እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መከላከል አትችሉም ተባሉ

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መከላከል አትችሉም ተባሉMahlet Fantahun's photo.
የካቲት 4/2008 ዓ.ም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል በዋለው ችሎት እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ( ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ) አቃቢ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በሰነድና በአንድ የሰው ምስክር ማስረጃዎች አስረድቷል በሚል ተከሳሾች መከላከል ይገባቸዋል ሲል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎም መከላከያ ማስረጃዎች ያቀርቡ ከሆነ በሚል ፍርድ ቤቱ ጠይቆ፣ ተከሳሾች 200 የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች በጋራ እንደሚያቀርቡ አሳውቀው ነበር፡፡ ከዛ በኋላ በነበሩ ቀጠሮዎችም ምስክሮቻቸውን በዝርዝር ያስገቡ ሲሆን ከዛሬ ግንቦት 30 እስከ ሰኔ 8 , 2008 ድረስ ምስክሮቻቸውን እንዲያሰሙ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም የቀጠሯቸው ቀን ሳይደርስ ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው ጭብጥ እንዲያሲዙ ተጠይቀዋል። እነሱም የምስክርነት ጭብጥ ምስክሮች መሃላ ሳይፈፅሙ መያዝ እንደሌለበት ለፍቤቱ አስረድተው ውሳኔውን ለመስማት ለዛሬ ተቀጥረው ነበር።

Mahlet Fantahun's photo.

የዛሬው ውሳኔ ግን በጣም የሚደንቅ ነው። አራት ወር ሙሉ ፍርድ ቤቱ ሲሰጥ የነበረውን ትእዛዝ ይቃረናል። “መከላከያ ምስክር ማሰማት የለባችሁም ስለዚህ ለፍርድ ብይን ሃምሌ 13, 2008 ቅረቡ” የሚል ውሳኔ አስተላልፋለች ዳኛዋ።

 

1 Comment on “እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መከላከል አትችሉም ተባሉ”

  1. የምን ስብዕና ነው የምታወራው ወንድም! ሰብዕናን ለማገኝት ወያኔን የወንዶች ስራ ማሳየት ነው!
    አማራ ተሸክሞ እየመራ አምጥቶ ዛሬ አማራ የለም! አከርካሪውን መትተናል! ኦርቶደክስንም እምነቱን አከረካሪውን መትተና! አማራ ሽንታም! አማራ ፈሪ! የአማራ ጀግና አልነበረውም ወደፊትም እንዳይኖረው መሬቱን፣ትውልዱን፣ዘሩን ተከታትሎ ማጥፋት የወያኔ የቤት ስራ ነው፡፡
    አማራ ዳቦ ቢከለከል ምንድን ነው ጉዱ! ከመቀሌ መጥተው ባህርዳን ፎቅ ሲሰሩባት አማራን እኮ ገድለው፣አስገድለው፣ዘረፈው አዘረፈው ነው!
    ሁመራን ሲያስለቅቁት ሲያበርሩት አማራ፣መተባበር አቅቶት ዛሬም ወልቃይ ጠገደይ የትግራይ ሪፓፒሊክ ክፍል ሆነች! ለምን ዳቦ አይከለክሉትም ነው የምትሉት
    ጥጋቡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*