ኤርትራ ውስጥ የሚማቅቁት ኢትዮጵያውያን

በቅርቡ ለኤርትራ አዋሳኝ ከሆነ ነው ከትግራይ ክልል በተለይ ፅርዓያ ግርማይ ተብሎ ከሚታወቀው አካባቢ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን በኤርትራ ታጣቂ ኃይሎች ተጠልፈው ተወስደው ነበር፡፡
በባህላዊ መንገድ ወርቅ ከሚወጣበት ካፍታ ሁመራ ወረዳ ወርቅ በማውጣት ላይ ከነበሩ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ድንበር ዘልቀው በገቡ የኤርትራ ታጣቂ ኃይሎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡ መጀመርያ አካባቢ ቁጥራቸው 85 መሆኑ የተነገረው እነዚህ የሻዕቢያ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን 32 እንደሆኑ በሱዳን አደራዳሪነት ከተመለሱ ዜጎች ቁጥር አንፃር ተመልክቷል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ጉዳዩ ይፋ የወጣው በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሆን፣ ከዚያም ከጠለፋው አመለጡ የተባሉትን ወጣቶች አነጋግሮ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዜናውን ማሠራጨቱ ይታወሳል፡፡
እነዚህ ዜጎች በሌላ አገር ለዚያውም በጠላት አገር ታጣቂ ኃይሎች ሲወሰዱ ለሁለት ሳምንታት ያህል የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው መግለጫ አልነበረም፡፡ የመንግሥት ሚዲያም ስለጉዳዩ ትንፍሽ ያለው ነገር አልነበረም፡፡ የግሉ ሚዲያም ቢሆን አጀንዳ ሲያደርገው አልተስተዋለም፡፡
ታፍነው የተወሰዱትን ዜጎች በተመለከተ የተለያዩ ሚዲያዎች የተለያየና አንዳንዶቹም ተቃራኒ የሆኑ ዜናዎች እያወጡ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ዝምታን መምረጡ፣ ከብዙዎች ዘንድ ወቀሳ የደረሰበት ሲሆን፣ ከገዛ አገራቸው በኃይል ታፍነው ስለተወሰዱት ዜጎች ሁኔታ የሕዝቡን የማወቅ መብት፣ መረጃን የማግኘትና ስለአገሩ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ የማወቅ መብት የጣሰ ሲሉም አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለዜጎች ያለው ተቆርቋሪነትም ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነው ያሉም አልጠፉ፡፡
ስለጠለፋው
ጠለፋው የተከናወነው ጥር 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ መሆኑ፣ ታጋቾቹ ለኢትዮጵያ ፈርስት ኦንላይን ሚዲያ ባለቤት ቢንያም ከበደ ተናግረዋል፡፡ ከተመለሱት ጋር ቅርበት ያላቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ምንጮች እንደሚሉት፣ የተጠለፉት ኢትዮጵያውያን በባህላዊ መንገድ ወርቅ ከሚወጣበት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ በግድ የተከዜን ወንዝ እንዲሻገሩ በማድረግ ለስምንት ሰዓታት በእግር ተጉዘው፣ ጉሊት በተባለ ቦታ ሻምበል ዳዊት የተባለና ሌሎች የኤርትራ መከላከያ ኃይል ወታደራዊ መኰንኖች አግኝተዋቸዋል፡፡
አንዳንድ ዘገባዎች ጠለፋውን ያከናወኑት ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር በመባል የሚታወቀው ድርጅት አባላት እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡ ሆኖም ከተመላሾቹ መካከል አንዳንዶቹ ለኢትዮጵያ ፈርስት እንደገለጹት፣ ከስድስቱ ታጣቂዎች መካከል የኤርትራ ሚሊሻና ትግርኛ ተናጋሪ የኤርትራ ወታደሮች ነበሩባቸው፡፡
ታጋቾቹ ከኤርትራ ወታደራዊ መኰንኖች ጋር ከተገናኙ በኋላ ልብሳቸውን አውልቀው ወታደራዊ ልብስ እንዲለብሱ የተደረገ መሆኑን፣ ‹‹ከአሁን በኋላ ወታደሮች ናችሁ፣ ትሠለጥናላችሁ፤›› ተብለው በእጃቸው የነበረውን ንብረት በሙሉ እንዲያስረክቡ መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚያም ወደ ጀርድን (የመስኖ እርሻ የሚከናወንበት ቦታ) ተወስደው ለአሥር ቀናት ያህል የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ መገደዳቸውን ይናገራሉ፡፡
ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሚሆናቸው እነዚህ ከታገቱ በኋላ የተመለሱት ዜጎች በኤርትራ ቆይታቸው አንዳንድ ነገሮች የተመለከቱ ሲሆን፣ በተለይ ከወታደሮቹ ውጪ ሲቪል ኤርትራዊያን እነሱን ዓይተው ተደብቀው ሲያለቅሱና ሐዘናቸውን ሲገልጹላቸው እንደነበሩ ታዝበዋል፡፡ ያለ ክፍያ ተገደው የእርሻ ሥራ በሚሠሩበት አካባቢ እንደነሱ ተጠልፈው የተወሰዱ ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቀን ቀን በዚሁ ተመሳሳይ የጉልበት ሥራ ተገደው ሲሠሩ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ታስረው እንደሚያድሩ መመልከታቸውንም ተናግረዋል፡፡
አብዛኞቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ በጥይት የተገደሉ፣ ተመትተው አካላቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የተረፉ መኖራቸውን፣ እንዲሁም በርካቶች ተገደው ወታደራዊ ሥልጠና ወስደው በተለይ ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር የተባለውን ድርጅት እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውንም ከዕገታው የተመለሱት ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው በኤርትራ አዋሳኝ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደሚናገሩት፣ የኤርትራ ወታደሮችና በኤርትራ የሚገኙ የኢትዮጵያ አማፂ ኃይሎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያውያንን እያፈኑ ይወስዳሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ በቅርቡ ጥያቄ የቀረበላቸው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ‹‹እያንዳንዱን የድንበር ወሰን ወታደር አስቁሞ መጠበቅ አይቻልም፤›› ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የኤርትራ መንግሥት ኃላፊነት የጎደለው የሽፍትነት ተግባር ላይ የተሰማራ በመሆኑ በተፈጸመው ጠለፋ እምብዛም አለመገረማቸውን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ተመጣጣኝ አንዳንዴም ‹‹የማያዳግም›› ዕርምጃ በመውሰድ አፀፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ዝቶ የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ የተጠለፉት ዜጎች በሱዳን አማካይነት በመመለሳቸው ዕርምጃ ከመውሰድ የተቆጠበ ይመስላል፡፡
በባድመ አካባቢ በ1990 ዓ.ም. በኤርትራ በተቀሰቀሰው ጦርነት ከሁለቱም አገሮች 70 ሺሕ ያህል ዜጎች ማለቃቸው ይታወሳል፡፡ የድንበሩ ጉዳይ እስካሁንም ዕልባት አላገኘም፡፡
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በድንበር አካባቢ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እየታፈኑ የሚወሰዱ ሲሆን፣ መንግሥት ግልጽ የሆነ የማጣራት ሥራና ዕርምጃ ሲወስድ ባለመታየቱ ወቀሳ ይቀርብበታል፡፡
በተለይ የኢሮብ ሕዝብ የመብት ተቆርቋሪ (IRAA) የተባለ ቡድን እንደሚለውኧ ቁጥራቸው በርከት ያሉ የኢሮብ አካባቢ ንፁኃን ነዋሪዎች ከቤታቸው ታፍነው ተወስደዋል፡፡ ስማቸውንና ማንነታቸውን በውል የዘረዘራቸው 97 አርሶ አደሮችን በግልጽ በመዝገብ አስፍሮ የገቡበት አለመታወቁን ቀደም ሲል አሳውቋል፡፡ ሌላ የአካባቢው ሕዝብ ተቆርቋሪ የሆነውና በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚኖረው ዓለም ተስፋዬ የተባለው ታዋቂ ጸሐፊ፣ ‹‹Neglected Irob Abductees›› (የተዘነጉት የተጠለፉ የኢሮብ ሕዝብ ተወላጆች) በሚል መጣጥፍ ተመሳሳይ ቅሬታ አሰምቷል፡፡
‹‹ቁጥራቸው ከ100 በላይ የሚሆኑ የኢሮብ ተወላጆች ሻዕቢያ አፍኖ ወስዶአቸው እስከዛሬ ምን እያደረጋቸው ይሆን?›› በማለት የሚጠይቀው አቶ ዓለም፣ ‹‹የሚገርመው የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለእነዚህ ንፁኃን ዜጎች ዝም ማለቱ ነው፤›› ይላል፡፡
‹‹በሌሎች አገሮች አንድ ዜጋ በጠላት ከተወሰደ ምን እንደሚሠራ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ዜጎቹ ተጠልፈው ለዘመናት እየማቀቁ ቁጭ ብሎ የሚመለከት ብቸኛ መንግሥት ነው፤›› ሲልም ጸሐፊው ይወቅሳል፡፡
ሪፖርተር ባደረገው ማጣራት ቀደም ሲል የገቡበት ስላልታወቀ እነዚህ ዜጎች የትግራይ ክልል መንግሥትና የፌደራል መንግሥት ከነዝርዝር ስማቸው የተገለጹላቸው ቢሆንም ምንም የሰጡት ምላሽ የለም፡፡
የኤርትራ መንግሥት ነፍጥ ያነገቡ የኢትዮጵያ የአማፂ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ በማስረግ የተለያዩ ጥቃቶች ሲፈጽም ይስተዋላል፡፡ ቀደም ሲል የአውሮፓ ቱሪስቶችና ኢትዮጵያውያን ከአፋር ክልል አፍኖ መውሰዱ የሚታወስ ሲሆን፣ በፈረንጆቹ ምክንያት ይመስላል ጉዳዩ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ መንግሥትም ሦስት ወታደራዊ የሻዕቢያ ካምፖች ማጥቃቱን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ሻዕቢያ ለፈጸመው ትንኮሳ አንዳንድ ወሳኝ ሥፍራዎች ላይ የአውሮፕላን ጥቃት በኢትዮጵያ መንግሥት ተፈጽሞ ነበር፡፡ እንዲሁም በ2004 ዓ.ም. በተመሳሳይ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማውጣት ላይ ከነበሩት መካከል እንደ አሁኑ 140 ኢትዮጵያውያን ተጠልፈው የተወሰዱ ሲሆን፣ እስከ ዛሬ የገቡበት አልታወቀም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሻዕቢያ ትንኮሳ የማይቆም ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ ባለፈው ዓመት ገልጸው ነበር፡፡
በኤርትራ እየተሰቃዩ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የመንግሥት ባለሥልጣን፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት እጅና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም፡፡ ጉዳዩን እያጠናው ይገኛል፡፡ የሚወስደውም ዕርምጃ እየተጠና ነው፤›› ብለው፣ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ በ1990 ዓ.ም. በድንበር ሰበብ ወደ ጦርነት ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 18 ዓመታት ሰላምም ጦርነትም በሌለበት ሁኔታ ይገኛሉ፡፡
Ech wodia, yihen chrana kend yelelewn weriachhun tewun…
አታሰልቹን አጠር አጠር አድርጉት
ሪፖርተር ምነው ትግሬዎቹ በኦሮሞው፣ በአማራው ፣በሱማሌው፣ በጋምቤላው፣ ወዘተ ወዘተ የሚፈፅሙትን ወንጀል እንዲህ አብራርቶ አልነገረንም? በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞወች በጠራራ ፀሀይ በትግሬውቹ መጨፍጨፋቸውን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወልቃይቶች በትግሬዎቹ ሲጨፈጨፉና ከቅያቸው ሲሰደዱ ምነው እንዲህ አብራርቶ አልፃፈም? አማረ አረጋዊ የምልህ ነገር ቢኖር ለእናትህ አልቅስላት ነው!!!
የማነ ነጋሽ ማንን ለማሞኘት ነው ሁሉግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ጥያቄ ስያቀርብ ለሆነው ኣይነት ችግር የምትጠየቀው ኤርትራና የኤርትራ ህዝብ ነው ይህ ደግሞ ከሃይለስላሴ ግዜ ጀምሮ የነበረ ስለሆነ ኣዲስ ነገር ኣይደለም ኣሁንም ሆነ ወደፊት የኦሮሞ ህዝብ ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ችግር ኣይደለም
Reporter is the spokesman for woyane. Don’t expect honeys from flies. For the last 25 years, how many Ethiopians are kidnapped and killed by TPLF? Woyane don’t care about Ethiopians.
Hello!!! Yemane Negash > don’t you have any thing to write about your Tplf masters crime agaist millions of Amaras, Oromos etc. What you wrote is none sense it is smelling as woyane cadres propaganda.
The so called yemane Negash! Shame on you we Ethiopians are awakend ,to day we are hand glove inorder to destroy your masters from Ethiopia soil.
ጎበዝ ይሄ ነገር የትግሬዎች ትያትር ነዉ ዳር ቁማችሁ ተመልከቱ። እዉነት ቢሆን ትግሬዎች ይጮሁ ነበር ኢትዮጵያዉያን ሀገራቸዉን ስለሚወዱ እስቲ በዚህ እንፈትናቸዉ ብለዉ ነዉ። አማረ አረጋዊ የአረጋዊ በርሄ ወንድም መሆኑን አትርሱ ጩሉሌ ለጩሉሌ ነዉ ነገሩ። የድር ገጾችም ከትግሬ ፕሮፓጋንዳ እራሳችሁን ጠብቁ ስንት የሚጻፍ ቁም ነገር ያለዉ ጽሁፍ ሲላክላችሁ አታወጡም ሐጎስ የሚጽፈዉን ተሺቀዳድማችሁ ታስነብቡናላችሁ። በበኩሌ ካሁን በሗላ ስለ ትግሬዎች መስማት የምፈልገዉ ሻቢያ የወያኔን ወይም ወያኔ የሻቢያን ጉሮሮ ይዣለሁ ብሎ ሲነገርኝ ብቻ ነዉ። እስከዛዉ የአቶ ጌታቸዉ ረዳን (ኢትዮ ሰማይ) ብሎግን ብቻ አነባለሁ።
አያችሁ ያገሬ ልጆች ! ! ! በዚህ forum ስሜን “ደደብ FROM ደደቢት” ብየ የሰየምኩት ወያኔዎች ምን ያህል idoitic እንደሆኑ ለማሳየት ነው። “ውሸትን ለወያኔ፥ዘፈንን ለከያኔ” ብያለሁ።
ባድሜ የ ኤርትራ መሬት ነው ። ወያኔ ባስቸኳይ መውጣት አለበት !! ! ! ወያኔ በየሃገራቱ ሰላም ጠባቂ እያለ እየላከ በየዓለማቱ ያስጨረሳቸውን ዜጎች ለቤተሰብ ያርዳ፥በስማቸው እስከዛሬ ከ united nation የደም ካሳ እየተቀበለ ወደግል ባንክ ያስቀመጠውን ገንዘብ ለቤተሰቦቻቸው ይስጥ ! ! ! ! ወያኔ በሚጥር እስር ቤት እየማቀቁ ያሉትን ዜጎች እና በሚጥር በ mass grave የቀበራቸውን ዜጎች ያጋልጥ።ከዝህ ሁሉ በኋላ ኤርትራ ውስጥ ስለሚሰቃዩት ኤትዮጵያዊያን ይንገረን።
Reporter – you worried only for Tigray.
Why don’t you worry about innocent ethiopians suffering in prisons.
Why don’t you worry about killing of Amhara Wolkayit, killing of oromos, Surma south ethnics
and others who are losing their land by the name of sugar factory by Tigrians.
Where is the sugar production?
>20 million people is in famine.
Where is double digit economic growth?
Of course one ethnic grows more that double economic growth.
Other ethnics have get nothing and losing what they had.
….Backfire….
The food is exported out of eth.
Thanks to TPLF, We lost our port 20 years ago.
And now, Sudan is ready to take our fertile border land.
I don’t think The Great Tigray Rep. to be established.
God keep this country.
yehenin new G7 netsa awchi memelun kkk
G7 rasun netsa yawta !!weym ke weyane Gar tederadro sitan yegara enji
shabya guya tekemto netsa awetahalehu teret teret yekum
yetebela equb new !
MOT LE WEYANE ;;SHABYA AND G7 !!!
ወያኔዎችና የወያኔ ኣገልጋዮች ሌላውን እያሞኙ እነሱ እየተንደላቀቁ የሚኖሩበት ግዜ ለኣስራ ሁልት ኣምስት ደቂቃ እንደጎደለው ኣልገባቸውም በባድመ ስም ማታለልም ኣይችሉም ምክንያቱም ባድመ በፍርድ ቤት ያለቀ ይግባኝ የማይባልበት ስለሆነ ምክንያት እየሰጡ በስልጣን ለመቆየት የሚያደርጉት ቤላቤለው ስለሆነ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ማወቅ ኣለባቸው
ወያኔዎችና የወያኔ ኣገልጋዮች ሌላውን እያሞኙ እነሱ እየተንደላቀቁ የሚኖሩበት ግዜ ለኣስራ ሁልት ኣምስት ደቂቃ እንደጎደለው ኣልገባቸውም በባድመ ስም ማታለልም ኣይችሉም ምክንያቱም ባድመ በፍርድ ቤት ያለቀ ይግባኝ የማይባልበት ስለሆነ ምክንያት እየሰጡ በስልጣን ለመቆየት የሚያደርጉት ቤላቤለው ስለሆነ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ማወቅ ኣለባቸው
Senu
meTegiya siyaTu mngedu siTefa eko new enmokrew blew lehulachn blew le mesewatnet jognochachn eritrea ye hiedut.
Le rasachew tegodu enj mnachn nektew mnregmachew.
Ay yhnma aywedew.
Meshelem ygebachewal belkam asbew bemeselefachew.
Ylq dehna ymTuln
Aye yeweyane propaganda YETHIOPIA WETAT BEFLAGOTU LENATSNETU LIWAGA WEDE ERITREA B 10000 BFLAGOT IYEGEBA NEW WEYEHWLIH WEYANE
የወልቃይት መሬት የኤርትራ መሬት ነው። የትግራይም የአምሓራም አይደለም።
Yemane Neash the Tigria kid to whom can cheated in this time.
Why not you expose the millions of Amharas and Oromos etc killed by your masters Tplf criminals.you are realy the member of the blood sucker woyane.
Yemane will you please go hell. There is no room for dirty game,rubbish game:
Why 95% of the Tigray people kept silent while all Ethiopians are taking part against the brutal woyane regime. Are they not Ethiopians?