የርሃብ አድማው በአምንስቲ ኢንተርናሽናል ህንጻ ፊት ለፊት ቀጥሏል ።

የሐብታሙ አያሌውን እግድ እንዲነሳለት ማመልከቻ የቀረበለት የወያኔ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዳዩን ከግንዛቤ ሳያስገባ ለማክሰኞ የቀጠረ ሲሆን በናይሮቢ ኬንያ የሚገኙ በስርዓቱ ጫና ለስደት የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ሐብታሙ አያሌው ከአገር የመውጣት መብቱ ተከብሮለት ህክምናውን እንዲከታተል ለመጠየቅ በናይሮቢ በሚገኘው የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ህንጻ ፊት ለፊት የርሃብ አድማ ማድረግ ቀጥሏል ፡፡