በኦሮሚያና በአማራ ክልል በግጭቶች የደረሱ ጉዳቶች በድጋሚ እንዲጣሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠየቁ

ከ”330 በላይ ሰዎች ስለመሞታቸው መረጃ አለኝ” – መድረክ
የኢሰመኮን ሪፖርት አንቀበለውም ብለዋል

Addis Admass ; የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰቱ ተቃውሞና ግጭቶችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት እንደማይቀበሉት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡ ከማንም የማይወግን ነፃ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ የጠፋው ህይወትና የደረሱት ጉዳቶቹ በድጋሚ እንዲጣሩም ጠይቀዋል፡፡
መድረክ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት ከ330 በላይ ዜጎች ስለመሞታቸው መረጃ እንዳለው ጠቁሞ የኮሚሽኑ ሪፖርት የሟቾችን ቁጥር በግማሽ ያሳነሰ ነው ብሏል፡፡  በኦሮሚያ ክልል የ292 ሟቾች ስምና ሙሉ መረጃ እንዳለው የገለፀው መድረክ፤ 41 ያህል ማንነታቸው ያልተለዩትን ጨምሮ የሟቾቹ ቁጥር ከ330 በላይ ነው ብሏል፡፡ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና የፀጥታ ኃይሉም ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀሙን የሚገልፅ ሪፖርት ማውጣታቸውን የጠቀሱት ሰማያዊና መድረክ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር 173 ብቻ ናቸው ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ “በተቃውሞ ወቅት በመንግስት የተወሰደው እርምጃ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” ማለቱም የፀጥታ ኃይሉንና መንግስትን ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ የተወጠነ ነው” ብለዋል፤ ፓርቲዎቹ ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ፡፡
ከኦሮሚያ በተጨማሪ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን እንዲሁም በደቡብ ክልል በኮንሶ ወረዳ፣ ዜጎች መብቶቻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ የኃይል እርምጃ ተወስዶባቸዋል ያሉት ፓርቲዎቹ፤ በዚህ ሂደት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል ብለው እንደሚያምኑ አስታውቀዋል፡፡
በየአካባቢው ተቃውሞና ግጭቱን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን ገለልተኛ አካል እንዲያጣራ በተደጋጋሚ መንግስትን ሲጠይቁ እንደነበር የጠቆሙት ፓርቲዎቹ፤ “መንግስት ጥያቄያችንን ቸል ብሎ ራሱ መርጦ ባቋቋመው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዲጣራ ማድረጉ የተቃዋሚዎችን ጥያቄና ማሳሰቢያ ወደ ጎን መግፋቱን ያመለክታል” ብለዋል፡፡ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ያልተጣራ በመሆኑም ኮሚሽኑ ያቀረበው ሪፖርት ተአማኒነትና ተቀባይነት የሌለው ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፤ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞና ጉዳዩ በድጋሚ ተጣርቶ፣ ጉዳቱ እንዲገለፅ አሳስበዋል፡፡ ተቃውሞና ግጭቶቹን ተከትሎ የታሰሩ የፓርቲ አባላት፣ አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን እንዲፈቱ የጠየቁት ፓርቲዎቹ፤ በማረሚያ ቤት ይደርሳሉ የሚባሉ የመብት ጥሰቶችም በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳስበዋል፡፡ በሌላ በኩል በቅርቡ በአዲስ አበባ “ህገወጥ ግንባታ ናቸው” በሚል እየፈረሱ ያሉ ቤቶች፤ የዜጎችን መጠለያ የማግኘት መብት የሚቃረንና የሰው ህይወትም እየቀጠፈ በመሆኑ ድርጊቱን እንቃወማለን ብለዋል – ፓርቲዎቹ፡፡
ቤቶችን የማፍረስ እርምጃ በርካቶችን ቤት አልባ አድርጎ፣ ለተጎሳቆለ ኑሮ እየዳረገ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፤ መንግሥት ከድርጊቱ እንዲታቀብ ጠይቀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግስት ተገቢውን ካሳ በመክፈል እንዲያቋቁማቸው የጠየቁት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ፤ የልማት ተነሺዎችም በአግባቡ መብታቸው ተጠብቆ መስተናገድ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

4 Comments on “በኦሮሚያና በአማራ ክልል በግጭቶች የደረሱ ጉዳቶች በድጋሚ እንዲጣሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠየቁ”

  1. ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሁለት ብሔሮችን ሞት ብቻ ለምን ይዘፍናሉ። በደቡብ ክልል የኮንሶ፣ የጎፋ…ወዘተ ከኢትዮጵያዊያን አይደሉም እንደ? ማረም የሚገባቸው ጉዳይ ነው።

  2. MEDREK AND SEMAYWI” where were you been while human right organization is acusing the brutal is killing more than 400 peace full protesters in oromia region and more masacre in Gonder,Wolkait Tegede,Tslemt,Gambela Afars and all over Ethiopia.Why now? Why noy before? According to human right documented record rhe death toll rise more than you say. How ever your sleepy manifesto seems as a poletical gambling.

  3. Specialy the so called “MEDREK”the same age with EPRDF> what good things have they done for the country and its people except warming the chair inside their office? Specially the so called Dr.BEYENE PETROS.

  4. To Dr Beyene petros haven’t you seen your hidden poletical gambling mission which is kept secertly for a long years but now exposed by Ato Asefa Chebo? If so we don’t expect you acting as a poletial leader. May be woyane will post you as Ambassador some thing like that.good by” papa”DR. Beyene Petros!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*