ቴአትርና ፊልም አሁንም ባርነት ላይ ናቸው፡፡ ክ/ሀገር ቴአትር ማሳየት አይታሰብም፡፡
ግንቦት 20፤ ለኪነ-ጥበቡ አበረከተየሚባለው ነገር ቅድመ ምርመራን ማስቀረቱቢሆንም ቴአትርና ፊልምን ግን ከደርግ ሳንሱርአልተላቀቁም፡፡ ለምሳሌ ሥነ ጽሑፍ፣ ስዕልናሙዚቃ ቅድመ ምርመራ አይካሄድባቸውም፤ቀድመው አይታዩም፤ አይመረመሩም፡፡ ይሄመጽሐፍንም ጋዜጣንም ጭምር ነው፡፡ ፊልምናቴአትር ግን ይገመገማሉ፡፡
በደርግ ጊዜ የነበረውአሰራር በፊልምና ቴአትር ላይ እስካሁን ቀጥሏል፡፡ለምሳሌ ቴአትር ለማሳየት ባህልና ቱሪዝምፈቃድ ካልሰጠሽ ቴአትርሽ አይታይም፡፡ ባህልናቱሪዝም ፈቃድ ካልፃፈ፣ ክ/ሀገር ሄደሽ ቴአትር ማሳየት አይታሰብም፡፡ ፊልምሽ ሲኒማ ቤት ለመታየት መጀመሪያ መገምገም አለበት፡፡በአንቺ ስራ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሰዎች(ገምጋሚዎቹ) “ይህን ነገር ጨምር፤ ይህንን ነገርአውጣ” የማለት መብት አላቸው፡፡ እስካሁን በግምገማ ምክንያት የታገዱ ምን ምን የመሳሰሉ ቴአትሮችና ፊልሞች አሉ፡፡
“ወይ አዲስ አበባ” የተባለ የጌትነት እንየው ቴአትር በግምገማ ምክንያት ከታገዱት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ ቴአትር ተገምግሞ ታግዷል፡፡ ይህ የሆነው ሊከፈት ለህዝቡ መጥሪያ ከተላከ በኋላ ነው፡፡ ኢህአዴግ ወይም ግንቦት 20፤ ፊልምና ቴአትርን ገና ነፃ አላወጣቸውም፡፡ በቃ ቴአትርና ፊልም አሁንም ባርነት ላይ ናቸው፡፡
This doesn’t surprise me since the people of Ethiopia themselves live in slavery. I agree with the use of the term “slavery” because a system that doesn’t allow individuals or group of people to exercise their right to freedom is nothing else but slavery.
ደርግ እኮ የኢትዮጵያ ጠላት አልነበረም!ነገር ግን ወያኔ ምንጊዜም ሲወለድ ጀምሮ ጸረ ኢትዮጵያ(ዊያን) መሆናቸውን በይፋ አረጋግጠዋል! ለዚህም አማራን፣ኦሮሞን ስንት ዜጎችን ገደሉ በምድር ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደው/የካሄደባት ሃገር/ ኢትዮጵያ ብቻ ናት! እስከ አሁን ድረስ የተገደሉት ሰዎች፣ስደት የሄዲት፣ደብዛቸው የጠፋ ስንት ናቸው? የጎሳ ወረርሽን በኢትዮጵያ ተሰራጭቶል!
ማሩ
ሰውን ገድሎ ዶክተር
ሰውን ገድሎ ሃብታም
ሰው ገድሎ ስልጣን
ሃገርን አጥፍቶ አዋቂ
ፈላስፋ፣ምሁር፣ወታደር ስንቱን ስንቱ የዚህች ሀገር በደል ማቆሚያ የሌለው!
አንድ ትውልድ እንኳን በቃ አይልም ወይ?
ቢዋ