ያልተነገረው የራስ አሉላ ታሪክ – Achamyeleh Tamiru

Achamyeleh Tamiru   ያልተነገረው የራስ አሉላ ታሪክ

ዳግማዊ አጼ ምኒልክን በአገር ሻጭነት የሚወነጅሉ ድርሳናትን በማሳተም ረገድ የትግራይ ብሔርተኞችን የሚስተካከላቸው የለም። መረን የለቀቀው ይህ ጸረ-ምኒልክ ዘመቻቸው ዳግማዊ ምኒልክ በአለም መድረክ የተደነቁበትን የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል የሆነውን የአድዋ ድልም እስከማጥቆር ይዘልቃል።

የጸረ ምኒልክ ፕሮግራማቸው ዋነኛ አላማ በምኒልክ ታሪክ ግብዓተ መሬት ላይ እነሱ «የትግራይ ናቸው» የሚሏቸውን ሰዎች ታሪክ መጻፍ ነው። ይህ ፕሮግራማቸው ጊዜ በሰጣቸው ሀይል እየተስፈነጠረ «ታሪክን እንደገና መጸፍ አለብን» በሚለው የጋራ ፕሮጀክታቸው ታግዞ ከቃል በማለፍ «የአድዋ ድል በትግራይ ህዝብ ተጋድሎ የተገኘ ነው» በሚል «አዲስ ትርክት» ወደ ተግባር ተሸጋግሮ ተመልክተናል።

«አፍሪካዊ ጀኔራል» በሚል ስም ሁላችንም የምንጠራቸው ራስ አሉላ አባ ነጋ በትግራይ ብሔርተኞች ዘንድ የምኒልክን ክብር እንዲወርሱ ከታጩት የጦር መሪዎች መካከል ቀዳሚው ናቸው።

ራስ አሉላ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ አካካቢ የነበረው የፖለቲካ መንፈስ ውጤት ናቸው። በዘመናቸው ለኢትዮጵያ አገራቸውና ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲሉ በጀግንነት ተጋድለዋል። እስከ ዛሬ ድረስ ስለራስ አሉላ ስንሰማ የኖርነው የበቃ የፖለቲካ ሰውነታቸውን ብቻ ነበር።

ሆኖም ግን ራስ አሉላ ከዘመኑ መንፈስ የመነጨ ጎደሎ ጎንም ነበራቸው። ምናልባት ይህንን ጎደሎ ጎናቸውን እስከዛሬ አልሰማነው ይሆናል። እኔ ዛሬ ይህንን ሰምተነው የማናውቀውን የራስ አሉላን ጎደሎ የማቀርበው የአሉላን ክብር ለማጉደል አይደለም። በፍጹም! አሉላ ኢትዮጵያዊ ጀግና ናቸው።

ሆኖም ግን ዛሬ አጼ ምኒልክን «በአገር ሻጭነትና በከሀዲነት» ተግባሮች ለሚከሷቸው የትግራይ ብሔርተኞች፤ «የአድዋን ድል መርተዋል» ብለው አዲስ ታሪክ የሚጽፉላቸው ራስ አሉላም በዘመናቸው ከአጼ ምኒልክ በላይ «በአገር ሻጭነትና በከሀዲነት» ጭቃ ውስጥ ሰጥመው እንደነበረ ማሳወቅ ያስፈልጋል።

Achamyeleh Tamiru's photo.

ይህንን ታሪክ የሚነግሩን እሥራኤላዊው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊክ ናቸው። የአሉላ አድናቂ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊክ «Ras Alula and the Scramble for Africa: A Political Biography : Ethiopia & Eritrea 1875-1897» በሚል ርዕስ የራስ አሉላን ደብዳቤዎች ከጥሊያን ቤተ መዘክር ሰብስበው በጻፉት የታሪክ መጽሀፋቸው ውስጥ ራስ አሉላ ከጥሊያኖች ጋር «ምኒልክ እ.ኤ.አ. በ ግንቦት 2፥1889 አ.ም. ውጫሌ ላይ ከናንተ ጋር ተፈራርሞ ሊሰጣችሁ ከተስማማው መሬት በላይ የሚልቅ አገር እኔ ልስጣችሁ» ብለው ተስማምተው እንደነበር ዶሴዎችን በአስረጂነት በማቀረብ የራስ ኣሉላ ሌላ ገጽታ ያስነብቡናል።

በመጽሀፉ ላይ የሚገኘው ማስረጃ «ነጻ ትግራይን ለመመስረት» ጣሊያኖች የሚረዷቸው ከሆነ ራስ አሉላ ቀደም ብለው ያስተዳድሩት የነበረውን የመረብ ምላሽ ምድር [ የዛሬውን ኤርትራ] ሙሉ በሙሉ ለጥሊያን ለመስጠት ተስማምተው እንደነበር ይነግረናል ። ይህ ማለት ራስ አሉላ አባ ነጋ ምኒልክ በውጫሌ ውል ለጥሊያን አሳልፈው ለመስጠት ከተስማሙት መሬት የሚበልጥ አገር ለጥሊያን አሰልፈው ለመስጠት ዝግጁ ነበሩ ማለት ነው።

የአሉላ አድናቂው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊክ ይህንን ታሪክ ከታች በታተመው የመጽሀፋቸው ገጽ 164 ላይ ሲገልጹ፤

«The rebellious Alula urgently needed a practical alternative to Mengesha’s policy, and he thought in terms of Italian support for an autonomous Tigre. Ras Alula was prepared to give the Italians more than Menilek had given them in Wuchale; the whole of Marab Mellash, his previous one and only domain» ይሉናል።

በግርድፉ ይህ ሲተረጎም፤

« እምቢተኛው አሉላ ራስ መንገሻ የምኒልክን ንጉሰ ነገስትነት አምነው ለመቀበል ቁርጥ ማድረጋቸውን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሊተገብሩት የሚችሉት አማራጭ ፖሊሲ ፍለጋ ገቡ፤ ነጻ የትግሬ መንግስትም ለማቆም ሻቱ፤ ለተፈጻሙነቱም የጣሊያንን ድጋፍ ፈለጉ። ለዚህ አግቦ ምላሽም ምኒልክ በውጫሌ ስምምነት ለጥሊያን እንዲሰጡ ከተገደደዱት መሬት የሚልቅ አገር ለጣልያን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ ነበሩ፤ ይህ ራስ አሉላ ለጥሊያን አሳልፈው ሊሰጡ የተዘጋጁት መሬት አሉላ ራሳቸው በሕይወት ዘመናቸው እንዲያስተዳድሩ የተሾሙበት አንድና ብቸኛው ግዛታቸው የነበረችውን [በኋላ ኤርትራ የተባለችውን] መረብ ምላሽን ነው።»

እንግዲህ አጼ ምኒልክን «በአገር ሻጭነትና በከሀዲነት» ሲወነጅል የኖረ ሁሉ ዛሬም በቃሉ ጸንቶ ከአጼ ምኒልክ በላይ አገር አሳልፈው ሊሸጡ የተስማሙትን ራስ አሉላንም አንደበቱ ሳይታጠፍ ድምጹን ከፍ አድርጎ «ውግዝ ከመ አርዮስ አሉላ እንግዳ እቁቢ» ማለት አለበት።

የኔ እምነት ግን ወዲህ ነው። ራስ አሉላ ምንም እንኳ የውጫሌ ስምምነት ለጥሊያን እንዲሰጥ ከሚፈቅደው መሬት በላይ አሳልፈው መረብ ምላሽን በሙሉ ለጥሊያን ለመስጠት ከሁሉ አስቀድመው ተስማምተው የነበሩ ቢሆኑም፤ በዘመናቸው በቻሉት መጠን ላገራቸው ባደረጉት በጎ ተግባር ግን ለዘላለም በትውልድ ሁሉ ሲከበሩ ሊኖሩ ይገባል እላለሁ። የአጼ ምኒልክም ታሪክ መያዝ ያለበት በዚህ መንፈስ ነው። ከዚህ ውጭ አንዱን አጥቅቶ ለሌለኛው የመከላከል አካሄድ ዘረኝነት ብቻ ነው የሚሆነው።

15 Comments on “ያልተነገረው የራስ አሉላ ታሪክ – Achamyeleh Tamiru”

  1. ኣይ እናንተ የሆነ ያልሆነ የነጮች ጽሁፎችን ከማንበብ ገልብጦ ከመጻፍ የሰላምና የጉርብትና ያተኮረ ነገሮችን ብትፈልጉ መልካም ነው ነጭ ጥቅሙን ለመጠበቅ የሰዎችን ግጭት ማባባስ የየቀኑ ስራቸው ነው ነጮች እውነት ቢኖራቸው ኢራቅ ኣፍጋኒስታን ልብያ ባህሬን የመን ኣሁንም የኦሮሞ ህዝቦች ብሶት ሃቅን ተከትለው በጻፉ ነበር ስለዚ ኣይንን መክፈት ያስፈልጋል

  2. Yes all the habeshas ortodox killers like minilik,yowhans,alula and many are bandas of banda.you said minelik is hero bls he killes and invaded oromia.Do not trust the habesha ortodox killers.Habesha ortodox out of oromia.habesha means beggars,liers,killers.death to habeshas.

  3. ዋይ…ራሥ አሉላ ጀግና ሳይሆኑ ባንዳ ናቸው ይህን ውርሥ ይዘው ብቅ ያሉት ወያኔና ሻብያ የራሳቸውን ትግራይና ኤራትራ ሪፐብሊክን ከ95 አመት በሃላ ተግባራዊ አደረጉ አሁንም ቀሪ የአማራና የአፋርን መሬቶች በልማት ሥም እየተቀራመቱ ድንበርን በሥውር አጀንዳ እየሰፈሩ ያው እንደ አሉላ ያልተናነሰ የከፋ ሥራ እየሰሩ ናቸው።

  4. This is absolutely a lie you don’t understand the diplomacy of that time.alula wants to overthrow minilik he wants power to do so.so like Otto von bismark before fighting minilik he wants the backing of Italians.that is the essence of his true thought.but minilik is clearly banda who sold Eritrea for his thirst of power.dont full yourself.we never change our hate towards minilik by your grab article.minilik is a traitor whose history have to be dismantled period

  5. Aregawi berhe your traitor behavior will not be forgotten by the people of Tigrai you are sold out Banda who tries to harm his own people.you poisonous snake we will never forget what you did on our people .death for aregawi berhe,death for Gidey zeratsion,death for bandas

  6. ወያኔዎች ከታሪክ እድፋቸው ነጽኣ የሆኑ መስሎዋችው ምንም ማሰረጃ ሳይኖራችው በጀግነነት ያለፉ መሪዎችን ሲከሱ ይሰማል::ያለፉ መሪዎች የጎጥ በሽታ ሳይዛቸው ሃገር አቆይትውልን አልፈዋል::ራስ አሉላም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነት ከተጋደሉት ጀግኖች አንዱ ስለሆኑ ምንም ግዘእ ሃገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ውለታቸውን ሲያስታውስ ይኖራል::እውነተኝኣም ኢትዮጵያዊ ሰለሆኑም ነው በቅርቡ በግለሰብ የተሰራው ሃውልታቸው ሲመረቅ አንድም የወያኔ ባለስልጥኣን ያልተገኜው::
    ለመሆኑ ወያኔዎች ያለፉ መሪዎችን ሃገር ሸጥኡ ብሎ ለመክሰስ አፍ አላችው?ከሻቢያ ጎን ተሰልፈው ኢትዮጵያን ወግተው ያስገነጤሉ እነሱ አይደሉም?ስልጥኣን ከያዙም በሁላ ከማንም ሃገር በፊት የኢርትራን ነጽኣነት ያወቁ ወያኔዎች አይደሉም?ከዚህም በላይ ኢትዮጵያን ለመበታተንና ለብጥብጥ እንደ ፋሽሽት ጥኣልያን ኢትዮጵያን በጎሳ ፌደራሊዝም የከፋፈሉ መሆናው ይረሱታል?

  7. Selewedefit edget atasebuna be dero tarik lay tegeterachihu keru!! Yeh hulu Tigren lemastelat new? Min yehonal beleh new? Tigre alko ante komeh atehed! Yefelegehew metelalek new? beje!Kelal new eko. Memelesu yekebdal enji! Yet honeh new lemehonu yehen yemetetsefew? Ende drone tekuash buna eyetetah letawaga new aydel? Chinkelateh gin kezih belay maseb aychlm! Awo semeh achamyeleh! Le denkurena acha yelehm! Tornet bimeta kedmeh yemtesheshew ante neh!

  8. አለም የት በደረሰበት ሰአት በወያኔ ተረት ተረት አንደነቅ

  9. ወያኔ ባንዳዎች እንዲህ ስም እየቀያየሩ እንደቤት ውሻ የሚጮሁት መርከባቸው እየሰመጠች መሆኗን ስላወቁ ነው። ይህንን ሁሉ ህዝብ ጨርሰሽ እዛች ሀገር ውስጥ በሰላም እኖራለሁ ብለሽ አታስቢ። እያንዳንድሽ የእጅሽን ታገኛለሽ። እስከዛው አምባሻሽን በሁለት ጉንጭሽ ብዪ።

  10. The book titled “Adafne” By Professor Mesfin Woldemariam has explained on how Atse Yohannes gave the land to Italians well before the Wuchale treaty. In Addition, Atse Yohannes was in favor of Italians as he was against Ras Alula. By the time Italians control the highland of Eritrea.

  11. ኤርትራን ለጣሊያን የሸጠው ያ ሲሸሽ ጭንቅላቱን ለአረብ ያስረከበው ትግሬ ነው ። ለሁለተኛም ጊዜ የሻብያን ጫማ እየወለወለ ኤርትራን ያስረከበው የትግራይ ባንዳው ያ የበሰበስው ለሃጫም ባንዳ ትግሬ ነው። አልፋና ኦሜጋው እምዬ ምኒልክ አይደለም። ምኒሊክ ስድስት ወር ተጉዞ አድዋ ሲደርስ ያገኘው ትግሬ ሁሉ ለጣሊያን መቀመጫውን ሰጥቶ ነበርና ይህ በግዛቴ መፈፀም የለበትም ብሎ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ወደሸዋ የተመለሰ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም የጥቁር ህዝቦች ኮከብ ነው። ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሀበሻ

  12. Banda Minlke sold Ertirea to Italian ..mr nothing van do about fact .
    Banda Amarhar Minlke hodam Minlke for power .
    For him to become a king he sold Ethiopian Djibouti ports to French .
    The painful truth .
    Banda Naftnga Amahara Minlke.
    You who died for his country fighting king of kings Yohans!
    Long live ethiopia ,
    Death to Banda Minlke who sold ethiopia!
    Death to hodam Neftgna hodam Amhara .
    Death to shabia Listro Banda Berhanu nega.
    Death to Banda Essayass!
    Death to Banda Ertirea !

  13. MINILK IS A HERO OF ALL FREEDOM LOVING PROUD BLACK PEOPLE AROUND THE WORLD. HE IS A SYMBOL OF RESISTANCE TO WHITE DOMINATION AND COLONIZATION.HE BROUGHT SHAME UPON WHITE SUPERMACISTS AND COLONIZORS.BY THE WAY , WHEN IS THE TIGRES OF BAHIRENEGSH GOING TO CHANGE THE NAME ERITERIA WHICH IS GIVEN BY ITALIAN COLONIZERS TO SOMETHING HONORABLE?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*