ጵጵስናና ፈተናው

ጵጵስና በምድር የከበረ በሰማይ የተመረጠ ሹመት ነው ። ለአማኞች ሞገስ ሊኢአማንያን ደግሞ ፈተና ነው፡፡ የማያምኑባቸው ሰዎች ከብረው ሲያቸው ኢአማንያን ይበሳጫሉ፡፡ ደግሞም የእነሱ ባለመሆናቸው አቃለው ወይም አናንቀው እንዲያም ሲል ሰድበው ለሰዳቢ በመስጠት ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ይጥራሉ። የአማኞች ልቡናን እሰከመከፋፈል ይደርሳሉ። ይህ በዘመን ብዛት የታየ እውነት ነው፡፡ አሁን ግን ግራ የሚያጋባው አማኞች እራሳቸው በግሩፕና በመንደር ተከፋፍለው የሚያደርጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ወሰን አልፎ የመጨረሻውን እስልጣን አካል የሆነውን ሲኖዶሱን ህልውና ላይ ሁኗል ሲኖዶስ ማለት ቀኖና የሚያወጣ የሚያስተካክል የቤተክርስቲያን እራስ መሆኑን ቀስበቀስ እንዲረሳ፤ ቀኖና የመደገግ አቅሙም እንዲያንስ ቢያወጣም ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚደርግ ዘመቻ ወደመሆን ተለውጧል። ይህ ለአማኞች ወድቀት፤ ለሃይማኖቱም ዋጋ የሚያስከፍል የመጀመሪያው መጨረሻ ነው።

ለሲኖዶስ ክብር የማይሰጥ ህዝብ ለጳጳስ አይታዘዝም ለጳጳስ የማይታዘዝ ለቤተክርስቲያን ሥራዓት አይገዛም ይህ ደግሞ ለካህኑም የክህነት አገልግሎት ዋጋ መስጠት ይቀርና ካህኑም ቅጥረኛ ምዕመኑን የቤተክርስቲያን ተመላላሽ ብቻ ይሆናል ። ይህ ማለት ያለ ዋጋ በሃሳብ የሚደክሙ የእግዚአበእሔር በረከት የተለያቸው አማኞች በዙ ማለት ነው ።ይህን ማንም አይፈልገውም ሲሰማም የሚቀፍ ነው ግን እየተደረገ ያለ ሃቅ ነው። ዛሬ አባቶችን የሚያከብር ፤ከሊቃውንቱ ስር ሁኖ የሚጠይቅ ብርቅ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። የጵጵስናን መንፈሳዊ ሃይልነትም ወደመርሳት አዘንብለናል። ጵጵስናን የምመዝነውም በተሾሆሙት አባቶች ልክ ብቻ እየሆነም ነው። በመሰረቱ ጵጵስና ሌላ ተሾአሚም ሌላ ነው፡፡ሁልጊዜም ሁሉ እንደፈለጉት አይገጥም ሁሉም ደግሞ ልክ አይሆንም ሁሉም ልክ ቢሆን ኑሮ መምረጥ ለምን አስፈለለገን መርጠን የገዛነው ሁሉ እንደፈለግነው ሁኖም አያውቅም፡፡ ማበላለጥና ፣ማድነቅን የመሳሰሉት እኮ የሚመጡት ተመሳሳይ በሆነ ቦታ ተመሳሳይ ሰዎች ተገኝተው በሚሰጡት አገልግሎትና ወሳኔ፤ ንግግርና ምክር ተበላልጠው ስለሚገኙ ነው ። በተሿሚዎች አባቶች በኩልም ይህ ሊኖር ግድ ነው ግን አናዳቸውን በምንፈልግበት ሌላኛውን አናገኝ ይሆናል ያንዳቸውን ክፍተት አንዳቸው ይሞላሉ ብሎ ማሰቡ ተገቢ ነው ሁልጊዜ ሰው ፍጹም አይደለምና ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳሃኔቱ የሚለውም ቃል ከዚህ ላይ ይሰራል በዘመኑ ካለው ህዝብ መካከል የተመረጡ ስለሆነ ችግር እንኳን ቢኖርባቸው የትውልዱ ነጸብራቅ ናቸው እናም አባቶች እናክብር።

በርግጥ ጵጵስና ፈተና የሆነበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ግብጾችን ስናመልክ ኑረን የእኛ የምንላቸው ሲሾሙ ከመጀመሪያው ጀምሮ በሽኩቻና በመንድር ተቧድነን ስማቸው ስናጠፋ ችሎታቸውን ስንደብቅ ኑረናል ፡እየኖርንም ነው ።ጣሊያን የገደላቸውን አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል በመቃብር እንኳን ስናበላልጥ! ከሞት ባሻገር ላለው አለም አንዱን ቅዱስ ሌላውን ግን አስታዋሽ የለሽ አድርገናል ። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቲዎፍሎስ ያለ መሪና በቀደመ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት የአሁኑ ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ የመሰለ ታታሪና ትጉህ ሠራተኛ አታገኝም ።ለነዚህ አባቶች የተሰጠው ክብር ስናየው እጅግ ያሳዝናል የስራ ችሎታ የሌላቸው ሰዎች ስራቸው ሲያደናቅፉ፤ ስማቸው ሲያጠፉ፤ በማያውቃቸው ትውልድ እንዲሰደቡ ክፉ መርዝ ዘርተው ያለፉ ብቻ ሳይሆን ያሉም አሉ። እኛም እያየን ፣እየሰማን ኑረናል እየኖርንም ነው። ግን እስከመቼ? ጵጵስና ክብሩ አንሶ ፈተናው በዝቷል። የሚሾሙ አባቶች እውቀታቸው ሳይሆን የተውልድ ሥፍራቸው እየተመዘነ ሃጢያታቸው በዝቶ በአማኙ ዘንድ እንዲጠሉ ማድረግ ቋሚ ሥራ ሁኗል። ለክርስትናውና ለቤተክርስቲያኒቱ ግን ሸክም እየሆነ ነው። ክርስትና ከመንደር ከወጣ ሁለት ሽህ ዓመት አልፎታል ከገሊላ መንደር የተመረጡት አሥራ ሁለቱ ሃዋሪያት ዓለምን ዙረው ክርስትናን የዓለም ሃይማኖት ካደርጉት ቆይተዋል ።

ጠባብ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች በመንደር እድንወስነው ወስነው ስለመንደር ይነግሩናል። እኛ ጳጳስ የሚያስፍልግ መሆኑን ስናምን እነሱ የየት መንደር ሰው ጳጳስ መሆን እንዳለበት ይጨነቃሉ። የሚፈለገው ጳጳስ ወይስ አጎት። ስንላቸው የብሄር ብሄረ ሰብእ ጉዳይ ያነሳሉ ክርስትና በብሄር አልተቋቋም የተመሰረተው ከአንድ መንደር ቢሆንም የዓለም ሁኗል ሲባሉ አይገባቸውም እንዲገባቸውም አይፈልጉም ይልቁንም ብዙ ችሎታ ያላቸውን አባቶች፤ በጥቂት ለሥራ ያልተጠሩ ለወሬ የተፈጠሩ በሚመስሉ ሰዎች ሞራላቸው እየተነካ፤ ስራቸው እየተዳከመ፤ የተፈለገው የአንድነትና የፍቅር አገልግሎት፤ የአባትነትና የልጅነት መንፈስ እየራቀ፤ ልዩነቱም ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ እንዲመጣ አድርገዋል ። የዚህ ክፉ ሥራ ተጠያቂው ወሬ ናፋቂው ትውልድ ነው ዓለም ቴክኖሌጅ ፈጥሮ ለመታወቅና ለመሸለም ሲሮጥ የእኛዎቹ ወሬ ፈጥረው እሮጣሉ፡፡ ታሪክ አዛብተው ይጽፋሉ፡ የእነሱ ሃሳብ ደጋፊ ወይም መንደርተኛ ካልሆነ በስድብ ናዳ ያዎርዱበታል ዓለም ሁሉ እንዲጠላው አቅማቸው በፈቀደ መጠን ይጥራሉ። ግን ለምን ? ዓላማቸውና ግባቸው ምንድነው? በርግጥ ይህን ጥያቄ ቢጠየቁ መልሳቸው ምንእንደሆነ አይታወቅም ከሁኔታዎቹ ግን ተነስቶ መተንተን ይቻላል ።
ይቀጥላል
ሊቀ መራህያን ነኝ
ማንኛውም ሰው እውነቱን ማወቅ ከፈለገ በንጹህ አይምሮ
በዚህ እሜል ሊያገኘኝ ይችላል [email protected]

 

 

7 Comments on “ጵጵስናና ፈተናው”

  1. This is reality & facts about the two Syndos:-

    ዘመድኩን ተሐድሶዎችን አጋለጠ ማለት ተሳስታችኋል ተመለሱ ከውስጥ ሆናችሁ አታድሟት ነው ያለው ምክንያቱም በአንድ ወቅት እነዚህ ስዎች የቤተክርስቲያኗ ጌጦች ነበሩ። ዛሬ ግን ዲያቢሎስ ምላሳቸውን፣ ልባቸውን ተቆጣጥሮ ገንዘብ እንደ አሞሌ ጨው እያሳየ ከመንገድ አወጣቸው ያሳዝናል አይ የስምንተኛ ሺ የካህናት ፈተና? እግዚአብሔር ይርዳቸው ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመልሳቸው። ይገርማል ዲያቢሎስ ካህናትን ከመንገድ ሲያወጣ ሎተሪ እንደደረሰው ነው የሚቆጥረው ምክንያቱም አንደኛ ከእውነተኛው ነጠለው እንዲሁም በሱ ላይ ያለው በሜዳ ላይ ያሉትን ሁሉ ያሳሰታል።

    በአጭሩ እራሳችዎን መመርመር አለባቸው።
    1ኛ አቡነ ማትያስ በውሸት ተመረጡ ከዚያ የኢሐዲግ አባላትን ና የታሐድሶ አቀንቃኞች አስተዳዳሪ አርገው ብሩን ከየቤቱ ክርስትያኑ ዘረፈ አዳራጆች ሌባው ንቡእረ እድ አልያስ የመሰሉ የስንት ፎቅ ባለቤት። ለቤተ ክርስቲያን የሚሰሩትን ማኅበራት እና ጥሩ አባቶችን በየቦታው አገለሉ። አሁን ማንኛውም ደብዳቤ ስፅፍ ግልባጭ ለኢሕአዴግ ሆነ ምሳም እንኳን ሲበሉ ግልባጭ ነው ነገሩ። ይገርማል ያሁሉ ሕዝባችን በኢትዮጵያ ሲያልቅ ፍታት እንኳን አላደረጉም። እነዚህ አይነቶቹ የተሰጣቸውን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስሱደዎል። ከእነሱ በረከት አገኛለሁ ብለህ ግዜህን አታጥፈ ነው የምለው ግን ሐይማኖትህን ጠብቅ ነው የምለው ለህዝባችን ጌታችን የለው እርስ በእርሳቹ ተዋደዱ እንደ እርግብ ሁኑ ግን ጠላትን ስታዩ እንደ እባብ ሁኑ ነው ያለው።
    2ኛ አቡነ መርቅሪዎስ ህጋዊ ጳጳስ ናቸው። እድሜ ለዛሬው አስመሳዪ ፓስተር ታምራት ላይኔ ዛሬ የሚናገረው ሁሉ ፍሬ ከርስኪ የሆነ እና ባክኖ ያለው በዚሁ ግፍ ነው። አገር ውስም ሆኑ ውጭ ህጋዊ ስለሆኑ እውነትን መናገር፣ ቡራኬ መስጠት መንጋውን ያለውን የተሐድሶ አመለካከት አስወግደው በፍቅር መንጋውን በውጭ ያለውን ሁሉ በአንድ ቤተክርስቲያን መሰባሰብ አለባቸው። እንደዚህ ሲሆን ነው እግዚአብሔር የሚለመነን እና ጥሩ ነገ ኢትዮጵያ የምትለው ምድር ላይ በፍቅር የምንሰባሰበው አለበለዚያ የመከራችን ግዜ እየረዘመ ይሄዳል ማለት ነው።
    ለማንኛውም የእነ አቡነ ጰጥሮስ፣ የእነ አቡነ ተክለኃይማኖት ዘኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን እላለሁ። አየህ ወንድሜ እግዚአብሔር የፈለገውን አስነስቶ ያስተምራል እንዳንጠፈ ግን የኛ ድርሻ ነጋ ጠባ ወደ ፈጣሪ መበርከክ ነው ከዚያ ለውጡን ከቤተስብ እስከ አገር ታዩታላቹ። እግዚአብሔር ይርዳን ቻው።
    ለማን ማድላት ይበልጣል ለነፍስ ወይስ ለነዋየ ስጋ?
    Watch ከቻላቹ?
    https://youtu.be/SOKcPeAux-M

    [Reply]

  2. የኢትዮጵያ ጠላቶች እያሉ ሻቢያ፣ወያኔ፣የጎጥ ጠባብ አስተሳሰብ ትንንሽ አስተሳሰብ ያላቸው የሠው ትንሾች ሰው ያልሆኑ የተከሉት ነቀርሳ ካሌ የአፍሪካ ቀንድ ተስፋ ሊኖረው አይችልም፡፡

    እውነቱ

  3. su ,, kkkkkkkkkkkkkkkkkkk

    Miqegna neh su kkk

    papas selaltegegne sayhon

    biqat ena tirat yegolachewal belew new ! teregaga !!!!

    ye ewqet bikat melekeya alew eko kk

    ye ende shabya qetregnoch ,,zem bilen anitereterim !

  4. ከሐይማኖትህ አልቅስ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ከልተገነኘህ በፓለቲካ ዲያቢሎስ ገብቶ ያበጣብጥሀል። ከአጠገብህ ሆኖ የአንተ ሐሳብ ትክክል ነው አያለ እያበጣበጠ ነው።
    የአገር ወስደው ሲኖዶስ የሚመሩት ጊዝያዊ ጳጳስ አባይፀሐይ ስኳሩ ቀጭን ትእዛዝ ቤተ ክርስቲያኗን የሚያዳክሙ እነዚህ የኢሐድግ አባላት የሆኑ መናፍስት ጠሪ ልምድ ያላቸው ተሐድሶዎች ለጰጰስና እንዲሾሙ ትእዛዝ ተላልፏል።
    የአገር ውጭው ደግሞ ስርአት ቤተክርስቲያን እየቀየሩ የሉትም ተሐድሶዎችን ሾማለች።

    ኦርቶዶክሳውያን ኢሕአዴግ እያባለህ የሐይማኖት መሠረትህን አያጠፈ ነው ንቃ!!!

  5. The time has change donot be inocent like before and you have to tell to every KES or PAPAS. Your founders relgion is first and if anything u see outside the rule and regulation tell them u are wrong. If u are not do your part to correct today and you are also responsible on our freedom day following the judgment day. Speak up the truth for what u see for it is not about u are from Tigeri or Gonder and your relgion is first than trash politics!!!!!!!!

  6. እውነትን በእውነት መመስከሩ መልካም ነው።በጅምላ ግምት ጳጳስ ሁሉ መመለክ አለበት ከሚሉት ጋር አልሰለፍም። በተለይ የምንወያየው በባዕድ አገር ስለከተመው ስኖዶስ ከሆነ በአንድ ጀልባ እይተሳፈፍን ነው።እንሰምጥ ዳርቻ እንድረስ መለኮት ነው አዋቂው።

    በተለምዶ ስደተኛው ሲኖዶስ፣ መሐከላዊነት የለውም።የዓመት በጀት የወር ፍጆቱ አልቦ ነው።ጳጳሳቱ አገር ስብከት ሊኖራቸው ቀርቶ አጥቢያ ቤተ ክርስትያነቸውን ማስተዳደር አልቻሉም።ሲኖዶሱ በየስድስት ወራት ከመሰብሰብ የበልጠ የሚፈይደውም የለ።ሲኖዶሱን በተግባር የምንለካው ከሆነ ትንሹ ሚዛን ይኽው ነው።

    ጳጳሳቱን ከነሳን አይቀር ሰማዕት የሆኑትን አቡነ ሚካኤልን ሳይሆን በተመሳሳይ ስም የሚጠሩትን የምዕራብ ካናዳውን ጳጳስ በተግባር ምን አደረጉ እንበል።በመጀመሪያ ወደ ቫንኩቨር ካናዳ አንደኛው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በመደወል እንዴት ቤተክስቲያናቱን እንደከፋፈሉ፣በኢትጵያውያን መካከል ጥላቻ እዳሰፈኑ፣ለክርስትናው ምንም ግድ እደሌላቸው ማስረጃ ማአግኘት ይቻላል።ዛሬ አንደኛው ቤተ ክርስቲያን ምዕራብ ካናዳ ጳጳስም አገረ ስብከትም የለም ብሎ አሜሪካ ሰያትል ካለው አገረ ስብከት ጋር ተጠቃሏል።
    እራሳቸው ወደ ሚያስተዳድሩት የካሊገሪው ቅዱስ ገብርኤል ስንቃኝ እስከዛሬ ለመድሐኒ ዓለም ታማኒ ሆነው በሐቅ ቤተ ክርስቲያኑን ያስተዳደሩ ሁሉ ከቤተ ክርስቲያኑ እንዲርቁ ተደርጓል። ይህም በነገር በማወሳሰብ፣ ተሳዳቢዎችን ቹ በማለት የሚደረግ ነው።ሲያመች እሳቸውም ሰው ለማዋረድ አይሰንፉም። የቤተክርስያን ሕግ አፍርሰው፣ተመራጩ ሳይጠሩት አቤት የሚል ነፈዝ ካሰባሰቡ ሰነበቱ።ስለዚህ ጳጳስ ገለባ ገለባውን ብቻ ሳይሆን በወንጀል የሚያስጠይቃቸው ምን አለ? ብሎ መጠየቁም በፖሊስ ሥራ መግባት እንዳይሆን። ምናልባት በአማኑኤል እውነት የተቃጠለ ከመድረኩ በቃዎት ብሎ ከሚወስደው እርምጃ ያድነን። አሜን።

  7. ሊቀ መራሂያን ነኝ የላከው? አንተ እራስህ የት ቡድን እንደሆንክ በጻፍክው ታስታውቃለህ ያቡነ መልክ ጻድቅ የአባ ወልደትንሳይ መምህር ልኡለቃል ፓስተር መላኩ ያትላንታው ገብሬል ዶክተር አባ ፓለቲከኛው ግሩብ ነህ አንድ ነገር ልንገርህ ቤተ ከርስቲያን አልተሰደደችም አትሰደድምም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*