአዋቂዎች እልህና ፉክክር ምክንያት መጎዳት እንደሌለባቸው እናምናለን። በዚህ ምክንያት በአሁኑ ወቅት እየተሰራጨ ያለውን የፈተና ወረቀት ይፋ ላለማድረግ አስበን ነበር። ሆኖም ለዚህ ውሳኔ ዘግይተናል። በርግጥ እኛ ባናሰራጨው ሌሎች ማሰራጨታቸው አልቀርም። ስለዚህ ቢያንስ ፈተናው 2ግዜ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው የትምህርት ሚንስቴር ተመሳሳይ ስህተት እንዳይሰራ፤ ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ፍትሃዊ አሰራር እንዲከተል በማሳሠብ ጭምር፤ ከዚህ በታች የእንግሊዘኛውን ጥያቄ ያህል ለህትመት አብቅተነዋል።http://server9.kproxy.com/servlet/redirect.srv/slxv/svecascxxkw/p1/amharic/%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93%e1%8b%8d-%e1%8a%a8%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8d%8a%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%8c%88%e1%8a%93-%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8c%a8-%e1%88%98/
ay wushet; twldn kemegdel yalefe sra yelachum.balefewm alteserekem stlu stsebkun koytachu yefetenaw let meserezun stnageru tnsh alaferachum.ahunm “ጅብ በቀደደዉ ዉሻ ይገባል” legna yebegen neger yelem.bewnet Ethiopia gena ahun motech. lelaw ykr yh fetena tkkli kehone ahunm motachu. egna gin smetachn begodam benante kanget belay enskalen,kkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
በሀገራችን ላይ ሰደይጣን እየተጫወተበት ሰለሆነ እባካተችሁ ከሰይጣን ጋራ አታብሩ።
@Tamene
You are right habesha seytan,debtera, tonkay zer.
Techemari mereja yanbibu http://www.mereja.com/amharic/503473
Ato shguxn mamen aychalm.
Bileq yshalal.
There was day that the wayane popet like Shiferawu Shugute speaks the truth, He is a microphones what someone says he repeat like echo, He is the walking dead who never thinks any for the sake of his people, country or believes for that matter Shiferaw Shugute is a pagan who dosen’t have God and know God ,he is someone who’s in total darkness and his mind is locked that is the reason he killed and washed his souls with innocent people’s blood if Shiferaw had he would have not killed innocent people who stands for their democractic value and right in his mind once he what his masters . There was no time that he stands for his own people, it was a golden time for someone like him to serve his own people rather he turned his ugly face to them and killed over 200 Amhara from Gurafarda and evicted 15,000 people and led other people to robe them.the most horrified and horrendous was that he led to burn down about 4 houses while 1 to 4 days maternity mothers who gave birth to child were in the house.
Shiferawu Shigute is still a fron runner to make harm to Oromo student by refusing to extend the exam date so that they may not get goo result to go to Uni
Shiferaw is killing generation by placing the policy of his colonial master Waya who killed us and robe our land and sold it to make rich their pockets
We shall win, We shall be free one day from the fascist. Wayane/ TPLF who killed 1000 Oromo and perisoned over 10,000 innocent people
Like konejit konejo ሁሌም አደቅሻለሁ
Thankyou
I am really sad of what is being happening in this country.