ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥመኞች ናቸው …. ቢሆኑማ ኖሮ …

ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥመኞች ናቸው …. ቢሆኑማ ኖሮ …
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሰሞኑን ወያኔዎች በሕዝብ እና ሃገር ሃብት ላይ የሚቀልዱት እያንገበገበን ለውጥ ፈላጊ ነን ባይ የማህበራዊ ድህረገጽ አሸብሻቢዎችም አብረው ቀልዱን ሲያሳምሩለት ማስተዋል በጣም ያማል:: ሕወሓት መራሹ አገዛዝ እና ካድሬዎቹ ለለውጥ የሚታገሉትን ሃይሎች የስልጣን ጥመኞች እንደሆኑ አድርገው ሲስሉ ይስተዋላል::አብዛኛውን ጊዜ ስለሃገር አንድነት እና ፍቅር ሲወራ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂ ብለው የሚፈርጁት ሕወሓቶች ተቃዋሚውን የስልጣን ጥመኛ ብለው የጭቃ ጅራፋቸውን ሲያጮኹት ይውላሉ:: ተቃዋሚዎችን የስልጣን ጥመኞች ቢሆኑ ኖሮ ስለ ሕዝብ ነጻነት እና መብት አገራቸውን ጥለው ባልተሰደዱ አልያም በሃገር ቤት ያሉ ከስራቸው ባልተፈናቀሉ ባልታሰሩ …የተወሰኑ ምሳሌዎች ብንወስድ …..

Minilik Salsawi's photo.

ከሃገር ቤት ዶክተር መረራ ጉዲና እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም ከውጪው ከተሰደዱት ውስጥ ዶክተር ብርሃኑ ነጋና መሰሎቻቸውን መመልከት በቂ ነው::ከነዚህ የለውጥ መሪዎች ጋር የተያያዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሉ:: በምሳሌ ደረጃ ስማቸውን ከላይ የጠቀስኳቸእ የስልጣን ጥማት ቢኖራቸው ኖሮ ዶክተር መረራ የአዲስ አበባን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት ጋዜጠኛ እስክንድር የሚዲያ ሚኒስትርነት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት መድረስ ይችሉ ነበር:: ሌሎችም የተሰደዱ የታሰሩ የሚንገላቱም የተገደሉም እንዲሁ…ወያኔ ጉያ ውስጥ ከሕዝብ ይልቅ ለሆድ ማደር ከተቻለ ስልጣን ማግኘት ቀላል ነው::ተቃዋሚዎች በአላማ ጽናት ለሕዝብ ነጻነት ና መብት መታገላቸው ስራቸው ብቻ ምስክር ይሆናቸዋል:: የተቃዋሚው ሃይል የስልጣን ጥመኛ ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል መንገድ እየተሽከረከረ አይንገላታም አይገደለም አይታሰርም አይሰደድም ነበር:: ጭንቅላት ያልፈጠረባቸው የሕወሓት ካድሬዎች ይህንን ቀላል አስተሳሰብ ደጋግመው በማውራት የበታችነታቸውን እያሳዩን ይገኛሉ::

የውሸት ጎተራው ሕወሓት ተቃዋሚዎችን ለመፈረጅ የሚጠቀምበት ጉዳይ ሁሉ የተበላበት እቁብ ነው::ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥማቱ ቢኖራቸው ኖሮ በአቋራኝ የተፈለገበት የስልጣን እርከን ላይ መድረስ ይችላሉ::ይህ ደግሞ በሆድ አደሮች እና በታማኝ ተቃዋሚዎች በፊትለፊት እያየነው ያለነው ጉዳይ ነው::ተቃዋሚዎችን የስልጣን ጥመኞች ማለት በራስ እኩይ ስራ ውስጥ ራስን ለመደበቅ የሚደረግ ሩጫ ነው::የስልታን ጥመኞች እነማን ናቸው የሚለውን ለመለየት ስልጣንን ሙጥኝ ብለው ሃገር በመዝረፍ አለቅም ያሉት የወያኔ ባለስልጣናት እና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ስልጣኑን ለሕዝብ ያስረክቡ::የስልጣን ጥመኝነት ያለበት ምንጊዜም በስልጣን ላይ ያለ አካል ነው::የስልጣን ጥማት ያለበት አምባገነን አገዛዝ ብቻ ነው!!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

12 Comments on “ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥመኞች ናቸው …. ቢሆኑማ ኖሮ …”

  1. aye Minilik kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

    Dr BIRHANUMA YE WEYANE BALESILTAN NEBERU EKO KKK

    antem ahun esachewin le aqme 4 kilo lemabkat

    betam guwagutehal

    yemechih ,kkkk

    shabya netsa kawetan tiru new !!!

  2. Ante weyane! Go back and enjoy your locust. ( Hageri temelise anbetahim zimble temegeb. Yewusha lij. Kikikikikikikkiki!!!!

  3. ግጥም አድርገዉ!!! የስልጣን ጥመኞችና እርሀብተኞችም ጭምር እንጂ።እንዲዉ ሌላው ይቅር በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተፃፈዉ መፅሐፍ” የነፃነት ጎሕ …”መፅሐፍን ያንብቡ።እንዲሁም ከልደቱ አያሌው እስከ ሐይሉ ሻዉል፣ከፕሮፌሰር መስፍን እስከ ዶክተር መራራ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1997 ወዲህ ከጋዜጠኞች እስከ ፖለቲከኞች የተፃፋት ከጋዜጣ እስከ መፃሕፍት በሙሉ የሚተርኩት ስለተቃዋሚዉ የስልጣን ጉጉት ብቻ አይደለም ስስታም ጭምር ነው።እኛም እንደ ዜጋ የምናየው ይሕን የሚረጋገጥ ነው።እርስዎ ከየትኛው ፕላኔት በፓራሹት ወደኢትዮጵያ ፖለቲካ ዱብ እንዳሉ ባላዉቅም ያለው እዉነታ ግን ከእርስዎ እይታ ጋር በተቃራኒው መስመር ላይ ነው የሚገኘው።ምናለ እንደ እርስዎ ሐሳብ በሆኑልን።ምናለ ባያስጎመጁን፣በኩዳዴ ፆም ዝልል የበግ ጥብስ መመኘት እንደማለት ነው የእርስዎ እይታ።ለማንኛዉም ከቆሙባት መርከብ ወረድ ብለዉ ዙሪያ ገባዉን ይቃኙ።ቸር ይሠንብቱልኝ።ኢሐድግ በግፍ ያሠርካቸዉን ከጋዜጠኛ እስከ ፖለቲከኛ ፍታቸዉ።ሕዝቡ መንግስትንም ሆነ ተቃዋሚዉን በሚገባ ያዉቀዋል።

  4. Manm sew slTan mefelegu mnm s-htet yelebet.
    SlTn lemeyaz masebna meTar tegeb tkkl new.
    SlTan lemeyaz memeñet manñawnm liela sra lemeyaz ke memeñet/mewded yetaleye aydelem.
    Bagerachn slTan ye yazu miqawomachewn slTan lemeza quamTo, yeslTan Tmun lemarkat tenqesaqsual bemalet yiwonjlalu.
    SlTan lay hunew lelielawn yeslTan Tmeña maletachew achiberbari, denqorowoch yasblachewal.
    BergT le rasu Tqm enj le agerna le hzb asbo aydelem yemiyasbl slTan ke yaze behuala beseraw meTfo neger tayto new.

  5. ” ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥመኞች ናቸው  ”

    Why pay attention at all and help spread TPLF propaganda ?

    Is “Minilik Salsawi” a CIA agent, or a TPLF supporter ?

  6. ምንሊክ ሳልሳዊ is not a trustworthy guy.

    He is tribalist, perhaps also CIA agent, also TPLF supporter.

  7. እከ ደከ ማን ችሎት በጉልበትም ሆነ በብልጠት ሁሌም ከወንድ በላይ አበጀ says:

    ትክክል ነህ! የሥልጣን ጥመኞች አይደሉም። ቢሆኑማ ፦
    1. አንድ ሆነው አንድ ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ በገነቡ።
    2. የሻዕብያ ተላላኪ ባልሆኑ።
    3. አንገትን በሜንጫ ባላሉ።
    4. ለ 25 ዓመት ያለ ለውጥ ባልተቀመጡ።
    5. ለኢትዮጵያ ሠላምና እድገት በተመኙ።

    ቀጣዩ የአሜሪካ ፕረሲዳንት ትራምፕ የምንመርጣቸው እኮ? ባለ ሜንጫዎችን አደብ ያስይዙልናል ብለን ነው።

  8. =========> 1. አንድ ሆነው አንድ ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ በገነቡ።

    What a retard, Qinijit is such a good example.

    But it was sabotaged by subhuman USA or CIA.

    ========> ቀጣዩ የአሜሪካ ፕረሲዳንት ትራምፕ የምንመርጣቸው እኮ

    Is this guy that retarded who votes or speaks positively about NAZI trump ?

  9. A guy who dares say things like this =====> ቀጣዩ የአሜሪካ ፕረሲዳንት ትራምፕ የምንመርጣቸው ( ! ) እኮ
    is an enemy !

    NAZI tRump is hated all over the world and the subhuman above says he will vote for tRump ? The subhuman also calls NAZI tRump “antu”, what a disgusting guy who should not call himself Ethiopian, African or black.

  10. በአዲስ አበባና በክልል ኮንደሚኒየሞቹ የት ተሰወሩ?ወደትስ አረጉ? በሞያሌ በኩል አድረገው ከሃገር ወጡ?በቦሌ በክብር በአውሮፓ በቦይነግ 777 ተጭነው ጀግኖቹ አውጡት! ወይስ በግንቦት ሰባትና በሻቢያ ተሰርቀው ተወሰዲ? ጉድይ ነው በዘመን ምናምን ልማታዊ መንግስት፣ሃገራዊ እይታ አለን እንዴ? በዘር መኮፈስ መመጻደቅ እኛ ብቻ ነው የምናውቅል/ሽ/ አይናችሁን ጨፍኑ እናሙኛችሁ ለጥፋት የመጣ ሁሉ ዛሬ ስለልማት ይወራልናል
    ስንቱን እድለኞች ከቤታቸው አላስወጡምና ነው ጅግኖቹ በጎጥ አስተሳሰብ የመጣ ሁሉ አቅጣጫው ይታወቃል ውጤቱ ውድቀት ብቻ ነውና ስግብግብነት ነግሶ ሃገር የለንም!
    ሳ.አ

  11. No matter what people talk about woyane , lease of life shall continue for another decades despite loosing support from the majority of people and getting weaker and weaker . The divide and conquer policy is working perfectly. Suspicion of one another between groups, parties and political organization who vowed to tear the woyane regime so long perpetuated, woyane continue to cling on power comfortably but with full alert of controlling group resentments and of course at time the rising tide of people’s disobedience like the one taken place in Oromo region exclusively would be quelled by means of merciless force and incarceration of ring leaders. Such measure does yield for woyane temporary relief to continue rule in more harsher way . Since there exists strong organization that lead the people struggle in coordinated manner , success is unthinkable in forseable future . Thus the woyane gradually but surely keep its iron hand ruling for many years to come The longer the Woyane on power , the more the resource of this country will be depleted as a result of the woyanes deliberate action of impoverishing the whole of Ethiopian people to guarrantee the continuation of Tigray as an independent Tigray republic . I think from what we witnessed so far, the situation seem more favorable to woyane to deal problems arising in various ethnic regions case by case . Because there are no signs so far the various ethnic demands for freedom has never commanded United plat form.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*