‹‹ወንዶች ያልተጠናቀቁ ሴቶች ናቸው›› ተፈሪ መኮንን
ባለፈው ሳምንት፤ ከእሸቴ አሰፋ ጋር የአድዋን ድል በጊዮርጊስ እያከበርን ነበር፡፡ እሸቴ ታሪክ እያስተማረኝ ነበር፡፡ ‹‹በጠቢቡ ሰለሞን›› ጠረጴዛ ተቀምጠናል፡፡ በዙሪያችን ብዙ ሰው አለ፡፡ በዚህ መሐል ለደረጀ ደወልንለት፡፡ ከደረጀ ደስታ ጋር በስልክ ተነጋገርኩ፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ ድምፁን ሰማሁት፡፡ ድምፁን ስሰማው፤ ‹‹አፈረሱት አሉ፤ ውቤ በርሃን…›› የሚል ዘፈን በሰማ ሰው ህሊና ሊፈጠር የሚችል ስሜት ነግሶብኝ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር አውርቼ ስጨርስ፤ ያለፈ ህይወታችን ትዝ አለኝ። ህይወታችን ‹‹በግል አብዮት›› ይናጥ የነበረ ህይወት ነበር፡፡
ከደረጀ ጋር አውርቼ ስጨርስ፤ ደምቆ የታወሰኝ አንድ ነገር ነው፡፡ ደረጀ አንዳንድ የሐሳብ ‹‹ጉዊሎቲን››ን (Guillotine) የማለፍ ልዩ ብቃት አለው፡፡ ደረጀ ሁሌም ሚዛን አለው፡፡ እኛንም ሚዛን ያስጠብቀናል፡፡ እርሱ ከባህር ጠለል ባላይ በአራት ሺህ (ወይም በላይ) ሜትር ከፍታ ላይ ለመተንፈስ ይችላል፡፡ ዳሎል ወርዶም እንደ ልቡ ይሆናል። ሳንባው ከባህር ጠለል በታች ወርዶ፤ እንጦጦም ወጥቶ አለ ችግር ያገለግለዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ፤ ትኩስ ጎረምሳ እና የሰከነ አዛውንት በአንድ ደረት ይዟል፡፡ በውስጡ ያለችውን ሴት እየቀሰቀሰ ሚዛኑን ይጠብቃል፡፡ እረኛ እንደ ሌለው ከብት በሐሳብ ዱር ልንጠፋ ስንባዝን፤ እረኛ ሆኖ አስታዋሽ ሐሳብ ያመጣል፡፡
ከዚህ ቀደም የሰው ህሊና ረግጦት ከማያውቅ (?) የሐሳብ ዱር ገብተን ስንባዝን፤ በተቦጫጨቁ የፍልስፍና ሐሳቦች ሰክረን፤ የስሜት ጽዋ አንስተን ስንጯጯህ፤ አንዳንድ የምስጢር ስንኞች እያነበነብን ስንቃዥ፤ እርሱም እስኪበቃው ከቃዠ በኋላ፤ ከእንቅልፍ ይቀሰቅሰናል፡፡ እርሱ ነፃነቱን የሚጠቀመው፤ ራሱን በረጅም ገመድ አስሮ ነው፡፡ ስለዚህ፤ እንዳንባዝን እንደ እረኛ ይመልሰናል፡፡ እሸቴ ከጉብታ ሆኖ ይመለከተናል፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ደረጀ እንዲህ አለኝ፤ ‹‹እኛ ወንዶች መሬት ለቅቀን ለመባከን የተጋለጥን ነን። በመባዘን አደጋ የተከበብን ነን፡፡ ስለዚህ ሴቶች ሁሌም ከአጠገባችን ሊኖሩ ያስፈልገናል፡፡ ሴት ሚዛን ታስጠብቅሃለች፡፡ አንተ ኒቼ እንዲህ ብሎ፣ ይህን አድርጎ ስትል፤ ዝም ብላ ትሰማሃለች፡፡ አንተ በሐሳብ አብደህ ልትጠፋ ስትል፤ ‹መቼ ነው ላንጋኖ የምትወስደኝ› ብላ ከሰማይ ወደ መሬት ታወርድሃለች፡፡ አንተ እንደ ደስተዮቪስኪ ሰማይ ሰማዩን ስታይ፤ እንደ ሄንሪ ሚለር ወደ መሬት ትመልስሃለች›› አለኝ፡፡
በአዲሱ (ደረጀ በማያውቀው) የሜክሲኮ ጎዳና በታክሲ ስጓዝ፤ ይህን የደረጀን ንግግር እየከለስኩ ነበር፡፡ ደረጀ ‹‹ሴት ሚዛን ታስጠብቅሃለች›› ይላል። ዛሬ (ጽሑፉ ሲፃፍ) ማርች 8 ነው፡፡ ስለዚህ የጓደኛዬን ንግግር ዛሬ ማስታወሴ፤ ‹‹መለኮታዊ ዲዛይን›› ይመስላል፡፡ ተገቢ ነው፡፡
ደራሲው ሔንሪ ሚለር፤ ‹‹ኔክሰስ›› ሲል በሰየመው መጽሐፉ፤ ደስተዮቭስኪን ይፎግረዋል፡፡ ‹‹እርሱ ሰማየ-ሰማያት ወጥቶ ረቂቅ ሐሳቦችን እንደ ጥጥ ሲያባዝት ይውላል፡፡ ግን አንድ ቀን እንኳን በሴቶች ቦርሳ ውስጥ ምን እንዳለ ለማየት ሞክሮ አያውቅም›› ይለዋል፡፡ ደስተዮቭስኪ ትልቅ ደራሲ ነው፡፡ ግን ‹‹አየራዊ ዕጽ›› (Aerial Plant) ነው፡፡ ዋርካ ደራሲ ነው፡፡ ‹‹ግን መሬት ያልዘ ዋርካ ነው›› ለማለት የፈለገ ይመስለኛል፡፡ ደስተዮቭስኪ፤ ከአየር ሳይሆን ከመሬት የበቀለ ዋርካ እንዲሆን የሴቶችን ቦርሳ ማየት አለበት፡፡ እንደ ደረጀ ሐሳብ ጤና ያገኛል፡፡
‹‹ፍልስፍናን የምትወድ ከሆነ›› ይላል ደረጀ፤ ‹‹ፍልስፍናን የምትወድ ከሆነ፤ ሁሌም አንዲት ሴት ከአጠገብህ ልትኖር ይገባል›› ይላል፡፡ ‹‹ሄግል፣ ስፒኖዛ፣ ካንት እያልክ መሬት ለመልቀቅ ስታቆበቁብ፤ እርሷ ‹የኔ ፍቅር ፂምህን አትላጭም፤ ያቺ መኪና አታምርም› ትልሃለች፡፡ መሬት ትይዛለህ።
‹‹ሾፐንአወር ምን እንዳለ ታውቂያለሽ ማለት ስትጀምር፤ ‹አንተ እከሊት እንዴት ተስማምቷታል›› ትልሃለች፡፡ ከሰው ጋር ትቀላቅልሃለች፡፡ ሳርትር፤ ‹Man is condemned to be free› የሚለው….ብለህ መሬት ለመልቀቅ ስትዘጋጅ፤ ‹በቀደም እንትና ሱቅ ያየሁት ሹራብ…› ትልሃለች፡፡ ቤትህን ለቅቀህ እንዳትሄድ ትጠብቅሃለች፡፡ ጨርቅህን ጥለህ እንዳትሄድ አደብ ታስገዛሃለች›› ይለኝ ነበር፡፡
የተነሳው ሐሳብ ጠበቅ አድርገው ሲይዙት ችግር ይኖረው ይሆናል፡፡ ግን የሆነ የእውነት ጥላ እንዳረፈበት አያለሁ፡፡ የዚህ ወሬ ትክክለኛው ዓውድ ካፌ ወይም የቢራ ጠረጴዛ ሆኖ የተሰማችሁ ካላችሁ፤ የወንድ ህይወት የሚቃናው በሴቶች መሆኑን ለመግለጽ የተነገረ ጨዋታ ነው፡፡
ፍልስፍና የዕውቀት ጉጉት ከሆነ፤ ሴቶች የመፈላሰፍ ፍላጎታቸውን በአዳም ፊት ጨርሰውታል። እፈላሰፋለሁ የሚለውን ወንድ በማህፀኗ ይዛ ለምትወልድ ሴት ፍልስፍና ምንድነው? አሻንጉሊቷ የሚጫወትበት ዕቃ ነው። አንዳንድ ሰዎች፤ ብዙ ወንዶች በኪነት አምባ ውርውር የሚሉት በሴቷ የመፍጠር ብቃት እየቀኑ ነው›› ይላሉ፡፡ እውነት ነው፤ ሴት ሰውን የመሰለ ረቂቅ ፍጡር ከወለደች በኋላ፤ የልብ ወለድ ገፀ ባህርይ የመፍጠር ፍላጎት ሊኖራት አይችልም፡፡
ህይወት፤ በሴቶች ማህጸን ለዘጠኝ ወር ቆይታ፤ ጡታቸውን ጠብታ፤ በእነሱ እጅ ጎርሳ፣ በእነሱ ምክር ጉዞዋን ትቀጥላለች፡፡ ሴቶች ስለህይወት ኃላፊነት ይሰማቸዋል፡፡ ስለዚህ ይጠነቀቃሉ። ወሲብ በወንዱ ዓይን ከደስታ ስሜት የተሻገረ ምዕራፍ የሌለው ጨዋታ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ለሴቶች ግን ከባድ ኃላፊነትን የሚያስከትል ግብር ነው። ወንዱ አስረግዞ ዘወር ሊል ይችላል፡፡ ሴቷ ግን አምጣ መውለድና አቅፋ ማጥባት ይኖርባታል። ስለዚህ ከአልጋ ለመውደቅ ስታስብ፤ ይህ ሰው ‹‹የምወልደውን ልጅ ለማሳደግ የሚችል ሰው ነው?›› ብሎ የማሰብ ኢቮልዩሽናዊ ዕዳ አለባት። ኢቮልዩሽን፤ ‹‹ብቁ የሆነ ይለፍ›› ሲል አውጇል፡፡ ስለዚህ የተጣማጇን አካላዊ ብቁነት ብቻ ሳይሆን፤ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ብቃቱንም ለማረጋገጥ ትሻለች፡፡ ምክንያቱም፤ ወንዱ በመኮብለል ወይም በሞት ቢለይ፤ አለያም ቤተሰቡን ለመደገፍ ባይችል፤ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርሳባት ሴቷ ነች፡፡
ስለዚህ ሴቷ መሬት ባልለቀቀ መንገድ የማሰብ ወይም የመመዘን ዝንባሌ አላት፡፡ አንዳንዱ ወንድ ይህችን ሴት በውስጡ ሊያገኛት ይችላል፡፡ ግን ይህች ውስጣዊ ሴት ስታንቀላፋበት ውጫዊ ሴት ታስፈልገዋለች፡፡
በእርግጥ ህይወት ሙሉ የምትሆነው በሴት እና በወንድ ህብረት ነው፡፡ እንደ ቻይናውያን አስተሳሰብ ህይወት Yin and Yang ነች፡፡ Yin and Yang የታኦ የህይወት ህግ ወይም ቀመር ነው፡፡ የህይወት ዚቅ በሳቅ እና በለቅሶ፤ በተስፋ እና በቀቢፀ ተስፋ፤ በመውደቅ እና በመነሳት የተቀናበረ መሆኑን የሚገልጽ ህግ ነው፡፡
ህይወት በዚህ ገጽ እንደምታዩት ስዕል ያለ ይዘት አላት፡፡ ጥቁር እና ነጭ ነች፡፡ ወንድ እና ሴት ነች። የጥቁሩ መጀመሪያ የነጩ መጨረሻ ነው፡፡ የነጩ መጀመሪያ የጥቁሩ መጨረሻ ነው፡፡ አንዱን ብቻ የያዘች ህይወት አትገኝም፡፡ እንዲህ መሆኗ ሙላት እንጂ ጉድለት አይደለም፡፡ በህይወት ጎዳና ረጋ ብሎ ለመጓዝ ይህን እውነታ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ህይወት Yin and Yang መሆኗን የተቀበለ ጤነኛ፣ አስተዋይ እና ጠቢብ ነው፡፡ ይህ የታኦ የህይወት ህግ ነው፡፡ ሴቶችን ማክበር ህይወትን ማክበር ነው፡፡
በእኔ አስተሳሰብ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰለጠነው ዓለም የምዕራቡ ዓለም የተሻለ ሴትነትን ያከብራል። በኢትዮጵያ ታሪክ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ብዙ ሴቶች እናገኛለን፡፡ ንግስተ ሳባን፣ በፖለቲካ ጥበባቸው የላቀ ብቃት የነበራቸው የሐድያ ተወላጅ ንግስት ኢሌኒ፣ በዘመነ ጎንደር የምናውቃቸው እቴጌ መነን፣ የወሎዋ መስታይት፣ እቴጌ ጣይቱ እንዲሁም የምኒልክ ልጅ ንግስት ዘውዲቱ ሊጠቀሱ የሚችሉ ሴቶች ናቸው፡፡ የአሜሪካን ወይም የእንግሊዝን ታሪክ ብትገልጡ አንድ ሴት አታገኙም፡፡ አሜሪካ ወ/ሮ ክሊንተንን ከመረጠች አዲስ ታሪክ ትሰራለች፡፡ በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ልትማር ትችላለች፡፡ ተመስገን፡፡
ኢትዮጵያውያን የሴቶችን ትልቅነት ለመቀበል የሚቸገሩ አይደሉም፡፡ እኛ ወንዶች (የደረጀን ምክር ተቀብለን) ሴቶችን በማክበር ኢትዮጵያን ራሳችንን ከጥፋት እንጠብቃለን፡፡ ኢትዮጵያን የተሻለች ሐገር እናደርጋታለን፡፡ ሴቶችን ለማክበር፤ የፍሬድሪክ ኒቼን አባባል በመቀየር፤ ‹‹ወንዶች ያልተጠናቀቁ ሴቶች ናቸው›› እላለሁ፡ Addis Admass
Asmare Mebratu says:
March 14, 2016 at 5:54 am
Matebu Mahari says:
March 14, 2016 at 5:42 am
keder yousf says:
March 12, 2016 at 5:16 pm
ንጉሡ ሞቱማ says:
March 11, 2016 at 6:09 am
ዳግም አደዎ ዘመቻ አስቸኳይ ጥሪ!!!
ነፃነት ወይም ባርነት!!!
በቁመና መሞት ወይም በማእረግ ለኢትዮጵያ ብሩህ ቀን መሞት!!!
ታህሣሥ 1 ቀን 2008 ዓ•ም•
••• መመረያ ቁጥር 4•••
Are you ready for radical change for equal opportunity blessed land Ethiopia for all in the name of ” ADOWA victory again in coming soon!!!”
ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው፣ሰሜን፣ደቡብ፣ምስራቅ አና ምዕራብ ፣ ኢትዮጵያዊ ማለት ማነው? ቅን ና እውነተኛ፣ሃይማኖተኛ/ፈረሃ እግዚአብሔር ያለው፣ጥበብን በልቡ ያሳደረ፣ ጠንካራ በአስተሳሰብ ጤነኛ ደፈር፣ ሃገር ወዳድ ጀግና አትንኩኝ ባይ፣ ሲጠቃ አሻፈረኝ ባይ ትውልድ አከባሪ ነው።
1• ኢሕአዴግ ስልጣን የማስረከብ የተሰጠው ጊዜ ገደብ አበቃ። የተላኩት ጠ/ሚ ሀ/ማርያም እንደ እስስት ፓርላማቸው ላይ በጭንቀት ሌላ አሰመሰልው አጥፈተናል ብለው ተናዘዙ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን በኋላ ሞኝ ነው። ወደኋላ የለም የሞቱ ት ሰዎች ቁንጫ አይደለሙ፣ በኦሮሚያ፣ በጉንደር፣በጋንቤላ፣በሱማሌ፣በአፈር፣ በትግራይ ክልል ከአደዎ ምርጥ 1000 ወርቃማ ባለስልጣቢች ቤተሰብ በስተቀር። በ25 አመት ውስጥ ሰንት መአት ሰው ጨርሳቸሃፀረ??? ከዚህ በኋላ በቃችሁ ሆዳም እሐዲግየ???
2• ጥሪያችን ለሁሉም ኢሐዲግ ስራዊት እና ፓሊስ ውስጥ ገብቷል፣ ተደራጅተዋል ፣ በተጠንቀቅ ከአሁን በኋላ በሕዝባችን ላይ የሚተኩስ ከላ ቀድመው እንዲመቱ ታዛዙን ሁሉ በአብዛኛው መመሪያው ደርሷል። ሁሉም ቀን እና ዶሮ ሲጮህ እየጠበቀ ነው።
3• ጦርነቱ ለይቶ በ1000 አደዎች ላይ ብቻ ነው፣ አንጂ ከጭቁኑ ወገናችን የትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም። ከዚያ በኋላ ዶ/ር ብርሐኑ የሽግግር መንግስቱን እና ጄነራል ከማል ጦሩን ይመራሉ።
4• ሕዝባችን በየአቅጣጫው ለለውጥ ስለተነሳ ጨዎነት በተምላበት ሁኔታ፣ነመፈጋገፈ በለውጡ ማእበል ውስጥ እንዲሳተፍ እናሣስባለን።
5• “ሮድ ማፕ(Blue print Ethiopia Road Map for new transition Gov’t ” (The final Core summary point form Ethiopian scholars) በሙሁራኖች አማካይነት በተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ በኩል ለህዝባችን በቅርብ ቀን ይገለፃል።
6• አገር ወዳድ በኢሐዲግ ውስጥ ያላችሁ ጦር ፣ ፓሊሶች የራሳችሁን ሂሊና ፍርድ ይዛቹ በለውጥ ውስጥ በሚስጣችሁ መመሪያ መሠረተ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ክፍተት ሳይፈጠር ከ ሽግግር መንግስቱ ጋር ተሠራላችሁ።
7• የተደራጀ ሐይል በየአቅጣጫው ስላለ በጨዎነት እና በመረዳዳት ከእግዚአብሔር ጋር እንወጣዋለን። በፀሎት ወደ ፈጣሪ እንደ ሐይማኖታችሁ የምናለቅስበት ግዜ ነው። እነዚህን በ 17 አህያዎች ተቀምጠው ቤተመንግሥት በሱዳን አሰማት ስም የገቡትን ሴይጣኖችን በእግዚአብሔር ስም ይነቅላሉ። በኤፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የዘረፈትን $50 ቢሎን ጋር ለፍርድ እናቀርባቨዎለን። ግን 50% ከ 1000 ውስጥ ተስፋ የቆረጡ የ ኤችአይቪ በሸተኞች ናቸው፣ ኢትዮጵያ የልጆቻቸው መኖሪያ እንኳን መሆኑን ረስተዎል???
8• አቡነ መርቆሬዎስ አሁን ለሕዝባችን አንድነት መናገር የለቦት አጣብቅኘ ጊዜ ላይ ነን። አንድ ኢትዮጵያ ፣ አንድ ሲኖዶስ የኣባቶቻችን ሰርአትን ዶግማ እና ቆኖና ሳይቀየር ወደ አንድነት ማምጣት በእግዚአብሔር ስም ይጠበቅባቸዎል።
ተራማጅ የኦሮሞ ታጋዬች ከ አምቦ ጫካ ጽሕፈት ቤት እና ይድረስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ታጋዮች በየአሉበት፣ ለውድ መሪዎቻችን የሽግግሩ ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ እና የጦሩ አሰረተባባረ ጀነራል ከማል ገልቹ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!!
ንጉሡ ሞቱማ አስተባባሪ CORE ከአምቦ። Strong Ethiopian is next to your door and Create connection for freedom!!! No more EPRDF foolish division based on linguistic. Ethiopians are smart now and united to make radical change than to form stable rule of law works for anyone.
FREEDOM! FREEDOM! FREEDOM!YOUR financial SUPPORT IS VERY IMPORTANT FOR GINBOT 7 AND ESAT MEDIA NOW AND MAIL SPILTED MONEY ORDER OR IN ANYWAY JUST TODAY PLEASE. WE ARE STANDING TOGETHER TODAY TO GET STABLE ETHIOPIAN FREEDOM OF LAND FOR YOUR KIDS TOMORROW THEN YOUR KIDS WILL PROUD ON YOU.
MATEBU MAHARI COMMENT ONE OF OPPORESSED TIGRAY AND LOVE MY COUNTRY ETHIOPIA. FORGET THOSE 1000 TRASH ADOWAS MAFIA/HITELERS CORRUPTED BLACK LIST IN HISTORY OF ETHIOPIA!!!
[Reply]
Thank you Matebu, by this time all Ethiopians pointed there fingers to 1000 trash Adowa’s only. Because the Tigray people mouth was shut off not to oppose them and simply say ok like a God. At the end only those corrupted bloody hand 1000 Adowa’s getting rich in Effort money over $50 billion. The poor Tigray people like any other Ethiopians has nothing. I was waiting such determined victory unity day. my fellow Tigrans speak up the truth not to go with the double liar.
Asmare Mebratu
[Reply]
All of u right wake up my Tigray people stand together with oppressed fellow Ethiopians. Tell to the Tigray Army’s not to fight anymore for 1000 Adowa woyanes interest. Your country is first than corruption money.
Azeb Tekely