“የፓለቲካ እስረኞች በቂሊንጦ በጨለማ ቤት ለብቻቸው እንዲቀመጡ ተደረጉ

በቂሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ማቆያ የፓለቲካ እስረኞችን ጨለማ ክፍል ለይቶ በማስቀመጥ መቅጣት የተለመደ አሰራር ነው። በተለይ ደግሞ እስረኞች በእስር ቤቱ አስተዳደር የሚደርስባቸውን በደል እና መድሎ ለፍርድ ቤት ወይም ለሚዲያ እንዲደርስ ካደረጉ ወይም የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ከጠየቁ ወደ ጨለማ ቤት ለቅጣት መላካቸው አይቀሬ እንደሆነ ይነገራል።
በ28/9/2008 አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦፌኮ አመራር አባላት ኦሮሚያ ክልል ላይ በተነሳው ተቃውሞ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለፅ ጥቁር ልብስ ለብሰው ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ መውጣታቸውን ተከትሎ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ጥቁር ልብስ ለብሰው ፍርድ ቤት አይሄዱም በማለት ከችሎት እንዳስቀሯቸው ይታወቃል፡፡ በተከታዩ ቀጠሮም ጥቁር ልብሳቸውና ሌሎች ልብሶቻቸው በብርበራ ወቅት በመቀማታቸው በፓካውት እና በቁምጣ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ከፍርድቤት ሲመለሱም አራቱን ከፍተኛ የኦፌኮ አመራሮች ጨለማ ቤት በመግባታቸው ቤተሰብ ሳያገኛቸው ተመልሰዋል።
በተመሳሳይ ቀን ቀጠሮ የነበራቸው ከኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ (‪#‎OromoProtests‬) ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 16 ሰዎች ከአምቦ ተይዘው የመጡ እና 11 የመድወላቡ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጥቁር ልብስ በመልበሳቸው ምክንያት በቀጠሯቸው ቀን ፍርድ ቤት ሳይወሰዱ ቀርተዋል። ይህ በሆነ በማግስቱ (29/9/2008) በግቢው ከሚገኙ ሶስት ዞኖች ውስጥ ከሁለቱ ስድስት የፓለቲካ እስረኞች አስተዳደር ቢሮ እንደሚፈለጉ ከተነገራቸው በኋላ እነ በቀለ የሚገኙበት ጨለማ ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል። የተሰጣቸው ምክንያት “እስረኞችን እያሳመፃችሁ እና እያደራጃችሁ ነው” የሚል ነው። አስሩ የፓለቲካ እስረኞች ብቻ ተዘግቶ የሚውል እና የሚያድር አንድ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲኖሩ ከተደረጉ ብዙ ቀናት ተቆጥረዋል። በቀን ለ2ት እና 3ት ደቂቃ ለምታክል ጊዜ ምግብ ከሚያቀብሉ ቤተሰቦች ጋር ብቻ ነው ለመገናኘት የሚፈቀድላቸው ሲሆን ከቤተሰብ ውጪ የሚመጡ ጠያቂዎች በእስር ቤቱ ፓሊሶች ” የት/መቼ/እንዴት ነው ምታቀው/ቂው? ” ፣”ምንሽ/ህ ነው?” እና መሰል የምርመራ ጥያቄዎችን ያቀርቡላቸውና እንደሁኔታው ለ2 ደቂቃ ለመገናኘት ሊፈቀድላቸውም ላይፈቀድላቸው ይችላል። ” ለብቻችሁ ያደረግናችሁ ሆን ብለን ከሌሎች እስረኞች ልናገላችሁ ስለፈለግን ነው” የተባሉ ሲሆን

Mahlet Fantahun's photo.
Mahlet Fantahun's photo.

አስሩ የፓለቲካ እስረኞች ፤
1. በቀለ ገርባ ፣
2. ጉርሜሳ አያና፣
3. ደጀኔ ጣፋ፣
4. አዲሱ ቡላላ፣
5. ዮናታን ተስፋዬ፣
6. አበበ ኡርጌሳ፣
7. ፍቅረማርያም አስማማው፣
8. ብርሃኑ ተ/ ያሬድ፣
9. ማስረሻ ታፈረ እና
10. መሰለ መሸሻ ናቸው።

በተመሳሳይ መልኩ የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር አስተባባሪ የነበረው አግባው ሰጠኝ በታሰረበት ቂሊንጦ ግንቦት 9/2008 ዓ.ም ‹‹ዘረኞች›› ብለህ ሰድበኸናል በሚል የሁለት ወር የጨለማ ክፍል እስር በእስር ቤቱ አስተዳደር ተፈርዶበት ከግንቦት 17/2008 ዓ.ም ጀምሮ ለብቻው ጨለማ ክፍል ውስጥ ይገኛል። አግባው ግንቦት 11/2008 ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ግፍ እያደረሰብኝ ነው ሲል አቤቱታ አሰምቶ የነበረ ሲሆን ‹‹ጨለማ ቤት እናስገባሃለን›› እያሉ እንደዛቱበትም በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡
★ማንኛውም አይነት ጥቁር ልብስ ለማንኛውም እስረኛ እንዳይገባ የተከለከለ ሲሆን ቀደም ብሎ የገባም ተሰብስቦ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።”
Ethiopia Human Rights
Project
‪#‎FreePoliticalPrisoners‬ ‪#‎HumanRights‬ #OromoProtests
‪#‎Ethiopia‬

9 Comments on ““የፓለቲካ እስረኞች በቂሊንጦ በጨለማ ቤት ለብቻቸው እንዲቀመጡ ተደረጉ”

  1. ሆ ብለን እንነሳ ጊዜው አሁን ነው አንፍራ ጎበዝ ወያነ ከአባቱ ከሻዕብያ ጋር ስዋ እየጠጡ ሀምባሻ እየበሉ እኮ ነው

  2. ahun chilema kefel wust sewn masqemet min yeteqmal? bemulu Ethiopian are in dark with in their own homes.no electric city. there is no difference at all.

  3. Woyane / TPLF has failed totally and completely in its mission. Woyane is set out to destroy Ethiopia will in the end self-destruct. Ethiopians will continue to watch on the sidelines with aching hearts and bellies. They gnash their teeth and wag their index fingers asking themselves when the day of reckoning will finally arrive.

    Woyane and all Tigre accomplices know that behind the deafening silence of millions of Ethiopians and apparent passivity is boiling anger just like liquefied magma before it erupts in a volcano.

    Or perhaps it is like the proverbial finger in the dam. You can’t stop the dam from collapsing by sticking a finger in the hole of the dam. What happens when the dam finally collapses?

    There is no doubt about it. The day of reckoning for the Woyane and all Tigre accomplices will come “unexpectedly, like a thief in the night.”

  4. Nothing surprises me anymore – What is clear for all to see is the fact that TIGRES (TPLF/WOYANE) HAVE NO SHAME. It is the identifying characteristics of Tigres – As one person sometime ago put it, there are no words or vocabulary in the Tigre language for humility and the sense of Shame – Period!!!!

    I think we can save our old, beautiful and historic country from degenerating into deeper divisions and hatred and falling into the traps set by Meles Zenawi and his Tigre thugs. We can do this by standing up together across ethnicities and rejecting the inhumanity that is being committed by this cruel regime and its elite that is blinded by greed. There is nothing symbolic than rejecting this cruelty and barbarism against the Oromo people together. By so doing, we will all be fighting not for the rights of the Oromo people only but for ourselves and a better posterity too

  5. Today Evil has triumphed in Ethiopia, and good Ethiopian men and women must forge solidarity to rescue their country from the clutches of a malignant dictator. A thuggish dictatorship in Ethiopia is on a crime spree: a leading opposition figure is snatched off the street and slammed into prison to serve out a life sentence. Mr. Bekele Gerba is put back in prison soon to be convicted a kangaroo court. Peaceful and lawful political parties and organizations are under the constant threat of dissolution, mindless bureaucratic control and regulation and vindictive prosecutions. Opposition political leaders and dissidents remain under 24-hour surveillance, relentless harassment and intimidation. Members of the independent press are subjected to police interrogation, constant harassment, arbitrary arrests, detentions and persecution. The charity work of international non-governmental organizations (NGOs) in Ethiopia has been criminalized; and by “law”, they are prohibited from working on human rights issues in the country. Human Rights Watch predicted that this pretentious and asinine law “will make Ethiopia one of the most inhospitable places in the world for both Ethiopian and international human rights groups.”

  6. Human rights violations in Ethiopia in the past year have intensified as thousands of political prisoners are held in detention facilities throughout the country in violation of the “laws” and “constitution” of the country and international law. The country’s limited resources continue to be squandered on a misbegotten war. The ruling thugs in Ethiopia have been accused of committing war crimes on a massive scale in Somalia, and crimes against humanity against Ethiopians. Famine threatens to destroy one-quarter of the Ethiopian population as the dictators sip on Remy Martin Louis XIII cognac and throw lavish balls and galas to entertain themselves. The cost of living in Ethiopia has reached astronomical levels, depriving the vast majority of Ethiopians the capacity to earn a living or feed their families. The corrupt and decadent plutocracy and its lackeys continue to rapaciously plunder the country’s economy and resources. Cumulatively, the ruling thugs have propelled Ethiopia to the top of the list of failed states in the world

  7. ሰውን መግደል አስፈላገና ተመጣጣኝ ነበር አለ የሰብአዊ ኮሚሽን ባለስልጣን ተብየው ዶ/ር አዲሱ——-
    ጎሳው ምንድን ነው?ረምጃው ተገቢና ተመጣጣኝ ግድያ!
    ሰውን መግደል አስፈላጊ ነበር!
    በጸጥታ ሃይሎች የተወሰደው ረምጃ ተገቢ ነው!አስፈላጊም ነው!
    ሕዝብን የሚወክለው ማን ነው? ካቢኔ የሚባለው ማን ነው?
    ሰውን ገድሎ ይቅርታ ይደረግለት? ለአማራው ሕዝብ ማን ነው?
    ሰማው

  8. Adissu G/Egzihabir was deputy Election Commissioner until he moved to the rank of Human Right Commission. He is a member of genocide organization, TPLF.

    YE AYIT MISIKIR DIMBIT.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*