የዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ 171 ገጾች ያካተተ የሚያሳፍር ‘የአዛውንት ምስክርነት’ ይፋ ሆነ!

ዶ/ር አክሊሉ እርስ በርሱ የሚጋጭ ምስክርነት ዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

Dr. Aklilu

የዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከመስከረም ጀምሮ ቤተክርስቲያኗ በዶ/ርና ሌሎች የተለያየ አጀንዳ የያዙ ቡድኖች ጋር በመተባበር በአባሎች ተመርጦ የነበረውን የባለአደራዎች ቦርድ በኃይል መፈንቅለ ቦርድ ማድረጋቸውን ከአሁን በፊት ዘግበናል።  

ይህንን ተከትሎ ቤተክርስቲያኗ በሯ ተሰብሮ በጉልበት በነ ቄስ ተስፋዬ መቆያና ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ቡድን ቁጥጥር ስር ከማድረጋቸው በፊት የመፈንቅለ ቦርድ የታቀደ እንደነበር የሚያረጋግጥ ከዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ምስክርነት ተገኝቷል።

ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የተለያዩ ሰዎችን በማነጋገር ባደርገውነው ማጣራት፤ ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ የርእሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የባለ አደራዎች ቦርድ አባል በመሆን ከ18 ዓመታት በላይ ሲያገለግሉ ቆይተው በራሳቸው ጥያቄ ከቦርድ አባልነት ተሰናበቱ። ብዙ ሳይቆዩ  በሕዝብ ፊት ቆሞ ማስጨብጨብ ስለጎደለባቸው ይመሰላል ፤ የለቀቁትን ስልጣን ቀጥታ  ባያገኙም እንደገና በጎ ፈቃደኛ በመሆን በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ማገልገል ጀመሩ። የቤተክርስቲያኑን ባኣደራዎች ቦርድ እንደፈለጉት ማድረግ እንደማይችሉ ሲያውቁ መጋጨት ጀመሩ። ይህ ግጭት እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ በየሳምንቱ ከህዝብ ፊት እየቀረቡ ውዳሴ ሲቀርብላቸው፣ ሲጨበጨብላቸው የማቱሳላ እድሜ ሲለመንላቸው እንደነበር ምዕመናን ይናገራሉ።

በአንድ ወቅት፣ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ተቆርቋሪ ብሎ ከሚጠራ ቡድን ጋር ሆነው እንደ ሁልጊዜው ሁሉ፤ በማንኛውም ስብሰባ መሪ የመሆን የሁሌ ባህሬአቸው  የገነቡትን ማፍረስም ጀመሩ። ይህንን ተከትሎ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ የሰጡት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሰነድ ይፋ ሆነ።

በዚሁ 171 ገጾች በያዘው የምስክርነት ሰነድ ውስጥ ብዙ ኢንኳን ‘ከአዛውንት’ና ከሌላም ሰው አንደበት ይውታል ተብሎ የማይገመት የክህደት ቃሎች መካከል ተናገሩ። አንድ ሁለቱን ለምጥቀስ ያህል:

  1.  በራሳቸው በዶ/ር አክሊሉ የቦርድ ሊቀ መንበር ሰብሳቢነት  በነበሩበት ወቅት ለጥምቀት አገልግሎት ተመድበው በአድማ በመቅረታቸው በቤተክርስቲያኗ ደንብ መሰረት ከስራ ያገዷቸውን ካህናት፣ እገዳው ትክክል አይደለም በተለይም በእኛ እምነት ምእመን ካህናትን ማገድ አይችሉም በማለት የራሳቸውን ውሳኔ የሚቃረን የሐሰት ምስክርነት ሰጥተዋል።
  2. የቤተ ክ/ኗ ህግ ማሻሻያ በአግባቡ አልጸደቀም የአባላት 2/3 ምልአተ ጉባዔ ያላጸደቁት ህግ እንደ ህግ ሊቆጠር አይችልም ሲሉ እርሳቸው ሰብሳቢ ሆነው በ2003 ያሳለፉትን 2/3 አባላት ያልተገኙበትን ማሻሻያ ግን ለቤ/ክርስትያኗ እድገት በማሰብ የተደረገ እንደ ሆነ ሊያስረዱ ሞክረዋል።
  3. የጊዜያዊ ኮሚቴውን የመረጠው አካል በቤ/ክኗ ህግ መሰረት ያልተቋቋመ መሆኑን አምነው ይህም የሆነው ለቤተክርስትያኗ እድገት እንደሆነ ያስረዳሉ።

በአጠቃላይ እርሳቸው የሰሩትን ስራ መለኮታዊ የሌሎችን ግን ሰውሰራሽ በማስመሰል ያቀረቡትን የሐሰት ምስክርነትና ሌሎችንም ከአንድ ‘አዛውንት’ የማይጠበቅ ዝርዝር ቃል ለማንበብ የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ።  የዶ/ር አክሊሉ ሀብተ የምስክርነት ቃል ሙሉውዝርዝር:  http://www.dskmariam.org/images/Board-News/Habte-Aklilu_full.pdf

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቤተክርስቲያን ዉጭ ያሉት የቤተክርስቲያን አባላአት ሲያከብሩ የሚይሳይ አጭር ቪድዮ ይመልከቱ።

የተገፉት የቤተክርስቲያኑ አባል ህዝበ ክርስቲያፋሲካን ሲያከብሩ።

39 Comments on “የዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ 171 ገጾች ያካተተ የሚያሳፍር ‘የአዛውንት ምስክርነት’ ይፋ ሆነ!”

  1. በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው እንደጠገበች አይጥ እዛና እዚህ መርገጥ ያስፈለጋቸው የለመዱት የስልጣን ጥማቸው እንዳይቀርባቸው እንጅ እውነትስ ለክርስትናቸው ብለው ቢሆንማ ቁልቁል ወርደው ከእነ ተስፋዬ መቆያ አዲሱ አበበ መንገሻ ዲያቆን ነኝ ባይ ተመስገን ቄስ ነኝ ባይ ጠንቋይ ሐይሉ ስንቱ ይቆጠራል የወንበዴ ስብስብ ጋር ሆነው ቤተክርስትያን ሊያፈርሱ ባልተነሱ ነበር ተስፋዬና ተመስገንም ቢጠየቁ ከዛ የባስ በመቀባጠር በቁማቸው ይቀዝኑ ነበር ገና ብዙ ብዙ ጉዳቸው ይወጣል መነሻቸው ጥቅም ሰለሆነ አሁንም እየተፋጁ ነው ተመስገን ከእሪችመንድ እዚህ ድረስ ሲሮጥ የመጣው የገንዘብ ችግሩን ለመወጣት ነበር እንዳሰበው አልተሳካለትም እንጅ እመቤቴ ገና ቤቷን በደንብ ታጸዳለች እግዚአብሔር ሐሙስ እለት ተአምር ያሳየናል እነኛም የነጭ ልብስ አስመሳይ ክርስትያኖች መንጋጋታቸው አይቀርም ጉዳቸውን እናያለን።

  2. ዶክተር አክሊሉ አገሩ አሜሪካ ሆኖባቸው ነው እንጂ በምዕመናን የተመረጠ ቦርድ ከህግ ውጭ በአድማና በ”ሞብ” ከማውረዳቸውም በላይ ሌላ ወንጀሎችንም ሊፈዕሙ እንደሚችሉ አይጠረጠርም። እኝህ ሰው ይህንን ዓይነት ድፍረት፣ ጋጠ ወጥትነትና ዱርየነት ይዘውት ዕድሜ ልካቸውን የኖሩት እንጅ በአንድ ቀን የመጣባቸው አይመስለኝም። ስለሆነም ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እንጠብቅ።

  3. ምነው አርፈን ነበር ተነሳባችው እኛ እንደሆነ በደመቀ ሁኔታ ፍሲጋን አክብረናአል እግዚአብሔር ቤቱን ሊያጠራ ቤቱን አዘግቶ መንጥቖ አወጣችሁ እሲቲ ተመልከቱ መቅደሱ አምሮ አሁንም ገና ያምራአል። ትቃጠላላችሁ እናንተም እራሔል ባመጣችላችሁ የቤተክርስትያን ልብስ መቼም እናንተን ያንገበገባችሁ ስለእምነቱ ሳይሆን የገንዘብ ጉዳይ ስለሆነ በከፈታችሁት አዳራሽ ቢዝነሳችሁን ማካሔድ ትችላላችሁ አይገኝም የማርያም ቤት ሕዝቡ እንደሆነ ነቅቶአል ከናንተው አባል ነኝ

  4. እግዚአብሔርን አላውቅም ብለው በራሳቸው አፍ የመሰከሩት ቄስ አማረ እንዴት አድርገው ነው እንደገና የእግዚአብሔርን ስም የሚጠሩት? ወይ የሰው ግብዝነት! እባክዎ ወደ ህሊናዎ ይመለሱ የሚከተልዎትን 20 የማይሞሉ ሰዎች ይዘው ገሃነም አይግቡ! የህዝቡን እምነት፡ ፍቅር፤ ሰላም አያዩትም ወይ? ለምን እረፍት ይነሱታል? ለምንስ ከአንደበትዎ የማይሆን ቃል ይወጣል? ለምንስ በጥቁር ራሶች፤በባለጌ ባልቴቶች አባቶቻችንን ያሰድባሉ? እባክዎ እግዚአብሔር የማይወደውን ነገር አያድርጉ። እኔ አንዲት መሃይም ሴት ነኝ፤ ሆኖም በናንተ ላይ የደረሰው ቅጣት ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር የመጣ እንደሆነ አምናለሁ፤እገነዘባለሁ። በወያህ አንደበቴ ልምከርዎ፤ እባክዎ ንስሃ ይግቡ!!!

    https://youtu.be/rATSyTO7Zww

  5. ምነው አታፍሩም ስደተኛዋ ማርያም ብላችሁ የለቌችሁት የተስደዳአችሁ እናንተ ማርያምማ አምሮባት ተውባ መቅደስዋ ውስጥ ጉብ ብላ አላያችሁም። የስራችሁት ስራ ገና እንቅልፍ ነው የሚነሳችሁ

  6. ጭፍን ነሽ ከዚህም በላይ ብትይም አንቺ አትገርሚም

  7. ጭፍን ነሽ ከዚህም በላይ ብትይም አንቺ አትገርሚም፤ ቄስ አማረ ካሣዬ ምንም አድመኛ፤ዋሾ፤ተሳዳቢ፤ የውሸት ቄስ ቢሆኑም፤ ሌብነት ግን ያለባቸው አይመስለኝም። አንድ እውነት ያገኘሁት ከናንተ እታች የለጠፍኩትን ብቻ ነው።

    https://youtu.be/pr9JaFlUeuc

  8. Ethiopian Christian art should be closer to the imagery of the people. Christ’s personification should not necessarily look so Caucasian in an Ethiopian church. Children growing especially in racist America can easily associate Caucasian image and God. That is not God’s intention.

    In any case, both sides of this ETOC of Kedest Mariam should not necessarily be what ETOC is like at its best. Both sides are a different kind, by now creating doubt about the very religion itself. At least for now,the other group carries services and liturgy in a separate place. No more hostility at the entrance of the church’s doors. The rest is in the care of the court. That is that. Both sides are not necessarily the path to the religion. Even passionate music, poetry, guest preacher can not undo the damage done.

  9. በጣም የምያሳፍረው ስደተኛዋ ማርያም ማለታችው ነው እባካችሁ እግዚአብሔርን እንፍራ የድርጅት ስም አደረጋችውት እንዴ የቤተክርትያንን ወይም የጻድቃንን ስም በየተከራያችውበት አዳራሽ ስም መስጠት ለነገሩ ምን ታደርጉ ቤተክርስትያን የትም ቦታ እንደ ሰበን እለበን እየከፈታችው ትሰይማላችው የናንተ የንግድ ስም በሀይማኖት ሽፋን ስለሆነ ምንም ሼም የለውም ማርያም ስደተኛ የሆነችው በናንተ ንግድ ስም እንጅ ስደተኛስ አይደለችም እዛው እናንተው ተሰደዱ ጥቅም ያሰከራችው የምጽዋት ገንዘብ የምትከፋፈሉት ስቀርባችው ያለውም አለቀ መሰለኝ በአድስ ርዕስ ተነሳችው ምድረ ማፈሪያ ይህንን ሀይማኖታዊ ነው አልለውም ሌላ 7/11 ወይም ዶላር ስቶር በሉት በድንግል አትቀልዱ በሳ ቀልድ የለም።

  10. Aradaw Amare Kassaye ye Mariamn nebret
    iyementefe Millioner honoal .
    Goadgnaw Asteraye indihu yeakrari delala
    huno be Barriyanet le Ethiopia Radio
    limot and qen keqerew Agasese Alemeye
    kemibal delala gar bemehon ye Orthodox
    qesochin sisadb neaw yemiwulw . Akrariwochu
    bebtesult kuter Christianun indawarede neaw .
    isu ahun beizh idmew yet lemedrs neaw nefsun
    le dollar yemishetw . Dr. Aklilu woyane ketebalu
    keahun jemero iniena wegnoche bemulu woyanewoch
    nen . kezeh behoala woyane inde melkam qal wosdnewal .

  11. ቅል ድንጋይ ነህ ማስተዋል ያልፈጠረብህ ክርስትያን ነኝ ያልከው እንደተነዳህ ብቻ ነው የምትሄደው አይምሮህ ለማሰቢያ ነው የተሰራው ተጠቀምበት ችግሩ ከምን ተነሳ ቢባል ማስረዳት እንካን የማትችል እዚጋ ያልገባህን ነገር ለመቸክቸክ ትቸኩላለህ ……

  12. የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ

    May 12, 2016

    ይህ የዛሬው የፍርድ ቤት ችሎት የመጨረሻ ስለነበር፤ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ምዕመናኑ በኩል የእፎይታ እና የእረፍት ፊት ሲታይ፤ በቦርዴ በኩል ለተሰለፉት ሰዎች፤ የጭንቀትና የመሸበር መልክ ይታይ ነበር። ችሎቱ የተጀመረው ቀደም ብሎ ወደ ጠዋት 10፡30 ሲሆን እኔ የደረስኩት ትንሽ አርፈድ ብዬ ነው። እንደገባሁ የመጀመርያ ተርታ ላይ መቀመጫ ክፍት ስለነበር፤ እራሴን ሰየምኩና እንደወትሮው ወደ ቦርዴ ዞር ብዬ ማን ማን እንደመጣና፤ መቼም ከተያየን ስለሰነባበትን፤ መናፈቅም አለ፤ አይኔ በሩቁ ሲማትር፤ በመጀመርያ ረድፍ ላይ፤ የቦርዴ ፈላስፋ፤ፓስተር ዘነበች፤ ጉብ ብለዋል። በሳምንት ሁለት ጊዜ ለሰዓታት አባቶችን፤ምዕመናኑን፤የምትሰድብበት፤ የምትዘልፍበት፤ ምላሷ፤ አርብ መስሎት ለመሳደብ ውጭ ወጥቶ ቁጭ ብሏል! እሷም ያስተዋለችው አልመሰለኝም፤ ለመክተትም አልሞከረችም። ጎኗ ወ/ሮ ወሰንየለሽ ደበላ፤ (ምን ቢሉ በስም ይደግፉ እንዲሉ) የፓስተር ዘነበችን ምላስ ቤቢ ሲት የምታደርግ ትመስል ታቅፋው ቁጭ ብላለች። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ወዴት እንደሚሄድ ስለጠረጠረች ይመስላል፤ በሰፈሩ ባለቤት የለሽ ውሾች ቆሌዋ የተገፈፈች፤ የጨርቆስ ድመት ይመስል፤አይኗን አፍጥጣ፤ ጥርሷን አግጥጣ፤ ፍለፊቷ ቃላቸውን የሚሰጡትን የቄስ ዘላለምን፤መስቀል የምትማፀን ትመስላለች።
    በመስኮት የሚገባው ጨረር፤ ከፍሬው አናት ጋር እየተጋጨ አይኔን ስላጭበረበረኝ በግልፅ ማየት ባልችልም፤ ፍሬው በቀለ አለወትሮው ህፃን ይዞ የመጣ ይመስላል። ከሩቅ እንደማየው፤ ገና ፀጉር ያላወጣ ክስት፤ ያለ ህፃን ልጅ፤ በጉያው አቅፎ እሽሩሩ የሚል ስለመሰለኝ፤ መቼም ቦርዴዎች፤ የማይሰሩት ጉድ የለም፤ ምን ጉድ ይዘው እንደመጡ ለማጣራት አይኔን አፍጥቼ ስመለከት፤ ለካ የታዘለ የመሰለኝ ማሙዬ፤ የኛው የቦርዴ ኤክስ-ፕሬዚዳንቴ ዶ/ር ጌታቸው ማፈሪያ ናቸው! ሰው ሊያሳስቱ ይሁን ሊዘንጡ፤ ያን ባጊ ሱሪና ባጊ ኮታቸውን (እኛ ባጊ ለሱሪ ነው፤የምናውቀው፤ የሳቸው ደግሞ ሁሉም ነገራቸው ባጊ ነው) ከባጊ ጫማ ጋር ፈፅሞ ሌላ ሰው መስለውኝ ነበር። ታዲያ እኮ ፍርድ ቤቱ ውስጥ ስገባ፤ አቶ ያሳርጉ፤ (ስማቸው ሁልጊዜ ይጠፋብኛል)፤ አቶ ለገሠ፤ ያለወትሯቸው፤ ጠበቃ ወንበር ላይ ተሰይመው አይቻለሁ። የመስማት ችግር ይሁን፤ ወይ በእንግሊዘኛቸው አለመግባባት፤ ከጳውሎስ አማረ ጋር፤ አንድ ሁለት ጊዜ ጆሮ ለጆሮ ገጥመው ሲጯጯሁ፤ ዳኛው በዛ በተለመደው አስተያየቱ ገረፍ ሲያድርጋቸው አይቻለሁ። አይ አቶ ያሳርጉ፤ ምን ምክር ሊያዋጡ ይሆን አሁን በአምስተኛው ሰዓት፤ እዛ የተሰየሙት?!
    ከኋላ የተቀመጡትን ሰዎች መሃል፤ ብዙዎቹ አዛውንት እህቶችና ወንድሞች ሲሆኑ፤ ቦርዴ ወይም ቄስ አማረ ምን አይነት ምግብ እያቀለባቸው እንደሆን አይታወቅም፤ ሁሉም የስምንት ወር እርጉዞች ስለሚመስሉ፤ ሴቱን ከወንዱ፤ማን ማን እንደሆኑ ለመለየት፤ጊዜ ማጥፋት ስለመሰለኝ፤ ሳያውቀው እየጮኸ ገብቶ እየጮኸ መውጣት ያቃተውን፤የትግል ጓዴንና ሰው በተሰበሰበ ቁጥር ሰላማዊ ሰልፍ መስሎት፤ ማይክና የጃማይካ ባንዲራ ከረባት አስሮ በጩኸት ሰው የሚያሸብረውን ጓደኛዬን ሽመልስን በሩቁ ሰላምታ ሰጠሁና ችሎቱን ለመከታተል ቀልቤን ወደ ፍርድ ቤቱ አደረግሁ።

    ችሎቱ የቀጠለው የቦርዴ ጠበቃ ለቄስ ዘላለም በሚያቀርበው ጥያቄ ነበር። አዲስ ነገር የጠፋበት ጠበቃ በነ ፍሬው፤ጌታቸው እና ወሰን… የተቀመመውን ተንኮል ለማራገፍ፤ ስራውን ተያይዘው።
    ከጠበቃው አጠያየቅ ወዴት ሊወስደው የገባው፤ ተጠያቂ ’አዎ’ ‘አይደለም’ ን መልስ፤ ከነማብራሪያው ያቀርብለት ጀመር፤ በዚህ የተናደደው የቦርዴ ጠበቃ፤ በንዴት እና በቁጭት ሲወናጨፍ፤ ቤቱ አልበቃ ብሎ ሲጓዝብን ዋለ!

    ከሞላ ጎደል ስናየው፤ የጠበቃው አላማ ሁለት ነበር፤ የመጀመሪያው ቄስ ዘላለም ከቀድሞው ቦርዴ እና አሁን ገንዘቡ የተያዘበት በቤተ ክርስቲያኗ ስር በተቋቋመው የዕድር ማህበር ውስጥ ይሰሩ ስለነበር እሳቸውንም አንዳንዴ የህፃን ልጅ ጨዋታ በሚመስል መንገድ ጥፋተኛ እና ነውረኛ ለማድረግ፤ የተገኘውን ዶሴ ሁሉ እርሳቸው ላይ በመወርወር ነበር። ሆኖም ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ሁሉ፤ በተደጋጋሚ የጠበቃውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውበታል።
    ሁለተኛውና የሚያስገርመው፤ በቤተ ክርስቲያኗ የተፈጠረውን ችግር ሀገር ቤት ካለው ሲኖዶስ፤ ውጭ ካለው እራሱን ስደተኛው ሲኖዶስ ብሎ ከሚጠራው አካል ጋር እና ከኢትዮጵያ ሰው በላ መንግሥት ጋር ሊያገናኝ መሞከሩ ነበር! የቦርዴ ጠበቃ እንደተመከረው፤ የመጨረሻ እና የሚያስደንቅ ጥያቄውን ቀጠለ፤

    የቦርዴ ጠበቃ፡ የደብረ ሰላም ቤ/ተ ክርስቲያን የምትተዳደረው፤ ከኢትዮጵያ ሲኖዶስ ውጭ ነው፤ አይደለም እንዴ?
    ቄስ ዘላለም፡ አዎ፤ በአስተዳደር፤ በሀብት በንብረት ነፃ ብትሆንም፤ በእምነት ግን ግንኙነት አለን።
    የቦርዴ ጠበቃ፡ ሲኖዶሱ ለሁለት ተከፍሏል፤ አይደለም?
    ቄስ ዘላለም፡ አዎ፤
    የቦርዴ ጠበቃ፡ በኢትዮጵያ የሚገኘውና፤ በዲያስፖራው የሚገኘው፤ አይደል?
    ቄስ ዘላለም፡ አዎ
    የቦርዴ ጠበቃ፡ ኢትዮጵያ ያለው መንግሥት እናት ቤተ ክርስቲያንን ለመቆጣጠር ይጥራል አይደል?
    ቄስ ዘላለም፡ ይህ ረዥም ታሪክ ያለው ጉዳይ ነው….ብሎ ለማብራራት ሲሞክር፤
    የቦርዴ ጠበቃ፡ በመንግሥት ግፊት ምክንያት የቀድሞው ፓትርያሪክ ‘አቡነ መርቆርዮስ’ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ አይደለም እንዴ?

    ጠበቃው በደንብ አድርጎ ስማቸውን ሲለማመድ እንደ ነበር ያስታውቃል፤ ግን አኪያሄዱን ዳኛውም ሆነ የኛ ጠበቃ የወደዱት አይመስልም። ዳኛው ያቺ አስተያየቱን ቦርዴ ጠበቃ ላይ ጥሏል፤ የኛም ጠበቃ ይቁነጠነጣል።
    ቄስ ዘላለም፡ ‘መረጋገጫ መኖር አለበት፤ ሰነድ መኖር አለበት! በዚህ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁም…’
    የቦርዴ ጠበቃ ግን ወዲያው፤ ‘የተከፈለው ሲኖዶስ መሪ አቡነ መርቆርዮስ አይደሉም ወይ?’ ብሎ ሲጠይቅ፤
    ቄስ ዘላለም፡ ‘አዎ ትክክል ነው’
    የቦርዴ ጠበቃ፡ ‘የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዝ መጥፎ አይደለም ወይ?’
    ቄስ ዘላለም፡ ‘እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም! እኔ የፖለቲካ ሀሳቦችን ከሀይማኖት ሀሳቦች ጋር ለይቼ ነው የማየው! ስለ ሀይማኖት ነው እንጂ የማወራው፤ መንግሥት እንደዚያ አይነት ቁጥጥር እንደሚያደርግ ለመናገር መረጃ ሊኖረኝ ይገባል!…’
    የቦርዴ ጠበቃ ግን ጥያቄውን ሊተወው ፈፅሞ አልፈለገም፤ በድጋሚ ’ይህ እውነት አይደለም ወይ? የኢትዮጵያ መንግሥት ኢሰብዓዊ እንደሆነ?’

    ወዲያው የኛ ጠበቃ ተቃውሞውን አሰማ ‘ክቡር ዳኛ ይህ ከጉዳዩ ጋር የሚሄድ አይደለም!’
    ሁላችንንም በሚያስቅ አባባል ዳኛው ቀጠለና፤ ‘ I thought we are talking about the church at Buchanan street?’ ብሎ ሰዉን ሁሉ ሳቅ በሳቅ አደረገው!
    ወዲያው ዳኛው በመሰላቸት ‘ How much time do you have with this witness?’
    የቦርዴ ጠበቃ፡ “about 10 minutes’
    ዳኘው ቀጠል አደረገና ’ Let’s see, THIS BETTER BE GOOD!’ ሲል፤ በውረፋው የቦርዴ ጠበቃ እና እድምተኞቹ የእፍረት ሳቅ ሲስቁ፤ በጠበቃችን መሪነት፤ሁላችንንም እንደተኮረኮርን ያህል ቤቱን በሳቅ አሞቅነው። ከኔ ሁለት ወንበር ወደ ኋላ የተቀመጠው ሰው፤ ሳቁን ያቆመው እንትና ጋቢ አፉ ላይ ጥሎበት ነው!

    አካሄዷ ያላማረላት የቦርዴ ጠበቃ እየተንፏቀቀች፤ ወደ አላማዋ መጣች፤
    የቦርዴ ጠበቃ፡ ’አንዳንድ ቄሶች ይህችን ቤ/ክ ወደ እናት ቤ/ክ ለመደባለቅ እየጣሩ አይደለም ወይ?’
    ቄስ ዘላለም፡ ‘ይህ የምትጠይቀኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ እና ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፤ በቀላሉ አዎ ወይ አይደለም የምለው ነገር አይደለም!’
    በቦርዴው ጠበቃ ስልችትችት ያለው ዳኛም ዘሎ ገባና
    ‘ I’m not objecting but, I’m totally lost as why we are going into a philosophical discussion and direction of the church, I thought we are talking about managing the church… ’
    የቦርዴ ጠበቃም፡ ’ your honor, part of the motivation behind this takeover is to move the church under the synod in Ethiopia which is contrary to the wishes of the vast majority of its members’
    ዳኛውም ዱላ ቀረሽ መልሱን ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ አወረደበት፤
    ‘ THAT IS AN UN APPROPRIATE ISSUE FOR ADJUDICATION!
    የቦርዴ ጠበቃ፡ In that case, your honor I don’t have any further question, I’M DONE!’
    ብሎ ዳኛው የተደገሰውን የቦርዴ ድግሥ፤ እንደቦርዴው አፈራረሰው! የሚገርመው ውጭ ከወጣን በኋላ የኛ ሰዎች፤ እንዴት የማታውቀው እና የማትረዳው የቤ/ክ ጉዳይ ውስጥ ትገባለህ፤ ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የቦርዴ ጠበቃ ሲመልስ፤ ‘ እኔ ምን አውቃለሁ እነቦርዴ በል ያሉኝን ነው ያልኩት’ ብሎ ተናዘዘ።

    ዳኛውም June 13, 2016 የሚያስፈልገውን ሁሉ ዶሴዎች እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ፤ በተለመደ ትረባው፤ወደ እኛ ጠበቃ ዞሮ
    ‘ ጓደኛህ ስራውን ተወ እንዴ? ብሎ ጠየቀው። ጠበቃችንም ‘ ውጭ ለስራ ጉዳይ ሄዶ ነው’ ብሎ ሲመልስለት፤ ‘ እርግጠኛ ነህ? ከዚህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመሸሽ መስሎኝ!’ ብሎ ሰዉን አስቆ
    ችሎቱን ዘጋው።

    ለሁላችንም ቸር ይግጠመን!

  13. በሚገባ ቁጭ አደረከው እውነት እውነት ነው ትክክል የተሰጠ ምስክርነት ማለት ይህ ነው፡፡ እነሱ ከፍርድ ቤት ከመውጣታቸው አንድ ሱቅ ዉስጥ የእነሱ ሴት በስልክ የምታወራው ውሸት ይዘገንናል በዕድሜ ትልቅ ሆና በተግባሯ ትንሽ ሴት የምታሳፍር ናት ይህ የተለጠፈውን የምያነብና የእሷ ውሽት ሰማይና ምድር ነው የምታወሯዋ ሴት በእውን የተከተለችው ቄስ ነኝ የሚለው የሰራውን ስራ ተክክል ነው የምትል ሴት ነች የተከተለችው ሰው ታሪኩን በደንብ ቢታውቅ ሱቅውስጥ እንደ ዕብድ ባለፈለፈች ነበር፡፡ እኔ ፍርድ ቤት ስለነበርኩ ውሸታም መሆናን ተረዳው ዛሬ ይህንን ስታነብ ጆሮዬ እመምተኛ ነው ብላ ወደ ዶክተር ጋር ቢትሄድ ጥሩ ነው

  14. ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
    በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
    አሰርዎ ለሰይጣን
    አግዓዝዎ ለአዳም
    ሰላም
    እምይእዜሰ
    ኮነ
    ፍሰሐ
    ለሰላም

    እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ አደረሰን። ትናንትና የነበረውን የፍርድ ቤት ሂደት ወንድማችን ይሔይስ ወርቅነህ ጨዋነት በጎደለው በግለሰቦች ላይ ባነጣጠረ መልክ ቀርቦ አይተናል። አሁን ደግሞ በሌላ በኩል የነበረ ታዛቢ ያዘጋጀውን እናቀርባለን። ዘገባው በእንግሊዘኛ ሲሆን የቤተ ክርቲያኗ ጠበቃ Mr. L በሚል በምጽኸረ ቃል የቀረበ ሲሆን የወንጀለኞቹ ጠበቃ ደግም Mr. G ተብሎ ይነበባል።

    2015 CA 007574 B: RE’ESE ADBARAT DEBRE SALAM KIDEST MARIAM ETHIOPIAN, et al. Vs. HABTE, AKLILU, et al.
    Court Session

    Thursday May 12, 2016

    Morning Session
    10:20 a.m. Judge Ross has arrived.
    Court session for the day has started.

    10:22 a.m. Attorneys and interpreters introduced themselves.
    Mr. George Lyon, attorney for the plaintiff
    Mr. Thomas Guiffre, attorney for defendants
    Miss Selam Legesse, interpreter,
    Mr. Amare Bekele, interpreter

    10:23 a.m. Judge Ross is giving a brief introduction about proceedings of the case.

    10:26 a.m. Testimony of Qes Zelalem will continue.
    Deposition of Dr. Aklilu Habte’s will be part of the court document.

    10:27 a.m. Mr. Guiffre objected, but the judge rejected his objection.

    10:29 a.m. Liqe-liqawunt Workneh Haile has arrived late at the court.

    10:32 a.m. Mr. Lyons raised the issue of the newly elected board, whether to submit the documents to the court.
    Judge Ross advised that, that will take additional court sessions, and as long as he (Mr. Lyons) can verify quorum was set, it is ok!

    10:33 a.m. Qes Zelalem is on witness stand.

    10:36 a.m. About the letter their group (the interim committee) wrote to the bank.
    Mr. L.: You have written a letter to the court that Dr. Amare has abandoned his post.
    Qes Zelalem: Dr. Amare has abandoned his position, though he was called to resume his work publicly.

    10:39 a.m. Mr. L.: Dr. Aklilu in his deposition admitted that he told Paulos Amare, Dr. Amare’s son, that Dr. Amare will never set foot in the church.
    Qes Zelalem: I do not know about that.

    10:44 a.m. About the Qedist Mariyam Idir
    Mr. L.: Does the Idir administer the church?
    Qes Zelalem: No it does not.
    Mr. L.: Why did you open a bank account in Eagle’s bank under the tax number of the Idir?
    Qes Zelalem: We were forced to open an account under the Idir, because the church account was blocked.
    Mr. L.: How did you do that?
    Qes Zelalem: We wrote a letter of cooperation to the Idir and they accepted our request.

    10:55 a.m. Mr. L.: But the church’s bank account was not blocked until you wrote a letter to the bank on December 9, 2015, while you opened a new bank account on November 4, 2015 using the Idir tax number?
    Qes Zelalem: We wrote the letter to the bank to protect the money of the church from embezzlement.
    Mr. L.: You opened an account under the Idir on November 4, 2015. Also in your petition to the court, you mentioned that the bank account of the church was frozen as of November 4, 2015; whereas it was active until you wrote a letter to the bank on Dec 9, 2015?
    Qes Zelalem: I do not remember that.

    11:13 a.m. Plaintiff’s exhibits 38 & 39
    Mr. L.: You opened two business accounts signed by you. Were these accounts opened for the benefit of the Idir?
    Qes Zelalem: No, rather it was for the benefit of the church.
    Mr. L.: These accounts are for business, not for a non-profit. Was this for paying the lawyer?
    Qes Zelalem: Our purpose is to protect the church.
    Mr. L.: About the $35,000 withdrawn from a Wells Fargo bank? Do you know who signed on that self-pay check?
    Qes Zelalem: I do not remember.
    Mr. L.: There is still $27,000.04 on that account. Who deposited that money?
    Qes Zelalem: I do not know, I have to see the documents.
    Mr. L.: Was the money deposited by the Ethiopian government?
    Qes Zelalem: No, we collected the money at church services.
    Mr. L.: There were several checks written and signed by you in the month of October. One for Elias Beneberu, another for Tewodros, etc. Were they paid as salary?
    Qes Zelalem: I do not know how much their salaries are. The signatures on those checks are not mine.

    11:19 a.m. Mr. L.: Who has authorized you to deposit money under the Idir account?
    Qes Zelalem: I, as an individual, am not authorized to deposit, however the church is given the permission to use the account by the Idir.

    11:35 a.m. About the church’s status with regard to the Synod in Ethiopia
    Mr. L.: Is the church’s administration is independent of the Synod in Ethiopia?
    Qes Zelalem: Yes, our church is independent administratively, but under the same spiritual authority.
    Mr. L.: In fact the Ethiopian Government exercises control over the synod of the church. Is that not true?
    Qes Zelalem: The Ethiopian Orthodox Tewahido Church (EOTC) has been established by Ethiopian governments in past history. So the church and the government have close link for a long time.
    Mr. L.: The government has removed Abune Merkorios, the Patriarch in exile, from his post. Is that not true?
    Qes Zelalem: I do not have evidence. It is a complicated matter.
    Mr. L.: It is known that the human rights records of the government of Ethiopia are poor. Do you agree?
    Qes Zelalem: I agree.
    Mr. L.: Was it not the intention of your group to incorporate the administration of this church under the Synod in Ethiopia
    Qes Zelalem: It is not true.
    Judge Ross: What is the purpose of asking such philosophical questions for this case?
    Mr. L: In that case I am done with this witness.

    11:36 a.m. Court is on recess for 20 minutes.

    11:57 a.m. Comments
    Qes Zelalem has denied outright that he is the person in-charge of administering their group’s finances, while admitting the fact that he authorized payments.
    He has denied entirely that he had signed on all the checks, while Mr. L., the plaintiff’s lawyer, has presented him with solid evidence of bank statements, copies of checks signed by Qes Zelalem himself. It seems that Qes Zelalem will try to save his skin by denying all facts that are supported by solid evidence.

    Afternoon Session
    12:09 p.m. Court session has resumed.

    12:10 p.m. Mr. G., defendant’s lawyer: How many of you, the defendants, are members of the clergy?
    Qes Zelalem: Five priests and four deacons.

    12:17 p.m. Mr. G.: When you were asked by Mr. Lyons about the Sep. 20 meeting, how many people were present at that meeting? Were there more than 1/3 of the total number of members at the meeting?
    Qes Zelalem: There were about 300 people, more than the 1/3 of the total number of members.
    Mr. G.: Was there any person, who objected the decision made at the meeting? (for dismissing the board members)
    Qes Zelalem: No one objected.

    12:24 p.m. Mr. G.: What did they ask the bank about freezing the accounts of the Idir?
    Qes Zelalem: The defendants have asked the freezing of all accounts of the Idir. So all accounts of the Idir have been frozen.
    Mr. G.: Have you assaulted or attacked any person in the church? Have you denied any person to get services in the church?
    Qes Zelalem: Not at all.

    12:29 p.m. Mr. G.: How are services conducted in the church?
    Qes Zelalem: Services have been conducted peacefully and beautifully. The inside walls of the church are painted, which never saw painting for 27 years. Outside, flower beds are planted. Everything is beautiful.

    12:33 p.m. Mr. G: Do you allow former members of the board or their supporters to participate in the church services?
    Qes Zelalem: Yes of course, they’re allowed. In fact we saw some supporters of the former board at the last holiday, Easter.

    12:46 p.m. Cross examination by Mr. Lyons, the plaintiff’s lawyer
    Mr. L.: Was the September 20, 2015 meeting a general assembly meeting?
    Qes Zelalem: It was a meeting of the members. About 300 were present more than half of the 540 or so members.
    Mr. L.: Was it a general assembly meeting? Who called that meeting? Was it a meeting to elect new board members?
    Qes Zelalem: It was a meeting of members. Everybody at the meeting was supportive of our actions.
    Mr. L.: Was there a vote to elect those new people of the interim committee to administer the church?
    Qes Zelalem: I say the vote was anonymous.
    Mr. L.: Was it not Dr. Aklilu who took a paper out of his pocket and listed their names to the people?
    Qes Zelalem: No.
    Mr. L.: In fact a decision was made the Wednesday before by the ‘Concerned Committee’ and Dr. Aklilu has testified that in his deposition.
    Qes Zelalem: I do not know about Dr. Aklilu’s deposition.

    12:53 p.m. About the Task Force
    Mr. L.: Who organized the Task Force?
    Qes Zelalem: They have organized themselves. Everybody in the church protects the church from those who cause trouble.
    Mr. L. Did you, the Interim Committee, gave them any orders to block the people who oppose you from entering for church services?
    Qes Zelalem: No we don’t, but we appreciate their actions.
    Judge Ross: Do you approve the actions of the Task Force?
    Qes Zelalem: Yes we do. Without their support church services wouldn’t have continued peacefully.
    Mr. L.: No further questions.

    1:01 p.m. House keeping
    Mr. L.: No more other witnesses, but on condition.
    Mr. G.: I have good news: We do not have any witnesses for testimony. Also I would like to give additional exhibit for exhibit 3.
    Mr. L.: Objection. We cannot accept an addition to an existing exhibit.
    Judge Ross: Objection accepted.
    Mr. G.: I would like to raise an objection on the acceptance of Dr. Aklilu’s deposition as a court document.
    Judge Ross: You can present your position on that deposition in written form.
    Judge Ross: Final court argument papers to be submitted to the court within 30 days. Ten days for reviewing the documents by me (the judge). Final court decision will be given on July 27.

    1:02 p.m. Court sessions are over for the day.

    My comments:

    Qes Zelalem Anteneh is of the opinion that if he denies everything, including facts corroborated by hard evidence, he can save his skin. He goes all the way to deny the fact that he signed all checks, payment statements and letters, which were dispatched by the ‘Interim Committee.’ He was repeatedly saying that ‘that signature on that and that … is not mine.’
    Except for one intervention, on the issue of the church’s administration and the Synod in Ethiopia, the judge has allowed a fair presentation of arguments on both sides.

  15. አባት ያላሳደገው በካዛንቺስ በረንዳ ጋዝ እየተሳበ ካደገ ባለጌ ከዚህ የተሻለ ነገር አይጠበቅም ጓደኞችህ በጎዳና ርሃብ ነው የገደላቸው አንተ እድለኛ ነህ አባትህ ከመንግስት በ ሚሰርቁት ገንዘብ ትንደላቀቃለህ። የሌባ ልጅ ውሸታም

  16. How about the edir money requested by Dr. Getachew when his passed away. The money is by the way paid. This shows how the edir members and church went beyond and above the fellow human being. Eventhough the same human beings (Dr. G and his crew) frozen the account. Shame on the person above deliberately skipping this fact.

  17. By the way, which ‘Kes’ run away from the court house when Kes Zelalem was giving testimony about the ‘self-pay’ check? Was it the same ‘Kes’ (Kes Hailu) who was allegedly ‘fired’ by the Board of Trustees back in August 2015? Anyway, these people get financed by TPLF for their takeover of DC Mariam. This is a proven fact in the court of law.

  18. Tsehay እያልሽ ስምሽን እየቀያየርሽ የምትጽፊ በመጀመርያ መሀይምነትሽን ማወቅሽ ጥሩ ነው እንዳንች ያለ ለደደብ ነው ቤተክርስትያኑን እየበጠበጠ ያለው ማንነትሽን ከምትጽፊውና ከምትለጥፊው መረዳት ይቻላል ዶክተር ቄስ አማረ እንደእናንት አይነቱን ተውሳኮች ችለው ነው የኖሩት ንስሀን ምን እንደሆን ካወቅሽ ከራስሽ በጀመርሽው አንቺ ወንድ አገረድ መሆንሽም የታወቀ ነው ለዚህ ነው ማንነትሽን ደብቀሽ የምትለቀልቂው ባልቴት ማለት የእድሜ ባለጸጋነትን ያሳያል እንጅ መሰደቢያ አይደለም እንዳንች አይነቱ ወንድ አገረድ ደንቆሮ ግን ሲሳደብ ይውላል የትኞቹ ይሆኑ የአንች አባቶቼ የምትያቸው እነኝህ ለጥቅም የተሰባሰቡትን ቤተክርስትያን አፍራሾች ከሀዲዎች ሌባው ተስፋዬ መቆያ ውሸታሙ ዘላለም ጠንቋዩ ሐይሉ አይ አለማፈር ምነው ወደ ህሊናሽ ብትመለሺ ሰውን ማምለክ ትተሽ አምላክሽን ብታመልኪ ልቦና ይስጥሽ

  19. የሚግርም ነው የአዲሱና የተስፋዬ መቆያ ተላላኪዎች እንዳበደ ትንጫጩ ጀመር አለማፈራችሁ ዶክተር አክሊሉና አለቃ ወርቅነህ በመሞቻቸው ዶላር አንቀው ቤተክርስትያን ሊያፈርሱ ተነሱ የውሸት ጎሬዎች አክሊሉማ ውሸቱ ማቆሚያ አጥቶ አላስታውስም እያለ በእድሜው ያሳብብ ጀመር ታዲያ መጀመርያውኑ አርፎ አይቀመጥም ነበር መጃጀቱን ካወቀ የደንቆሮው እባቡ ውሸትማ አያድርስ ነው ፍርድ ቤት በአደባባይ የተነገረውን እንኳን ልክ እንደሱ አጣሞ የሚያወራ ተስፋ ቢስ እንደው እሱን የወለደች እናት በእሱ ጊዜዋን ክምታጠፋ ደህና ጉቶ ብትተክል ኖሮ ለማገዶ እንኳን ያገለግላት ነበር ምን ያህል አተላ ጨበረር እንደሆነ ላዩት እንኳን ይቀፋል

  20. አይ ጸሀይ ተመልካች ብለሽ ስምሽን ለምን ደብቀሽ ትጽፊያለሽ በጣም የምታሳዝኝ ማፈሪያ ነሽ ይህች የምትያት እህት ካንች በጣም የምታንስ ናት ስታወራ እኔም ሰምቻልሁ እንደውም እየሰማሽ ዝም ማለትሽ በጣም ገርሞኝ ነበር በአጋጣሚ ሁለታችሁንም በማወቄ ጥሩ ሆነ ጠየቅኋት ነገሩን ዘርዝራ ነገረችኝ በቀጥታ ፍርድቤት ሆኖ ሲከታተል የነበረ ሰው ያስተላለፈውን አሳየችኝ አሁን ግን ይህንን ያንችን ጽሁፍ ሳይ በጣም ታዘብኩሽ እሷም እንዳንችው ፍርድ ቤት ነበረች እንደውም ልታነጋግርሽም አስባ ተሸማቀሽ ልብስ ስር ስትገቢ ነው ትታሽ የሄደችው ይልቅ ማፈርማ ያለብሽ አንች ነሽ በእስተእርጅና ስትዋሽና ከከሀዲዎች ጋር ገጥመሽ ቤተክርስትያን ስታፈርሽ አታፍሪም ከርስቲያን ነኝ ትይ ይሆናል ግርድና ሰርተሽ ያመጣሽውን ገንዘብሽን ከምትበትኝ ለመጦርያሽ ብታደርጊው እንዴት በጠቀመሽ መቼም እርግጠኛ ነኝ እሷም ይሄንን ብልግናሽን ማየቷ አይቀርም መልስ እንኳን አትሰጥሽም ምን ያህል የወረድሽ እንደሆን አይታ ንቃ ትተውሻለች ለወደፊቱ ግን ተጠንቀቂ ሰው አያቀኝም ማለት አይቻልም ትዝብት ነው ትርፉ በጣም ትልቅ ውሸታም ነሽ የአሮጊት ቀላል ነሽ ቀለም ስለተቀባሽ ወጣት የሆንሽ መስሎሽ ከሆነ ተሳስተሻል ከእጥረትሽ ጋር ሰባራ ማሰሮ ነው የምትመስይው ለማንኛውም ውሸት ጥሩ አይደለም በመሞቻሽ ንስሀ ነው እንጅ ውሸት ጥሩ አይደለም ልቦና ይስጥሽ ውነትሽን ነው ያንች ውሸት እንኳን ጆሮ ሌላም ያሳምማል ይሄ ግን የሚነበብ ጽሁፍ ነው እንደው ለነገሩ አንች ፍርድ ቤት ከነበርሽ እንዴት በዚያ ሰአት እሱቁ ለመድረስስ ቻልሽ ልብስሽንስ መንገድ ላይ ነው የለወጥሽው? አበሻቀሚስ እየለበሳችሁም እንደምትሄዱ ነግራኛለች በጣም አሳፋሪ ነው ምን ለብሳችሁ እንደምትሄዱ እንኳን አታውቁም ትእዛዝ እየተሰጣችሁ ነው ለማንኛውም በሀሰት የምትወነጅያቸው አባት በእንዳንች አይነት ከንቱ አፍ የሚነሱም አይደሉም። አንድ ቀን በቅርቡ በአካል አገኝሻለሁ ሌላ የምትጨምሪው ውሸት ስለማይጠፋ ትነግሪኛለሽ ያችን እህት ይዤ መጥቼ እስቲ እሷፊት የምትይውን እሰማለሁ በመጨረሻ የምመክርሽ ስምሽን አትደብቂ እውነተኛ ከሆንሽ ምንም የሚያስፈራሽ ነገር የለም መዋሸትሽን ስለምታውቂ ነው እንጅ።

  21. እሮጦ የወጣው ቄስ ሀይሉ ነው ድንገት የታደለን ስም እንደጠራው የእኔንም ስም ይጠራና ገድ ይሰራኛል ብሎ እግሬ አውጭኝ አለ ቅቅቅቅቅቅ ምኑ ሞኝ ነው እዛ ቁጭ ብሎ ላብ ላብ እስኪለው ከሚያምጥ ፈትለክ ነው እንጅ ያ ሌባ የአድማ መሪ ቄስ ተስፋዬም የቀረው ለዚሁ ነው በጣም የሚያሳዝነው ግን የየኔታ ነው እግዚኦ ምን መሬት ይሆን እንዲህ አይነቱን ከሀዲ የምትቀበለው አቤት አለማፈር ያ ውሃ የገባች አይጥ የመሰለ ልጃቸው እየጎተተ ይዞአቸው ሲመጣ በጣም ነው የሚያሳፍረው እይ መካሪ ማጣት እሱስ የለየለት ዱርዬ ነው የካዛንችስ በረንዳ አዳሪ እዚህ እንኳን መጥቶ የማይሰለጥን አዛባ ቢሞት ይሻለዋል።

  22. lene beleh Sema says:
    May 13, 2016 at 11:26 am

    Your report of the day in court is commendable, purposeful, practical and should be appreciated. Please continue to document is as will be.
    ————–
    Otherwise the devil seems busy on comments from both sides as it is in everyday life everywhere. If possible this very web site should not have allowed a distorted version of the day in court. At least the person’s name is identified as one individual now, assuming that is true. It is a sad irony the pseudo name, “Memenan” is misused since it can easily represent “all” or “some” members of the congregation.

    Ethiopians need to get out of this mentality of sharp insult and name smearing as weapon, let alone among religion societies. It is not all Ethiopians, but when you find such hell among the EOTC, obviously, it is a cut throat groupies, may be well filled in that “church” unfortunately. Those who can be exemplary and defend the name of that community of church and religion need to post here and equally guide in their wisdom. That is assuming the good ones are reading some of all this non sense.

  23. አይ የአቶ አማረ ካሳዬ ጉጅሌዎች በጣም ትገርማላችሁ የድንግል ማርያም ቤት መዘረፍና የጥቂት ወረበሎች ኪስ ማዳበሪያ መሆን ያንገበገባቸውንና በቁጭት ተነስተው የሚያጋልጧችሁን ለቤተክርስቲያኗ በሐቅ የቆሙትን የተከበሩ ግለሰቦች ባልተገራና ባልታረመ ፅሁፋችሁና በዛ አራት ግለሰቦች በምንትጫጩበት የስልክ ኮንፍራንሳችሁ ስትዘልፏቸውና ስታንጏጥጡ ስሰማና ፅሁፋችሁን ሳነብ ምን ያህል የወረዳችሁና የዘቀጣችሁ የደናቁርት ጥርቅም እንደሆናችሁ እረዳለሁ። እባካችሁ መላው የድንግል ማርያም ምእመን ጠንቅቆ ስላወቃችሁ ዳግም አጭበርብረን ለመኖር ተመልሰን እንገባለን ብላችሁ ከሆነ don’t even think about it እላችኋለሁ።

  24. Memenen፤አባቡ የምትባል የስው መልክ የሌለህ ድዊ ድኩማን አስቀያም የስው መልክ የለህ ዝንጀሮ።እራ ለመሆኑ አይምሮህ ጤና ነው ውይስ ታውኮል።ቢሆን ነው እንጅ እብድ ብለህ ያበድክው ምነው አባትህ ሊቀ ሊቃውነት አይደልም እንዴ እብደቱ ሳይብስብህ ጠበል ቢያስጠምቅህ፣ ለነገሩ የካህን አለቃ ተብዬው ጎጉንቸሩ ሊሞት አንድ ሀሙስ የቀረው በእስተርጅና የወረደው የቀለለው አባትህ ለራሱ ፀበል ያስፈልገዋል።በእርግጥ የስው ልጅ ከትውልድ ከህፃንነት ከጨቅላ ዕድሜ ጀምሮ በስነስርአት ፣በባህላዊ፣ በሃይማኖት ፣በግብረገብነት፣ ተኮትኩቶ ካላሳደጉ።ከአደጉ ወይም ከአረጁ በሃላ ያደገባቸውን መጥፍ ብልሹባህሪን ማስተካከል አይቻልም ፣ ዋናው ልጅን በመልካም ስነምግቧር ጨዋነት ጥሩ ዜጋ እንዲሆን ከፍተኞውን ሚና መጫወት የነበረብት ወላጅ መሆን ነበረባቸው።ደሩ ምን ያደርጋል የአባቡ እድገት አስተዳደግ ግን።ከእናት ተወልዶ በእናት ፍቅር እና እንክብካቤ ያላደገ፣ አባትዬው ደግሞ ያሁኑ የካህናት አለቃ የድሮው የግለስቦች ሹፌር፣ የትምህርት ብልጭታ በአጠገቡ ያላለፍ ተራ ጠብደል መህይም።ታዲያ ይሄ ከንቱ ትውልድ አባቡ የሚባለው የካዛንችስ ዱርዬ ምን ልንጠብቅ እንችላለን።በእናት ፍቅር እንክብካቤ፣ አድጎ ቢሆን ኖሮ የእድሜ ባለፅጋዎችን እናቶች አሮጊቶች እያለ እያወረደ ሲስድባቸው መስማት በጣም ያማል እነሱ የደረሱበት እድሜ አያድርስህ እድሜህ ይጠር።ሌላው አባትህ በጥሩ ዲሲፕሊን በሃይማኖት ተንፅህ ቢያሳድጉት ኖሮ። እነሆ ዛሬ የስውን አባት ታላላቅ የአይማኖት መሪዎችን ታላላቅ ሙሁራን አባቶችን እንደዚህ ከፍ ዝቅ እያደረገ ባላወረዳቸው ።በስለጠነው ሀገር እየኖረ እንደዚህ አይነት በውሽት የተሞላ ዘለፍ ስድብ ከእሱ አይጠበቅም ነበር ያውም የስሙ የካህን ልጅ ተብሎ ባሌጌ ያስደገው ስድ አደግ ነህ እንጅ ።

  25. ጎጉንቸሩ፣ አባቡ ዝንጀሮ የመስልክ ድዊ የስው ግማሽ ኩርንችት ጎደሎ።የራስህን የስውነት አፈጣጠር ምን እንደምትምስል እንኮን ለይተህ ሳትረዳ ፣የፍርድ ቤቱ ዉሎ ብለህ የሞነጫጨርከው እንዲያው ትንሽ እፍረት የሚባል ነገር አልተቀርፅብህም መቼም።እውነታውን ደብቀህ ውሽት ስትለቀልቅ እረ ፈጣሪን ፍራ ምንም ባታውቀውም መቸስ።ዳኞው ፣ ሆነ ጠበቆች የሚለዋወጡትን ቃላት አንድ የእንግሊዘኞ ሴንቴንስ ተጠቅመህ እንኮን ትክክለኞውን የነበረውን ግልፅነት ፣እውነት እና፣ ውሽትን መለየት አቅቶህ እውር ድንብርህ ተወላግዶብህ እየሞነጫጨርክ አይናቸው ለታወረ ማንበብ ለማይችሉ ሂሊናቸው ለዳሽቀ ማስብ ለማይችሉ የአንተና የአባትህ ካህን አለቃ ተብይው ቀሚስ ጎታቾች ስው አምላኪዎች ተከታዬቻችው የምታስተላልፍው በውሽት እና የግለስቦችን ስብህና የሚነካ ስድብ የተሞላው መልእክት በጣም የሳዝናል ያሳፍራል አልፎም በብዙሀን ንፁ ወገኖቻችን ላይ የምታድርስባቸው መስመር የለቀቀ የሞራል ፣የስብህና ፣የስም ማጥፍት ሌብል የማድረግ ክልራክተር አሳስኔሽን በአጠቃላይ እየፈፀምክ ያለው ወንጃል በቅርቡ ወደ ህግ ደጃፍ እንደሚያስቀርብህ አትዘንጋ።ይህን ካልኩ ብሆላ ስለ ፍርድ ቤት የችሎት ውሎ እኔም እዚያው ተገኝቼ ስለ ነበር የተመለከትኩትን በእለቱ የነበረው የፍልሚ ትርእት እጅጉን አስደናቂ አስቂኝ ነበር በጣም ተደስቼቤት አለሁኝ ቅቅቅቅቅቅ የፍልሙ መሪ ተዋኒያን የካህን ገፅ ባህሪን ይዞ ይተውን የነበረው ግለስብ።የቲውነት የሙያ ችሎታውን በብቃት የተወጣ ነው የሚመስለው።ቅቅቅቅ አንዴ እንደ ካድሬም ያደርገዋል፣ ዞውር ብሎ ደግሞ የእንፕ አባቡን የአባትዩውን ፍት ሲያይ ደግሞ ወይኔ ገደሉኝ ብሎ ይመሳላል መስቀሉን እያወራጭ እሪፍ ቄስ ይመስላል።ከ ጠበቃው የሚውርድበትን የጥያቄ ዱላ አንድንዴም የዳኞውም ተጨምሮበት መመለስ ሲያቅተው ድንግልን ከነልጆዋ የድረሽልኝ ጥሪ ሲማፀናት እያየን ያም ሆኖ የጣር ሲቃ ሲይጣጥር የነበረው ትእይንት ድራማውን በደንብ አድርጎ ተውኖታል አስቂኝ ካህን ቄስ ዘላለም።እውነትን የማይነገር አንደበት በውሽት የሚዘላብድ ምላስ ያውም ቄስ ተብሎ ከተስየመ ካህን በእጁ መስቀል ይዞ፤መስቀል ከሚያሳልም በጭንቅላቱ የተከበረውን ታቦት ከሚሽከም አዛውንት፣ አንደበት ያንን የመሰለ ቅልምድምድ ያለ ሀስት ማስማት ምን አይነት መጥፎ ዘመን ላይ እንደደረሰን እያየን እየተረዳን ነው ልቦና ይስጣችው ።

  26. Dr. Aklilu had been doing a reasonable defense the way he saw it. There are two sides to a case, and there is no perfection (so far managed to read through 60% of his deposition, will continue when time is available). It is lengthy, but recommendable to understand one step further the nature of what exactly took place.
    – One thing which stood out as bothersome was that the “illegal” board was not given a written notice that it will be replaced, although the three years prior to that the same “illegal” board had been asked to change its ways.
    -It seems he was in a delicate position between trying to work with the board when it came to construction work on the church and the fact that he considered their 2012 By-law as only a draft.
    – He is representing different branches of the church; he should not be singled out to take all the blame. His followers, or vice versa (most times, he gives due respect to people who brought the complaints to his and attention of others) trusted and counted on each other.
    In a way the fact that it went to court and observers have the opportunity to get facts from depositions is much better than the confusion which is passed through conversation. In fact once everything is heard from both sides, and better clarity is attained through the court documents, a new form of hope and healing can be possible.
    -He stated something to the effect that, we built a first class institution.
    Those years also included Kesis Amare, right? I hope after all is completed, by July? A mutually renewed possibility exists to work together for both sides.

  27. Anonymous 1. I understand that you are trying to stay neutral. But Dr. Aklilu’s testimony is full of contradictions. He is a narcissist if you ask me. I think he really did a real damage to their case. Especially , that they have been planning this coup de board for 3 years.

    We will see in July one way or the other but Dr Aklilu is a damaged good either way.

    The most amazing thing is I don’t think most of their folks have read his testimony based on the comments they are giving. He has done them wrong. The chickens are coming home to roost.

    And at the last court hearing their lawyer was trying hard to have this testimony removed from being a court document but the judge refused to do so.

  28. It is about knowing the truth, and where matters went wrong. It is also about questioning one’s faith; and what exactly it is, when the façade is removed. It is about the church as an institution which has a great potential to do much good, but in all its high volume, much seems to have been boiling behind the scene. Whichever way one looks at matters, its first mission is an EOTC. They are all humans and not angels, but this kind of trashy hostility among its members is discouraging to have trust in the church as a place of faith and an “institution”.

    I am most curious why Dr. Aklilu’s side found the 2012 by-law as “illegal” vs. why the board changed the 1996/2004 original by-law. I might, or not, find the answer as I continue to read the rest of Dr. Aklilu’s testimony.

    As far as Dr. Aklilu contradicting himself, it is obviously some form of cross examination, and the lawyer is trying to squeeze the right catch out of him. That seems to be why the deposition is lengthy; it is at times redundant. He might be of advanced age and resisted to give account of specific dates from memory (a good strategy in his defense); his mind is sharp enough not to give into the attorney’s questioning and be trapped. As he said, it is the first of its kind, going to court this way for the church. The unanticipated process of handling the “concerned people’s committee” transition is at least accounted for and videotaped. Where is the three years response from the board and Church administrator?

    Along the way, an observer/reader can get a glimpse into an understanding of the dilemma of being a religion institution. It shows how the church’s existence gravitated between trust and administration; between faith and the by-law; between the mentalities of the young task force and the responsibility of the elders; between canon law and common law. I am aware the attorney requested for the testimony not to be a part of the court’s document. We don’t know what exactly his reasons are.

    The plaintiffs legal cost seems to be covered by the church’s account since they consider themselves as the “legal” representatives of the church. I wonder what fund is available for legal cost of Dr. Aklilu’s side.

    Ethiopian Review at least without any pretense, is on the plaintiff’s side at times misleadingly. At least it gets credit for keeping up in posting such critical matter of faith and community.

  29. SHAME ON YOU, Mereja.com, Ethiopian Review, shame on you! You just left Amare & Asteraye’s… posts and removed all the other posts!!!! What is your problem?! Why don’t you open your media to all to use?! Shame on you! I could say a lot but you guys don’t even deserve my insults!

  30. ቄስ አማረ ካሣዬ አበዱ!!!
    የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላምን ቤተ ክርስቲያን ከ20 አመታት ሲመዘብሩ፤ ሲያስመዘብሩ፤ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያዛዝኑ፤ ሲያስጨንቁ፤ በህዝቡ ባልተመረጠ ቦርድ ጋር ቂጥ ለቂጥ ገጥመው ቤተ ክርስቲያኗን እንደ ወያኔ በአምባ ገነንነት ሲገዙ የነበሩት ቄስ አማረ እንዳበዱ በሀኪም ተረጋገጠ!
    ግለሰቡ እጅግ በጣም ጭንቀት ውስጥ በመግባታቸው፤ 24 ሰዓት አእምሯቸው ባለማረፉ፤ ሶስት የመንፈስ ማረጋጊያ መድሃኒት እንደታዘዘላቸው ሲታወቅ፤የሀኪሙን ምክር ሰምተው አኗኗራቸውን ካለወጡ፤ የሚቀጥለው ደረጃ በግዳጅ አእምሮ ሀኪም ቤት መግባት እንደሆነ ተነግሯቸዋል። የቅርብ ወዳጆችም ሊሞክሯቸው ቢሞክሩም፤ ቄሱ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም።
    በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች እንደገለፁት፤ ሰውየው እቤትም እረፍት እንደሌላቸውና፤ እንደ እብድ የሚደባደቡ ሚስታቸው፤ ወ/ሮ ነገደ ግርማም፤ ይህ አመላቸው ባላቸውን ለባሰ የጤንነት በሽታ ሊጥላቸው ስለሚችል፤ በቅርብ ወዳጆቻቸው እየተመከሩ እንደሆነ ነው።
    ብዙ ሰዎች የቄስ አማረ ካሣዬን የአዕሞሮ መናጋት፤ ከሚሰጡት ድብልቅልቅ ያለ ‘ስብከት’ ታዝቦ ከርሟል! ሰውየው በሳምንት ሁለት ቀን ከሚለፈልፉት ስድብ አይሉት ትምህርት ስብከታቸው፤ ሲጮሁ፤ ሲሳደቡ፤ ትርጉም የሌለው ነገር ሲዘበራርቁ ተሰምተዋል። ሚስታቸውም ወ/ሮ ነገደ ግርማም፤ ባላቸው ቄስ አማረ ካሣዬ ምንም እንቅልፍ እንደለሌላቸውና፤ ሌሊቱን ሙሉ እቤት ውስጥ በጭለማ ሲመላለሱ እንደሚያድሩ ሲገልፁ፤ ከሳቸውም ጋር ምንም ሰላም እንደሌላቸውና ትተዋቸው ድንገት ቢወጡ፤ እራሳቸውን ያጠፋሉ ብለው እንደሚፈሩ በፍርሃት ገልፀዋል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*