በአማራ ክልል ወልቃይትና ዳንሻ ህዝቡ ሀይለኛ ውጥረት ላይ ይገኛል። አባቶች ክተት አውጀዋል
በአማራ ክልል ወልቃይትና ዳንሻ ህዝቡ ሀይለኛ ውጥረት ላይ ይገኛል። አባቶች ክተት አውጀዋል
#Ethiopia #Welkaite #Tigray #Dansha #MinilikSalsawi #RDH
በወልቃይት የተነሳው የመሬት እና የማንነት ጥያቄ እንደተካረር ይገኛል ከተመረጡት ሽማግሌዎች 1 ተገድለው ጥለውት የተገኘ ሲሆን 1 ሽማግሌ ያለበት አልታወቀም።የሰሮቋ አርማጭሆ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል ። በሺህ በሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮች ለእርዳታ እየተመሙ ነው !!
የዳንሻው ጉዳይ ከተሰማ በውሃላ የአብድራፊ አባቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ማርዘነብ የተባለች ቦታ ላይ ተሰብስበው ክተት አውጀዋል ከተማዋም እጅግ አስፈሪ ድባብ ላይ ነው።ምንም እንኩዋን ነገሩ በሽምግልና የተያዘ ቢሆንም ከአካባቢው የሚወጡት መረጃ እንደሚያመላክተው በወልቃይት የመሬት አለመግባባት ከተመረጡት ሽማግሌዎች 1 ሰው ገድለው ጥለውት የተገኘ ሲሆን 1 ሽማግሌ ያለበት አልታወቀም በዚሁ ጉዳይ በወልቃይትና በዳሻ ህዝቡ ሀይለኛ ውጥረት ላይ ይገኛል።
በዚሁ ጎዳይ አንድ የትግሬ አቀንቃኝ የዳሻ ወረዳ ፓሊስ የተገደለ እና መንገዶች ተዘጋግተዋል ትላትና ዛሬ ማለት መጋቢት 11እና12 መንገዱ እንደተዘጋ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል ።