ወያኔ በላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈተ

ወያኔ በውጭ የሚገኙ የተደራጁ የኢትዮጵያዊያንን ተቋማት ለመቆጣጠርና መጠቀሚያው ለማድረግ ካልቻለም ለማፈፍረስ ወይም ለማዳከም የነደፈው ዕቅድ አካል የሆነ አዲስ የጥቃት ዘመቻ በላስ ቬጋስ የቅዱስ ሚካኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ መጀመሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወያኔ ቀደም ሲል ወደዚህ ደብር ውስጥ አሰርጎ ባስገባው ሲሳይ ኪዳኔ በተባለው የህ.ወ.ሃ.ት. ሰላይ አማካይነት በደብሩ ውስጥ ክፍፍልና ብጥብጥ ለማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ጀምሯል። የላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን ጠንካራ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያሉበትና በውጭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ሕጋዊው ሲኖዶስ) ስር ያለ መሆኑ በስፍራው የሚያንዣብቡ የወያኔ ተላላኪዎች ላይ ጥርስ ተነክሶበት የነበረና ጊዜ ሲጠበቅለት የነበረ መሆኑንን ተገልጾልናል። የደብሩ ምዕመናን ከሁለት ዓመታት በፊት የራሳቸው ሕንጻ ገዝተው በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ማስመረቃቸው ይታወሳል።

የህወሃቱ ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ በደብሩ ውስጥ አንዳንድ ጥቃቅን ስራዎችን በነጻ እሰራለሁ በማለት አጭበርብሮ የተጠጋ ከመሆኑም በላይ አለችሎታውና አለዕውቀቱ የተለያዩ ስራዎች ላይ ገብቶ ለመፈትፈት ጥረት ሲያደርግም እንደነበር ተጠቁመናል። ግለሰቡ ወያኔን ይቃወማሉ ብሎ የሚገምታቸውን የደብሩን የቀድሞና የአሁን የሰበካ ጉባኤአባላትን ስም ለማጥፋትና እርስ በርስ ለማጋጨት የተለያዩ ደባዎችን ሲሸርብ የነበረ መሆኑና አሁን ግን መጋለጡ ታውቋል። ይህ ግለሰብ የማይመለከተው ጉዳይ ውስጥ ዘው ብሎ ለመግባትና የደብሩን መገልገያዎች በግል ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም እንዳልተሳካለት ተገልጾልናል። ሲሳይ ኪዳኔ የሚሰነዝራቸውን ፍሬ ቢስ ሃሳቦችና መሰሪ ዕቅዶች ላይ ተቃውሞ የሚያቀርቡ አባላት ላይ የተለያዩ ስድቦችን እንደሚለጥፍባቸው ለምሳሌም “እብድ” “የአይምሮ በሽተኛ” እያለ እንደሚያዋርዳቸውና ምንም ዓይነት ግብ ረገብና ሥነምግባር የጎደለው ተራ ካድሬ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።

ከደብሩ ውስጥ አወቆች በደረሰን ጥቆማ መሠረት የወያኔው ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ ዓላማ በዋናነት ያነጣጠረው በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ በመገኘት አዘውትረው አባታዊ ምክር የሚሰጡትንና ደብሩ አሁን ለደረሰበት እድገት ገንቢ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ እንደሆነ ታውቋል። አቡነ መቃሪዎስ የግንባር ስጋ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዓለም ማዕዘናት በመዘዋወር ኢትዮጵያዊያን ላይ ወያኔ የሚያደርገውን ግድያ፣ እስር፣ማሰቃየትና ማሰደድ በማጋለጥ እንዲቆም የሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳው ይታወቃል። አቡነ መቃሪዎስ በሚሰሩት ስራዎች  “የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ” ተብለው ቢጠሩ የማይበዛባቸው መሆኑን የሚናገሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገሮች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል። በተለይም ከአንድ ዓመት በፊት ሊቢያ ውስጥ ስለታረዱት ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተገኝተው ያሰሙት ታሪካዊ ንግግር ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያ በፋሽት ኢጣሊያ በተወረረችበት ጊዜ ”ሊግ ኦፍ ኔሽንስ” ጄኔቫ ውስጥ ተገኝተው እ.አ.አ. ሰኔ 1936 ካደረጉት ንግግር ጋር የሚያመሳስሉ በርካቶች ናችው። ከዚህም በተጨማሪ አቡነ መቃሪዎስ የዋልድባ ገዳም ውስጥ ወያኔ የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ መናንያንና ገዳማዊያንን መኖሪያ ቤቶችና መቃብሮችን በግሬደር ሲያፈርስና ሲጠርግ እንድሁም ከገዳም ሲያባርር በግምባር ቀደም ያወገዙና የተቃወሙ ለእውነትና ለፍትህ ግምባራቸውን የማያጥፉ እውነተኛ የሐይማኖት አባት ናቸው።

እኝህ ታላቅ አባት ለአገራችን ኢትዮጵያ የሚሰሩትን ታላላቅ ስራዎችን ለማኮላሸትና ተሸማቀው እንዲቀመጡ ለማድረግ ክብራቸውንና ስብዕናቸውን የሚያጎድፍ የተለያየ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን ወያኔ በተደጋጋሚ ሲያደርግ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። የዚህ መሰሪ እንቅስቃሴ ቀጣይ የሆነ አዲሲ ጥቃት በላስ ቬጋሱ ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ አማካይነት ወያኔ በአቡነ መቃሪዎስ ላይ ከፍቷል። የወያኔው ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ በአቡነ መቃሪዎስ ላይ የከረረ ጥላቻ ያለው ከመሆኑም በላይ እሳችው ላይ የተለያየ የሃሰት ወሬ ማስወራትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ስልክ በመደወልና ለተለያዩ ሰዎች በግምባር በመገኘት ሲቀሰቅስ እንደነበር ተገልጾልናል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ሲሳይ ኪዳኔ በአቡነ መቃሪዎስና በሌሎችም የቀድሞና የአሁን የቦርድ አባላት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በጽሁፍ ማውጣቱንና ይህንንም አስመልክቶ ሪፖርት ለማድረግ በነገው ዕለት ወደ አዲስ አበባ እንደሚሄድ ጥቆማ ደርሶናል። ይህ ግለሰብ ሲለሚያደርገው አኩይ እንቅስቃሴና በአካባቢው ያሉ ኢትዮጵያዊያን ማድረግ ሰለሚገባቸው ጥንቃቄ ተጨማሪ መረጃ አሰባስበን እናወጣለን።

23 Comments on “ወያኔ በላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈተ”

  1. I remember at D.C Debre Selam church when disturbace Kise Tesfaye mekoia leading the chaos he was using different words to confirm what he is doing during sundau morning to the congrigation its one the word ” its “this is one lesson for those who are serve the Ethiopian church who leads the church as addminsterate their own (all Ethiopia christian ) local churches without Ethiopia based senod interference execpt all the religon’s “Dogema , kenona and other church law and norms but , I see it its not about unification of our church with such a unchristian movement its purposely pland by collanizer TPLF oiled temporary cadre so called kise .Its what it my sisters or brother fellow Ethiopian the truth we need to understand this and do what we can do , praaise the Lord Read this “Psalm chap 68 vers 31.good day my people.

  2. YWYANE SLAY KADREWOCH BYE BETKRSTYANU TMDEBAW EYAMSUN NEW BEDMONTEN CANADA MEDHANEALEM BETKRSTYAN GIRMA HADIS WELDU YTBALE YWEYANE KADREM ENDE SESAY
    SERGO BMGBAT EYESERA NEW .

  3. Abet wshet. Ere bakachuh wshet ykir. I am a member of the church and there is no disterbance nor such name at all. Why all this lies. Mhretu Tegegn.

  4. Addis abeba lay ye PENTE ..PASTEROCH …set Mamaget…Bet Mashet…Genzeb Kesewech Mezref …Be kebad huneta Ketlewal…Pasteroch mengst yektatlachew..lijagered…baletdar setochn chrswachew…Genzeb zerefu….

  5. Abune Makrios is one of the few honest, dedicated and true defender of Ethiopians throughout the world. In deed he can be called today’s Abune Petros.

  6. በጣም የሚገርም ጉዳይ ነው ከላይ ያነበብኩት። ሲሳይ ኪዳኔ የተባለው ሰው እንደዚህ የሰበካ ጉባዔ አባላትን ስም ጭቃ ሲለቀልቅና ታላላቅ ስራዎችን በማካናወን ላይ ያሉትን ብጹዕ አቡነ መቃሪዎጽን ሲያዋርድ ዝም ብሎ የሚመለከት የአስተዳደር ቦርድ (ሰበካ ጉባዔ) እራሱ የችግሩ አካል እንጅ የመፍትሄው ሊሆን አይችልም። መደረግ ያለበት የወያኔውን ተላላኪ ሲሳይ ኪዳኔን ከደብሩ ድርሽ እንዳይል ማባረር ነው። ይህ ካልሆነ ምናልባ ከሰበካው ጉብዔ አባልት መካካል የወያኔ ኮሶ የተጣባቸው ይኖሩ ይሆን እንዴ ነው የሚያስብለው። ሲሳይ ኪዳኔ ከላከው ኢሜል ማንነቱ ስለታወቀ ምን እስኪያደርግ ድረስ ነው የሚጠብቁት?

  7. እግዚአብሔር ይታረቅህ/ሽ። ምናለበት ለሰዎች አንድነት እንደዚ አድርገህ ብትጽፍ/ፊ። ይቅርታ አድርግልኝና ጥቅምህ የተነካ ግን ይመስላል።

    በእውነቱ ከሆነ እንደ ሲሳይ እና እንደሱ የመሰሉ ሰዎች ለበተክርስተያኑ ሲሰሩም ሆነ ስለህዝብ ንብረት ጥያቄ ሲያቀርቡ በስልጣን በያዘው ክፍል አይወደዱም።

  8. በምዕመናን የተመረጠ የሰበካ ጉባኤ እያለ በምን ውክልና ነው ሲሳይ የተባለው ሰው በቤተክርስቲያን ጉዳይ ገብቶ ሊያቦካ የሚፈልገው? አባታችን አቡነ መቃሪዎስ ምን ስላጠፉ ነው ሲሳይ ኪዳኔ የሚያዋርዳቸውና የሚያብጠለጥላቸው? አቶ ታምሩስ ቢሆኑ ለቤተክርስቲያኒቷ የማዕዘን ድንጋይና ምሶሶ የሆኑ ሰውን ስም ማጥፋት እጅግ የሚያሳዝን ነው። ሲሳይ ኪዳኔም አሁን ስለተጋለጠና እርቃኑን ስለቀረ ምንም የሚታሳስብ ነገር የለም።

  9. ወያኔ እዚህ ድረስ መጥቶ ሲበጠብጠን ምንም የማይሰማቸው ድንጋዮች ከመሃላችን መኖራቸው እጅግ ያሳዝነኛል። የቤተክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤ አፋጣኝና የማያዳግም እርምጃ በወያኔ ሰላዮች ላይ መውሰድ አለበት።

  10. What I read above was totally fabricated lie. The person who accused Sisay is the ones who are angry at him for bringing the truth. I bet this is one of the board member who wrote this nonsense. The board members at St. Michael Church in Las Vegas are milking the church’s money. Let us not forget, the same board members are the one who insulted our priest, called a police on the them, and kicked them out of the compound. Those priests were the one who built the church before anyone of the members existed. Especially the two thieves/dictatorships are Frezewde and Alebachew. They think they know it all just because they aren’t taxi driver us most of the fellow in Vegas. Sisay is truly a dedicated member of the church. He is not associated with any party. They are trying to destroy his name which is so disgusting. Whoever posted this post should be ashamed. I can’t believe someone could write this long just to humiliate a human being who is so innocent. Let God forgive your sin ! I will pray for your sin !

  11. Sisay Kidane is a TPLF spy. Enough is enough. TPLF will never sleep unless they destroy the whole country.

  12. ይህ ሁሉ የተቃጣው በብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ ነው። እኝህ ምትክ የሌላቸው አባት ደብረ ምሕረት ውስጥ እየተገኙ ኃይማኖታዊና አገራዊ ስራዎችን መስራታቸው ሲሳይ ኪዳኔንና ሌሎችንም የወያኔ ተስፈኞች እንቅልፍ ስለነሳ የተከሰተ ችግር ነው። ለቤተክርስቲያን የቆሙትን የቦርድ አባላት እዚህ ላይ ስማቸውን ለማርከስ የሚሞከረው በሙሉ አይሳካም። ሰዎቹ በስራቸው ማንነታቸውን አረጋግጠዋልና።

  13. This website is so corrupted. They have deleted all the people comment who are opposing the writer who is wrongly accused of an innocent man. This is American and anybody can exercise their first amendment . Freedom of speech is one of them if you don’t know what I am talking about – Please don’t smear his name on a mud – you are so disguising and rubbish to try to humiliate an innocent man on earth – I will pray for you – Asshole – leave the comment – Don’t delete any post supporting his innocent

  14. Wrongly accusing an innocent man – sad that you put all this time to write about a guy who loves his church – put your time on something constructive – silly and non sense – I am not buying your post – even Jesus is crucified for what believed – when someone is telling you the truth , you tired around and gave a name that he doesn’t deserved

  15. You guys have to understand the whole thing . Don’t rush to judge. Wrongly accusing someone is illegal –

  16. አቶ ለማ ከላይ ስለዚህ ድረ ገጽ የጻፉት እጅግ የተዛባ ነው። እርስዎ የድረገጹን አዘጋጅ ለአንድ ወገን ያጋደለ ነው እያሉ በውሸት እያወገዙ እራስዎ ግን ሚዛን የስተና የተጣረሰ አስተያየት ሰጥተዋል። አስተያየት የመስጠት መንትዎን አከብርልዎታለሁ። ይህ ድረገጽ ለሁሉም አስተያየት የእርስዎንም ስድብ ጭምር እያስተናገደ ነው። እርስዎ በተከታታይ የጻፏቸውን 3 ስድቦች/አስተያየቶች አውጥቶልዎታል።

    Lemma says:
    May 17, 2016 at 6:21 pm

    This website is so corrupted. They have deleted all the people comment who are opposing the writer who is wrongly accused of an innocent man. This is American and anybody can exercise their first amendment . Freedom of speech is one of them if you don’t know what I am talking about – Please don’t smear his name on a mud – you are so disguising and rubbish to try to humiliate an innocent man on earth – I will pray for you – Asshole – leave the comment – Don’t delete any post supporting his innocent

    Fafa says:
    May 17, 2016 at 6:34 pm

    Wrongly accusing an innocent man – sad that you put all this time to write about a guy who loves his church – put your time on something constructive – silly and non sense – I am not buying your post – even Jesus is crucified for what believed – when someone is telling you the truth , you tired around and gave a name that he doesn’t deserved

    Derge says:
    May 17, 2016 at 9:55 pm

    You guys have to understand the whole thing . Don’t rush to judge. Wrongly accusing someone is illegal –

    እንዲሁም ከእርስዎም በፊት ሌሎችም ሲሳይ ኪዳኔን በመደገፍ ከዚህ በታች የሰፈረውን አስተያየት ጽፈዋል። ለመሳሌ አቶ ምህረቱ ተገኝ ይህን ብለዋል።
    Mhretu Tegegn says:
    May 12, 2016 at 8:15 pm

    Abet wshet. Ere bakachuh wshet ykir. I am a member of the church and there is no disterbance nor such name at all. Why all this
    lies. Mhretu Tegegn.

    እንዲሁም ሌላ አስተያየት ሰጭ ይህንን በደረገጹ ላይ የወጣውን ጽሁፍ የሚቃወም ሃሳብ አቅርበዋል።
    DAG says:
    May 15, 2016 at 10:56 am

    “እግዚአብሔር ይታረቅህ/ሽ። ምናለበት ለሰዎች አንድነት እንደዚ አድርገህ ብትጽፍ/ፊ። ይቅርታ አድርግልኝና ጥቅምህ የተነካ ግን ይመስላል።በእውነቱ ከሆነ እንደ ሲሳይ እና እንደሱ የመሰሉ ሰዎች ለበተክርስተያኑ ሲሰሩም ሆነ ስለህዝብ ንብረት ጥያቄ ሲያቀርቡ በስልጣን በያዘው ክፍል አይወደዱም።”

    በአጠቃላይ ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚ ሃሳቡን የሚያንሸረሽበትንና በተለይም በወያኔ የታፈንን ሰዎች የምንተነፍስበትን ድረገጽ ጥላሸት መቀባት ምን ማለት እንደሆነ አንባቢ ይፍረደው። እኔ እንደርስዎ ወደ ስድብ ለመውረድ አስተዳደጌ አይፈቅድልኝም።

  17. አቶ ለማ ከላይ ስለዚህ ድረ ገጽ የጻፉት እጅግ የተዛባ ነው። እርስዎ የድረገጹን አዘጋጅ ለአንድ ወገን ያጋደለ ነው እያሉ በውሸት እያወገዙ እራስዎ ግን ሚዛን የስተና የተጣረሰ አስተያየት ሰጥተዋል። አስተያየት የመስጠት መንትዎን አከብርልዎታለሁ። ይህ ድረገጽ ለሁሉም አስተያየት የእርስዎንም ስድብ ጭምር እያስተናገደ ነው። እርስዎ በተከታታይ የጻፏቸውን 3 ስድቦች/አስተያየቶች አውጥቶልዎታል።

    Lemma says:
    May 17, 2016 at 6:21 pm

    This website is so corrupted. They have deleted all the people comment who are opposing the writer who is wrongly accused of an innocent man. This is American and anybody can exercise their first amendment . Freedom of speech is one of them if you don’t know what I am talking about – Please don’t smear his name on a mud – you are so disguising and rubbish to try to humiliate an innocent man on earth – I will pray for you – Asshole – leave the comment – Don’t delete any post supporting his innocent

    Fafa says:
    May 17, 2016 at 6:34 pm

    Wrongly accusing an innocent man – sad that you put all this time to write about a guy who loves his church – put your time on something constructive – silly and non sense – I am not buying your post – even Jesus is crucified for what believed – when someone is telling you the truth , you tired around and gave a name that he doesn’t deserved

    Derge says:
    May 17, 2016 at 9:55 pm

    You guys have to understand the whole thing . Don’t rush to judge. Wrongly accusing someone is illegal –

    እንዲሁም ከእርስዎም በፊት ሌሎችም ሲሳይ ኪዳኔን በመደገፍ ከዚህ በታች የሰፈረውን አስተያየት ጽፈዋል። ለመሳሌ አቶ ምህረቱ ተገኝ ይህን ብለዋል።
    Mhretu Tegegn says:
    May 12, 2016 at 8:15 pm

    Abet wshet. Ere bakachuh wshet ykir. I am a member of the church and there is no disterbance nor such name at all. Why all this
    lies. Mhretu Tegegn.

    እንዲሁም ሌላ አስተያየት ሰጭ ይህንን በደረገጹ ላይ የወጣውን ጽሁፍ የሚቃወም ሃሳብ አቅርበዋል።
    DAG says:
    May 15, 2016 at 10:56 am

    “እግዚአብሔር ይታረቅህ/ሽ። ምናለበት ለሰዎች አንድነት እንደዚ አድርገህ ብትጽፍ/ፊ። ይቅርታ አድርግልኝና ጥቅምህ የተነካ ግን ይመስላል።በእውነቱ ከሆነ እንደ ሲሳይ እና እንደሱ የመሰሉ ሰዎች ለበተክርስተያኑ ሲሰሩም ሆነ ስለህዝብ ንብረት ጥያቄ ሲያቀርቡ በስልጣን በያዘው ክፍል አይወደዱም።”

    በአጠቃላይ ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚ ሃሳቡን የሚያንሸረሽበትንና በተለይም በወያኔ የታፈንን ሰዎች የምንተነፍስበትን ድረገጽ ጥላሸት መቀባት ምን ማለት እንደሆነ አንባቢ ይፍረደው። እኔ እንደርስዎ ወደ ስድብ ለመውረድ አስተዳደጌ አይፈቅድልኝም።

  18. You are so stupid to accuse someone that you don’t even know. What do you think he is spying from the church . He built the church – he donates more than anyone – you don’t know so please keep your mouth shut.

  19. Gebre above, how much does the TPLF paying you to spy on us {Ethiopians}? You and Sisay Kidane are trying to control and hand over our church to your boss TPLF. Most of the church members are in the USA to save their lives from the authoritarian and murderer rulers of TPLL. I am 100% certain that TPLF will NEVER buy our church here in Las Vegas.

  20. You’re leaving in a primitive society if you don’t know what the platform of the constitution is?? You should go back and read – Don’t try to smear names – plesse see facts before you speak – God bless you

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*