ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሆኖ አያውቅም (ኤርሚያስ ቶኩማ)

ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሆኖ አያውቅም
(ኤርሚያስ ቶኩማ)
ግንቦት 7 ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል ተብሎ የተፃፈውን የኖአሚን በጋሻውን ፅሁፍ አነበብኩት። ይህንን ፅሁፍ እንዳነበብኩኝ ቀጥታ የአበበ በለውን ድህረ ገጽ ከፍቼ አበበ በለው ከአቶ ከግንቦት 7 አመራር ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ሰማሁት። አቶ ንአመን ሻአቢያን በመደገፍ ፒቲሽን እንድንፈርም ጠይቀዋል። ኤርትራ ውስጥ ማህበራዊ ፍትህ አለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደግሞ ኤርትራ ብቻ ሳይሆን አሜሪካም አለ ብለውናል እዚህ ጋር ረሐብ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን አሜሪካ ውስጥም አለ ያሉትን የቀድሞ የወያኔ መሪ መለስ ዜናዊን አስታወሱኝ። ህፃናት እና አዛውንትም ሳዋ ማሰልጠኛ የሚገቡት በፍላጎታቸው ነው ብለውናል። የኤርትራ መሪዎች በህዝባቸው ላይ አይፈነጭም፤ ከፈለክ ፕሮፌሰር መስፍንን ጠይቀው ብለዋል አቶ ንአመን።
አቶ ንአመን Neamin Zelekeየሻአቢያን አመራር ውብ አድርገው ስለው አቅርበውልናል። የሻአቢያ እና የወያኔ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት ለሁሉም በግልጽ የሚታይ ሆኖ ሳለ አቶ ንአመን ለምን የሻአቢያን ውብነት ለምን መግለፅ እንደፈለጉ ሊገባኝ አልቻለም። የኢሳያስና የወያኔ ሰዎች ሰው በላነት የጥቁር ህዝብ ያፈረበት በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ መፃፍ አልፈልግም እኔ ማሳየት የፈለግኩት የሻአቢያን ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነው። በዚህም ዙሪያ ስለሻእቢያ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ፌስቡክ ላይ የፃፍኩትን ደግሜ ላስነብባቹህ።
አንዳንድ ወዳጆቼ ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደሆነ ለማሳየት ሲሞክሩ በተደጋጋሚ አያለው ሆኖም የሻአቢያን ተፈጥሯዊ ባህሪና ድርጊት ለተመለከተ ሰው ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለውም ለዚህም ማስረጃዎችን ላቅርብ
ደራሲው “ሻዕቢያ” ወይም “ህዝባዊ ግምባር” ተብሎ በሚጠራው የኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅት ውስጥ ከ1974 ዓ.ም ታጋይ የነበረው ግለሰብ “ትልሚ ንዘርኢ ክርዳድ” ብሎ በፃፈው መፅሀፍ ላይ ስለአማርኛ ቋንቋ የሻአቢያ አመራሮች የነበራቸውን ጥላቻ ፅፎታል በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ሰማይ ብሎግ አዘጋጁ ጌታቸው ረዳ ወደአማርኛ ተርጉሞት በመፅሀፉ ውስጥ ደራሲው ስለአማርኛ ቋንቋ የገለፀውን እንዲህ አስቀምጦት ነበር።
“ኤርትራ ውስጥ የአማርኛ ሙዚቃ እንዳይደመጥ በሕግ ተከልክሎ ነበር። በየሙዚቃ መሸጫ መደብሮች ውስጥ የነበሩ የአማርኛ ሙዚቃ ካሴቶች፤ሲዲዎች እና ቪዲዮዎች በዘመቻ እንዲሰበሰቡ ተደረገ። አማርኛ ሙዚቃን ያዳመጠ ወይንም ያዳመጠች ከባድ ቅጣት እንደሚደርስባት ማስጠንቀቂያ ተላለፈ።” ይላል የሻአቢያ አባል የነበረው ደራሲ
ከዚህ ደራሲ ውጭ የሻአቢያን ፀረ ኢትዮጵያዊነት ያጋለጡት የጀብሃ ታጋይ በሗላ ድርጅቱን ከድተው በሰላም ወደ አገራቸው በመመለስ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማጋለጥ የታሪክ ባለውለታ የሆኑት ኤርትራዊው አቶ ተስፋሚካል ጆርጆ በወቅቱ ስለሻእቢያ ፀረ ኢትዮጵያዊነት በሰፊው ገልጸውታል። ይህ መረጃ ይፋ በማድረጋቸውም በኢሳያስ ትዕዛዝ አገሬ ብለው ሰላምና መረጋጋት አለ ብለው ያለስጋት እኖራለሁ ብለው አዲስ አበባ ይኖሩ በነበሩበትት ወቅት ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በሗላ እቤታቸው ድረስ ስልክ ተደውሎ ትፈለጋለህ ተብለው ከቤታቸው ሲወጡ በነብሰ ገዳዮች ጥይት አዲስ አበባ ውስጥ ተገድለዋል።
ስለሻእቢያ ሲወራ ሻአቢያ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ በየጊዜው የሚፈፅመው በደልም መነሳት አለበት ሁላችንም ልናውቀው የሚገባው በትግራይ ወገኖቻችን ላይ በሻእቢያ የሚፈፀመው ግፍ እንደኢትዮጵያዊ ሊያመን ይገባል የትግራይ ገበሬዎችን እያፈነ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል የሻአቢያ መሪ ካለ ገደል ይግባ። በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ላይ ምንም አይነት ጥቃት የሚፈጽም የኢትዮጵያ ጠላት ነው በኢትዮጵያ ልንደራደር አይገባም አንጋፋው ፖለቲከኛ አሰገደ ገብረሥላሴም በቅርቡ በፃፈው መፅሀፍ ላይ ስለጉዳዩ ሲገልጽ
“በሰሜኑ (ትግራይ) አገራችን የሚኖሩ ዜጎቻችን ከሚኖሩባቸው ገጠሮች ደንቅ ደፈጣ እየተደረገባቸው እየታፈሱ በሺዎቹ የሚቆጠሩ በሻዕቢያ ታፍሰው በሳሕል በረሃዎች በ15ኛው ክፍለዘመን የሰው ፍጡር “ጊላ/ባርያ” እየተባለ ግፍ ሲፈጸምበት አንደነበረው ዓይነት አያያዝ የተያዙ ዜጎቻችን አሉ።” ይላል ሻአቢያ ያፈነው የትግራይ ወገኖቻችንን ብቻ አይደለም ከአንጋፋው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እስከ ወጣቱ ተስፋሁን አለምነህ ድረስ በሻእቢያ ደብዛቸው ጠፍቷል።
ኢሳያስ አፈወርቂ ሲፈልግ የኢትዮጵያ ታሪክ ተንታኝ መሆን ይፈልጋል በ2013 የአዲስ አመት መግለጫ ለኤርትራውያን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ‹‹ኢትዮጵያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች አገር ነች›› በማለት መናገሩ ይታወሣል ይህንን መሀይም ሠው ነው የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም የምትሉት? የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሱ ባሉ መሀይም የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚነገር አይደለም ስለኢትዮጵያ ማወቅ የፈለገ the martyr Dom of Man የተሰኘ በ1850ዎቹ የተፃፈ በግብጾች ካለበት እየተሰበሰበ ይቃጠል የነበረን መጽሐፍ ያንብብ መጽሐፉን ለማታገኙ በቅርቡ በፒዲኤፍ ጀባ እላችኋለሁ
በመጨረሻም ኢሣያስ አፈወርቂ የአባቱን ስም ከአፈወርቅ ወደአፈወርቂ የእናቱን ስም ከአዳነች ወደአድሀኖት የቀየረው ለአማርኛ ያለውን ጥላቻ ሲገልጽ መሆኑን እንኳን ልንረዳ ይገባል። በተረፈ እኔ ስለኢሳያስ ጸረ ኢትዮጵያዊነት እንደፃፍኩት ሁሉ ኢሣያስ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ነው የምትሉ ሰዎች ማስረጃ ብትሰጡኝ ደስ ይለኛል።
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም ሞት ለፀረ ኢትዮጵያ ሐይሎች በሙሉ
[email protected]
‪#‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬

27 Comments on “ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሆኖ አያውቅም (ኤርሚያስ ቶኩማ)”

  1. እንዲ ነው እንዲያ ነው የሚለውን ትተን መፍትሄውን እናስቀምጥ ፍልስፍናውን ሌላ ጊዜ እንደርስበታለን

  2. Nigat minew amemesh ???

    ye shabya wedajoch ,,ye Ethiopia telatoch selehonu

    meweged alebachew ?

    YE SILTAN timm yasabedachew enezeh

    bandoch 4 kilo begebu yefejunal

    they r anti Ethiopia and andinet !!

  3. it seems woyane is on a death row. this is a sign that when a regime is about to die.

    how cool would that be to see the end of banda TPLF?

    long live ethiopia!
    Long live ethiopian fighters for freedom and democracy, including to those in Eritrea!

  4. ወንድሜ አትድከም ብዙ ብታወራ ስምህን እየቀያየርክ ብትመጣ ትግሉ ተጀምሯል። አዛኝ መስለህ ለወያኔ አጎብዳጅ ለማድረግ አትሞክረው ጊዜው አልፏል። ምነው እንደዚህ ግንቦት 7 ን ጥምድ አደረጋችሁት? ገብቶናል እግር አውጥቶ መቆምና መራመድ ስለጀመረ አንገበገባችሁ። ወያኔን ሻቢያ አዲስአበባ ባያስገበው ኖሮ አራሱ የትም እንደማይደርስ ስለምታውቁ እርር ድብን አላችሁ። ግንቦት ሰባትን ለቀቅ

  5. We now have no ethiopia.which ethiopia are yoy talking about?esyas gelemele bulshit.no body mis that.don’t tell meabput how bad afuerki is.tell me which way i can get my ethiopiqinet ,where i can’t find it.be ouse tell me if i cqn go to oromiya or tigei how to get land ownership or even rind a job there with out being dedeb like tplf.?that is ther burning issue.why can’t you write about a solution instead of of submiting your telltale story.

  6. Olf ena Oromo meleyet ayichalim onlf ena ethio somalenim meleyet ayichalim g7 ena yeandinet hayiloch ethiopiyswi endihu enezih degmo be Eritrea yidegefalu .yeshabiyanina ye g7 wedajinet lemin anadedachihu sile olf ena onlf be shabiya meredat gin atawerum

  7. kedami measike neriwo akimi.brise mitihat zisake zelo futur eyu.hasab orom hasab amhar konka etemestaka kem nefahito hibrika mikiyyari eyu.dil le AG7 TPDM OLF biretim mansatachew min talekisale. Lenegeru rasi aydelem biretim endyanesu yawejikew. malikesim lemindinew ahun.

  8. የኢትዮፒያ ወዳጅ ሆኖ የሚያውቀው ቀንደኛው ጠላታችን ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ ከትግሪና ከኢርትሪያ የተውጣጡ ኢርትሪያን ነጻ አውጥተው ትግሪን ነጻ ለማውጣት ኢትዮፒያን ማጥፋት ብለው ያለሙ እየሰሩ ናቸው 25 አመት ሙሉ ምርጥ የኢትዮፒያ ዚጎችን ሲስተማቲካሊ በዘር በመከፋፈል በተራ በተራ የጨፈጨፈው ዘር እያጠፋ ያለ በስማችን ከሃያላን አገሮች ጋር የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ለትግሪ ህልውና እየሰራ ያለ ዘሩን አምላኪ የትግሪ ነጻ አውጭ ህወሃት ነው:: የኢትዮፒያ ህዝብ ሆይ ህወሃት የአምሃራን ህዝብ ለመቀነስ ያደረገው እስትራቲጂ እያንዳንዳን የኢትዮፒያ ብሂር እያካንካች በተራ በተራ ዘር በመጨፍጨፍ የህዝብ ቅነሳ ጋቢላውን , ኦሮሞውን, ሱማሊውን , አፋሩን,ሲዳማውን…..እያለ የኢትዮፒያን ህዝቦች እያጠፋ በወረራ አገር በመቀማት የትግሪ መስፋፋት እየተካሂደ ነው ስለዚህ እያንዳንዱ ብሂር ከመከፋፈል አንድ በመሆን ለነጻነት መታገል ያስፈልጋል ዛሪ ህወሃት ሻቢያ ጠላት ይለናል ትናት አገራችንን ወደብ እና ድንበር ሳይቀር ኢርትሪያ የኒነች ብሎ ያስረከበ ህወሃት ኢትዮፒያን የማይወክል ነው ጠላታችን በስማችን የሚነግድ ነው ሞት ለኢትዮፒያ ጠላቶች!!

  9. ፕሮፌሰር አስራትን በአደባባይ ያዉም በገዛ አገራቸው ያዋረደዉ፣እኛ አባቶቻችሁ አሕያዉን የኢትዮጵያን ወራሪው ጦር ቀጥቅጠን አባረን አዲስ ሀገርን ሰራን እያለ በየዐመቱ ግንቦት በአደባባይ የሚደሰኩረው፣100ዓመት የቤት ስራ ሠተናቸዋል፣ባንዲራችንን በነፃነት በዐሉ በአደባባይ በአሕያ እያሰረገጠ ያዋረደ…የምድር 666 ዐዉሬ እንዴት ደግፉት ይሉናል እነዚህ ወራዶች።ባንዳ ሁሉ የዘመናችን ባንዳዎች ትዉልድ አሠዳቢ በእናንተ እኛ እንመዛለ።ቴዎድሮስ፣ዮሐንስ፣ምንሊክ፣አቡነ ጴጥሮስ…አለማየታቸዉ ምንኛ ታደሉ!!!።ካላስገደዷችሁ ዝምታን ብትመርጡና ለቆማችሁለት ዑላማ ሌት ተቀን ብትደክሙ መልካም ነበር ።እናንተ የታሪክ አተላ የወንድሞቻችን ደም ይፋረዳችሁ።ማፈሪያዉ ነዐመን ፕሮፌሰር መስፍንን እንደዋቢ አርጎ ማስቀመጡ በእዉነቱ አሣፋሪ ነዉ።

  10. እነ ዶ/ር ካሣ ከበደ በሺዎች የሚቆጠሩ የድሮ ጓዶቻቸውን ማለት ኤርትራውያን የደርግና የኢሠፓ ባለስልጣናት የነበሩ ለምሣሌ፥ የአሥመራ ኢሠፓ አንደኛ ፀሓፊ አቶ መብራህቱ ለባሲ ሻዕብያ የት እንደከተታቸው ሣይነግሩን ሥለ አቶ ኢሣያስ ደግነት ያወራሉ።
    ኤርትራ ውስጥ ሥለ ታሠሩት የኢሠፓ ባለስልጣናት ማንሣት ሆነ ማውራት ወንጀል ነው።
    እነዛ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ ጀግኖች የኤርትራ ልጆች በሻዕብያ ደብዛቸው እንዲጠፋ ላደረገው ኢሣያስ ከ ICC ለማዳን ፔትሽን ፈርሙ ይሉናል እነ ካሣ ከበደ።

  11. ኢትዮጵያ ወዳጅ ኖሯት አያውቅም!
    በውስጥ ልጀቾ፣በውጭ ወራሪዎች ስትደማ ዛሬም እያደማች በጎሳ እሳት እየተለበለበች ነው! ይህም የሆነው በሻቢያ፣በወያቤ በኦነግ፣በሱዳን፣በግብጽ፣በእስራኤል በአረብ ሃገሮች ጥርስ ውስጥ ገብታ አሁንም በደም እየታጠበች ነው!
    መቼ ነው ጦርነት የሚቆመው

    እሸቱ

  12. ኢትዮጵያ ወዳጅ ኖሯት አያውቅም!
    በውስጥ ልጀቾ፣በውጭ ወራሪዎች ስትደማ ዛሬም እያደማች በጎሳ እሳት እየተለበለበች ነው! ይህም የሆነው በሻቢያ፣በወያኔ በኦነግ፣በሱዳን፣በግብጽ፣በእስራኤል በአረብ ሃገሮች ጥርስ ውስጥ ገብታ አሁንም በደም እየታጠበች ነው!
    መቼ ነው ጦርነት የሚቆመው
    እሸቱ

  13. ለመሆኑ ነአመን ዘለቀ ምን ያድርጋችሁ ? ነአመን 100%ኢትዮፒያዊነው የሚታገለው ለኢትዮፒያኖች ነው ስለዚህ አሁን የናተ እንዲህ ተቃጥሎ ስለ ነአመን አስተያየት መስጠት ያንገበገባችሁ ኢትዮፒያኖች በ ግቦት 7 የኢትዮፒያ የቁርጥ ቀን ልጆች የዘር ከረጢት ውስጥ ሳይገቡ እንደ አባቶቻቸው በአንድነት ይህ የባንዳ ቀንደኛ የኢትዮፒያኖች ጠላት ኢርትሪያን ነጻ አውጥቺ ለትግሪ ነጻነት ኢትዮፒያን ከፋፍዪ የትግሪ ዘር ነጻነቱ እና ህልውናው እንዲከበር በኢትዮፒያ ህዝብ እና በኢርትሪያ ህዝብ የውጭውን ፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ግዚውን እያራዘመ ለትግሪ ነጻነት ህልውና ለኢትዮፒያ ሞት እየሰራ መሆኑ የኢትዮፒያ ህዝብ ሻቢያን እና ህወሃትን ልዩነታቸውን እንዲያውቁ ስላጋለጣችሁ ነው :: ነአመን ሻቢያ የኢትዮፒያ ጠላት እንደነበረ ያውቃል አዎ ሻቢያ ግን ኢትዮፒያን የወጋው ለ ኢርትሪያ ነጻነት ኢትዮፒያን አንፈልግም በማለት አላማውን ሊያሳካለት የሚያስችለውን ሁሉ ተጠቅሞ 25 አመት ኢርትሪያ እኮ ሊላ አገር ሆናለች የአለም መንግስታቶች ወስነው የጸደቁት ነው ጎረቢት አገሮች ነን ስለዚህ ከመጀመሪያውም ኢርትሪያ ስትገነጠል የሁለቱ ጎረቢት አገሮች ፍቺ ፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ አይሆንም አንፈላለግም ካላችሁ በስረአት ይሁን ሲሉ ቀንደኛው የኢትዮፒያ ጠላት ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ በኢርትሪያ መገንጠል የትግሪን ነጻነት አመጣለው በሚል የኢትዮፒያዊያንን የኢትዮፒያን ምርጥ ዚጎች አስተያየት መብት በመርገጥ የኢትዮፒያን ነጻነት ቀምቶ ኢርትሪያ ከኢትዮፒያ የሚያስፈልጋት ነገርን ሁሉ ተከራክሮ ቃሚ ጠበቃ ሆኖ አስረክባል ስለዚህ ሻቢያም ወይም ኢርትራዊያኑ ለሚያደርጉት የነጻነት ትግል በፈቃደኝነት በኢትዮፒያ ስም ተቀምጦ ጥቅማቸውን የሚያስፈጽምላቸው መንግስት ሲኖር ለመሆኑ ኢርትራዊያኖች ወይም ኢሳያስ እቢ ማለት ነበረበት ወይ? የትኛዋ አገር ነች ለዚጎቻ ህልውና የሚጠቅማትን ሁሉ አደርግልችሃለው የሚላትን መንግስት እቢ የምትለው? አሚሪካ በስማችን የሚነግደው የህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ ኢትዮፒያን እንደወጋ ጠላታችን እንደነበረ እና ከኢርትሪያጋር እኩል ኢትዮፒያን የወጋ መሆኑን ታውቃለች ስለዚህ ኢትዮፒያን ወግቶ ኢትዮፒያ ቁንጮላይ የተቀመጠ የትግሪ ነጻ አውጭ በምን ምክንያት ነው የኢትዮፒያኖችን የትልቃን አገር ህዝብ ፈላጭ ቆራጭ የሆነበት? ለዚህም አሚሪካን የመሰለች ታላቅ ሃብታም አገር ለቲሮሪስት ወታደር ሆነ ከኢትዮፒያ የምትፈልገውን ነገር ወያኒ የትግሪ ነጻ አውጭ በኢትዮፒያ ስም ተቀምጦ ከኢርትራዊያን ይልቅ እኒ አለሁሽ ኢርትሪያ ትንሽ አገር ነች ትልቁ ጥቅም ያለው ትልቅ አገር ኢትዮፒያ ነች አሚሪካ እኒ የምትፈልጊውን ሁሉ እኒ አደርግልሻለው ሲላት ለመሆኑ እቢ አለች ወይ? ኢርትሪያም ህወሃትን ተጠቅማ ከኢትዮፒያ የምትፈልገውን አግኝታ ሂዳለች ኢርትሪያውያኑም ህወሃት በዘር አንድ ስለሆንን ነጻነታችንን ያጸደቀ በማለት ህወሃት ለሚያደርገው የትግሪ ነጻነት የኢትዮፒያን ተቃዋሚዎች እንዳይረዱ ኢርትራዊያኑ የተቀሩትን ኢትዮፒያኖች በተለይ አምሃራውን ጠላታችን የኢርትሪያን ነጻነት የማይቀበል በማለት ለህወሃት ቃሚ ጠበቃ ነበሩ:: ጎበዝ በዋናነት ኢትዮፒያ ነጻነታን ተቀምታ የፈረሰችው የዛሪ 25 አመት ነው:: ይሂውም በሻቢያ እና በህወሃት ስምምነት ስለዚህ የፖለቲካ ቁማሩ እነሱጋ ነው :: የተቀረው ኢትዮፒያዊ ይህ የባንዳ የትግሪ ነጻ አውጭ በተለይ ኦሮሞውን እና አምሃራውን በዘር እና በመሪት ለማባላት ኦሮሞን ይዚ አምሃራን አጠፋለው በሚል አሁንም ኦሮሞ ከኢትዮፒያ ተገንጥሎ የራሱን እድል በራሱ እንዳይወስን የኦሮሞ ጠላት ያለፉ የአምሃራ ገዚዎች ነበሩ ኦሮሞን ወረው ነው በማለት በሁለቱ ማህበረሰቦች ላይ ትልቅ የፖለቲካ ቁማር በመጫወት ኢትዮፒያን ለመዝረፍ እና በኢትዮፒያ ስም የውጭ ሃይሎችን ፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ እርዳታውን ለማግኘትና የትግሪን ህዝብ ነጻነት ህልውና አስከብራለው የሚለውን አላማውን እየተጠቀመበት ነው:: ዛሪ በህወሃት 25 አመት በዘር ማንነታቸው የተጨፈጨፉት ትግሪዎች ሳይሆኑ የተቀሩት ኢትዮፒያኖች ናቸው የትግሪ ተቃዋሚነን የሚሉና የተቀሩት ኢትዮፒያኖች ተቃውሞ እንካን በጣም በጣም ልዩነት አለው የትግሪ ጠቃዋሚዎች በህወሃት የትግሪን ህዝብ አልጠቀመም ደሃ ነው በስማችን ምንም አላደረገልንም የሚል ነው:: የአምሃራው ጥያቂ ከድህነት ያለፈ የማንነት መብት መረገጥ አገር መቀማት መወረር የዘር መትፋት ችግር ነው:: የጋቢላውም እንደዛው , የሱማሊው , የአፋሩ, ዛሪ ኦሮሞ ይገነጠላል የራሱን እድል በራሱ ይወስናል እየተባለ የኦሮሞን ህዝብ የውስጭ ፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ሲያደርገው የነበረው ወያኒ ህወሃት ኦሮሞም የማንነቱ ጥያቂ የዘር ማጥፋት ወረራ እየተደረገብኝ ነው በሚል የሚደረግ ጥያቂ ነው :: ስለዚህ ወያኒ የትግሪ ነጻ አውጭ የብዙ ሚሊዮን ህዝብ መብትና ነጻነት ለማጥፋት በዋናነት ሲጠቀምባት የነበረችውን አገር ኢትዮፒያ ከኢርትሪያ ሲጣላ ነው እንዲ ሁሊ ኢሳያስ ጠላታችን ነው የሚባለው ? ኢሳያስ በቃ እንደነ አሚሪካ ቁጠሩት ህወሃት እኒ የምትፈልገውን አደርጋለው ብሎ አንተ ደግሞ ለኒ ጥቀመኝ የነበረ የፖለቲካ ጨዋታው አለቀ:: የኢሳያስ ፍላጎት የኢርትሪያን ህልውና ለማስከበር ነው የህወሃት ፍላጎት የትግሪን ነጻነት ህልውና ለማስከበር ነው ስለዚህ በምን ተአምር ነው ኢሳያስን እና ህወሃትን የምታወዳድሩት? ነአመን ዘለከ ያለው የሱም ቢተሰቦች ይሁን የኢትዮፒያ ህዝቦች በኢርትሪያ ጉዳይ ያልሞተበት ህዝብ የለም ከአድዋ ጀምሮ ግን ሃቁ እና መሪት ላይ ያለው እውነታ ኢርትራዊያን ኢትዮፒያን አንፈልግም ብለው በኢሳያስ ነጻ ወተው እንደ ጎረቢት ኪንያ ጅቡቲ ያሉ ህዝቦች ናቸው ::ስለዚህ ይህንን መቀበል አለብን እኛ ኢትዮፒያኖች ግን በህወሃት ነጻነታችንን እና መብታችንን ተረግጠን አገራችንን አተናል ዘሮቻችን እየጠፉነው ትግሉ ይህ ነው :: የኛ ትግርል ከኢርትራዊያን ጋር ሳይሆን ከህወሃት ጋር ነው :: ህወሃት የኢርትሪያን ነጻነት እንደ አገር መቆም ተቀብሎ ለምን ኢርትሪያ እኒ በምለው መሰረት ለትግሪ ህልውና አትቆምልኝም ብሎ ኢርትሪያን የኢትዮፒያ ጠላት ነች ሲለን እንደው የኢትዮፒያ ህዝብ ደንቆሮ መሰላችሁ ወይ ? በሊላ በኩል እኛ ኢትዮፒያኖች ኢርትሪያን ከኛ ጋ አወዳድረን ልዩነቱን የመናገር መብት አለን የምናየው ከኛ ከራሳችን ጋር ስለሆነ ኢትዮፒያኖች አሁን ነአማን የሚለውን ነገር ቢደግፉ ችግሩ ምንድነው? ነአመን ኢሳያስ የሚያስተዳድረው ለኢርትራዊያን ወቅ በወርቅ ነው አላለም:: በዋነኛነት ግን ኢሳያስ ኢርትሪያን እንደ አገር እየገደለ አይደለም ሰው እየገደለና አገር እየገደለ ያለ ትልቅ ልዩነት አለው:: የኢርትሪያ ህዝቦች የሚፈልጉት ዲሞክራሲ ነው :: የዘር ማንነታቸውን እያጠፋ ለዘሪ ብሎ በኢርትሪያ ሃብትና ንብረት ሃያላን አገሮችን ተጠቅሞ ለዘሩ ህልውና እየሰራ ያለ መንግስት አይደለም:: ይህ ነው የኢትዮፒያዊያን እና የኢርትሪያ ልዩነት:: ስለዚህ ነአመንን የምትቃወሙ አስመሳዮች የኢትዮፒያ ጠላቶች ናችሁ በተለይ ኢትዮፒያውስጥ በዘር ማንነታችን እየተጨፈጨፍን ላለነው አምሃራ , ኦሮሞ, ጋቢላ, አፋር,……የሞት ሞታችንን እና ውድቀታችንን የምትመኙ በህወሃት ተጠቅማችሁ በኛ ሃብት የትግሪ ዘር ነጻነትና ህልውና ይገኛል ብላችሁ ሊት ተቀን አስመስላችሁ በታክቲክ እና በሲስተም ለማጥፋት የቆማችሁ የትግሪ ዘር የምትሉ የህወሃት አስፈጻሚዎች ከኢርትሪያና ከትግሪ የተውጣጣችሁ የኢትዮፒያ ቀንደኛ ጠላቶች ናችሁ :: አሁን የኢሳያስ ከህወሃት ጋርም ጦርነት የሚያሳስባችሁ እና በኢርትራዊነት ኢሳያስን የምትቃወሙ ህወሃት እኒ ከሊለሁ ኢርትሪያ አትኖርም በማለት የሚያዘርፋችሁ ለጥቅማችሁ ስትሉ ነው ኢርትሪያን ይዛችሁ ኢትዮፒያን ለማጥፋት የምትተባበሩት:: ለመሆኑ ወደብም ሆነ ድንበር ህወሃት የኛ ስለሆነ ተስማምቶ ነጻነታችንን አጸደቀ ብላችሁ አልነበር ታዲያ ህወሃት ድንበር አጽድቆ የኢርትሪያን ነጻነት የተቀበለ ዛሪ ኢሳያስን የሰጠሁህን ድንበር መልስ ይሂ የኒነው እያለ ህወሃት ኢርትሪያን እወጋለው ኢሳያስ ጠላቲነው ሲል ጎበዝ አገር እኮነው በአገር ጉዳይ ላይ ህወሃት እንደ ህጻን ልጅ አንዲ ባድሚን አንዲ ጸሮና, ሲለው ወደብ እያለ እኛ ኢትዮፒያኖችን ለማዘናጋት ልባችንን በኢትዮፒያዊነት ለመስለብ ህወሃት ቦታ የለውም ነቂ ብለናል ቁማራና ጨዋታዋ ህወሃት የውጭ ሃይሎችን የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት የሚያደርገው ጥረትና ኢርትራዊያኖች ኢሳያስ ከነ አሚሪካም ሆነ ከተቀሩት ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው የሚደረግ ይህወሃት ሲራ ነው:: እኛ ኢትዮፒያኖች ግን ተወደደም ተጠላም በአንድነት ለነጻነታችን እንታገላለን ኦሮሞና አምሃራ ደግሞ የአንድ እናት ልጆች ናቸው የኢትዮፒያ ጀግኖች ናቸው አምሃራውን አጥፋታችሁ ኦሮሞውን ከኢትዮፒያዊነት አውጥታችሁ መላው የኢትዮፒያን ህዝብ ለትግሪ ዘር ህልውና ነጻነት አገር ለማስረከብ እየሰራችሁበት መሆኑን ነቂ ብለናል ስለዚህ አሁን ያለው እውነታ ሻቢያ ከመጀመሪያውም ለኢርትሪያ ነጻነት የሞተ ኢርትሪያን ይዞ የተቀመጠ ::
    ህወሃት ለትግሪ ነጻነት የሞተ ከትግሪና ከኢርትሪያ የተውጣጡ ኢትዮፒያን ለማጥፋት ከውጭ ሃይሎች ጋራ የፖለቲካ ቁማር የሚጫወት ከውስጥ የዘር ልሂቃኖችን እየፐወዙ በኢትዮፒያ ስም እየነገዱ ያሉ ለመሆናቸው ግቦት 7 አይደለም በዘር ማንነቲ እነግሳለው ያለ ሃላቀር ሁሉ ህወሃት ማለትና ሻቢያ ማለት ልዩነቱን ጠንቅቆ አውቃል ሞት ለህወሃት ለኢትዮፒያ ጠላት!!!

  14. Tell them more for those fortune hunters and HODAM BANDITS. Note: Ato Ermias Tokuma-all your article is a folk tale and tottaly sensless.bla bla bla….

  15. Barriya arg yetbalwn madrg neaw
    Ke Neamin yenefsgeday betseb weder
    Yemaygnlt Shumbash banda tesfa kortwal . Inezih sewoch yalachew
    Ke barriya huno mqetl bicha neaw.
    Shabiya indiet qesblo belo enslave
    indemiyaderg ine Elias Kefle , Demis Belete ena Solomon Tekalgne
    asredtwunal. Ahun inkoan netsa mawtat yerasachewnm netsant
    aswesdew arefut. Yemigrmew ahunm
    Kokeb Ethiopianohin beadebabay
    lehodachw baderu yetawku yeketemw
    Leboch Tilahunin Gesessen kasedbu
    Wediyaw le Slave Masteru
    ISIS AFEWORKI petition fermu silu
    neaw yehienin min yahil indenaqut
    yetegenezebneaw.
    ” BALEBETUN KALNAQU ATERUN AYNEQENI ” Ale Amhara sitert.

  16. BEAND GIEZE BE HULETUM HIZBOCH
    Be Ethiopians ina be Eritrean yetetefa Sebesb binor betarik
    GIMATAM 7 BICHA Neaw.
    Long live EPRDF
    LONG LIVE U S A

  17. የማነህ ጭገራም ወያኔስ ለኢትዮጽያ መቼ ጥሩ ሆኖ ያውቃልና ነው የከረፋ አፍህን የምትከፍት8ው ቁልቆል ፊት ወይኔ ሌባ

  18. It sound like long way to go before we see any other regime. Oppositions are weak. We expected G7 but nothing is happening. What do u think olf. Just banch of damp. They talk nonesence while our people suffering . The main core problem is here. OLF full stop. Can anyone foresee the hope of ourcpeople. Nothing. We are just dreaming. If we want to liberate our people those banch of damps have to drop their old idiology or ignore them and lets prepair to make history. Please do not deny the fact. It is too late now to be deplomatic.

  19. It looks like G7 and Co. are in the verge of collapse. Neamin’s ridiculously blind support for Eritrean Thug is a testimony that G7 is no longer operating independently. It becomes an appendage for Eritrea political offensive against UN condemnation. It is becoming increasingly apparent that G7 is no longer perusing its goal, instead coerced to do the dirty laundry of Shaebiya. Eritrea is a police state dubbed as the North Korea of Africa, and Neamine is sweating to tell us a story on head on collision with the objective reality the world already know. He is really lame, clumsy and exposed his ignorance when Abebe confronted him Eritrea without constitution for a quarter of a century and how that could be attributed with the war with TPLF. In my view, let alone a country, a small association will not run without constitution unless you are in the good old stone age. Anyway, Mr. Yared just dressed Neamin down with a level headed of maturity and logical wisdom that Neamin should no longer dare open his mouth to defend the brutal dictator the world would love to see go down the trash bins of tyrants history. Neamin, when you open your mouth, we have an excellent chance to see your empty head. Thanks.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*