የኦሮሚያ ኣምቦ ዩንቨርስቲ ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ ኣንድ ክፉኛ ቆሰለ ::

የኦሮሚያ ኣምቦ ዩንቨርስቲ ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ ኣንድ ክፉኛ ቆሰለ ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Ambo‬ ‪#‎BekeleGerba‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – mereja.com በኦሮሚያ ክልል ኣምቦ ዩንቨርስቱ አዋሮ ካምፓስ በተነሳ ግጭት ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ ኣንዱ ክፉኛ መቁሰሉን የካምፓሱ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል፤ በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ያልቆመ ሲሆን በሃረርጌ በወለጋ እና በሌሎች የሸዋ ወረዳዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት እነበቀለ ገርባ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን በቦታው የነበረችው ማህሌት Mahlet Fantahun እንደጻፈችው የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር የሚያደርስባቸውን ሰብአዊ መብት ጥሰት እና ጫና በተያያዘ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ዛሬ የእስር ቤቱ አስተዳደር የሚሰጠውን ምላሽ ለመስማት ነበር ቀጠሮ የተሰጠው። አስተዳደሩ ምላሽ ያለውን በፅሁፍ አቅርቧል። ምላሹን አይቶ ትእዛዝ ለመስጠት ለሃምሌ 8/2008 ቀጠሮ ተሰጥቷል። አቶ በቀለ እና አቶ ደጀኔ ካቀረቡት አቤቱታ ውስጥ ከጤናቸው ጋር የተያያዘ የሆነው ጊዜ መውሰድ ስለሌለበት ቶሎ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠበቃቸው አቶ አመሃ ለፍርድቤቱ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን የሁለቱን የጤና ጉዳይ በተመለከተ ትእዛዝ ተሰጥቷል። በቀለ እና ደጀኔ የታዘዘላቸው መድሃኒት በእስር ቤቱ ግቢ ውስጥ በሚገኘው መድሃኒት ቤት የለም ከተባለ እንኳን ከውጪ ተገዝቶ እንዲገባላቸው እንዲያደርጉ ከቂሊንጦ ለመጡ ኦፊሰሮች ተነግሯል።

በተያያዘ ደጀኔ ጣፋ እናቱ የታደሰ መታወቂያ ስለሌላቸው እስርቤት ገብተው ሊጠይቁት አለመቻላቸውን ገልፆ ወይ ችሎት ውስጥ እንዲገናኙ ወይ በጡረታ መታወቂያ መግባት እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው አቤቱታ አቅርቧል። ዳኛውም እንዲተባበሩት ለኦፊሰሮች ጠይቀዋል። የደጀኔ እናት የሚኖሩበት አካባቢ ቀበሌ መታወቂያቸውን ሊያድስላቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው መታወቂያቸው ያልታደሰው እና እስካሁን ልጃቸውን ማየት ያልቻሉት።ከክሳቸው ጋር በተያያዘ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ዳኞች የሚሰጡት ብይን ለማሰማት ለሃምሌ 25/2008 የተሰጠው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው።

8 Comments on “የኦሮሚያ ኣምቦ ዩንቨርስቲ ሁለት ኦፊሰሮች ሲገደሉ ኣንድ ክፉኛ ቆሰለ ::”

  1. እሚገርም አገር ነው ያለን ።መታውቂያ ለአዛውንት የማይታደስበት ሀገር።ያሳዝናል

  2. መታወቂያ፡ የሌለው፡ ወንበዴ፡ሕዝብ፡የማያውቀው፡ሕዝብን፡የማያውቅ፡ወንበዴ፡መታወቂያ፡ቢከለክል፡ምን፡ይደንቃል?ወያኔ፡ከእግዚአብሔር፡የተጣለብን፡ቦንብ፡ነውና፡የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ወይ፡አንድ፡ሆነህ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አምላካችን፡አልቅስ፡እግዚአብሔር፡ጩኸትህን፡ስምቶ፡ወያኔን፡ኤርትራ፡ባሕር፡ውስጥ፡ያሰጥመዋል፡

    እግዚአብሔር ይርዳን፡ አሜን!

  3. TPLF/Tigray People Liberation Front/Woyane yalteqotaterew neger binor-
    Yemnbelawn,Yemntetawn ena Yemntenefsewn Air bcha new!! Enezihnm beteleyayu ESR bietoch teqotatrotal !!
    Ye Ethiopia Hzb Hoy ! Min eskthon new yemtitebqew ??
    Gobezna Jegnoch Ljochihn eand beand eyaschefechefk new yalehew !!
    100,000,000 Ethiopians BEANDLAY TENESS !!!!
    Yemtitegnabet Gizie eadelem !!!!

  4. Be Millions Yemiqoteru Wogenochachin Beisr biet wst eyemaqequ sihonu, Ethiopia Hagerachin ena bemulu Hzbuwa degmo beTPLF/Tigray People Liberation Front ayne quragna ESR lay new Yalenew !!!! Yih bedenb Metaweq alebet !!!!
    Wogenochie Beand Lay Amriren Eninesa !!!!
    Egziabhier Ethiopian ena Hzbuwan Yitebq !!!!
    Amien !!!!

  5. ትምህርት ቤቶች የነፍሰ ገዳዩች ሆነች! በሰው ደም ታጠበች!

    ተዋበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*