የጆሮና የቀንድ ዘመን! ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
አንድ ጥጃ የሚያሳድግ ሰው ነበር፡፡ ጥጃውን ሲፈልግ ጆሮውን ይጎትተዋል፣ ሲፈልግ በዱላ ይዠልጠዋል፣ ሲፈልግ ጨው እያላሰ ይስበዋል፣ ሲፈልግ ደግሞ በገመድ አሥሮ ያስከትለዋል፡፡ በዚህ መንገድ ሄዶ ጥጃው አደገና ወይፈን ሆኖ ቀንድ አበቀለ፡፡ የጥጃውም ባለቤት እንደለመደው በዱላ ሊመታው፣ ጆሮውን ሊጎትተው፣ በዱላም ሊዠልጠው ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ጥጃው አፍንጫውን ወደ መሬት አስነክቶ አኩረፈረፈና እንደ ስፔን በሬ ተወርውሮ በቀንዱ ወጋው፡፡ ሰውየውም ወገቡን ይዞ እየተጎተተ ቤቱ ደረሰ፡፡
ታሞ ሊጠይቁት የሄዱ ጎረቤቱ፤ የሆነው ነገር ሰሙና፤ ‹ወዳጄ የጆሮና የቀንድን ዘመን እንዴት መለየት አቃተህ?› አሉት፡፡ ‹የጆሮና የቀንድ ዘመን ምንድን ነው?› አላቸው፤ ወገቡን አሥሮ እየተገላበጠ፡፡ ‹በመጀመሪያ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ በለጠው› ሲባል አልሰማህም። ጥጃው መጀመሪያ ጆሮ ብቻ ስለነበረው ያልከውን ሁሉ ይሰማህ፣ ይታዘዝህ ነበር፤ ብትመታው ይችላል፣ ብትጎትተው ይከተላል፣ ብታሥረው ይታሠራል፡፡ ጆሮ ብቻ ስለነበረው መስማት ብቻ ነበር የሚችለው፡፡ በኋላ ግን ቀንድ አበቀለ፡፡ ቀንድ ካበቀለ በኋላ እንደ ድሮው እጎትተዋለሁ ብትል አይሆንም፡፡ አሁን ከተስማማው ይቀበልሃል፤ ካልተስማማው ግን መዋጋት ይጀምራል፡፡ አሁን አንተ ያደረግከውን ማድረግ የሚቻለው በጆሮ ዘመን ነው፡፡ በቀንድ ዘመን እንደዚህ ማድረግ ሞኝነት ነው፡፡
ሁሉም ነገር የጆሮና የቀንድ ዘመን አለው፡፡ በሀገራችን አንድ መንግሥት ሲተከል ሕዝቡ የጆሮ ዘመን ይሰጠዋል። ዝም ይላል፣ ይሰማል፣ ይቀበላል፤ አልጋው እንዲረጋ፣ ዙፋኑ እንደዲጸና ይተጋል፤ ከትናንት ዛሬ፣ ከዛሬም ነገ ይሻላል ብሎ በተስፋ ይጠብቃል፡፡ ባያምንም ይቀበላል፤ ባይስማማም ይተባበራል፤ ባይግባባም አብሮ ይሠራል። ይሄ የጆሮ ዘመን ነው፡፡ ብልህ መሪ ከጆሮ ዘመን በኋላ የቀንድ ዘመን እንደሚመጣ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ሥርዓት ሠርቶ፣ ሕግ አጽንቶ፣ አገር አልምቶ፣ ሕዝብን አስማምቶ ይጠብቃል፡፡ በጆሮ ዘመን ያልሠራውን ሥራ በቀንድ ዘመን እሠራለሁ ቢል የሚያምነው የለም፡፡ እንደ ቀድሞው ዝም ብሎ የሚሰማ፣ አሜን ብሎ የሚቀበል፣ እሺ ብሎ የሚከተል፣ ጎንበስ ብሎ የሚጎተት አይገኝም፡፡ ለተስማማው ጆሮውን ላልተስማማው ቀንዱን ያቀርባል። ሥራውን በግድ ብትሠራ እንኳን ትግሉ ብዙ ነው፡፡ ሕዝብ ቀንድ ከማብቀሉ በፊት እንደ ቀንዱ ዘመን ማድረግ እንደማይቻለው ሁሉ፣ ቀንድ ካበቀለ በኋላም እንደ ጆሮው ዘመን ማድረግ አይቻልም፡፡ ራሱ ቀንድ አብቃዩም እንደ ድሮው ልሁን ቢል እሺ አይለውም፡፡ ያላወቁትን እንዳላወቁ፤ ያልሰሙትን እንዳልሰሙ፣ ያላዩትን እንዳላዩ፣ ያልደረሱበትን እንዳልደረሱ መሆን አይቻልም፡፡ ለውጥን ፈልገህው ብቻ አታመጣውም፤ የቀንድ ዘመን ሲሆን ሳትፈልግም ትለወጣለህ፡፡
አገር ብቻ ሳይሆን ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲና ተቋምም ቀንድ ያበቅላሉ፡፡ በጆሮ ዘመን አባሉ ሁሉ ይሰማሃል፤ ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደ ላይ ብሎ ያምናል። አንድ ቦታ የበሰለውን በልቶ፣ አንድ ቦታ የተጠመቀውን ጠጥቶ፣ የተባለውን ሁሉ ሰምቶ፣ ውደድ የተባለውን ወድዶ፣ ጥላ የተባለውን ጠልቶ ይኖራል፡፡ በአንድ ዓላማ የተመመ፤ በአንድ አቋም የቆመ፤ አንድ ግብ የጨበጠ፤ በአንድ መሥመር የሠለጠ የሚመስልበት የጆሮ ዘመን አለው፡፡ እንደ አህያ ጆሮ፣ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ ሆኖ ተካክሎ የሚታይበት፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ የሚመስልበት ዘመን አለ፤ያኔ አባሉና አካሉ የተግባባና የተስማማ የመሰለው ተግባብቶና ተስማምቶ ብቻ አይደለም፡፡ ጊዜው የጆሮ ጊዜ ስለሆነ ነው እንጂ፡፡
የቀንዱ ዘመን ሲመጣ ጠያቂ፣ መርማሪ፣ ተከራካሪ፣ ሞጋች ተች፣ ይበዛል፡፡ በፊት የጣመው አሁን ይመረዋል፤ በፊት ያስደሰተው አሁን ያስከፋዋል፤ በፊት ዝም ያለው አሁን ያስጮኸዋል፣ በፊት የታገሠውን አሁን ይሰለቸዋል። በፊት የፈራውን አሁን ይደፍረዋል፡፡ በፊት የተወውን አሁን ያነሣዋል፡፡ ‹ቀኝ ኋላ ዙር› ስለተባለ ብቻ አይዞርም፡፡፡ አባል ስለሆነ ብቻ የድርጅቱን ነገር ሁሉ አይቀበልም፡፡ መለኮታውያን ናቸው ያላቸውን መሪዎቹን ሰው አድርጎ መመልከት ይጀምራል፡፡ ላመነው ነገር እንኳ ቢሆን ተጨማሪ ማስረጃ ይፈልጋል፡፡ የጥንቱን ትርክት ብትተርክ፣ የጥንቱን ዘፈን ብትዘፍን፣ የጥንቱን ፉከራ ብትፎክር እንደ ሞኝ ይቆጥርሃል፡:፡ ያ ሁሉ የጆሮ ዘመን ታሪክ ነውና፡፡ በዚህ ጊዜ ለምን እንደ ጥንቱ ጆሮውን ስንጎትተው አልተጎተልንም፣ ስንመታው ለምን አልሄደም፣ ስንስበው ለምን አልተሳበም፤ ስንቆነጥጠው ለምን አልተቆነጠጠም ብለው የሚያስቡ ዘመንን ማንበብ የማይችሉ ናቸው፡፡ አሁን የቀንድ ዘመን ነው፡፡ የጆሮ ጊዜ አልፏል፤ ማሳመን ማግባባት፣ ማስረዳት፣ ይፈልጋል፡፡ መስማት ብቻ ሳይሆን መሰማትም ይሻል፡፡
ቤተ እምነቶች በዘመናችን ያልተረዱት ቁም ነገር ይሄ ነው፡፡ አንተ ምእመን ነህ ዝም ብለህ ገንዘብህን ስጥ፣ የምንልህን ብቻ ተቀበል፣ ለምን? የት? መቼ? እንዴት? ብለህ አትጠይቅ፤ አባቶችህ ከአንተ በላይ ያውቃሉ፤ አገልጋዮቹ ከአንተ ይሻላሉ፤ አትከራከር፣ ቁጣ፣ መቅሰፍት፣ መዓት ይወርድብሃል፣ ስለተባለ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፡፡ መስጠት ብቻ ሳይሆን የሰጠው ገንዘብ የት እንደዋለ ማወቅም ይፈልጋል፤ አባቶቹን ማክበር ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን ሲጠብቁ ማየትም ይፈልጋል፤ የሚባለውን መስማት ብቻ ሳይሆን ለሚባለው ነገር ማስረጃም ይሻል፤ ይመዝናል፤ ያመዛዝናል፤ የጥንቱን ከዛሬው፣ ድርጊቱን ከሕጉ ያመሳክራል፤ በሕጋዊው ቤት ሕገ ወጥነት፣ በመንፈሳዊው ቤት ዓለማዊነት፣ በእግዚአብሔር ቤት ቄሣር፣ በጽድቁ ቤት ርኩሰት ሲሠለጥን እያየ ዝም የሚልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፤ አሁን የቀንድ ጊዜ ነው፡፡
ተገለጠልኝ፣ ታየኝ፣ በራልኝ፣ ወረደልኝ፣ ፈለቀልኝ፣ ሰማይ ደርሼ መጣሁ፤ አሥር ሺ ሰይጣን አወጣሁ ስላልክ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል። ይመዝነዋል፣ ይፈትነዋል፤ ያነጥረዋል፣ ያበጥረዋል። ‹ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ ግበሩ› ነውና የተባለው፡፡ ከቻለ ይሞግትሃል፤ ካልቻለ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ዝም ብለህ ተቀበል የሚባልበት የጆሮ ዘመን አሁን የለም፡፡ እንደ ጆሮው ዘመን ወደፈለግከው አዳራሽና ጸሎት ቤት፣ ወደፈለግከው የራእይና የተአምራት ቦታ አትጎትተውም፡፡ አሁን አልሄድም ብሎ ሊወጋህም ይችላል፡፡ በዚህ ዘመን በየቤተ እምነቱ በምእመናኑና በእምነት አለቆች መካከል የምናየው ውጊያ ይሄ ነው፡፡ ወደፈለግነው አቅጣጫ እንጎትታለን በሚሉ የጆሮ ዘመን አለቆችና ‹ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ› በሚሉ ቀንድ ባበቀሉ ምእመናን መካከል፡፡
ድርጅትህን ስትመሠርተው ልጅ ስለነበር እንደፈለግክ ታደርገው ይሆናል፡፡ እየሰፋ፣ እያደገ፣ እየተለጠጠ፣ እየታወቀና እየሠለጠነ ሲሄድ ግን ከጆሮው ዘመን አልፎ የቀንዱ ዘመን ላይ ይደርሳል፡፡አንተ ድርጅቱን መምራት ብቻ ሳይሆን ድርጅቱም አንተን ሊወጋህም ይችላል፡፡ ብዙዎች በገዛ ድርጅታቸው ቀንድ ተወግተው ታሥረዋል፣ ከሥረዋል፣ ጠፍተዋል፣ በሽተኞች ሆነዋል፡፡ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፤ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል። ብልህ ነጋዴ በጆሮው ዘመን ቀድሞ ያስባል፡፡ እንደ ጥንቱ እመራዋለሁ፣ አስተዳድረዋለሁ፣ እኔ እበቃዋለሁ፣ ለዚህ ደግሞ መቼ አንሳለሁ አይልም፡፡ የልጅነቱን ልብስ አሁን ልልበስ እንደማይለው ሁሉ የጥንቱን አሠራር አሁን ልከተል አይልም፡፡ ለቀንዱ ዘመን የሚመጥን አሠራር፣ ሥርዓት፣ አስተዳደር፣ ባለሞያ፣ ሕግ፣ አደረጃጀት፣ የደረጃ ምጣኔና አስተሳሰብን ይገነባል እንጂ፡፡
በሀገራችን ዘመን ተሻግሮ ከልጅ ልጅ የሚተርፍ ድርጅት ያጣነው፣ ባለቤቶቹ ድርጅቱን በጆሮው ዘመን አስተሳሰብ በቀንዱ ዘመን እንምራው ስለሚሉ ነው። ድርጅቱ አድጎ አድጎ ከዐቅማቸው በላይ ይሆንና ያሳደገው አውሬ እንደሚበላው አዳኝ ያሳደጉት ድርጅት እነርሱንም ይበላቸዋል፡፡ ስንት ዘመን መርቼው፣ ድንጋይ ጥዬ መሥርቼው፣ ላቤን ጠብ አድርጌ እዚህ አድርሼው ማለቱ አይጠቅምም፡፡ ያ የጆሮ ዘመን ነውና፡፡
Addis Admass
Danile ante Woselata, your ear and your horn is ruthless MK attacking our fathers, robber ing our church . The group of robberies MK with satanic horn. this the oviouse interpretation of your trash as always! Fabricators !
I like it.
Danail ante WOSELATA , Your ear and horn is ruthless MK attacking our fathers robbing EThiopian Orthodox Tewahedo church. The group of robberies MK satanic horn. This is the obviouse interpretation of your trash as always. Fabricator Danaile.
What a stupied trash? No nanimals with ear or horn always, if want write write some thing substantial clearly . This is the total meaningless. May you wanted have horn.
Daniel kibret kkk
ante ye weyane digis admaki,, ye weyane zeke leqami
antem sew honeh ,weyanen lemasdeset ye Quwarawin Anbesa atse Tewodrosin , bezeh be shul afih tesadebk !!
Meyisaw kassan mesdebih weyanen yasdestal,, antem firifafe tagegnaleh
Atse TEWODROSIN LEMESDEB MIN MORAL ALEH ?? ante yemender tomor
YEGIZEW BALEGIZE DEBTERA dANIEL KIBRET ;; TEREGAGA !!AYNEGA MESLOH
weyanem yehedina ,, antem beye weyane digesu Dabo mequresi serah yekomina
yastezazbenal yehe Qen yalfina !!
Daniel your article is good but why Amsalu Gebrekidan the one called himself artist criticise you.?
የፅላት ሌባ ነህ አሁን ነቄ ብለናል ለአረብ እየሸጥህ የቤተክርስትያንን ቅርስ ጨርሰህ ያጠፋኸው ሳያንስ የማይረባ ፅሑፍ እየለቀቅህ ባታዝገን ይሻልሀል፡፡አንድ ቀን ሆ ብሎ የተነሳ እንደሆነ መድረሻ ይጠፋብሀል፡፡አበሻ አይነካም እንጅ ሲነካ አይወድምና አርፈህ ብትቀመጥ ጥሩ ነው፡፡
i wonder you! all in my life because you are the right person at the right time VIVA DNA the lion man
lebe lalew teru meker new…. lebe-lelelew gen….melkamum meker lesedeb menesha new…. ke-balegewoch bezu atetebek….small people talk about people… may God bless you Daniel….
Hi guys look the message how it is true at the right time .This is also a good message for who open their minds for good .Lemisemaa mikerew lemisadeb merekew lemayawek ezenelet tseleyeletem …….melkam ken.
እንደው ፈራ ተባ አልክ እንጂ ምሳሌህ ለጨቋኝ መንግስትም ጭምር ያገለግላል። ህዝብ ሲቆጣና ለምን ብሎ ሲነሳ መንግስትና አደግዳጊ ሰዎቹ እንደ ጀላቲ መቅለጥ ይጀምራሉ።
ATSE TEWODROS IS AGEW IT’S NOT AMARA I DON’T KNOW WHY HE MAKE SUSIDE BY HIM SELF AMARA JUST KEEP YOUR LAND ONLY YOU ARE ENEMY OF OROMO OUT FROM OUR LAND NOW
What MK got to do with this. Mamo lela metawekiaw lela. I’m sure you didn’t even read it.
በወያኔ ትታማለህ፥፥ ይህ የቀንድና የጆሮ ታሪክ ግን በጣም ጊዚዊና ለወያንኔ ቢገባቸው ትምርታዊ
ነው፥፥ ገልቱዎች ስለሆኑ ኣይገባቸውም፤፤
ኣመሰግንሃለሁ፥፥
Thanks! Great Idea for those wants to change in all aspects and headache for others!!!
ወያኔ ሞቶም አይታመንም ምክንያም በዚች ሃገር ላይ የተከለው ነቅርሳ ማጥፋት ይከብዳል (የጎሳ፣የጎጥ፣የሰው ባህሪ የለሌው አስተሳሰብ ተክለውት( ኢትዮጵያን ሲያቆስሉ ሲነክሱ ሲያስነክሱ ይኖራሉ ስለዚህ ወያኔን ማመን ቀብሮ ነውየሚለው አሁን አይሰራም!
ሳ.አ
Daniel you have written a very good article. I have benefited from it and it is applicable to every aspect of our life. If you are genuine please tell me in which stage is your Mahebere Kidusan.Is it on the ear or on the horn stage? I think Mahebere Kidusan is neither on the ear nor on the horn stage.For me not all it’s members the leadership is on the stage of organised Mafia -cult stage
ሰላም ለሁላችን ይሁን። ፀሐፊዉ የመሰለዉን ፃፈ። ሀሳብ ሰጪዎችም አንብቦ ዝም አሊያም ገንቢ ሀሳብ መስጠት ይጠበቃል።መሳደብ ለማን ይጠቅማል? ለሀገር፡ለወገን፡ለድርጅት፡ወይስ ለኃይማኖት ወዘተ።ፀሐፊዉ ከመፃፍ ወደ ኃላ ይላል ብዬ አላስብም እኛም መሰረታዊ ነገር በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሀሳብ መስጠት ግንባታዉ ጥሩ ነዉ።ቢቻለን ሁላችንም መሰረታዊ ነገር ላይ ብንስማማ።ለማንኛዉም ለሁሉም ጊዜ አለዉ።
Oromo1 = tesfa gebreb = luTi
from bednua eritrea.
you homosexual tefa gmat i am here to kill you for your crime committed against amara.
Your idea is putrified as your fucken rectum anus/finTiTa.
arif new dani
Oromo 1 is not oromo he is woyane. He want to do his evil master job by that name . careful
tiru eyita nw
Reptile Daniel is pritender and atantion seeker, doesn’t know any thing, his action and reaction is depend on the weather, now he trying to change his colore after he damaged a lots. Reptile Daniel.