‪የሚሰማ ጆሮ ካለ … በማምታታት ላይ የተመረኮዘ ስትራቴጂ ወደ እውነተኛው የትግል ስልት ሊቀየር ይገባዋል::

‪#‎Ethiopia‬ የሚሰማ ጆሮ ካለ … የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ:: በማምታታት ላይ የተመረኮዘ ስትራቴጂ ወደ እውነተኛው የትግል ስልት ሊቀየር ይገባዋል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሰላማዊ ትግል ይሁን በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ሃይሎች ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመምራት የሁሉንም የጋራ ልብ ለመግዛት የሚችሉት በአንድነት ቆመው የህዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመደምሰስ የፖለቲካ ቆራጥነት እና የትግል ጽናት ሲኖር ነው::ተበታትኖ ትግል አንድም ለወያኔ ክፍተት መፍጠር ሲሆን በሌላውም በር የህዝብን ዝምተኝነት ማበርታት ይሆናል:: መሰራት ያለባቸው የለውጥ ስራዎች ሁሉ በመደጋገፍ እና በመቻቻል መሆን ይገባዋል::በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል:: በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል:: ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል::የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው::

Minilik Salsawi's photo.

ይህንን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ይኖርባቸዋል::የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ይሁን በውጪው አለም ያሉ የለውጥ ሃይሎች ለሕዝብ ነጻነት እና መብት እንታገላለን እስካሉ ድረስ እርስ በእርስ መናከስ አቁመው በመደማመጥ እና በመወያየት በመመካከር እና በመቻቻል በመግባባት እና በመፋቃር ለሃገራዊ አጀንዳ በጋራ መቆም ችላ የማይባልበት ወቅት ላይ ተደርሷል::የሕዝብን ታማኝነት ለማግኘት የለውጥ ሃይሎች እርስ በርሳቸው እየተባሉ እንዴት እኛን ነጻ ያወጣሉ የሚለውን ቅብብሎሽ ለመቁረጥ እና በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ፈጥሮ ትልቅ የለውጥ ስራ በመስራት አገዛዙን ማስወገድ ይቻላል::

በዚህ ግፎች እየበረቱ በሄዱበት ወቅት ላይ የሕዝቡ የለውጥ ፍላጎት አብሮ እየጨመረ ይመጣል::ሕዝቡ ዝምታው ለምንድነው? እኛ ጋር ምን ችግር አለ? መቻቻል እና መተባበር የምንችለው እንዴት ነው? ለስልጣን የሚቋምጠው እና ልለውጥ የመሰራው እንዴት ይለይ?የሃሳብ ልዩነቶችን ማግባባት እና ማቻቻል የምንችለው እንዼት ነው? የሕዝቡን ዝምታ እንዴት መስበር ይቻላል?ሕዝባዊ ታማኝነትን በጋራ ሃገራዊ አጀንዳ እንዴት መፍጠር እንችላለን? የያዝነው ስትራቴጄ አዋጭነቱ ምን ያህል ነው..ተጠባባቂ ስትራቴጂ አለን ወይ? ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በአንድነት ማቆም የሚቻለው የትኛው ግድፈት ቢቀረፍ ነው? ሰላም እና ዲሞክራሲን ለመተግበር ተነሳሽነት ምን ያህል ነው? ባለፉ 20 አመታት የተበታተነው ትግል እና የተበታተኑ ድርጅቶች ምን ፈጠሩ ? ካለፈው የትግል ተሞክሮ ምን እንማራለን ?…ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ የለውጥ ሃይሎች ግዴታ ነው::ዋናው ነጥብ ግን በአንድነት መቆም ነው::ሃገራዊ አጀንዳ ይዞ የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በማጥፋት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው:: የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

6 Comments on “‪የሚሰማ ጆሮ ካለ … በማምታታት ላይ የተመረኮዘ ስትራቴጂ ወደ እውነተኛው የትግል ስልት ሊቀየር ይገባዋል::”

  1. ወንድሜ፣አንድነት ገነት ነው ሁሉም ይፈልገዋል።ሀይማኖቶች ቢያንስ በኛ ዘንድ የሚዘወተሩቱ መግባባት ያልቻሉት ገነትን ስለመውረስ አስፈላጊነት ሳይሆን እንዴት በሚለው ላይ ነው።የአንተ የፖለትካ አንድነት ስብከት ማተኮር የነበረበት ስምምነት በጠፋበት አንድነት እንዴት በሚለው ላይ መሆን ሲገባው ስምምነት ባልጠፋበት በአንድነት አስፈላጊነት ላይ መሆን ነበረበት?ሌላው ግር የሚለው “የህዝብ ዝምታ”የሚለው ሀረግ ነው። በአለፉት አራት ወራት በዝህ ምድር ላይ አልነበረክም ማለት ነው?የኦሮሞ ህዝብ ከገጠር እስከ ከተማ ያደረገውን ግልጽ የወጣ ተቃውሞ (open revolt) በመገናኛ ብዙኃን ስዘገብ ስለነበረ ነው።ወይም የአንተ “ህዝብ”የሚለው ቃል የተለየ ትርጉም አለው ማለት ነው።በርግጥ “ኢትዮዺያ”፣ “ህዝብ” የሚሉት ቃላት በ ‘አንዳንድ’ ወገኖች ዘንድ አማራ ከሚለው ጋር በተለዋጭነት ጥቅም ላይ ይውላል። ያንተም የህዝብ ትርጉም በዚህ መንፈስ ይመስላል።የሚታወራው ስለ ኢትዮዺያ የፖለትካ ሀይሎች አንድነት ከሆነ ለመጻፍ ያለምከውና የጻፍከው ለየቅል ነው። በነገራችን ላይ ዛሬም ሆነ ወደፊት ስለ ወደፊቷ ኢትዮዺያ ዕጣ ፈንታ መወያየት የግድ ከሆነ አገሪታን ያዋቀሩት የሁሉም ብሄርችና ብሄረሰቦችን ጥቅም፣ፍላጎትና ራዕይ የሚያንጸባሪቁ ሀይሎች መሳተፍ ይኖርባቸዋል። ለዚህ አንዱ እንቅፋት የአማራን ብሄር በወርድና ቁመቱ ልክ የሚወክለው የፖለትካ ስብስብ ከማግኘቱ ላይ ነው።የኢትዮዺያን ፖለትካ ከብሄር ጥያቄ ውጪ ለማየት መሞከር መሬት ጋር ከአለው እውነታ ጋር መላተም ነው። ወንድሜ፣የአንተም ጽሁፍ ውል ያጣው በዝህ ምክንያት ነው።

  2. አሁንም እናንተ የእፉኝት መለሲዝም ደቀመዝሙሮች አንድ ነገር ወይም አስተያየት በተፃፈ ቁጥር ቶሎ ብሄሮች ላይ ትሮጣላችሁ አየ አለመታደል ምንይልክ ያቀረበው ሀሳብ ወቅትዊና ግሩም የሆነ ገንቢ አስተያየት ሲሆን አንተ ግን አስቀድመህ የምትንዛው የመልሲዝምን መርዛም የሆነ እራእይ
    ነው አውቀናችሁዋል አትድድከሙ

  3. WARNING !

    ዘ ር ጋ ው is Tesfaye Gebreab !

    Zero chance for tribal politics in Ethiopia, but the retarded Eritrean desperately preaches for tribalism in Ethiopia.

    Tribalism dead in Ethiopia.

  4. ሚኒልክ ሆይ ስለአንድነት ሲፃፍና ሲነገር በርካታ ጌዜ ነው ማውራት እንደ መተግበር ስለማይከብድም ይሆናል።
    የቪዥን የኢትዮጵያ ጥረት ወደ አንድነት የሚመራ ሰለሆነ በቅንነት እንዲጠናከር ቢደረግ ያንተን ማሳሰቤያ መልስ ያገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*