አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ተከሰው በዲሲ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

(አዲስ መረጃ ተካቷል )  መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.  (April 6, 2016)

ይህንን ጉዳይ እየተከታተልን አዳዲስ መረጃዎችን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን ለሕዝብ ማሳየት የሚቻለውን መረጃ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨምረናል። ሙሉውን የፍርድ ቤት የመጀምሪያውን ትዕዛዝ የሚቀጥለውን ሰንሰለት በመጫን ያንብቡ። (አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዙበት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ)

በአቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ፊታውራሪነት የሚመራው ”ዘመቻ አባ መላኩ” የተሰኘው አቀፍ ዘመቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ከበደ ያለ ፈተና ገጠመው። አቡነ ፋኑኤል የናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ው ሲኖዶስ እንዲገባ መደረጉን ተከትሎ በተነሳው ዉዝግብ  ምክንያት የዘመቻው ፊታውራሪ  የሆኑት አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው። አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት ላለመቅረብ ብዙ ሲከላከሉ ቆይተው ጉዳዩ ስለከበደና መሄጃ ስላጡ በመጨረሻ በሚያዚያ ወር ፍርድ ቤት ሊቀርቡ መስማማታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጉዳዩ አቡነ ፋኑኤል አስተዳድረዋለሁ የሚሉትንና በአሜሪካን ግዛቶች አገረ ስብከት ዉስጥ ብዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስራቸው ለማድረግ የሚደረገው ዘመቻ ተከትሎ የተከስተ ሁኔታ ነው። እንደሚታወቀው አቡነ ፋኑኤል ብዙ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በመክፈት፣ ድርብ ታቦት በማደል፣ ሹመት በመስጠት ‘የግዛት ማስፋፋት’ ርምጃቸውን የወያኔ ታዛዥ ልሆኙት ለአቡነ ማትያስ አድናቆትን ሳያተርፉ እንዳልቀሩ ብዙዎች ይናገራሉ። ከአሁን በፊት እንደዘግብነው የአባ መላኩ የተሰጣቸው ትልቁ ግብ ስለሰባዊነትና ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆሩትን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማዳከም እንደሆነ ታውቋል። ይህ በተለይም በዲያስፖራ ያለውን ተቃውሞ እንዳይጠነክር ለማፈን የታለመ ዘመቻ መሆኑ በተለያዩ መረጃዎችና በሚደረጉት ተግባራት ለማወቅ ተችሏል።  ለዘመቻው አፈጻጸም የተነደፈው ስትራቴጂው ሦስት አማራጮችን ጎን ለጎን አድርጎ መንቀሳቀስን ያካተተ ነው። እነዚህም፤

  • ከተቻለ እያንዳዱን ቤተክርስቲያን በአባ መላኩ ቁጥጥር ስር ማዋል፣  
  • ካልተቻለ ደግሞ ሥርዓተ አልበኝነትን በማስፈን መበጥበጥ። በተለይ የጸረ-ወያኔን ጎራ በትርምስ ማወክና ስለወገኑና ስለ እምነቱ የሚቆረቆረው ሁሉ በተረጋጋ መንፈስ መኖር እንዳይችል ማድረግ ነው። ይሄ በአገር ቤት የሚደረገው አይነተኛ መገለጫው ነው። በአንድ ከተማ ውስጥ ሌላ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ስም በየማዕዘኑ መክፈትና፣

የሚገርመው አቡነ ፋኑኤል የማይገባቸውን የፓትርያርክ ልብስ በመልበስ ከሌሎች ጳጳሳት በላይ መሆናቸውን ለማሳየት ቢሞክሩም ምንም አይነት ተቃውሞ ሲደርስባቸው አላየንም። ይህም ወያኔ ስራውን ስለሚሰሩለት ሊናገራቸው አልፈለገም። አቡነ ማትያስም ወያኔ ያዘዛቸውን ማስፈፀም እንጂ በውነት ለቆሙበት እምነት የሚያገለግሉ አለመሆናቸውን ደጋግመን ያየነው ስለሆነ እዚህ ላይ ማንሳት አያሻም። ምናልባት ባለፉት 4 ወራት በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመሬታችን ተዘረፈብን ጥያቄ ዋልድባ ገዳምን ያስታውሱ።  ወያኔ ዘርፎ  ለስኳር ፋፍሪካ ምርት ማቅረቢያ ለማድረግ የዋልድባን ገዳም በግማሽ ወስዶታል።

የEthiopianreview ባደረገው ክትትል አቡነ ፋኑኤል የሚመለከት ከአገር ቤት ድረስ የሚዘልቁ መረጃዎችን አሰባስቧል። በቅርቡ መረጃዎቹን በዘገባችን እናቀርባለን።

ምናልባት አሁን ፍርድ ቤት የሚቀርበው ዝርዝር ሁኔታ አቡነ ፋኑኤል  ‘ፓትሪያርክ’ የመሆን ምኞታቸውን ለማሳካት እጅግ የሚያስቸግር እንደሆነ መገመት ይችላል።  አሁን ያላቸው አማራጭ ማንኛውንም ኃይላቸውን ከዚህ ክስ ሊያመልጡ የሚችሉበትን ሁኔታ መሻት ይሆናል።  ነገር ግን የገጠማቸው ክስ በቀላል መንገድ መውጫ የሚያገኙበት እንደማይኖር የክስ ሁኔታውን ከሚያውቁት መረዳት ተችሏል። ከነዚህ አመልካች ነገሮች አንዱ የተከሰሱበት መነሻ የሆነው የናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም የአኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ምእመኑ ያውቃል። እንደውም እባካችሁ ይቅርታ እንዲደራረጉ እያሉ የወያኔን ታክቲክ ለመጠቀም ቢሞክሩም ጉዳይ ጊዜ ስላለፈበት የፍርድ ሂደቱን መጠበቅ ብቻ ነው ያለው አማራጭ።  

 

33 Comments on “አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ተከሰው በዲሲ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው”

  1. እረ ምን ይህ ብቻ የጽላት ማደሪያ ማሰሪያ ከሀገር ቤት ተወካዮቻቸው ጋር በመሆን 35000 ዶላር በእዚሁ ቤተክርነነስቲያን እንዳስመጡና ደላሎቻቸው በሹመት የሚሰጡዋቸው ካህን እንደሆኑ ያውቃሉ?ብዙ ጉድ አለ ጊዜ ይነስጠን፡፡

  2. አጭበርባሪ ናቸው እኛም እዚ ቬጋስ አበጣብጠውን ሁለተኛ እንዳይደርሱብን አስደርገናል

  3. Inante isachewun yemetksu ISLAMOCH NACHU
    Abatachin ye Orthodox Betkristian Mesoso
    nachew inde Amare Kassyw ina achiberbariw
    Asteraye beyeadebabau Allah Akbar iyale yemichoh
    Hajji neaw .

  4. ይስማሽዋና ጋዲሳ ውሻ በበላበት ይጮሀል ማለት እናንተን ነው ምሰሶ ትርጉሙን የምታውቁ አትመስሉም የእናንተ አይነቱ ደነዝ ነው ቄሶቹን የሰይጣን ስራ የሚያሰራቸው ዶክተር አማረና ቀሲስ አስተርአይ ለእውነት የቆሙ ስለ ሀይማኖታቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው የእናንተ በባዶ ሜዳ መጮህ ክሱን አያቆመውም በሁአላ ከማፈር ሁኔታውን በትእግስት መጠበቅ ይሻል ነበር እራሳችሁን እንኳን ማዳን እማትችሉ ከንቱ ፍጥረቶች የወያኔ ተላላኪዎች በባዶ ሜዳ ስትጮሁ አለማፈራችሁና ንፁህ አባቶች ላይ ጣታችሁን መቀሰራችሁ የማትረቡ ለሆዳችሁ የምትኖሩ መሆናችሁን ይገልጻል።

  5.  30, 2016 at 8:05 pm

    እውነቱ ይርደው says:
    B
    March 29, 2016 at 8:18 pm

    እግዚኦ ማለት የለብን ጊዜ ላይ ነን ከመሪ የራሳችን ዜጎች አረመኔ ጋኔን እና ዲያቢሎስ ሆነው ይገሉናል። በሐይማኖትም ያልታደልን ሆን ታጋይ አባ ጳውሎስ ሲሄዱ ታጋይ ማትያስ በመለስ ሰም እየማሉ ይገኛሉ ሐይማኖቱን ከተሐድሶ ሰዎች ጋር አመሰት፣ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ የለህም እንዳልል የ365 ቀናት ፓውዛህ መብራት ኢትዮጵያ ላይ በቃልህ ስታበራ አይተናል፣ ግን አምላክዬ ትግስትህ በዛ አንድ በል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይብቃህ ዝምታ? በሥልጣን ላይ በህይወት ያሉትን አቡነ መርቆርዩስ አልናገርም እሳቸው ለ ቡራኬ እንኳን ዝም ብለዎል፣ አንተ አንደበታቸውን ክፈትልን!!! እሳቸው ዝም በማለታቸው ሐይማኖቱን እናድስው ብለው ኦርጋን ና የግዜውን ፍልስፍና ጨምረው፣አጅበው ከሐይማኖቱ ታሪክ ጋር ያልተለመደ ጉዞ እነ አባ መልከ ፀደቅ፣ አባ ወ/ትንሣኤ ፣ አባ መላኩ፣ ልኡለቃል ሕዝቡን በተሐድሶ መንገድ ኢትዮጵያዊውን ጋራ እያጋቡ ነው። ተው ተብለው ሲመክሩ ያለመታደል ከእኔ በላይ ከፈጣሪ የቀረበ የለም ይሉናል። ብዞዎቹ በጎንደርነት ያከብሯቸዎል ማክበር ጥሩ ነው ሲሰታቱ ከለነገራቹ ግን እነሱን ገደለ ውስጥ ከታችሁ ማለት ነው። አባቶቻችን ያስረከቡንን ዶግማ እና ቀኖና አንዲት ነገር ሳትቀየር፣ ስርአቱን ጠብቀው ህዝብን በአንዲት ቤተክርስቲያን መሰብሰብ አልቻሉም እባካችሁ ስህተት ጎዳና ላይ ናቹ ተመለሱ። እባካችሁ የአገራችን ፈተና ለይ ነች፣ ይቅርታ ህዝቡን ጠይቃችሁ፣ ህዝቡን እንደገና አሰባስቡ፣ የጥላቻ ቤተክርስቲያን በዛ ፍቅር ከሌለ በመሀከላችሁ እግዚያብሔር የለም ማለት ነው ባዶ ባዶ ባዶ ከደመና በታች ስጋን ለማስደስት ይሆንባቸዎል!!! እርስ በእርስ በሁለቱም ጎራ ዲየቢሎስ በረሱ መንገድ እየመራችሁ፣ እያረሰረባችሁ ነው ቆም ብላችሁ ሁለቴ በአሰቸኳይ ዛሬ አስቡ ነገ ፈራጅ ይመጣል። ስሙኝ እኔን ዛሬ የወደቁ ሐጥያተኛውን እኔ እንደ እናንተ አልሆንም ኤኔን ሐጥያተኛውን ስማኝ አምላኬ ብዬ እፀልይላቸዎለሁ። እባካቹ የማህበሩ ቅዱሳን ተግባር አትኮኑኑ ፈራጅ ያያል በአንፃሩ አንዳንዱቹ ከኔ በላይ ክርስትያን የለም ብለው የሚታበዩ አሉ እነሱን ቀጥታ ለይቶ ማስተማር እና ወደ ስርአቱ መመለስ ይበጃል ደካማው ወገኔ ብዙ ደም የተከፈለበት ነው።

    [Reply]

  6. ወያኔ መሪ አልባ ሥርአትን በሀይማኖት በፖለቲካ እጅግ ተንሰራፍቶ ይገኛል በጃዙር የወያኔ ሥርአት ውቅያኖስ ተሻግሮም በዘራፊ ዲያሥፖራ ብብት ውሥጥ ተሸጉጦ ይገኛል ታድያ ይህ የተማረ ሀይል ያለበት ሀገር እንዴት የወያኔ የብብት ቅማሎችን ማሥወገድ ተሳነው?

  7. እግዚአብሔር እድሜ ከሰጠን ግፕና ብዙ እናያለን እግዚአብሔር ትእግስቱ ቢበዛም ሰራው እረቂቅ ሰለሆነ በስሙ የሚነግዱትን ሁሉ ያጠፋቸዋል አባመላኩ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ዘበነ ለማ አቡኑ ተስፋዬ መቆያ አባ ጽጌ ቄስ ይስሐቅ ሌሎችም ብዙ አሉ እነ አቶ ታደስ ሲሳይ ቀንደኛ አመንዝራ የንስሀ ልጁን ሳይቀር የደፈር ሁሉም አንድ በአንድ ይጋለጣሉ በሀይማኖታችን የሚቀልዱ በስማቸው ቤተክርስትያን እየከፈቱ ከአምልኮት ይልቅ ንግዳቸውንና በስውር የወያኔን ተልእኮ በማስፋፋት ዲያስፓራውን የሚከፋፍሉ አውሬዎች በሙሉ ይጋለጣሉ የአባመላኩ የመጀመርያ ነው ሁሉም ተራውን እየጠበቀ ነው ይጋለጣል ዝም ብላችሁ እንደከብት የምትነዱ ክርስትያኖች ወደልባችሁ ተመለሱ ክርስትና ቀላል አይደለም የህይወት መስዋእትነት ተከፍሎበታል ክርስትና ማለት የካህን ጭራ ይዞ መሮጥ አይደለም እውነትን እውነት ማለት ነው ክርስቶስ የሞተልን እኛን ከሀጢያት ለማዳን እንጅ ሀጢያተኛን እንድናጅብ አይደለም በሀይማኖት ሰም ህዝብ ለመዝረፍ ቤተክርስትያን ለማፍረስ የተነሳችሁ መስቀል ይዛችሁ ሀሰት ይምታስተምሩ አውደምህረት ላይ በድፍረ ቆማችሁ ጥላቻን የምትዘሩ መቅደሱን የምታረክሱ ሰጋ ወደሙን የምትዳፈሩ ጊዜው ደርሶአልና ንስሀ ገብታችሁ ወደ ልባችሁ ተመለሱ

  8. እግዚአብሔር እድሜ ከሰጠን ግፕና ብዙ እናያለን እግዚአብሔር ትእግስቱ ቢበዛም ሰራው እረቂቅ ሰለሆነ በስሙ የሚነግዱትን ሁሉ ያጠፋቸዋል አባመላኩ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ዘበነ ለማ አቡኑ ተስፋዬ መቆያ አባ ጽጌ ቄስ ይስሐቅ ሌሎችም ብዙ አሉ እነ አቶ ታደስ ሲሳይ ቀንደኛ አመንዝራ የንስሀ ልጁን ሳይቀር የደፈር ሁሉም አንድ በአንድ ይጋለጣሉ በሀይማኖታችን የሚቀልዱ በስማቸው ቤተክርስትያን እየከፈቱ ከአምልኮት ይልቅ ንግዳቸውንና በስውር የወያኔን ተልእኮ በማስፋፋት ዲያስፓራውን የሚከፋፍሉ አውሬዎች በሙሉ ይጋለጣሉ የአባመላኩ የመጀመርያ ነው ሁሉም ተራውን እየጠበቀ ነው ይጋለጣል ዝም ብላችሁ እንደከብት የምትነዱ ክርስትያኖች ወደልባችሁ ተመለሱ ክርስትና ቀላል አይደለም የህይወት መስዋእትነት ተከፍሎበታል ክርስትና ማለት የካህን ጭራ ይዞ መሮጥ አይደለም እውነትን እውነት ማለት ነው ክርስቶስ የሞተልን እኛን ከሀጢያት ለማዳን እንጅ ሀጢያተኛን እንድናጅብ አይደለም በሀይማኖት ሰም ህዝብ ለመዝረፍ ቤተክርስትያን ለማፍረስ የተነሳችሁ መስቀል ይዛችሁ ሀሰት ይምታስተምሩ አውደምህረት ላይ በድፍረ ቆማችሁ ጥላቻን የምትዘሩ መቅደሱን የምታረክሱ ሰጋ ወደሙን የምትዳፈሩ ጊዜው ደርሶአልና ንስሀ ገብታችሁ ወደ ልባችሁ ተመለሱ

  9. Diaspora Kebtoch nachihu…ende Set were becha…..esti beyalachihubet Anbebu…Anbebu….awaki tehonalachihu

  10. የአስተራየ ልቅሶ መልሶ መላልሶ። አጥፍተው ከሆነ ለምን አይከሰሱም ከሕግ በላይ እኮ አይደሉም «ሕግ እሰ መልዕልተ ኩሉ» ቤተ ክርስቲያ የሃይማኖት ተቋዋም ብትሆንም በሕግ የመክሰስ የመከሰስ መብቷ የተከብረ ነው። መቸም አስተራየ የቤተ ክርስቲያንን ሕግ አፍርሶ ገለልተኛ በሚል እራስ ገዝ አቋቁሞ ከተዋሕዶ የወጣ ሥራ ከሰራ ወዲህ ሁሉም የሱ ጓደኞች እንዲሆኑ መወንጀል መወንጀል፤ ሰውን ለመክሰስ የማይቦዝን እኩይ ፍልስጣ ማለት አስተራየ ነው። እስቲ መልካም ለማሰብ ሞክር፡፡ አቡነ ፋኑኤል በባሌም ሆነ በቦሌ አንድ ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ሆነዋል አለቀ በቃ፤ የቀሳውስት አለቃ ናቸው። ቄስ ልያውግዛቸው ሊከሳቸው ሊንቃቸው ትዛዛቸውን አልቀበልም ማለት ዓይችልም ሕገ ቤተ ክርስቲያን ፍትህ መንፈሳዊ ያዛል። ቀሱ ሊቀ ጳጳሱን ንቀት ካሳየ ከአገልግሎቱ ይሻር ይላል። ምን ይደርገ እንግዲህ ሕጉን ማፍረስ አይቻል ቤተ ክርስቲያንን በገለልተኛ ዶማ እንዳፈረሳችሁ፡ ጨጓራችሁ ይፍረስና።

  11. ታሪክ ድንቁርናህን/ድንቁርናሽን ይሳያል አነጋገርህ እንደ አንተ አይነቱ እውር ማስተዋል ያቃተው በማንበብ ብዛት ይሆን? ወሬኛ የአንተ አይነቱ ነው ስንት ጀግና ሴቶች እንዳሉ ማወቅ ነበረብህ አንባቢ ከሆንክ

  12. አይ ዲሲ ለንደን እንዳበደ ውሻ የሚያስጮህ በሽታ ስለያዘህ ነው የምትቀባጥረው ከአርእስት ውጭ የምትቀባጥረው የከሰሳቸው የበጠበጡት ቤተክርስቲያን ያንተ በሽታ ቄስ አስተርአይን መሳደብ በጣም ደደብ ነህ በገንዘብና ለወያኔ በማጎብደድ ከተገኘ ፕፕስና የቀሲስ አስተርአዬ ቅስና ሸህ ጊዜ ይበልጣል አለመገንዘብህ እንጅ ደግሞ አዋቂ ለመምሰል ግእዝ ቢጤ ጠቀስ አድርገሃል ወገኛ ነህ የደንቆሮ ወገኛ

  13. እዚህ ላይ የምትለቀልቁት፣ Tarik፣ዲስ ለንደን፣ yesmasho…..እናንት ድንንበኞ የወያኔ፣ እና የመላኩ አሽከሮች እና አልቅላቂዎች ደካማ ፍጡሮች ናችው። ቄስ አስቴርዬ እና ዶ/ር አማረ በእናንት ዶማ እራስች አፍ የሚስደቡ አይደለም።የእናንተ አለቆች ከነ ጭፍሮቻቸው በዝሙት፣ በሌብነት የታህድሶ እምነት እራጋቢነት የፅዱ ንፁህ አባቶች ናችው።ይሄን የእለቃችውን ጉድ ግድፈት ሊነገራችው የሚገባችው ናችው በየትኞው የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ደንብና ስርአት ነው አንድ ተራ መለኩሴ ነኝ ባይ የቤተክርስቲያን፣የህዝብ ገንዘብ እየዘረፈ ሀገር ቤት የተለያዬ ህንፃዎች የሚገነባ።በየትኞው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህግና ቀኖና ነው አንድ የውጭ ሀገር ዜግነት ምሎና ተገዝቶ ዜጋ የሆነ ቄስ ውይም መነኩሴ ነኝ ባይ የኢትዬጵያ ኦርተዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትራያርክ ወይም ጳጳስ ሆኖ የሚሾመው።አባ መላኩ ተብይው ውንበዴ፣ ተኩላው አጭበርባር ታዲያ በሁለት ፓስፖርት። እያጭበረበረ እምነታችን ቤተክርስቲያን ህግና ደንብ ተጥሶና ተረግጦ አጭቤው፡ አሜሪካዊው መላኩ ጳጳስ ሆኖ ይሾማል?? ዳሩስ ማቲያስ ያው አይደል ።እነ አበይ ፅሐዬይ፣ስብሃት ነጋ።ይችን ጥንታዊት የተዋእዶ እምነታችን ሊይጠፍት እነ አሜርካዊው mr melaku ደንበኞ መሣሪያነት እየተጠቀሙባችው ነው።ተኩላው መላኩ በቅርቡ በእዚሁ ሀገርህን ክደህ ዜግነትን በተቀብልክብት አሜሪካን ህግ መስረት አስፈላጊውን ፍርድ እንደሚፈረድብህ የተረጋገጠ ነው የጅህን ይክፈልህ የዲስዋን ማሪያም ለወያኔ አሳልፈህ ልትሽጠት እንደዚህ እንደበጠበጥካት የአንተ ጭንቅላት በቅርቡ ይበጠበጣል።shame on u የውሽት ጳጳስ።

  14. If you claim to be a Christian you need to control your tounge. You must know another aba Melaku than the hopeful knows. We are talking about the one that had robbed DC St. Michael and bought 2 houses worth $2 million dollars each in Ethiopia and is back for the second round robbery. Not only that he and his recruites plundering the churches under him but they are also extending their tentacles into the independent churches as well as the churches under the legal synod. As the writer rightfully stated, those that are deceitful and spreading lies and false teachings in the name of the Lord, they will pay dearly both in this life and in the next. They are doing saitan’s work spreading a different kind of gospel leading astray the sheep they’re supposed to shepherd. The writer is right, their days are numbered, maybe they all need to visit the inside of America’s jails, they might learn a thing or two.

  15. እኔ ያልገባኝ ለዚህ ፅሁፍ አላፊነት የሚወስደው ማን ነው ? ሌላው ቤተክርስቲያኑን ከሰዋል የሚባሉት የክሱ ሂደት እየታየ ያለው እዚያው ናሽቪል ቴነሲ ነው። ታዲያ አባ ፋኑኤል ለምንድነው በዋሺንግተን ዲሲ ፍርድ ቤት የሚቀርቡት? የክሱ ጉዳይ የናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድኀኒዓለም ቤተክርስትያን ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ መግባት ከሆነ?

  16. ይገረም የሞኝ ጥያቄ ነው የምትጠይቀው መልሱን አንተው መልሰው ጉዳዩ ለምን ዲሲ መጣ ለምን ሰው ሰማው ከሆነ አርፍደሃል መጀመርያ አርፎ መቀመጥ ነበር የትም ሆነ የትም አይቀሬ ነው ሲከስ ሲያስደበድብ በማንአለብኝንት ሃገር ሲጥስ በሁለት ፓስፓርት ሲየጭበረብር የነበረ ዛሬ ተራው የሱ ሆነ ከፈለግህ የቀጠሮው ቀን እዛው ሄደህ መጠየቅ መብትህ ነው ባለጉዳዩም ዲሲ እንዳይሆንበት ሁለት ወር ታግሎ አልተሳካለትም

  17. Ato Yegerem halafinetun ante betewesedes mini yemselehal. hege metasu sayasasebeh sele sehufu halafi mawek felege sehafiwuma ye ageru yewegenu yehayemanotu huneta ye mikorekurewu tiru kirestiyan newu. legizewu gin des endileh halafi endethon fekdenlihal des yebeleh.

  18. 1. HagosAbreha says:
    April 5, 2016 at 8:21 pm
    Negussu Motoma says:
    April 5, 2016 at 8:13 pm
    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 8 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ላለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። አበው እንደሚሉት ይቺን የመከራ ጊዜ ካለፈን ኢትዬጰያዊ መሆን እንደ ሎተሪ የሚታይበት ቀን በቅርቡ ይደርሳል። የአገር ውስጥ ኦርሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። የተደራጅው ንኡስ ኮር በወልቃይት፣ በትግራይ፣ በሐረ ር ፣ በአምቦ እና በመተከል ኮሩን ዘርግቶ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል። ሕዝባችን አየሞተ ነው በኢሕአዴግ አጋዚ እና በረሐብ እርዳታ የሚሰጠው ቅድሚያ ለሆዳሞች ብቻ ከዚያ በሚድያቸው ረዥሙን ይሉኝታ የሌለውን ምላስ ይለቁብናል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ እኛ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ከታች ያለውን አብዛኛውን ፈሸካው ሲነፈ የአገር ግዴታ የሚሰሩትን አዘጋጅተን ጨርሰናል። ለምሳሌ በመተማ የሰፈረውን ጦር እንደቋንቋው መረጃውን አግኝቶ ከወገኔ ጋር ብሎ ኢትዬጰያዊነቱን አስቀድሞ በተጠንቀቅ ይጠብቃል። የጦር መሪዎች ስንት የሰረቁት ዶላር አስቀምጠው ጦር ሜዳአይሞክሩትም።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን ከዘር ነፃ የሆነ ተራማጅ አትዬጰያን የሚያሰቀድም በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣሉ።
    እኛ አሁን ለወሬ እና ለዘር ፓለቲካ ጊዜ የለንም የፈለገ መሪ በቋሚ ሰርአትን ተከትሉ እኩል ማስተዳደር የሚችል ብቻ ነው የምንፈልገው ከዚህ ውጭ የሆናችሁ የራሳችሁን ሙያ ቀጥሉ እንጂ የማይሁን ቃላት አቁሙ እና ተራማጅ የለውጥ ሐዋሪያዎችን እንድትደግፍ እናሳስባለን።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የ አክሱም ትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ሌሎችን ጳጳሳት ጉባኤ በማግለል ከገንዘብ አፍቃሪ ተሐድሶዎች ጋር በመሆን የውሸት ተቦት አስቀምጠው፣ ትክክለኛውን ለመሸጥ ውሉን ጨርሰዎል ከዚህ ቀን ጀምሮ አቡነ ማቲያስ እንቅልፍ የላቸውም፣ የሚሰሩትን ምንም አያቁም። የግፍ ወንበር በተራው እንደዚህ ያረጋል።
    4ኛ አቡነ መርቆርዮስ በሕገ ወንበር ላይ ስላሉ፣ የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን አንድነት ቡራኬ እና ጥሪ እንዲያደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን። ይህንን ስንል የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል ማለታችን ነው!!!
    የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር እንወጠዋለን። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ አምቦ ኮር
    [Reply]
    Reply
    2. አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:22 pm
    አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:02 pm
    ጀግኖች ናቹ የሚያሳዝነው ነገር እንደ ተባለውእንደ አህያዋ በድን ሆኖ ስለ አገሩ ቅንጣት እንኳን የማይሰማው
    ብዞች አሉ። በስደቱ አለም ላይ የተዋረደውን ኢትዮጵያዊ አስቡት። ነገ ጠዋት በፍቅር የምንሰባሰበት አገር አለችኝ ግን እኔ ይህንን የጥላቻ አጥር ልበጣጥሰውብለን ዛሬ እርምጃ መወሰድ አለብን። የትም አገር በስደት ያለህው አገርህን እንዳይረሳ። በቅርብ ቀን ኢሐዲጎች በእራት ላይ ተሰባስበው እኛ በየጨቅጣጫው 25 አመት ሙሉ የሐይማኖት ታጋይ አንበሶች ኮራንባችሁ አንድም ቀን መንግሥትን አላወገዛሁም። በቁመና እያላችሁ ይችን ሸልማትአዘገጅተናላችሃለን ብለው ጠቅልለው አንድ አንድ ሽጉጥ አርገው አቦይ ስብሐት፣አባዬች ሆነው ሸለሟቸው። እንዲያውም የሉት በስተመጨረሻ የሚያስደስት ነገር ስላጣን ነው ይህንን ያበረከትናችሁ። የ25 አመት ታሪካችን ቀድመን ከሲቪል ኮሌጅ ለሲኦል የሚሆን ስለሆነ እወቁት ግን አሁን በእስር ቤት ያሉትን ጨካኝ ገራፈዎችን የዘን አንሄድም እዛው ያለው የሱዳኑ ጋኔን ይሻለናሉ አሉ እየሳቁ። አሰቡት እናንተ ስላላቹ ኦርቶዶክስ፣መስሊሙን ልናጣላ ሙከራን አልሆነም ግን ሰሰነጣጥቅናቸው። እና ፓስተር ዳንኤልን ሱቃችሁን አብዝታቹ ወንጌልና ትታዘቹ ይህንን ግራ የገባውን ህዝብ ቢዚይ አርፋችሁ ቸርቹ ውስጥ ታስረግጡታላችሁ አሉን ። እነዚህ ናቸው እንግዲ የአገር እና ሐይማኖትን መሪዎች። አይ 8ኛ ሺየመጨረሻ ሰአት።
    [Reply]
    [Reply]

  19. Bemegemerya tehufeshene astekakye seketele astesasebesh hulu haymanotawe aydelem sedeb keseytane selhone kezawe new yememedebesh

  20. የፍርድ ቤት ወረቀቱን አየነው ግን ተከሳሽ የሚለው ላይ ያለው ስም የቤ/ኑ ስም ነው። እናም እስኪህ ግልፅ አድርጉልን ። ከሳሽ ማነው? ጳጳሱ ምን ለማስረዳት ነው የተጠሩት?

  21. Geremew,

    ፍርድ ቤቱ የሚያሳየው የቤተክርስቲያኑን ስም ነው። ነገር ጉዳዩን ምርመራ ለማድረግ አቡነ ፋኑኤል የእምነት ክደት ቃላቸውን መስጠት አለባቸው። የሚቀጥለውን ብታነብ የበለጠ ግልፅ ይሆናል።

    http://www.mereja.com/amharic/491154

  22. ምድረ ወረኆ ተሀድሳ ብቻ ለምን የእራሳች የሆነ እዳራቭ እትሄድም ቤተክርስቲያን እንድሆን የእግዚአብሔር ምድሪ እንጅ የፕለትካ እይደለችም ሁናም እታውቅም።

  23. አሁን ይሔ ሁሉ መነታረክ ምንም አያመጣም እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ሠው በመወንጀል ምንም አታመጡም እግዚአብሔር። ጊዜ አለው ለሁሉም። ወይ እናንተ ግቡና ወይ ስልጣኑን ያዙ ፀቡ ከእግዚአብሔር ጋር ነው በለፈለፍችሁበት ምላስ ፍርድ እንዳይጠብቃችሁ አሁን ስላለው ስለሐገራችን የድርቅ ሁኔታ ስለሕዝባችን ብናስብ እኛ ከጠገብን ነው እባካችሁ ከልባችሁ ሁኑ

  24. አንዳንዴ የናሽቪል ደብረ ቀራኒዮ መድኃኔዓለም የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ሁኔታ ሳስበው በጣም ይገርመኛል።አስመሳይ እንጂ እውነቱን ለእምነቱ የሚናገር የቁርጥ ቀን ሊገኝባት አልቻለም። ዝምታን የመረጡ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜና ሰዓት ይናገር ብለው እውነቱን እቅፈው የተቀመጡ በርካታዎች እያሉባት ቤተክርስቲያኑ የወንበዴዎችና የፖለቲከኞች መጨፈሪያ ሆኖ ማየት እንዴት ይከብዳል? በናሽቪል ደ/ቀ/ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ለሰሚ በሚከብዱ ሁኔታ ከቤተክርስቲያናችን ስርዓትና ትውፊት ውጭ ከቤተመቅደሱ ስንከታተል ኖረናል። ከነዚህም በጥቂቱ፦ ሲጀመር ስርዓተ ቤተክርስቲያን ይጠበቅ ብለው የተነሱትን ወጣቶች ፖለቲካዊ ስም በመስጠት አንዴ ወያኔዎች ሲሻቸውም ማህበረ ቅዱሳን በማለት ሐይማኖታዊ ጥያቄዎቻቸውን ሳያስተናግዱቸው ለመለያየት በቅተዋል። ደብሩ ካህናትንም ቢሆን በተደጋጋሚ ከቤተክርስቲያኗ ስርዓት ውጭ በግለሰብ ሲያባሩ በተደጋጋሚ እማኝ ለመሆን ችለናል። እንዲሁም ቤተክርስቲያኑ በተለያዩ ጊዜ በተለያዩ ግለሰቦች የግል ጥቅም መነካት በሚደርስባቸው ጊዜ ለተለያዩ ችግሮችና ጭቅጭቅ ሲዳረግ ማየት ሳምንታዊ ተግባር ከሆነ ውሎ አድሯል። ሲያሻቸው የግል ጥቅማችን ተነካ በማለት እርስ በእርስ መካሰስ ሲብስባቸው ደግሞ ቅድስት ቤተክርስቲያንን መክሰስ በዚሁ ቤተክርስቲያን የተለመደ ነው። አሁን ደግሞ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ፍርድ ቤት ማቆም ምን የሚሉት እብደት ነው? ሲጀመር በጣት የሚቆጡሩ ግለሰቦች ጥሩም ይስሩ መጥፎ ጳጳሱን ፍርድ ቤት ማቆም ባልተገባ ነበር። ምክንያታቸውም በጣም የሚያሳዝን ነው ቤተክርስቲያናችንን ወደ እናት ቤተክርስቲያን ወይም ቅዱስ ሲኖዶስ አስገብቷል። የወያኔ ተላላኪ ናቸው በሚል መላምትና ቅዥት ይህ ሁላ ጩአትና ስድብ በአደባባይ አስፈላጊ አልነበረም። ይህ ስድብና ጩአት ግራ ለገባቸውም ፖለቲከኞቻችንም አልበጃቸውም። በየጊዜው እንደ ውሻ በየዳባባዩ ከመጮህና ደግሞ ጀመራቸው ከመባል ውጭ የትኛውም ተቋም ጩአታቸውን ሲሰማ አለየንም። ዛሬ ደግሞ የሐይማኖት አባቶች ላይ ይህን ያህል ስድብና ማጉላላት ማድረስ ካላዋቂነት የመጣ ሰይጣናዊ ስልጠና ካልሆነ በቀር ለቤተክርስቲያን ከማሰብ እንዳልሆነ እሊናችሁ ይነግራችኋል። በእርግጥ በትክክል የሚያስብ እሊና ካለው ሰው ይህ አይጠበቅም።ወደድንም ጠላንም የክርስቶስን መስቀል እስከያዙት ድረስ ያዋረድናቸውና የሰደብናቸው ቢመስለንም ለእሳቸው ግን ክብራቸው ነው። እንኳን አንድ ካህን(ጳጳስ) ይቅርና ባለቤቱንስ ቢሆን ልባቸው በገንዘብና በጥቅም የደነደነው መቼ አምላክነቱን በውል ተቀበሉት??? ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ ይህ የናሽቪል ደብረ ቀራኒዮ መድኃኔአለም ቤ/ክ ችግሩ ዘርፈ ብዙ ነው። ከመንፈሳዊና ስርዓተ ቤተክርስቲያን አካሄድ ይልቅ ወደ “social አገልግሎት” የሚያደላ አካሄድ ይታይበታል። አገልጋይ ካህናቱም ቢሆኑ እውነትን ከማስተማርና ቤተክርስቲያኑን ወደ ስርዓት ከመመለስ ይልቅ የግል ጥቅማቸውን የሚያስከብሩ የሚኖሩ ናቸው። ቀደም ብለው የነበሩት ካህን የሰንበት ት/ቤቱ አባላት የቤተክርስቲያን ስርዓት ይጠበቅ ብለው ላነሱት ጥያቄ እንኳን ሰሚ አጥተው ከቤተክርስቲያኑ ሲቀሩ ምንም አላሉም እንዳውም ተመልሰው ከመጡ አብሬያቸው መስራት አልችልም ከማለት በስተቀር። ለጊዜው የተመቻቸው ቢመስላቸውም በኃላ ግን በግለሰብ ተባረው ወጥተዋል። ብዙም ሳይቆዩ በሳቸው ቦታ የተተኩትም ካህን ቢሆኑም ተመሳሳይ ጽዋ ነው የተጎነጩት የሰሩበትንም አገልግሎት እስከመከልከል ደርሰው ነበር። እንግዲህ የቀደመውን ታሪክ እንኳን ባንመለከት በዚህቺ 2 ና 3 አመታት 2 ካህናትን ያባረሩ ጃግና ቦርድ ያለው ቤተክርስቲያን ነው ማለት ነው። አሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉት ካህናትም (በተደጋጋሚ የሚሞገሱት) ካህን እጣ መቸ እንዳሚባረሩ ባይታወቅም የሚጠብቃቸው ግን ከቀደሙት ካህናት ውጭ የተለየ ነገር አይኖርም። ቤተክርስቲያኑን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እናስገባለን በማለት ብዙ “ፕትሽን” ያሰባሰቡ ቢሆንም በቃል ከማውራት ይልቅ በተግባር በትክክል ሲፈጸም ግን አለየንም። አሁንም ቢሆን ቤተክርስቲያኑን የሚያስተዳድረው ጀግና የቦርድ ሰራዊት ነው። ለዛውም ሶስት(3) ካህናትን በማባረር የሚታወቀው። እንግዲህ ይህ ነው በእናት ቤተክርስቲያን ስር ገብቷል የሚባለው። የታየው ለውጥ የሚመሰገንና አሰየው የሚያስብ ሆኖ ሳለ ፍጻሜ ማግኘት ግን ነበረበት። ካህናቱን ጥቅማቸው እስካልተነካ ድረስ ስርዓቱን በግልጽ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ። እግዚአብሔር ፈቅዶ ቤተክርስቲያኑ በስርዓትና ኦርቶዶክሳዊ በጠበቀ መልኩ ሆኖ እንዲናኝ የሁላችንም ምኞት ነው። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት ናት እንጂ በአንድ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አዋጥቼ ስለነበር እኔ እንደፈለኩኝ ትሁንልኝ ማለት አግባብ አይደለም። ለቤተክርስቲያን ያደረግነው ሆነ እያደረግን ያለው መዋጮም ሆነ ስጦታ የምንጠይቀው በሰማይ ቤት እንጂ በምድር አይደለም። እንዴ እስከሰጠን ድረስ ደግመን ማስታወስም አይጠበቅብንም። በማይረሳ መዝገብ አንዴ ተጽፏልና። በናሽቪል የሚታየውም የዚህ ችግር ነው። ሰዎች ቤተክርስቲያን የራሴ ናት፤ እንደ አክሲዮንም ይመለከቷቷል። ለዚህም ነው በየሳምንቱ የገላጋይ የበዛበት። ያ ባይሄንማ ኖሮ ትላንት አንድ ቤተክርስቲያን የነበረው ዛሬ 3 ቤተክርስቲያን ደርሷል። ቤተክርስቲያን ተሽጣ ወይም ድርሻዬ ይሰጠኝ ከማለት ይልቅ ወደ ፈለጉት ሄደው መገልገል እያቻሉ ለሰው ፈተና ባልሆኑ ነበር። ሲያሻቸው ጸብና አተካራ መፍጠር አሊያም ፍርድ ቤት መመላለስ የነዚሁ ሰዎች መለያ ሆኗል። በመጨረሻም እነዚህ ሰዎች በብዛትም ብዙ አይደላችሁም በደንም እናውቃችኃለን ሲሆን ወደ ልባችሁ ተመለሱ። ካልሆነም ግን ምንም በማታመጡት ነገር ላይ የራችሁንም ሆነ የሌላውም ሰው ጊዜና ገንዘብ ለበላተኛ ከመስጠት ተቆጠቡ። አጉል ፖለቲከኛ በመሆን ቤተክርስቲያኗን ሰድባችሁ ለተሳዳቢዎች አትስጧት። በግላችሁ የፈለጋችሁትን ፓሪቲም ሆነ መንግስት መደገፍም ሆነ መቃወም መብታችሁን ወደ ቤተክርስቲያን እያመጣችሁ ግራ ገብቷችሁ ሌላውንም ግራ አታጋቡት። ሁሉም በቦታው ያምራልና በቦታው ይከበር። ይህ ጉዳይ ቢሆንም አሰየው የሚያስብል እንጂ ፍርድ የሚያስቆማቸው ጉዳይ ባልሆነ ነበር። እናነተ ጥቂቶቹ እንደምትቃወሙት ብዙአኑ ደግሞ ይህን ጉዳይ በደስታ ተቀብለውታልና በልዩነት ተስማምታችው መቀበል ካልሆነም ግን ከቀደሙት ሰንበት ት/ቤት አባላት ብዙ መማር አለባችሁ። እንዚህ ወጣቶች ስርዓት ይጠበቅ ብለው ጠየቁ ሰሚ አጡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ወጡ። ይህ ይሰጠን ድርሻችን ይገባናል አላሉም እስከዛሬም ቢሆን የተሰማ ነገር የለም። ወይስ እናነተ ትከፍሉ የነበረው ገንዘብ የተለየ ሆኖ ነው???? ስለዚህ እንደ ነቀዝ ከመሆን እንቆጠብ ነቀዝ ከእህሉ ጋር እየኖረ እህሉን ቦርቡሮ ይበለዋል። ዛሬም እየታየ ያለው ይህ ነው። በመጨረሻም የቤተክርስቲያኑ አባላት ምዕመናት እንዲሁም አገልጋይ ካህናት እውነቱን ለመቀበል ተነሱ። ተመሳስሎ መኖር ይብቃ። ቤተክርስቲያኑንም ስርዓት ባለው መልኩ ይመራ ምንድነው ሞቅ በረድ ዛላቂነት የለውምና ወድ ሲኖዶስ ከገባችሁ ሁሉም ነገር በስርዓቱ ይሁን ቦርድና ሰበካ ጉባኤ አብሮ አይሄዱም። ቦርድ የሚባል ነገር የቤተክርስቲያን ደንቃራ አስወግዱ። ካህናቱ ከግል ጥቅማችሁ ይልቅ ቤተክርስቲያኗን አስቀድሙ። ብዙ አለፊነት ይጠበቅባችሃልና መንፈሳዊውንና ማህበራዊው ሕይወት የተደበላለቀበትን ሕዝብ በማስተማር ልዩነቱንና እንዴት አብሮ ማስኬድ እንደሚቻል አስተምሯቸው። ያኔ ስርዓቱን የጠበቀ እምልኮ ምን እንደሆነ ይረዳል። ቤተክርስቲያኑንም አጥብቆ ይወዳል። ኦርቶዶክሳዊ ስርዓት ከዘርና ከፖለቲካ የጸዳ መሆኑን ይረዳል። ይህ ነው ከሕዝባችን የራቀው የቤተክርስቲያን ስርዓት ይጠበቅ ሲባል ከእውቀት ማነስ የመጠ ሊባሉ ያልተገቡትን የተለያዩ ስሞችን በመስጠት ግራ የተጋባው። የዚህን ልዩነት ስንረዳ በሐይማኖት መኖር እንጀምራለን። እግዚአብሔር ለከተማችን ሰላሙን ያምጣልን። ቅድስት ቤተክርስቲያናችንንም ከፈታናው ሁሉ ይጠብቅልን። ይቆየን።

  25. እንካን እይደልም $35000 ዶላር ይቅርና ግና ለመድንይልም ከዝህ በላይ እና ውጣለን። ምን እይታች ገና እናንተ ዝም ብላችሁ እትቀ ባጥሩ ሁልንም ነግር እኝ ምእመናን እናውቃለን ። ነግር ግን ለቤትተክርሱትይናችን ደህናንት ስንል እስከ ዝሬ ደረስ ዝም ብለናል እሁን ግን ዝምታው ይስብርል ። እሶከዝሬም ትመለሳላችሁ ብለን ነው። ረጅም እድሜ ለእባቱችችን እና የግልግሉት ዘመን ይጥልን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*