መድረክ ንጉሣዊ ነው እንዴ? Girma Seifu Maru
ለመድረክ ቅርብ የሆነ አንድ ወዳጄ የመድረክን የእሁድ ግንቦት 28/2008 ጉባዔን አስመልክቶ የነገረኝ ነገር መድረክ ንጉሣዊ ነው እንዴ? የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል፡፡ መቼም በመድረክ ስም ፓርላማ ስለነበርኩ ለመድረክ ቅርብ የምመሰላቸው ካሉ ተሳስተዋል፡፡ የመድረክ ስብሰባ እንደሚታወቀው ውሣኔ የሚሰጠው የጉባዔ አባላት ተሰብሰበው በውይየት አቋም ይዘው በነፃነት በሚሰጥ ድምፅ አይደለም፡፡ አባል ድርጅቶች አድማ መተው የሚመጡበት ነው፡፡ ሌላው በመድረክ ውስጥ ኃላፊነት የሚያዘው በአባል ድርጅቶች በዙር ነው፡፡ ከአባል ድርጅቶቹ ደግሞ የሚልኩትን መሪ ቀይረው የማያውቁት ደግሞ ፕሮፌስር በየነ እና ዶክተር መረራ ናቸው፡፡ አሁን ባለኝ መረጃ መሰረት መድረክን የመምራት ተራው የሀረና ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን የስብሳቢነት ቦታው ለሀረና እንዲሲጠው ሀረና ለቦታ የሚያቀርበው ዕጩ ወሳኝነት አለው፡፡ ሰለዚህም ሀረና ያቀረበው ዕጩ ለመድረክ ሊቀመንበርነት አይደለም፣ ለምክትልም አይሆንም በሚል ቦታው በቃኝ ለማያውቁት ለፕሮፌሰር በየነ አንዲሰጥ ተደርጎ ዶክተር መረራም ምክትል ሆነው ቀጥለዋል፡፡
አቶ አስፋ ጫቦ በቅርቡ ባሳተመው መፅኃፍ ውስጥ የሸዋ ንግስና ከተመለሰ የእኛም መመለስ አለበት የሚል ስላቅ አቅርቦ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር በየነም ቤተሰቦቻቸው በአካባቢው እንዲህ ዓይነት የንግሰና ጥያቄ ከመጠ ከሚጠይቁት ወገን ናቸው ስለሚባል፤ ይህ እስኪመጣ ድረስ መድረክን የንግስና መለማመጃ ያደረጉት መስለኝ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብዙ ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን የአመራር ቦታ ቢቻል ፖለቲካውን ጭምር መተው ለምን ተቸገሩ?
ከወዳጄ ጋር ሰለምርጫው ስናወራ የፕሮፌሰሩ በተደጋጋሚ ከሚቀርብባቸው ከተቃዋሚ መሪነት እራሳቸውን ያግልሉ ጥያቄ ችላ ማለት ብቻ ሳይሆን ሃያም ሆነ ሰላሣ ሰዎች ድምፅ ሰጥተዋቸው በሃላፊነት የሚቆይቱ ባለፈው የሃላፊነት ዘመናቸው ምን ሰርተው ነው? የሚል ጥያቄ ለምን አያነሱም ነው፡፡ በፕሮፌሰር በየነ አመራር ወቅት መድረክ ምን ውጤት አስገኝቶ ያን ውጤት ለማስቀጠል ሲባል ነው የተሰጠው ሊባል የሚችል ውጤት አልታየም፡፡ በኦሮሚያ ለነበረው ህዝባው ንቅናቄ እንኳን በቂ ድጋፍ መስጠት ያልቻለ ስብሰብ እንደሆነ በስብሰባው ወቅት ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡
የተነሳው ጥያቄም “በኦሮሚያ ለነበረው እንቅስቃሴ ኦፌኩ ብቻውን ለምን ተንቀሳቀሰ?” በሚል ነበር፡፡ መልሱ ግን የበለጠ አስደማሚ ነበር፡፡ “ኦሮሞዎች የተለየ ጉዳይ ስለነበረን ነው” የሚል እንደምታ ያለው መልስ ተሰጥቷል፡፡ አስገራሚው ነገር በአንድ ወቅት ሀብታሙ አያሌው “ሰለ ኦሮሞ ችግር ለመናገር ኦሮሞ መሆን አያስፈልግም ሰው መሆን ይበቃል” ብሎ በሰጠው አስተያየት መድረክ አጀንዳ አድርጎት ኦሮሞ ያልሆነ የኦሮሞ ችግር አይገባውም የሚል መልስ ተሰጥቶ አንድነት እና ሀረና ታዲያ እዚህ ምን እንሰራለን? በሚል ስብሰባው ተቀውጦ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ አሁንም መድረኮች አብረን ነን ይበሉ እንጁ የትግሬው ችግር የሀረና፣ የኦሮሞ ችግር የኦፌኮ አድርገው በመያዝ ዳር ይዘው ተቀምጠዋል፡፡ በነገራችን ላይ መድረኮች አንድነትን ካስወጡ በኋላ የአማራ ተወካይ የሚያደርጉት ወይም የሚመስልላቸው ሳያገኙ እስከ አሁን አሉ፡፡ በቅርቡ የተመሰረተው የአንድነት ሽራፊ “ነፃነት” የሚባለው ፓርቲ ይህን ቀዳዳ ለመሙላት ተሰፋ ሳያደርጉ አይቀሩም፡፡ ወይም “ሰመያዊ” ፓርቲ ዓይኑ በጨው ታጥቦ ሊቀላቀላቸው ይችላል፡፡ የመድረክ አመራሮች ይህ ያለባቸውን የአማራ ወኪል ክፍተት በመሙላት “ፎርጂድ” የኢህአዴግ ኮፒ አደረጃጀት እንዲሳካ መጣራቸው የማይቀር ነው፡፡ ለህወሃት-ሀረና፣ ለኦህዴድ-ኦፌኮ፣ ለደህዴን-የበየነ ፓርቲዎች፣ ለብአዴን- ? ? ? ? – ፡፡ ክፍቱን ቦታ ለመሙላት እንግዲ ነፃነትና ሰማያዊ እድሉ አላቸው፡፡
የሀረና ልጆች በመድረኮች ፊት ዓይን የማይሞሉ ሆነው የተገኙት በመተካካት ፖሊሲ የቀድሞውን መሪ አቶ ገብሩ አስራትን ለዕጩነት ባለማቅረባቸው ነው፡፡ አስገራሚው ነገር በመድረክ አንፃር የተሻለ የውጭ ደጋፊ ያለው ሀረና ለክፉም ለደጉ በሚል የፋይናንስ ኮሚቴ ሃላፊነት እንደተሰጠው ተሰምቷል፡፡ በእርግጥ ዶክተር መረራም ከውጭ ድጋፍ ያለው ቢሆንም ድጋፉን በግል ከፈለገ ለኦፌኮ ካልሆነ ለመድረክ የማድረግ ፍላጎት የለውም፡፡ ለማነኛውም ፕሮፌሰሩ ሲመሩት ከነበሯቸው ድርጅቶች የተወሰኑትን “ምርጫ ቦርድ” ተብዬው ቢሰርዘውም በንግሰና በሚመስል መልኩ የመድረክን ሃላፊነት አለቅ ብለው ቀጥለው፡፡ ወይም ደግሞ አባላቱ በግድ ጭነውባቸዋል፡፡ በዚህ የሃላፊነት ዘመናቸው መቼም በቀጣይ ሊያድርጉት ያሰቡትን መርዓ ግብር በሆነ መልኩ ይፋ ያድርጋሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡ በእኔ ግምት የመድረክ ሰዎች ይህን ኃለፊነት ይዘው መቆየት የፈለጉት በአንድ አጋጣሚ ኢህአዴግ ሸብረክ ቢል አለን!!! ለማለት ካልሆነ በስተቀር በተጠና ሰትራቴጂ ትግሉን መርተው መንግሰት ለመሆን አይደለም፡፡ እራሱን ለመንግሰትነት ያላዘጋጀ ፓርቲ/ሰብሰብ፣ ህዝቡን ለማድራጀት የማይተጋ ስብስብ ፋይዳው አይታየኝም፡፡
ሀገራዊ ሰብስብ ነኝ የሚል መድረክ ጠቅላላ ጉባዔ ሲያካሂድ በማህበራዊ ድረ ገጽ እንኳን የውይይት አጀንዳ አለመሆኑ አሳዝኖች ይህችን አካፈልኳቹ፤ እናንተስ ምን ታዘባችሁ፡፡ ከመድረክ ስብሰባ ተካፋዮች ዝርዝር እንጠብቃለን ….. ዘላለማዊ ስልጣን ….
Posted by GIRMA SEIFU MARU
በጣም የሚገርም እና የሚያሳዝን ነው ።ዶ/ር በየነ በእውቀት የዳበረ ችሎታ ቢኖራቸውም ስልጣን ላይ ለመቆየት ያላቸው ፍላጎት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ያስታውቃል የሀገር መሪ ቢሆኑም ለሌላ በምርጫ ያስተላልፋሉ ብዬ አላምንም ምክምያቱም የስልጣን ጥም እንደሌላቸው ያሳዩበት መድረክ የለም።
Docter BEYENE PETROS! You have tried to be a poletical leader for years, unfortunately,you are not and you have done nothing for the people that means you are failed so why not you leave the leader ship for the new generation?
አስተያየት ስጭወቹ እነማን ናችሁ? ወያኔ ወያኔን ይሽታል ፅሁፋችሁ ከዚህ በሁዋላ እንደናንተ አይነት ከፋፋዮች ቦታ ያላችሁ አይመስለንም ድሮ ነበር ሳናውቅ እንደዚ ህ መርዛችሁን ስትረጩ ባለ ማወቅ ስንጠፋና ስናጠፋ የነበርነው ይልቅስ ወያኔ ግብኣተመሬቱ በጣም የቀረበ ስለ ሆን ተነሱና አፈር እናልብስው እሽ? በቃ!
@Tokuma how do you know?
ሀሜት ምን ይጠቅማል?የሚትለው እውነት ሊሆን ይችላል ግን አቀራረቡ የሀሜት ነው።ለመድረክ ቅርብ አይደለሁም ማለት ምን ማለት ነው? የማትዛመደውን ድርጅትስ እንዴት ወክለህ የምክር ቤት ወንበር ያዝክ?ግርማ በምትሞነጫጭረው ፍረከርስክ ራስህን አታስገምት።
ሃሳቡን በማስረጃ መሞገት ነው ጥሩ የሚመስለኝ።
እና እንግዲህ እርሳቸውን ልተካ መጥቻለሁ የሚል ወጣት የት ተገኘና ነው አሁን እርሳቸውን እቤት ለማዋል ይህ ሁሉ ሩጫው።
አንተ እንኳን አቶ ግርማ ገና በወጣትነትህ በቃኝ ስትል,እርሳቸውም እንዳንተ እንዲሆኑ መምከር ያለብህ አልመሰለኝም። ይልቅስ ግባና እንደገና አንቀሳቅሰው።
ante hodam.Dr&prof.lehager yelefu yedekemu nachew enesun lemenager yetignawin serteh new.ante lidetu neh.kehadi. mechachal yematak kehadi
በቀል ይቁም! ከፕሮፈሰር በየነ ጋር ቅሬታ እንዳለህ ግልፅ ነው፡፡
Ato Girma,you think we don’t know any thing? when you take the parliament seat medrek said he don’t represent us coz they know who you are,they know exactly that you trying to play Lidetu’s roll that’s why they reject you, Now here you are biting everybody like a Dog you should do something for your country by this age instead attacking someone who try to do his best sham on you, Of course my self have disagreement on some issues but I know that they are a lot better me by doing something.
Medrek ke tgrie woyanie wodqet behuala ye woyanie qriet/remains yemihon yimeslal.
Enam gcit/conflict wsT endaygeba yasegal.
Mkniyatum ye enie neged bebeqi yewokel slTan yigebanal kemil yalemegbabat lifeTr yichlal.
SlTan be hzb yedmT blca enji yih woim ya behier/neged blo neger aschegari new.
Beneged mehonu qerto be ager aqef bideraju Tru neber/ahunm ager aqef syamie yimreTu.
I haven’t ever seen the opportunist and power mongerer pro. like beyene petros. even he is shameless. how and by what moral ground could he persist on being and forming the so called coilation for 25 years. no one of his colleagues have done so. he had found or been given the so called south hibiret then AMarach hailoch then Edihak then Hibret then Andinet then again the so called debub hibret then now medrek. in all these coilation 25 years period he has been talking only about his very nation hadiya. no single word on any of the coilation nations varying from time to time what ever happened to any of them. this man is not trustworthy. what happen on kinijit during the 1997 election. they were together. but all the eminent professors and doctors the country ever had put to jail and then made to disappear. but he remained safe by magic or what. most of the people say that he definitely has strong conspiracy linkage with tplf higher officials. some of the inner source of the man leaked that the tplf officials know his weak side of money mindedness fill his pocket and send him to already baked coalition or hibiret or medrek the tplf cooked from time to time. so he is getting elected in the format of tplf through tplf’s tactics and so on. for me, if no other option the country denied, let the existing devil of tplf satans continue than the man like beyene who changes his skin colour like chameleons betraying his yesterday coalition colleagues for today’s colleagues by turning his back to them. the Sidama nation and colleagues know him well even though those who joined him at medrek in the name of slm some of them are inefficient and baseless individuals who simply manipulated by beyene. as to me, even though I have reservation to some extent, pro.merara is by far more politician popular and a colleague to be trusted and truely express his point of discussion boldly naming spade is spade. he merara has courage that he has every day been on air and other media means for the last 6-7 years in communicating the every minute atrocities committed on innocent but brave oromia qerros and all section of the oromia nation. but no words from beyene. even though he uttered a word that is full of ambiguities. he has no courage. so he will remain the leader of the hollow and surrogot individuals coalition to be cooked in the tplf kitchen. let him enjoy the money. but I feel ashamed on behalf of the eminent professor beyene petros
Bezu mukara adrgew yaltesakalachew? Manew mukera yaderegew?pro beyene? Be 97 mircha gize le ene bereket\” kingit Amara selhone enante Eprdf tegre Teshalunalachihu\” yale sew aydelem ende? Esuko prtin ende Bussnes new yemyayew enji le seket aydelem…ena yehen Jil negade mebarer new.
ጥያቄ፡- መድረክ ንጉሣዊ ነው እንዴ?
መልስ፡- አዎ
@king medrk negusawi new? Awo?…hahaha
no medrek kuli…ye Kuliwoch derjit new…Dirito
Ahunma beye 5 ametu yetewosenu glesebochn parlama bemasgebt yibeluat yeneberechwn demoz kelekelu achew.