ሕወሓቶች በቻይኖች ስም እንደለመዱት የከብቶች ሀሞት ጠጠር ከአገር ሊያወጡ ሲሉ ተባነነባቸው::
ከከብቶች ሀሞት ውስጥ የሚገኘውንና ውድ ዋጋ እንደሚያወጣ የሚነገርለትን ጠጠር በድብቅ ከአገር ሊያስወጡ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡ ከአገር ሊወጣ ነበር የተባለው የከብቶች የሀሞት ጠጠር የ20 ሚሊዮን ብር ግምት እንዳለው ተነግሯል፡፡
ቀና በሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ አማካይነት እንደተደረሰበት የተገለጸው የሀሞት ጠጠር ዲኤችኤልን ጨምሮ በተለያዩ ዘዴዎች ከአገር በድብቅ ሊወጣ ሲል መያዙን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እንደ ምንጮች ማብራሪያ፣ አገሪቱ ከከብቶች የሚገኘውን የሀሞት ጠጠር የሚመለከት ምንም ዓይነት ገዥ ሕግ የሌላት በመሆኑ እስካሁን ድረስ ጥቅሙ ሳይታወቅ ነበር፡፡ ይሁንና አንድ ግራም የሀሞት ጠጠር እስከ 25 ዶላር በማውጣት በዓለም ገበያ ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ገበያው ተቀዛቅዞ ወደ 15 ዶላር ዝቅ ማለቱን ምንጮች አብራርተዋል፡፡
በግራም ይህንን ያህል የሚያወጣው የሀሞት ጠጠር፣ በተለያዩ መንገዶች ከአገር ሲወጣ ቆይቶ በቅርቡ በተደረገ የሕግ ማስከበር ክትትል ግን በአንድ ቻይናዊና በኢትዮጵያውያን አማካይነት በሥውር እንዲወጣ ሊደረግ ሲል ተይዟል፡፡ ከተያዘው የሀሞት ጠጠር ውስጥ 11 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በቦሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አማካይነት ለጨረታ ቀርቦ ነበር፡፡ በመሆኑም አራት ያህል ተጫራቾች በተሳተፉበት ጨረታ ከ14 ዶላር ጀምሮ እስከ 16 ዶላር የሚደርስ ዋጋ ሊቀርብ መቻሉ ታውቋል፡፡
በቦሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ገብረ ሕይወት ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ለጨረታ በቀረበው የከብቶች ሀሞት ጠጠር ተወዳዳሪዎች ቀርበው ተጫርተዋል፡፡ ይህም ሆኖ እስካሁን በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታወቁና ፈቃድ ኖሯቸው ወደ ውጭ ኤክስፖርት የሚያደርጉ ሁለት ድርጅቶች ብቻ መሆናቸውን አቶ ገብረ ሕይወት ገልጸዋል፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ስለሀሞት ጠጠር ያን ያህል ግንዛቤ እንዳልነበረና የኤክስፖርት ጥቅሙም ብዙ የታወቀ እንዳልነበር አልሸሸጉም፡፡
ከከብቶች የሀሞት ከረጢት ውስጥ የሚገኘው ጠጠር በአብዛኛው የዱቄት ወርቅ ባህርይ እንዳለው ይነገርለታል፡፡ ከወርቅነቱ ባሻገር ግን የተለያዩ ውድ ጌጣጌጦችን ለመሥራት፣ እንዲሁም ለባህላዊ መድኃኒት መቀመሚያነት የሚያገለግል የማዕድን ይዘት ያለው ነው፡፡
በዓለም ገበያ በሰፊው ግብይት የሚፈጸምበት የሀሞት ጠጠር፣ በተለይ በቻይናውያን የባህል ሕክምና መስክ ሰፊ ተፈላጊነት ያለው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ተከትሎም ከፍተኛ መጠን ያለው የከብቶች የሀሞት ጠጠር ወደ ቻይና ከተለያዩ አገሮች እየተላከ ይገኛል፡፡
ከፍተኛ የጥራት ደረጃ እንዳለው የሚነገርለርለት ከቀንድ ከብቶች በተለይ ከበሬና ከላም የሚገኘው የሀሞት ጠጠር ሲሆን፣ በቻይና የሚገኙ ቄራዎች ሠራተኞቻቸው የሀሞት ጠጠር እንዳይሰርቋቸው በማሰብ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉበት ሀብት መሆኑም ይነገራል፡፡
መንግሥት ግንዛቤው እንዲኖረውና ሕጋዊ ግብይት እንዲካሄድበት መንገዱን የጠረጉ ግለሰቦች ባደረጉት አስተዋጽኦ፣ ከአገር ሊወጣ ሲል የታየዘውን የሀሞት ጠጠር ደብቀው ሊያስወጡ ነበር ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የመሠረተው ዓቃቤ ሕግ፣ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡ የተያዙት ተጠርጣሪዎችም በመጪው ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በከፍተኛው ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ ቀጠሮ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
http://www.dailymail.co.uk/news/article-3098846/They-like-gemstones-good-ones-bad-ones-Man-arrested-stealing-cow-GALLSTONES-abattoir-Chinese-herbal-medicine-market-worth-20-000-kilo.html
If you love your country and your people don’t steal from your country. Instead be a part of a solution.
WEYANEA DEROM LABA AHUNEM MOLACHA LABA SHEFTA.NEW AGER MESHET WEGEN MEGEDEL HABET MEZEREFE NEW SERAW. YE BANDA TEREKEM.
Ethiopians you are behind of the world about 200 years.
በሃገራችን መቼ ነው ስርቆት የሚቀረው?
የሃገርን ልዕልና የካደው ትውልድ ማን ነው?
የቀደሙትን መንግስታት የሰሩትን ስህተት ለማስተካከል እውነት ሃገርን መስረቅና መውደም ነው ቁም ነገሩ ተሳስተው አሳስተው ዛሬም ትክክል ነን የምንለው/የምትሉት/ ቀደምት መንግስታት ምን አይነት ስህተት በኢትዮጵያ ላይ አልፈጸሙም/ሃገራቸውን አልካዱም፣አላፈረሱም ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፈው አልስጡም! እንወዳቸዋለን! መንጌንም እንወደዋል፣ሃይሌን! ምኒልክንም፣ዩሃንስንም! ጡት አልነከሱም እኮ!
1- ጤፍ ተሰረቀ
2- ቡና ተረሰቀ
3- ብር ከባንክ ተሰረቀ
4- ወርቅ ተሰረቀ (200ኪግ ወርቅ ባሌስትራ ሆነ ተሰረቀ)
5- ልጆች ተሰረቁ
6- ኮንዶሚኒየም ተሰረቀ( አረጉ፣ጠፋ)
7- ስኳር ተሰረቀ
8- መኪና ተሰረቀ
9- ድንበር ተሰረቀ
10- ታቦት ተሰረቀ
11- ፈተና ተሰረቀ
12- ወደብ ተሰረቀ
ይህች ሃገር የማትሰረቀው ምን ምን ይሆን? ይህ ሁሉ መሰረታዊ ምክንያት ምንድን ነው ትላላችሁ?
No matter what , woyane is solely responsible for all crimes being committed. It is a public secret that these individuals did not commit the crime with out prior knowledge and blessing of the big woyane Sharks . I think this is a petty crime as compared to the disappearance of 77 bl Birr stolen by Woyane military and civil party functionaries. In light of the facts, there had not been a single person, among Woyane big Sharks, so far had been sued and appeared in kangaroo court. Similarly these criminals too will be acquitted free by the order of the same infamous woyane hoodlums .