መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ (መስፍን ወልደ ማርያም)

መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ  ( መስፍን ወልደ ማርያም )

መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡


ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን የነበረውን ይዘን ዛሬ ትንፋሽ የማትችለዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል እያወቅን ለገዳይ ብንዘፍን ለሰውነታችን ውርደት ይሆናል፤ ይህንን ብለን ጉዳዩን እንዳንዘጋው በመግደል ልቡ የደነደነ፣ በድን ያልሆነለትን ሁሉ መግደል ልማዱ የሆነ፣ ከመግደል በቀር እምነቱን የሚገልጽበት መንገድ የሌለው፣ ከመግደል ሌላ እንጀራ የሚበላበት ሙያ የሌለው … እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው መገዳደልን የኑሮአቸው ዓላማና ዘዴ ሲያደርጉ በዝምታ መቀበል፣ ማለት አባቱ ሲገደል ልጁ ዝም ሲል፣ ባልዋ ሲገደል ሚስት ዝም ስትል፣ … ማንም ሰው አለፍርድ ሲጠቃ እያዩ ዝም ማለት ገዳዮችን ያራባል እንጂ ግድያን አያቆምም፤ እንዲህ ያለው በመንፈስ የሞቱ የበድኖች ዓለም ነው፤ በአውሬዎች ዓለም ጉልበት ያለው ደካማውን እየበላ ይኖራል፤ የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ የሰው ልጅ በዚህ በአውሬዎች የተፈጥሮ ሕግ አይመራም፡፡


የሰው ልጅ በተፈጥሮ ሕግ የማይመራበት ምክንያት ምንድን ነው? አውሬዎች አያስቡም፤ የሰው ልጅ ግን ያስባል፤ የሰው ልጅ አእምሮ አለው፤ አእምሮ ስላለው ያስባል፤ ያስባል ማለት ከተግባር በፊት ትክክለኛውንና ስሕተት ያለበትን ለይቶ ያውቃል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ልጅ ሕግ ነው፤ ያሰበውንም ይናገራል፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ስሜቱን ለይቶ ይናገራል፤ የሰው ልጅ ኅሊናም አለው፤ ‹‹ሌሎች ለአንተ እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን አንተም ለሌሎች አድርግ!›› ይላል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ሕግ ነው፤ ስለዚህም መግደል፣ በተለይም የመግደል ሱስ፣ የአራዊት እንጂ የሰው ልጅ የችግር መፍቻ ዘዴ አይደለም፤ አራዊት የሚገድሉት ሊበሉ ነው፤ ሰውም ወደአራዊትነት ሲለወጥ የሚገድለው ሊበላ ነው፤ እዚህ ላይ ሰውና አራዊት ይመሳሰላሉ፡፡


በመሠረቱ የመግደል ዓላማ ዝም ለማሰኘት ነው፤ ድንቁርና ነው እንጂ ካፍ ከወጣ አፋፍ ነውና የሚጠሉት ሀሳብ በሌላ ሰው አንደበት ይደገማል፤ መግደል የመጨረሻውን ዝምታ የሚያስከትል ቢሆን ክርስትናም እስልምናም 2007 ዓ.ም. አይደርሱም ነበር፤ ገዳዮች ሰዎችን ሁሉ ጨርሰው ብቻቸውን በመቅረት የሚያገኙት ጥቅም እንደሌለ ስለሚያውቁ የመግደል አማራጮች በሆኑ ሌሎች ዘዴዎች ይጠቀማሉ፤ አንዱ ማሰቃየት ነው፤ ሌላው ማሰር ነው፡፡
ሰዎችን በሀሳብና በእምነት ገባር ለማድረግ ጉልበተኞች የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መግደል፣ መግደል አላዋጣ ሲል ማሰቃየት፣ ማሰቃየት አላዋጣ ሲል ማሰር፣ ማሰር አላዋጣ ሲል አስሮ ማሰቃየት ነው፡፡
አውሬነትን የተላበሱ ሰዎች የማይገባቸው አንድ ነገር አለ፤ የሚጠሉትና ሰዎችን እስከመግደል፣ እስከማሰርና ማሰቃየት የሚያደርሳቸው ነገር በውስጣቸው ተቀብሮ አለ፤ ነፍሳቸው ከዚያ ነገር ጋር ተቆራኝታለች፤ በመጨረሻም የሚሸነፉት በዚያው ነፍሳቸው ውስጥ በተቀበረው ነገር ነው፤ በውስጣቸው የተቀበረው ነገር አስገድሎ አስገድሎ በመጨረሻ ይገድላቸዋል፤ ጥላቻም አስገድሎ አስገድሎ ይገድላል! በጥላቻና በመጋደል ሰላም አይገኝም፤ ‹‹ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር!›› (ኢሳይያስ 48/22)
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ለሰላም!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ንስሐ ለመግባት!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ይቅር ለእግዚአብሔር ለመባባል!
የዛሬ ዕብሪተኞች የሙሶሊኒን (ተዘቅዝቆ የተሰቀለውን)ና የጋዳፊን ቦይ ውስጥ ተወትፎ የተገኘውን አስበው ልባቸውን ለምሕረትና ለእርቅ እንዲከፍቱና ለልጆቻቸው የፍቅርና የመተማመን ዘመን እንዲያውጁ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ወኔ ይስጣቸው፡፡

11 Comments on “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ (መስፍን ወልደ ማርያም)”

  1. Shunma metrames bicha hunoal. Mehurun ke weyalaw.
    Hqegnawun ke qetregnaw meleyet alchalnim. Bezih yemiteqemu AKERARIWOCH nachew.
    Beteigust yemitbkut
    yerasachwun qen neaw .

  2. long live Geday Jegna !!

    Geday ewedalehu

    tekuwashim altela

    sedekmegn arfalehu begoferew tila

    prof jaju mesel ! KKKKK

  3. Weyanes are worser than animals. That is the reson to come out of woods.they must go back to the jungle.

  4. You BARBARIC “Senu – your dirty empty mind does never has the right to critisize the great son of Ethiopia

  5. ወያኔ ጡት የጣለው አማራ መሞጣብ፣የወያኔ ጠላት አማራ ነው ድህነትም ያመጣው አማራ ነው፣በትክክል አላማቸው እኮ ማፍረስ፣ማናከስ፣መግደል፣መስረቅ፣ሃገር ማስገንጠል መሬትን ማራቆት፣ማስጠፋት፣አማራን ማጥፋት ከሃገሩ ማባረርና ማፈናቀል፣ማቃጠል ቤታቸውን በቦንብ መደብደብ፣በስውር መግደል በይፋ መግደል ዛሬ የጀመሩት አልነበረም አልገባን ብሎ እንጅ የጥፋት ምኞታቸው ተሳክቶላቸው እነሆ የባንዳ ልጅ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያወጅትን ክህደት በስራ እያተገበሩት ነው፡፡
    ሕገ ሰውና ሕገ ጅብ (የዱር እንሰሳት) በስራ ላይ የዋለው የትኛ ነው
    የዲር እንሰሳት ሕግጋት በተግባር ያሳያሉ ሰው ግን ሕግ አለኝ ይላል እውነቱ ግን በዚህች ሃገር በተለይ በተለይ አሁን ሕግ የሚባል የለም አይሰራም አለመስራቱን ደግሞ በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ግድያ በመፈጸም አሳይተውናል
    አከረካሪውን የተመታው አማራና ኦሮሞ! አንገቱን ማስደፋትና ማዋርድ የተሰጣቸው የቤት ስራ ነው!

    አንባቸው

  6. ወያኔ ጡት የጣለው አማራ መሞጣብ፣የወያኔ ጠላት አማራ ነው ድህነትም ያመጣው አማራ ነው፣በትክክል አላማቸው እኮ ማፍረስ፣ማናከስ፣መግደል፣መስረቅ፣ሃገር ማስገንጠል መሬትን ማራቆት፣ማስጠፋት፣አማራን ማጥፋት ከሃገሩ ማባረርና ማፈናቀል፣ማቃጠል ቤታቸውን በቦንብ መደብደብ፣በስውር መግደል በይፋ መግደል ዛሬ የጀመሩት አልነበረም አልገባን ብሎ እንጅ የጥፋት ምኞታቸው ተሳክቶላቸው እነሆ የባንዳ ልጅ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያወጅትን ክህደት በስራ እያተገበሩት ነው፡፡
    ሕገ ሰውና ሕገ ጅብ (የዱር እንሰሳት) በስራ ላይ የዋለው የትኛ ነው
    የዲር እንሰሳት ሕግጋት በተግባር ያሳያሉ ሰው ግን ሕግ አለኝ ይላል እውነቱ ግን በዚህች ሃገር በተለይ በተለይ አሁን ሕግ የሚባል የለም አይሰራም አለመስራቱን ደግሞ በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ግድያ በመፈጸም አሳይተውናል
    አከረካሪውን የተመታው አማራና ኦሮሞ! አንገቱን ማስደፋትና ማዋርድ የተሰጣቸው የቤት ስራ ነው!
    አንባቸው

  7. ይህ መልዕክት አሁንም ለገዳዮች አይነበብም
    ይህንንማ እሚመለከት በዙርያቸው ቢኖር
    ሰው ሆነው ነበር፡ ሰው ሶሻል አኒማልስ ቢባልም ነገር ግን እነዚህ ?ገዳዮቹ በሁለት
    እግር የሚሄደው ዶሮ ራስ ናቸው ድሮ ያለትላትል እነሱ ካልገደሉ አይረኩም፡
    በሃይል ካልተገደዱ በምሁሮች አያምኑም
    ይህንን ጊዜ የግድያ መፍትሄ እያፈላልጉ
    ነው።

  8. uly 27, 2012 at 8:32 am

    መለስ ፍጹም አይሙት:-
    XXXXXXXXXXXXX
    የለም አይገባም መለስ ፍጹም አይሙት:-
    ሊሞትም ከሆነ በግፉ አክሙት::
    ሞትማ ይ-ሞ-ታል፣ጣሊያን ወደድክና፤
    ያንተ ግን ቅስፈት ነው፣ሁለቴ ሞትክና።
    አንዱ በቁምህ ነው፣የባንዳ ልጅ ሆነህ፤
    ሌላው በትውልድ ነው ሁሌም ተኮንነህ።
    እንኳን ጨርቅ ብሎን የሰንደቅ ዓላማን፤
    በተንኮል ጠቅልሎ:-
    የጨርቅ መንገዱን ሰማን።
    እየረገመኽ ነው ሕዝቡ የሚያወሳ፤
    ሬሳህን ሲያነድ ክፋትክን ላይረሳ።
    ኢትዮጵያን ለቅርጫ በዓመታት ያረደ:-
    ያለአንገት ያስቀራት ሕዝቧን ያዋረደ:-
    ቅስፈተ-ሥቃዩን ባይኑ ሳያይ ሕዝቡ:-
    ያምላክን ታምራት ሳያሳድር ልቡ:-
    በዚህች ምድር ፍርዱን በቁም ሳይቀጣ:-
    እንደምንስ ብላ ነብሱ ቶሎ ትውጣ??
    የለም አይገባም ወቸገሉ አይሙት:-
    ሊሞትም ከሆነ በመጥረቢያ አክሙት::
    አውቃለሁ ይሞታል፣የሕዝብ ደም ደፍቆት፤
    አደራ ሬሳውን፣ጽዕብ አይብላው ሰርቆት።
    ይህንን አደራ በሚሥጥር ይዛችሁ፤
    ሌላውን ጉጅሌ ቃኙ በርትታችሁ።
    እንደጋናው መሪ ለሕዝብ አትንገሩ:-
    የመለስ አሟሟት:-
    ብዙ ነው ሚሥጥሩ::
    በሚሊዮን አስፈጅቶ ቢሊዮን ብር ያካበተ:-
    ሠራዊት ጅብ አደራጅቶ በቁሙ ነው የሞተ::
    እናም ደብቁለት ዋሹለት በቁሙ:-
    እየተላ ገላው ይከርፋበት ደሙ::
    አውቃለሁ ይሞታል፣የሕዝብ ደም ደፍቆት፤
    አደራ ሬሳውን፣ጽዕብ አይብላው ሰርቆት።
    ግና እንደገደለ:-
    እንደወቸገለ:-
    ይወላልቅ አጥንቱ አቅም ይንሳው ጌታ:-
    ሞቱን አዘግይቶ ያቆየው መኝታ:-
    እናም የምትዋሹ በጎ ነው በሉለት:-
    ግና ተናገሩ ሕዝብ የሰቀለው ዕለት::
    ሊሞትም ከሆነ በግፉ አክሙት:-
    አይገባም የለም መለስ ፍጹም አይሙት:

  9. እንግሊዝ ለኢትዮጵያ እስር ቤት መገንቢያ 27000000 (ሃያ ሰባት ሚሊዪን ፓውንድ) ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኖ ቶኒቢሌር አዲስ አበባ የመጣው ለጉብኝት ወይም ኢትዮጵያ ናፍቃው አይደለም ለተንኮል መምጣቱን ማወቅ አለብን!
    እስር ቤቱ የሚገነባው በአማራ ክልል ሲሆን ጥናቶች ተጠናቀዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*