የተስፋሁን አለምነህ ጉዳይ እኔም ያሳስበኛል (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የተስፋሁን አለምነህ ጉዳይ እኔም ያሳስበኛል (ኤርሚያስ ቶኩማ) ተስፋሁን በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ብቅ ካሉ ጠንካራ ወጣት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነው። ተስፋሁን በይፋ ፖለቲካዊ ድርጅት ውስጥ ገብቶ መታገል የጀመረው በ1996 አመተ ምህረት ገና በለጋ እድሜው በመኢአድ ፓርቲ ነው።

በመኢአድ ውስጥም በቆየባቸው ድፍን አሥራ አንድ አመታት የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን ጅምር ሥራ ከዳር ለማድረስ ሲታሰር እና ሲገረፍ የነበረ ነው በኋላም በሰላማዊ ትግል ላይ የነበረው እምነት በመሟጠጡ ምክንያት ወደኤርትራ በረሃ ወርዶ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሐይሎች ንቅናቄን መቀላቀሉን በፌስቡክ መልእክት ሲልክልኝ በጣም መደንገጤን እና እንደተገረምኩኝ አጫውቼው ነበር የመገረሜ ምክንያት ሰምቼው የማላውቀው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሐይሎች ንቅናቄ የሚባል መኖሩ ሲሆን ድንጋጤዬ ደግሞ ሻእቢያን ስለማላምን ነው።

ተስፋሁን ጋር የነበረን ግንኙነት ከህዳር አካባቢ ጀምሮ ተቋርጧል ሆኖም ያን ያህል አላሳሰበኝም ነበር ምክንያቱም ኤርትራ የገባው ሊታገል እንጂ ከእኔ ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ሊያወራ አይደለም ሆኖም በቅርቡ እየሰማሁት ያለው ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነው። አንዳንዶቹ ተስፋሁን ኤርትራ የሚደረገው ትግል እንደጠበቀው ስላልሆነለት ጥሎ ለመውጣት ሲሞክር ተይዞ በሻእቢያ ወታደሮች ተረሽኗል ሲሉ የተቀሩት ደግሞ ይሄ አሉባልታ ነው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ይላሉ። እኔ ሁለተኛው ቡድን የሚለው እውነት እንዲሆን እመኛለሁ ያ ሳይሆን ቀርቶ ግን እንደተባለው ተስፋሁን ላይ ጥቃት ከተፈፀመበት ወይም ከታሰረ በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ያለውን ትግል የሚጎዳ ይሆናል ምክንያቱም ዛሬ በረሃ ወርደው የትጥቅ ትግል ታጋዮችን መቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶችን ቅስም የሚሰብር ከመሆኑም በላይ ድሮም በቋፍ ላይ የነበረው ኢትዮጵያውያን ለኢሳያስና ለሻእቢያ ያላቸው ጥቂት እምነት ገደል የሚገባ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ በኤርትራ በሚገኙ ፖለቲካዊ ቡድኖች ላይ የሚደርሰው ፖለቲካዊ ኪሣራ ከፍተኛ ይሆናል። የተስፋሁን ጉዳይ አሁን የጥቂቶች መነጋገሪያ መሆኑ አብቅቶ አሁን በርካቶች በአደባባይ የሚያወሩት የአደባባይ ወሬ ሆኗል።

የተስፋሁን ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው ደግሞ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሐይሎች ንቅናቄ የተሰኘው ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት እውነት እንደተባለው በሕይወት ያለ ድርጅት ከሆነ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ መልስ ሊሰጠን ይገባል። 1, ተስፋሁን አለምነህ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? 2, ተስፋሁን አለምነህ እንደተባለው ተረሽኖ ከሆነ በምን ጥፋት ተረሸነ? የረሸነውስ አካል ማነው? 3, ድርጅቱ እስካሁን በተስፋሁን ጉዳይ ላይ ስለምን ዝምታን መረጠ? እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ጥያቄዎች የእኔ ጥያቄ ብቻ አይደለም የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። ተስፋሁን አለምነህ ኤርትራ የገባው ሊታገል እንጂ በሻእቢያ ሊረሸን አይደለም በመሆኑም የተስፋሁን ጉዳይ ያገባኛል። የተስፋሁን ጉዳይ ያገባኛል ስል ተስፋሁን ጓደኛዬ ስለሆነ አይደለም የዚህ ትውልድ ቀንዲል ስለሆነ እንጂ። #ኤርሚያስ_ቶኩማ

6 Comments on “የተስፋሁን አለምነህ ጉዳይ እኔም ያሳስበኛል (ኤርሚያስ ቶኩማ)”

  1. Shabia shiba new. Bederg wedemeceresha yewsT dkmet enj neTa balwoTa neber.
    Jegnochachin eritrea hidew min belachew minm mitay wgiya yelem.
    NeTa mawTatu qerto dehna yhunu.

  2. Ato Ermias Tokuma You are quietly smelling the smell of woyane bandits.2he armed strugle to destroy woyane is stepd up day to day and that is why the new generation the dynmic of the society have fled Eritrea to join and are joining the patriots front So,your article based on Tesfahun Alemneh is completly sensless,he has left his family,his people lnorder to fight your masters tplf and he is doing on. But shame on you no one could stop the struggle it is on and on:

  3. @gilentufa what is the proplem with you.that is nothing with woyane.he was asked about his frind.one thing if you are a man go to eritrea.nothing to change in internet.ethiopian le mesadeb andena le sira zero.ygermal ethiopia agere.

  4. I agree with @gilentufa, this is the new strategy of woyane. We will destroy woyane with our Eretrian brothers. No one support woyane except Devil himself.

  5. እኔ የሚገርመኝ እነዛ ኢሳት የሚባሉት አሁንማ ተስፋ አስቆረጡኝ ገንዘብ አዋጡ ለማለት የሚቀድማቸው የለም ስለተስፋሁን የአንድ ደቂቃ ዜና ለመሥራት ግን ፍቃደኛ አልሆኑም።
    ኤርምያስ አንተ ይህንን በመፃፍህ አመሰግናለሁ ሊሰድቡህ ይችላሉ ተስፋሁንን እንኳን ገድለውት የለ።
    አሁን ማወቅ ያለብን ወያኔም ሆኑ ሻእቢያ ሁለቱም የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው።

  6. እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል። በርግጠኝነት ማንኛውም ወያኔ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ በማንኛውም አካል በምንም መንገድ የሚካሄድ ፀረ-ወያኔ ትግል እንዲጐለብት እንዲስፋፋ እንዲጠናከር ይፈልጋል። የተስፋሁን ዜና ከወያኔም መጣ ከሌላ፤ ለወሬ አነፍንፈው የሚገኙት ሚዲያዎቻችን ውሸት ነው ብለው ቢያስደስቱን ምንኛ ደስ ባለን ነበር። ለነገሩ አብዛኛዎቹ ሚዲያዎቻችን እኛው ፌስቡክ ላይ የፃፍነውን ሰበር ዜና እያሉ ይነግሩናል እንጂ የተጠናከረ የመረጃ መረብ እንደሌላቸው በተደጋጋሚ አይተነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*