የሕወሓት ካድሬዎች በኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ የሚያደርጉት ሕገወጥ ተግባር በቆጠራ ተደረሰበት::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አሥር ዓመታት የገነባቸውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ በጀመረው ቆጠራ፣ በሕወሓት ካድሬዎች  በርካታ ሕገወጥ ተግባራት የተፈጸሙባቸው ቤቶች መኖራቸው ታወቀ፡፡


የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው ቆጠራ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፣ ይቆጠራሉ ከተባሉት 104,258 ቤቶች ውስጥ 35 ሺሕ ያህሉ ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ መሠረት በሕወሓት ካድሬዎች   ተሰብረው የተከራዩ፣ ፈርሰው ተቀላቅለው የተሠሩ፣ በግለሰቦች የተያዙ በርካታ ቤቶች መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ትዳር እየፈረሰና ፍቺ እየተፈጸመ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በትዳር ውስጥ እየኖሩ ነገር ግን ከሁለት በላይ ቤቶች ይዘው የተገኙ ፍቺ እስከመፈጸም የደረሱ ክስተቶች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ከዚህ በላይ ተገቢው ክፍያ ያልተፈጸመባቸው ቤቶችን መያዝና ሕጋዊ መረጃ የሌላቸው ቤቶችም መገኘታቸው ተመልክቷል፡፡
ለባንክ ተገቢውን ክፍያ በወቅቱ ያልፈጸሙ፣ በሕገወጥ ድርጊት ከያዙት ቤት የኮበለሉና በሕገወጥ ድርጊታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ መኖራቸውም ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘጠኝ ዙሮች ለተጠቃሚዎች ያስተላለፈውን 104,258 ቤቶች ቆጠራ ጀምሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ቆጠራ ብዙ ቤቶች በተገነቡባቸው ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ የካ፣ አቃቂና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍላተ ከተሞች ነው፡፡
በቆጠራው 2,500 ባለሙያዎች፣ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበርና የንግድ ቢሮ ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡
ቆጠራውን በሚመለከት የአዲስ አበባ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝና የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መስፍን መንግሥቴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ አስተዳደሩ በእነዚህ ቤቶች ሕገወጥ ተግባራት እየተፈጸመ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት እንደደረሰው ገልጸው ነበር፡፡
አስተዳደሩ ለልማት ተነሺዎች 8,400 ባለአንድ ክፍልና ስቱዲዮ ቤቶችን አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ነገር ግን የልማት ተነሺዎች ፍላጐት ባለሁለት ክፍልና ባለሦስት ክፍል በመሆኑ፣ በርካታ ቤቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ ተዘግተው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለተጠቃሚዎች ቢቀርቡም ውል ስላልተፈጸመባቸው ርክክብ ያልተፈጸመባቸው 4,137 ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሒደት በሕወሓት ካድሬዎች  ደላሎች፣ የጥበቃ ሠራተኞችና ሌሎች አካላት አብዛኛዎቹን ቤቶች በመስበርና በመቀላቀል ለግል ጥቅም ማዋላቸው ተነግሯል፡፡
ቆጠራው ትኩረት የሚያደርገው መኖሪያ ቤቶች፣ ንግድ ቤቶችና የጋራ መጠቀሚያዎች ላይ ነው፡፡ በእነዚህ ግንባታዎች ላይ ሕገወጥ ድርጊት ተፈጽሞ ከተገኘ፣ ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚሠራ አቶ መስፍን በወቅቱ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቆጠራ የሚጠበቀው ከተጠቃሚዎች የሚገኘው መረጃ ከአስተዳደሩ መረጃ ጋር ተመሳክሮ ዕርምጃ እንደሚወስድ ነው፡፡ ቆጠራው ከዚህ በተጨማሪ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ማስተካከያ ማድረግ እንደሚያስችል  ይድነቃቸው ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተደረገው ቆጠራ 42 በመቶ ቤቶች እንደተሸፈኑ፣ 1,339 ቤቶች ባዶ ሆነው መገኘታቸውንና በሕገወጥ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙት መሀል 60 ያህሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

11 Comments on “የሕወሓት ካድሬዎች በኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ የሚያደርጉት ሕገወጥ ተግባር በቆጠራ ተደረሰበት::”

  1. The War Lord woyane and his cadres have a full right to do every things in Ethiopia to take the home, to remove any one and demolish his house in the name of development,to break the house to take for themselves,to take the land they like from any one, to change the identity of any one they don’t like e.g wolkite,to give the land of Ethiopia as a gift for any one they like,if they don’t like you they send you to court and passed the verdict in absentia like life sentences and death penalty etc. They have a power to do everything. The people of Ethiopia keep silent and submit themselves for slavery. Please rise up for your right.

  2. በየህንፃው ቢያንሥ 5 የወያኔ ካድሬዎች የህዝቡን ትርታ የሚያዳምጡ የሚሰልሉ አሉ።

  3. ለመሆኑ የአዲስ አበባ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ በእንጦጦ ኪዳነምህረትና ቁስቋም አካባቢዎች ከብዙዎቹ በጥቂቱ የመንግስትና የህዝብ ቤቶችን ከነግብረ አበሮቹ (አባተ ስቶታውን ጨምሮ) ቁልፍ ከመሸጥም በላይ ሌሎች ወንጀሎችን እንደሰራስ ማን ይናገር? እራሳቸውንም በቆዩባቸው ጉለሌና አራዳ ለምን አያስገመግሙም።

  4. አባተ ስቶታውን ጨምሮ ቁልፍ
    ከመሸጥም በላይ ሌሎች ወንጀሎችን
    እንደሰራስ ማን ይናገር? Ene linager ABATE BEKOLFE KERANIYO MUSINA SEFERIN MERET KEGOLF KIBEB FITLEFIT YENEBEREWN TILKIK YEGIR KUWAS MEDAN BEAND WERU YASCHEBECHEBE NEW, YEkeraniyon chaka Abiro yechebechebe new. Ahun degimo meniged ginbata lay ehhhhhh……….

  5. ይድረስ ለአማራ ክልል አስተዳዳሪ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቼም ስው ሲኖር ለሃገሩና ለወገኑ እንጂ ለሆድ አይደለም እላለሁ ወንድሜ ሃገርን ያክል ነገር ከሕዝብ ጋር ተጣልታችሁ አጣልታችሁ አዋግታችሁ ወደም ዘላቂ ችግር አጋድማችሁ በወያኔ ልብ እየተነፈሳችሁ ነገ ከስልጣን መውረድ አይቀሬ ነው ልብልትሉት ይገባል የእናንተ ካድሬዎችና ነፍሰ በላይ ወታደራችሁ ይህ ሕዝብ እንዳላሳገደ፣እንዳላስተማረ እነሆ መሬቱን ለወያኔ ስትሰጡበት እንደ ዲር እንሰሳት ከክልሉ ከሃገሩ፣ከቤት፣ከሰፈሩ፣ከእምነቱ ስታፈናቅሉት እስከ ዛሬ ድረሰ ከሻቢያና ከወያኔ፣ከሱዳን ጋር በማበር የጎንደርን መሬት ይህ መሬት የኢትዮጵያዊያን መሆኑ ዘንግታችሁ.አለቆቻችሁ ቢያዞችሁም አይሆንም ማለት ስትችሉ ወልቃይቲ ጸገደይ ለትግራ እንስጥ ስትሉ ህሊናችሁ እንደት እንዳሰበ ለሕዝብ በይፋ ግልጽ ይሁን ያሉትን ሰዎች ስትገድሉ ነበር አሁንም እየገደላችሁ ነው!
    ጎርፍና መንግስት ያልፋል ግን ሕዝብ ይቀጥላል ነው ያሉት የላስታው አዛውንት! ገብቶሃል

  6. አሄ ሄ እህ

    ጆሮ አይሰማው የለ !

    ታዲያ እንዲህ እንዲያ ሆነ በማለት ብቻ ሳይሆን መረጃ ያለው ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ ስም አጥፊና አሉባልተኛ መባልን ያመጣል። ውጤትም አይኖረውም።

  7. ኮንዶሚኒያም ለሃብታም ወይስ ለድሃ? ማህበረሰብ ተው ወዳጄ እባክህ እራስህን አታታል በአንድ ኮንዶሚኒያም እንዳለ አንድ ባለሃብት ገዝቶት ነገር ግን አንዱ እድለኛ አልሽጥም ሲለው ባለሃብቱን በየቀኑ ከፍተኛ ገንዘብ በመጨመር ለማታለል እየሞከረ ነው
    ሌላው የዐዲስ አበባ ኮንዶሚኒያም 35 በመቶውን ለኤትራዊያን በትዕዛዝ ተሰጥቶል ይሕን ያምናሉ በላስልጣኖች እድል የሚገባው ኢትዮጵያዊያን ወይስ ኤትራዊያን የውጭ ዜጋ የቤት ተጠቃሚ ያደረጋል በሕግ አምላክ ተውን ተውን ሲበሉ ሲያስበሉ ሲያሳድዱን እስከ መቼ?
    ሃይሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*