ቤተ ክርስቲያን አባቶች ዕርቀ ሰላም እና የዘመናችን ፖለቲካ

መግቢያ
 
በሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ግርግር የሁልጊዜ ተጠቂ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት መከራ በመቀበል ኖራለች።  የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳን ብናነሳ በኢጣልያ ወረራ ወቅት ስለሀገር ሉዓላዊነት የመሰከሩና ህዝቡ ለወራሪው እንዳይገዛ ያወገዙ ሁለት ብጹዓን ኣባቶች (ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል) በመትረየስ ጥይት ተደብደበው ተገደሉ። እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና ካህናት በየገዳማቱና አድባራቱ በግፍ ተጨፈጨፉ። በ1966ቱ አብዮት ማግሥት ፓትርያርኳ በግፍ እና በአረመኔያዊ ጭካኔ በሲባጎ ታንቀው በደርግ ኮማንዶዎች ተገደሉ። 
 
የዛሬ 25 ዓመት ገደማ በትረ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወያኔ በስልታዊ መንገድ በቀሰቀሰው “የቤተ ክህነት ነውጥ” የቤተ ክርስቲያኗ 4ኛ ፓትርያርክ ከመንበራቸው እንዲወርዱ አድርጎ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ፈጸመ። በዚሁ የወያኔ ጣልቃ ገብነት የቤተ ክርስቲያን አባቶች በአንዲት እምነት እያመኑ እና የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ጠላት ማን እንደሆነ ልባቸው እያወቀው “ሕጋዊ እኛ ነን፣ እናንተ አይደላችሁም” እየተባባሉ መለያየት ጀመሩ። የሚገርመው “ሕጋዊ”  የምትለው ቃል በሁለቱም የአባቶች ቡድን ዘንድ የምትጠቀሰው በተለያየ መንገድ ነው። 4ኛው ፖትርያርክ በሕይወት እያሉ በመንበረ ፓትርያርኩ ሌላ አይሾምበትም የሚሉት አሁን በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙት አባቶች የሚጠቅሱት የቤተ ክርስቲያኗን ሕግ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ያሉት የተቀሩት አባቶች ደግሞ 4ኛው ፖትርያርክ በፖለቲካ ጫናው ከመንበራቸው መውረዳቸውን [ሳይክዱ] በተግባር ሊፈጸም የሚችለው (ወያኔ የሚፈቅደው) የሚቀጥለውን አባት መርጦ መቀጠል ብቻ እንጂ ፓትርያርኩ ይመለሱ ብለን ልንከራከር የምንችልበት አቅም አጥተን ያደረግነው ስለሆነ ሕግ እንደጣስን መቆጠር የለበትም ባይ ናቸው። (በዘመነ ደርግ የፖትርያርኩ በህይወት ያለመኖር ሳይረጋገጠ 3ኛው ፖትርያርክ እንደተሾሙት ማለት ነው።)
 
በዚህ ሁኔታ ፍጹም አስተዳደራዊ የነበረውና በአባቶች ውይይት በቀላሉ ሊፈታ የሚችለው ችግር በዋነኛነት በፖለቲከኞች ጫና (በሀገር ቤት በወያኔ በውጭ ሀገር ደግሞ በተቃዋሚዎች) ተካሮ በተለይም ከጥቂት ዓመታት በፊት አሜሪካ ባሉት አባቶች በተደረገ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ምክንያት ልዩነቱ ተካሮ እስከመወጋገዝ ተደረሰ። በሀገር ቤትም በአሜሪካም ያሉት አባቶች ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ሲያያዝ በመጣው የሥልጣነ ክህነት ቅብብሎሽ መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሾሙ በመሆናቸው (የተላለፈው ውግዘት እምብዛም ክብደት አይሰጠው) እንጂ ለመጪው ትውልድ  መዘዙ ብዙ ነው። (ውግዘት ትልቅ ሃይማኖታዊ ትርጉም ያለው ጽንሰ ሐሳብ በመሆኑ)። 
 
ይህን እንድናነሳ የሚያስገድደን ….
 
ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና በአሜሪካ የተደረጉትን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጉባኤ ሂደትና በጉባኤያቱ የወጡት መግለጫዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባዎች አንዱ ሰሞኑን ሲካሄድ ሰንብቶ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ብቻ በዝግ ቤት በፍጹም መንፈሳዊ ሥርዓት የሚያደርጉት ይህ ስብሰባ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ፍጹም መንፈሳዊ እና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንዲፈጸም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያዛል። የቤተ ክህነቱን “ፓለቲካ” ወደ ጎን ትተን ከዚህ በላይ በተመለከተው ማዕቀፍ ብንመለከተው በሀገር ቤትም ሆነ በአሜሪካ ያሉት አባቶች በሁለት የመሰብሰቢያ ቦታዎች ሆነው ስለ ነገረ ቤተ ክርስቲያን መክረዋል ብለን ልንነሳ እንችላለን።
 
 በሥልጣነ ክህነት ተዋረድ ለምትመራው ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወሳኝ የሆኑ ሃይማኖታዊ ጕዳዮች የሚታዩበትና በመሆኑ በፍጹም ነጻነት መከናወን አለበት። ይሁንና በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉት አባቶች ይህ ነጻነት እንደሌላቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። የወጡትን መግለጫዎች ይዘት በሚገባ ብንመለከታቸውም በሁለቱም ቦታዎች ያሉት አባቶች በፖለቲካ ጫና ሥር (የሀገር ቤቱ በወያኔ፥ የአሜሪካው ደግሞ በተቃዋሚው) እንዳሉ መገንዘብ አያዳግትም። ይህ ማለት ግን አባቶቻችን ስለ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚወስኑት ውሳኔ ተቀባይነት የለውም ወደሚል መደምደሚያ አያደርሰንም። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ የአላውያን ነገሥታትና ፖለቲካኞች ተጽእኖ የሁልጊዜም ፈተናዋ ነውና። ልዩነቱ በየዘመኑ ተጽእኖውን የሚረዱና የሚቋቋሙ፣ ለቤተ ክርስቲያን ወግነው ለወንጌል ዓላማ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ አባቶች መብዛትና ማነስ ብቻ ነው።
 
 ፓለቲካ ነክና ሌሎች አስተዳዳራዊ ጉዳዮችን የተመለከተውን ትተን “እርቀ ሰላሙን” የተመለከተውን በሁለቱም ቦታ የተሰበሰቡትን አባቶች መግለጫ ክፍል ስንመለከት አባቶቻችን ምን እየሠሩ ነው ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል። በእርግጥ በሁለቱም አባቶች መግለጫዎች ላይ አንዳቸው ሌላውን አካል የሚገልፁበት ቋንቋ (በውጭ አህጉረ ስብከት ካሉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር (ከሀገር ቤት)፣ በቤተ ክርስቲያናችን መሰደድ ምክንያት የተፈጠረው የሰላም እጦት (አሜሪካ)) ለዘብ ያለ መሆኑ በጣም ያስመሰግናቸዋል። (ሌሎችም ይህንኑ ብንከተልና የቃላት አጠቃቀማችንን በማስተካከል ልዩነቱን ለማጥበብ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ብናደርግ መልካም ነው።)
 
ሆኖም ግን በየዓመቱ “የዕርቀ ሰላሙ ጥረት ይቀጥል!” የሚለው መግለጫ ጋጋታ ትርጉም የሚኖረው ከእውነተኛ ፍላጎትና ችግሩን ለመጭው ትውልድ ላለማውረስ ከመነጨ ቁርጠኝነት ሲመነጭ ብቻ ነው። ይህ ውሳኔ ከሁለቱም አባቶች ስብሰባዎች በኋላ ሁልጊዜ የሚካተት መሆኑ ያላቸውን የአንድነት ፍላጎት የሚያመለክት ቢሆንም ተግባራዊነቱ ላይ ቁርጠኝነት መጥፋቱ ጉዳዩ ከፍተኛ የፖለቲካ ጥላ ያጠላበት መሆኑን ያሳብቃል። በእርግጥም በተግባር እንደታየው ሁለቱን አባቶች ለማስታረቅ የተደረገው ጥረት ጫፍ ከደረሰ በኋላ በዋነኛነት በወያኔ ጣልቃ ገብነት ተቋርጧል። በተቃዋሚው ወገንም (በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ በወያኔ የደረሰው ጥቃት ዋነኛ የሥርዓቱን ሕገ ወጥነት ማሳያ ስለሆነ ችግሩ ከተፈታ ፖለቲካው ይዳከማል በሚል የተሳሳተ ስሌት) አንድነቱን በሙሉ ስሜት የመደገፍ ስሜት እንደሌለ ይታወቃል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ “የእርቀ ሰላሙ ጥረት ይቀጥል” ሲሉ የወሰኑት አባቶች (በተለይም በአሜሪካ የሚገኙት) በሌላው መሥመር የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲከናወን ቀን መቁረጣቸው በእርቀ ሰላሙ በቅርብ ጊዜ መፈፀም ተስፋ እንድንቆርጥ እየነገሩን ይመስላል። እርቀ ሰላሙን ማውረድ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባ ነበርና። ይህ ይደረጋል የሚባለው የጳጳሳት ሹመት (በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ) በእርቀ ሰላሙ ሂደት ላይ ሌላ የተጋረጠ ፈተና መሆኑ የማይቀር ሲሆን ወደ ሌላ እልህ እንዳያጋባም ያሰጋል። 
 
ምኞታችን
 
እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና ምእመናን ምኞት አባቶቻችን ሁሉ ከፖለቲካው ቅኝት ወጥተው የተሰጣቸውን መንፈሳዊ አደራ የፓለቲከኞችን ፊት እያዩ ሳይሆን በፍጹም መንፈሳዊ ነጻነት እንዲያከናውኑ ነው። ምክንያቱም የዘመናችን የፖለቲካ ሥራ በሰለጠኑት ሀገሮች ጭምር እንደምናየው በባህርይው ሐሰትን ከእውነት ጋር ደባልቆ መያዝን የሚጠይቅ፣ ሥጋዊ ጥቅምንና ዝናን ከኅሊና ክብር የሚያስቀደም፣ ጉልበተኞችና የዓለም ባለፀጎች ፍላጎት የሚፈፀምበት፣ የአንዱ ጥፋት እየተጋነነ ለሌላ የከፋ ጥፋት ዝግጅት የሚደረግበት፣ ግፋም ሲል ሃይማኖት የለሽነትን የሚያበረታታ ነውና። ሀገራችን ባለችበት ሁኔታ አባቶቻችን በፍፁም የኅሊና ልዕልና እንዲኖሩና ማንንም ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንዲያስተምሩና እንዲገስጹ እንጂ የየትኛውም ፖለቲካ እጀታ እንዳይሆኑ መመኘት “ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ቢሆንም ምኞታችን ነው። (አሁን ካሉት አባቶች አብዛኛዎቹ ይህን ማድረግ እንደሚቻል  (ማለትም የትኛውንም የፖለቲካ አመለካከትም ሆነ ስልት አንደግፍም የማለት መብት እንዳላቸው) ለማመን እንኳን ይቸገራሉና)።
 
ይሁንና እርቀ ሰላሙ ለቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ጉዳይ ነው። በየትኛውም ሰበብ ችግሩ ለሌላ ትውልድ መተላለፍ የለበትም። የችግሩን እውነተኛ ምንጭ እንዲህ ፍንትው ብሎ በታወቀበት ሁኔታ (ፖለቲካ እና መንደርተኝነት) የተለያዩ የማያሳምኑ ምክንያቶች እየተደረደሩ የቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚታወክበት ምክንያት የለም። እውነተኛ ሊቃውንትም በትምህርታቸው ይህንን መግለጥና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ የተቻላቸውን ሁሉ ሊያደርጉ ይገባል። እንኳን ተከፋፍለን አንድም ሆነን የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ለመፈጸም አልቻልንምና። ስለሆነም አባቶቻችን እንዲህ እያልን እንለምናለን ። እባካችሁን! በሀገር ቤትም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትገኙ አባቶች፥ ፖለቲከኞች በዘርና በወንዝ እየከፋፈሉት ያሉትን ሕዝብ እናንተ ደግሞ ከቁብ በማይገባ “ሃይማኖታዊ” ሰበብ በመከፋፈል መከራውን እንዳታጸኑበት በቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም እንለምናችኋለን። ዕርቀ ሰላሙን ፈጽማችሁ ታሪክ ሳታበላሹ ብታልፉ ሰማያዊ ክብር ብቻ ሳይሆን ታሪክም በበጎነታችሁ ሲያዘክራችሁ ይኖራልና። 
 
ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ከምእመናን ምን ይጠበቃል?
 
ከላይ እንደተገለጸው በዘመናችን ከሁሉ በላይ የሚያሳስበን የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ጉዳይ ሊሆን ይገባል። በቤተ ክርስቲያናችን የተከሰተው አስተዳደራዊ ችግር ሊፈታ የሚችለው በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና በምእመናን አንድነትና መግባባት ነው። የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ለመፍታት ስንሞክር መሠረታዊ የሆነውን የአንድነቱን ምሰሶ እያናጋን ችግሮች የበለጠ እንዳይወሳሰቡ በተቻለ መጠን መጠንቀቅ አለብን። የውስጥ ጉዳዮቻችን መፍትሔ የሚያገኙት፣ ዕቅበተ እምነት በአግባቡ ሊፈጸም የሚችለው ሁላችንም የእገሌ ወእገሌ ሳንባባል በአንዲት ጥምቀት ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን የተወለድን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በማመን በአንድነት በመቆም ብቻ ነው። በመሆኑም አባቶቻችን የወሰኗቸውን ውሳኔዎች አክበረን የምንኖረው አባቶቻችን የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የምንረዳበት ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ  የሆነ የመታዘዝ ሥነ ምግባር በመሆኑ ነው። ይህ ማለት ግን በተለያዩ የአባቶች አስተዳደር ሥር በማገልገላችን እና በመገልገላችን ሁለት የተለያየ ሃይማኖት የምንከተል አይደለንም። ስለሆነም በየአከባቢያችን ላሉት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እውነተኛ እምነታችን ይኸው መሆኑን በመግለጽ ወደ አንድነት እንዲመጡ የተቻለንን ጥረት እናድርግ። በተለይም በፖለቲካው እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ክርስቲያኖች፥ ከክርስትና እምነታችን ጋር የማይጋጨውን የትኛውንም ፖለቲካዊ አቋም የማራመድ መብታችንን ቤተ ክርስቲያን ታከብርልናለች። ሆኖም ግን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና የእርቀሰላሙን ሂደት በፖለቲካ አመለካከታችን አንጻር እያሰላን በአባቶቻችን መከከል የተከተውን ልዩነት ከማስፋት እና የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ጥረት ከማደናቀፍ ልንቆጠብ ይገባል።
 
የሰላም አምላክ ሰላሙን ያድለን!
ዲባባ ዘለቀ ([email protected])
 

7 Comments on “ቤተ ክርስቲያን አባቶች ዕርቀ ሰላም እና የዘመናችን ፖለቲካ”

  1. በሥልጣነ ክህነት ተዋረድ ለምትመራው ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወሳኝ የሆኑ ሃይማኖታዊ ጕዳዮች የሚታዩበትና በመሆኑ በፍጹም ነጻነት መከናወን አለበት። ይሁንና በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉት አባቶች ይህ ነጻነት እንደሌላቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። የወጡትን መግለጫዎች ይዘት በሚገባ ብንመለከታቸውም በሁለቱም ቦታዎች ያሉት አባቶች በፖለቲካ ጫና ሥር (የሀገር ቤቱ በወያኔ፥ የአሜሪካው ደግሞ በተቃዋሚው) እንዳሉ መገንዘብ አያዳግትም። ይህ ማለት ግን አባቶቻችን ስለ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚወስኑት ውሳኔ ተቀባይነት የለውም ወደሚል መደምደሚያ አያደርሰንም። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ የአላውያን ነገሥታትና ፖለቲካኞች ተጽእኖ የሁልጊዜም ፈተናዋ ነውና። ልዩነቱ በየዘመኑ ተጽእኖውን የሚረዱና የሚቋቋሙ፣ ለቤተ ክርስቲያን ወግነው ለወንጌል ዓላማ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ አባቶች መብዛትና ማነስ ብቻ ነው

  2. Mn waga alew.
    Gizie yeseTew tgrie woyanie yewosenew, “papasu tgrie mehon alebet, betewaredm tegriewoch meshome ena yetekemachewn yebietkrstian habt le tgrie ena le tgrai lmat yisebsbu, sle ye tgrie woyanie hzbun sbeku.”, blo new.
    Yih yemifetaw tgrie woyanie tegedlo siqeber bcha new.
    Slezih tegrie woyanien gelo lemeqber yihun wanew weqtawi tkuretachn.
    Atazengu enante woyaniewoch nachuh.

  3. እምነት አለ እንደ ዛሬ አታምኑም፣አትሰግዲም፣አታስቡም እምነት የለሽ ሁኑ ነው እያሉና እየገደሉን ያሉት!

  4. አቤል መኮንን says:

    June 20, 2016 at 2:45 pm

    እንደ አባ ወልደተንሳይ ያለ የለየለት መናፍቅ በጵጵስና ማዕረግ በቤተ እግዚአብሔር መመረጥ በእውነት የቤተክርስቲያንን ፈተና መወሳሰብ ያሳያል፡፡ አባቶችን የማጣት እርግማን ደርሶብናል፡፡ ባለቤቱን እግዚአብሔርን ብቻ መመልከት ነው ያለብን፡፡ እግዚአብሔር ቤ/ያንን ይጠብቅልን ይህን የኑፋቄ መንፈስ ከቤ/ያን ነቅሎ በሲኦል ይጣልልን፡፡ አሜን!

    [Reply]

    Reply

    ጎንደሬው says:

    June 20, 2016 at 9:37 pm

    መጀመሪያ በራሳችን አይን ውስጥ ያለውን ግንድ እናውጣ በሰው አይን ያለውን ስንጥር ለማውጣት ከመሮጥ ። ለመሆኑ ትንሽ አናፍርም በእውቀት፣በእድሜ፣ወዘተ ከእኛ በላይ የሆኑ አባቶችን ለመዝለፍ ወያኔ ላይ የተመረገ አፋችን ለመክፈት የተነሳነው።ኧረ በፈጠራችሁ ከወያኔ ባሳነሳችሁት ሁሉን በፈጠረ በአንድዪ ልለምናችሁ የተፈቀደልንን ብቻ እናድርግ ሌላውን ለእርሱ እንተወው።

    [Reply]

    Reply

    Haymanot says:

    June 21, 2016 at 1:44 am

    Eneko algebagn yalew. Ye Ethiopia orthodox new ye America orthodox new? Haymanot lela poletica lela. Ezih yalew sinodos ye Ethiopia hizb almeretewm malet and neger new. Yalew sinodos ye weyane selehone new and neger new. America kuch belo meto shih yemaymola “amagn” anja fetero engna nen tekekel malet min aynet neket new? Ezih yalew be million yemikoter amgn sehetet enante lek mehonachihu new? Tekekel yemihonew america lay ende shifta meshego makrarat sayhon ezih metetachehu amagnun yemiwokel sinodos hizb asamenachu asmeretu. Alezia gin engna enawkalen atebelu. America selehonachihu new? Dinkem!!

    [Reply]

    Reply

    አለም ግላዝጊ says:

    June 21, 2016 at 11:07 am

    እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ያበቃን እሱ የሚሳነው ነገር የለምና አንድ ያድርገን ያብዛን ለአንድነት መፅልይ ይሻላል።

    [Reply]

    Reply

    እየሩሳሌም እውነቱ says:

    June 21, 2016 at 1:57 pm

    ወይ ጉድ ኦርቶዶክስ መቀለጃ ሆነች።
    የውጭ አባቶች ሁሉም ጰጰስ መሆን አለባቸው ተባለ አፈቸወን የሚያሾሉ ታሐድሶ የኦርጋን እና አርጋኖ አፍቃሪ እና የስድብ መንፈስ ዲያቢሎስ ያጠመቃቸው ከጎንደር ብቻ ተሾሙ።

    የአገር ውስጥ ደግሞ አባ ማትያስ ደግም ከአደዎ ብቻ ጉበኞችን እና ተሐድሶዎችን እየሰበሰቡ ሰሞኑን ሊሾሙ ነው። ለመሾም የህዝቡን ገንዘብ ስብስቦ ጉቦ መስጠት ያስፈልጋል። ውሸት በ እውነት ላይ አንግሻለሁ እያለ ነው ማን ዲያቢሉስ እየሳቀባቸው ነው።
    አቡነ መርቆርዮስ ሆኑ አቡነ ማትያስ ዲያቢሎስ በውሸት ሰንሰለት አስሮአቸዎል። አባካቹ ፀልዪላቸወ!!!
    እናንተ ወገኖቼ ስለ ሐይማኖታቹ ስትሉ ቆም ብለው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ፀልዪላቸው። እውነቱን ይዘው የሞቱ አባቶቻችን አምላክ ይርዳን አይ ክፍ ትውልድ ኢትዮጵያዊ እግዚኦ ማረን ከመጥፈታችን በፈት። ለእዚች አጭር ህይወት ከሥጋ ስም ድሎት አይ ቀልድ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ስራው ረቂቅ ነው ትዕግሥቱ ሲያልቅ ወላፈኑን ይዞ ይመጣላችሀል። ለራሳችሁ ወየሁ በሉ

    [Reply]

    Reply

    Yemer says:

    June 21, 2016 at 5:41 pm

    Whenever there is spiritual revival and the work of the Holy Spirit is revealed the devil will roar like devouring lion.who cares for the devil except woyane and it’s agents?On the day of the Pentecost and Arch-Angel Michael God have given us additional Apostles like the then Aba Wolde Tensae and the now “Abune Bernabas”

    [Reply]

    Reply

    Yemer says:

    June 21, 2016 at 6:39 pm

    አንተ መቼም የተጠመክ ይመስለኛል ታድያ በሜሮን ከታተመው አፍህ እንዲህ አይነት ርኩሰት፤እንዲህ አይነት ስድብ እንዲህ አይነት ፍርድ እንዲህ አይነት ክፋት እንዴት ወጣ ወይስ ማህተሙን አፈረስከው?አባ ወልደ ትንሣኤን መናፍቅ ያላቸው የትኛው ጉባኤ ነው ወይስ የትኛው ሲኖዶስ ነው፡፡እንደ ዲያብሎስ ለምን ውሸት ትናገራለህ?(ዮሐንስ 8:44)መናፍቃን እኮ ሲወገዙ ጉባኤ ተጠርቶ ስላስተማሩት ኑፋቄ ተጠይቀው አባቶች መጽሐፍ ገልጸው አስተምረዋቸው እምቢ ብለው በኑፋቄ ትምህርታቸው ሲቅጥሉ ተወግዘው ይለያሉ፡፡የነአርዮስ፤የነንስጥሮስ፤የነ መቅድንዮስና የሌሎችም መናፍቃን ውግዘት ከላይ የተጠቀሰውን መንገድ የተከተለና የኦርቶዶክስ አስተምህሮም ነው፡፡ታድያ አንተ የየዋሁን የአቤልን ስም ይዘህ ለምን ወደዚህ ጥላቻና ነፍስ ግድያ ውስጥ ገባህ?ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው ተብሎ ተጽፎአል (1ኛ ዮሐንስ 3:15)ስለዚህ መናፍቅ ያልካቸው አባት ያስተማሩትን ኑፋቄ መጽሐፍ ጠቅሰህ አቅርብ እንጂ በጥላቻ ተነሳስተህ ለቤዛ ቀን የታተምክበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝን፡፡አቤል ሆነህ የቃኤልን ስራ አትስራ ተቅበዝባዥ እንዳትሆን፡፡
    እግዚአብሔር ለንስሐ ሕይወት ያብቃን

    [Reply]

    Reply

    እየሩሳሌም እውነቱ says:

    June 21, 2016 at 7:04 pm

    አባቶቻችን ከሰቀመጡት ትውፈት፣ ቀኖና እና ዶግማ ውጪ የሆነ በራስ ፈልስፈና ተነስቶ ቃላት እየሰነጣጠቁ በኦርጋን ማስጨፈር በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደንብ ውጪ የሚካሄድ ሁሉ ኑፈቄ እና ሕዝባችንን ግራማጋባት ነው። ከስርአት ውጪ ከሆነ ህዝቡ አሁን ስለ ሐይማኖት የነቃ ስለሆነ መሽወድ አይቻልም። እውነት ዛሬም ነገም እውነት ነች ሰለዚህ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያላችሁ መስቀሉን ለጌጥ የተሸከማቹ ተመለስ የወላፈን እሳቱ ከእናንተ ከምላሳችሁ ላይ ይጀምራል ባለቀ ሰአት ህዝቡ እየተቀወማቹ ዲያቢሎስ እየተሳለቀባቹ ነው ቆም ብላችሁ ለነፍሳችሁን አድኑ። ስድብ ሁሉ ከዲያቢሎስ ወገን ነው። ሕዝባችን
    ግን ጠልቶአችሁ ሳይሆን ገንዘብን ንዋይ አርጋችሁ በአገር ውስጥ እና ውጭ በተሐድሶ ጎዳና የገባችሁ ተመለሱ እያለን ነው። በክርስቶስ ደም ላይ ቆመን መሾፍ አይቻልም።

    [Reply]

    Reply

    እየሩሳሌም እውነቱ says:

    June 21, 2016 at 7:57 pm

    ማንኛውም ክህን አለማዊ ትምህርት ቢማረ ቢመራመር ተምሯል ለማገናዘብ ለስጋው ተብሎ ነው የሚነገርለት ግን እንጂ ከላይ እስከ ታች የሉት የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ እና እውቀት በሙሉ አባቶቻችን እግር ስር ቁጭ ብለን የተማርናት ትምህርት አይቀየርም። ዶግማ እና ቀኖናውን መቀየርም ሆነ ጥቅስ እየጠቀሱ አሁን የነቃውን የኦርቶዶክስ አማኝን በድጋሚ መሸወድ አይቻልም። ዱሮ ከህኑ ትክክለኛ ስለነበረ እንደዚህ ስተት የምትስሩ ከሆነ አውግዣለሁ ይሉ ነበር። አሁን አሰመሳዪች ሰርፀው በሐይማኖቱ ውስጥ ስለገቡ ቢያወግዝ እንኳን አሰመሳዬቹ ከእነሱ ጋር ዲያቢሎስ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ሰለሌላቸው፣ ለማውገዝ ቢሞክሩ እንኳን ማንም አይቀበለም።
    እራሳችሁን ምርምሩ እኛ የእናንተን ሐጥአት ማመላለስ አንፈልግም ቀና ብላችሁ ወደ ፈጣሪያችን ተመልከት። ለማን ማድላት ይበልጣል ለነፍስ ወይስ ለነዋየ ስጋ?
    Watch ከቻላቹ?
    https://youtu.be/SOKcPeAux-M

    [Reply]

  5. አቶ ዘውገና አቶ ዘነበ በጋራ የምቀኝነት ጽሁፋቸውን አስነበቡ ተነቃባቹ ከመሃል ገብታቹህ ትከፋፍሉ ነበር ምንፍቅናቹህ ለመዝራት ቤተክርስቲያኗን ለማዳከም በስልት ተጉዛቹህ ነበር በቃ ተነቃ አባቶች ላይከፋፈሉ ቆርጠው ተነስተዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*