በባሕር ዳር ለአንድ ቤተሰብ አምስት ዳቦ በፊርማ እየተሸጠ ነው

Muluken Tesfaw's photo.

በባሕር ዳር ዳቦ በፊርማ እየተሸጠ ነው — By Muluken Tesfaw
እንደ ባሕር ዳር ባሉ የዐማራ ክልል ከተሞች ለአንድ ቤተሰብ አምስት ዳቦ በፊርማ ብቻ እንዲገዙ ተደርጓል፡፡ አንድ ቤተሰብ ዐሥር ልጆች ይኑሩት ወይም ከዚያ ያነሰ ዳቦ ቤት ሒዶ ከአምስት ዳቦ በላይ መግዛት አይችልም፤ ለዚያውም በፊርማ፡፡
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የዱቄት ፋብሪካዎች የሚያመርቱትን ዱቄት ለዳቦ ጋጋሪዎች አከፋፍላለሁ በሚል ከተቆጣጠረ በኋላ ዱቄቱን ለሕወሓትና ጀሌዎቻቸው በጥቁር ገበያ ያስረክባል፡፡ ለገዢው ቡድን ቅርበት የሌላቸው ባለዳቦ ቤቶች ደግሞ ዱቄት በጣም ትንሽ (ከ10 ኩንታል በወር ያነሰ) ይሰጣቸዋል፡፡
ንግድና ኢንዱስትሪ የሚያከፋፍለው ዱቄት በኩንታል 800.00 ብር ሲሆን በዚሁ ዋጋ የተቀበሉ ጥቅመኞች ደግሞ በጥቁር ገበያ ከ1200.00 እስከ 1400.00 ብር ድረስ ለባለ ዳቦ ቤቶች ያከፋፍላሉ፡፡ በዚህ መሠረት በሕጋዊና በጥቁር ገበያ የሚሸጡ ሁለት የመንግሥት አካላት ተፈጠሩ ማለት ነው፡፡ በጥቁር ገበያ የሚሸጡት የሥርዓቱ ታማኞች አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወደ ሚሊኒየርነት ተቀይረዋል፤ ሆኖም ግን አሁንም አልጠገቡም፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ የሚገርመው ግን ከሰሞኑ የዳቦ ቤት ባለንብረቶች ለደንበኞቻቸው ከአምሰት ዳቦ በላይ እንዳይሸጡ መወሰኑ ነው፡፡ የዳቦ ደንበኞችም ዳቦ ቤት ሒደው በመታወቂያቸው ፈርመው ገዝተው መመለስ አለባቸው፡፡
ዐሥር ቤተሰብ ያለው ሰው አንድ ዳቦ ለሁለት ሰው ማካፈል ግድ ሊለው ነው ማለት ነው፡፡ በዳቦ ቤት ሥራ የተሠማሩ ግለሰቦች በዚህ ሳምንት እንደገለጹልኝ ድርጊቱ ለመንግሥት ቅርበት የሌላቸውን ወይም ገልለተኛ አቋም ያላቸውን ነጋዴዎች ከጨዋታ ውጭ ማድረግ ነው፡፡ ለአንድ ሰው አምስት ዳቦ በቀን ተሸጦ ምንም ቢሆን የመብራት፣ የቤት ኪራይና፣ የሠራተኞች ወጭ ችሎ ንግዱ መቀጠል አይችልም፡፡
ይህ የለየለት የዘረፋና የዐማራ ነጋዴዎችን የማደኽየት ሴራ በአስቸኳይ እንዲስተካከል ነጋዴው ብቻም ሳይሆን ተጠቃሚው ሕብረተሰብም ተቃውሞ ማሰማት አለበት፡፡
(መረጃ በመስጠት ለተባበራችሁኝ በባሕር ዳር፣ መራዊና አዲስ ዘመን ከተማ ነዋሪዎች አመሰግናለሁ፤ ወደፊትም ትብብራችሁ እንደሚቀጥል አምናለሁ)

9 Comments on “በባሕር ዳር ለአንድ ቤተሰብ አምስት ዳቦ በፊርማ እየተሸጠ ነው”

  1. Non sense lier.lie lie. there is no other news.there is no fight like this.there is many to say about ethiopia.so plz change another film.

  2. የምን ስብዕና ነው የምታወራው ወንድም! ሰብዕናን ለማገኝት ወያኔን የወንዶች ስራ ማሳየት ነው!
    አማራ ተሸክሞ እየመራ አምጥቶ ዛሬ አማራ የለም! አከርካሪውን መትተናል! ኦርቶደክስንም እምነቱን አከረካሪውን መትተና! አማራ ሽንታም! አማራ ፈሪ! የአማራ ጀግና አልነበረውም ወደፊትም እንዳይኖረው መሬቱን፣ትውልዱን፣ዘሩን ተከታትሎ ማጥፋት የወያኔ የቤት ስራ ነው፡፡
    አማራ ዳቦ ቢከለከል ምንድን ነው ጉዱ! ከመቀሌ መጥተው ባህርዳን ፎቅ ሲሰሩባት አማራን እኮ ገድለው፣አስገድለው፣ዘረፈው አዘረፈው ነው!
    ሁመራን ሲያስለቅቁት ሲያበርሩት አማራ፣መተባበር አቅቶት ዛሬም ወልቃይ ጠገደይ የትግራይ ሪፓፒሊክ ክፍል ሆነች! ለምን ዳቦ አይከለክሉትም ነው የምትሉት
    ጥጋቡ

  3. ታዲያ ምን ሆነ? ዳቦ አጣህና ምን ይሁን? መብትህን አትጠይቅና ስለ ዳቦ ታወራለህ!! ስለዳቦ ብቻ እንድታስብ ተፈልጎ ነዉ እንዲህ የሆነዉ፡፡ ገባህ? አሁን አፍህን ዘግተህ አምስት ዳቦሀን ተቀራመት፡፡ እሽ!!

  4. The Amharas have strong muscle to keep the load of slavery. What is the big deal here . Woyane can play the Amharas and even use them like pack animals if he wishes knowing that the Amharas are thick skinned and arrant fools of the century. Still begging woyanes for crumb of bread instead of snatching the bread and die for his inalienable rights to survive and exist like human being.

  5. To those of you who claiming this news is false: It is only very small part of the truth on the ground. I am witnessing this as one of the victims.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*