በኦሮሚያ ዘገባ ለማቅረብ የተንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር ውለው ተለቀቁ:: (VOA)

ሁለት የዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች እና አስተርጓሚያቸው በኦሮሚያ ተቃውሞና ድርቅ ዙሪያ ዘገባ ለማቅረብ በተንቀሳቀሱበት ወቅት፤ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ተመለሱ። ጋዜጠኞቹ ለ24 ሰዓታት ታስረው ተለቀዋል።

በኢትዮጵያ ሁለት ዓለምአቀፍ ጋዜጠኞችና አስተርጓሚያቸው በኦሮሚያ የተከሰተው ድርቅና የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ዘገባ ለማቅረብ ሲንቀሳቀሱ ለ24 ሰዓታት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቁ።

የብሉምበርግ የዜና ምንጭ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰን፣ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የምትዘግበው ጄሲ ፎርትንና አስተርጓሚያቸው በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ያለምንም ማብራሪያ ከአዋሽ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በፌዴራል ፖሊስ ታጅበው እንዲመለሱ ከተደረገ በኋላ አዳር ታስረው መለቀቃቸውን አቅታውቀዋል።

ጋዜጠኞቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል ያመሩት ባለፈው ሮብለት ሲሆን፤ ቀዳሚው ቆይታቸው በአዳማ ዩኒቨርስቲ ነበር። በዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በተለይ በኦሮሚያ የሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን አስመልክቶ የብሉምበርግ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰንን አነጋግረንው ነበር።

ሐሙስ ጠዋት ተነስተው ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ አመሩ። የጉዟቸው አላማ በምእራብ ሐረርጌ በቅርቡ በአሰቦች ሒርናና ሌሎች ከተሞች የተቀሰቀሱ ሰልፎችን አስምልክቶ ሁኔታውን ለመከታተልና ለመዘገብ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በመጉዳት ላይ ያለው ድርቅ፤ በምእራብ ሀረርጌ ያስክተለውን ጉዳትም ለመመልከትና ለመመዘን እንደሆነ ዊሊያም ዴቪድሰን ያስረዳል።

በአዋሽ ከተማ ምሳ በልተው ከከተማ ወጣ እንዳሉ፣ “ከምሥራቅ ወደ ደቡብ ምሥራቅ እያመራን ሳለ፤ አንድ የፍተሻ ጣቢያን አለፈን ከዚያ በኋላ የፌደራል ፖሊስ መኪና የኛን መኪና አስቆመንና (የኔ የራሴ መኪና ነበር ይዤ የነበር የምጓዘው) ከሌላ የውጭ ጋዜጠኛ እና ከ አስተርጓሚ ጋር፣ ፌደራል ፖሊሶች ፓስፖርታችንን፣ የመኖርያ ፍቃዳችንና ዜግነታችንን እንድሳይ ጠየቁን ።” ይላይ ዊልያም።

ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ የምታቀርበው ጄሲ ፎርትን እና ኢትዮጵያዊ አስተርጓሚያቸው ነበሩ በመኪናው ውስጥ። በወቅቱ ከጸጥታ ባለስልጣኖችም ሆነ ከያዟቸው የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች ለምን እንደተያዙ በህግም ሆነ በአሰራር ተጠቅሶ የተነገራቸው ምንም አይነት ነገር እንደሌለ ዊሊያም ዴቪድሰን ለቪኦኤ አስረድቷል።

የብሉምበርግ የዜና ምንጭ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰን

የብሉምበርግ የዜና ምንጭ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰን

በአዋሽ የነበራቸው ቆይታ አጭር ነበር በጥቂት ደቂቃዎች ወስጥ፣ “በፖሊስ ታጅበን ወደ አዲስ አበባ እንድንመለስ ተወሰነ። ውሳኔው በ10 ደቂቃ ውስጥ ነው የተወሰደው።” በማለት ገልጾልናል ዊልያም።

በተጨማሪም “ምን እንዳጠፋን የሚገልጽ ምልክት አልነበረም። ምን እንዳጠፋንም ግልጽ አልነበረም። በቀጥታ የምናነጋግራቸው የነበርንው ሰዎች ግን ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ብቻ ነው የነገሩን።” ብሏል።

ጄሲ ፎርትን

ጄሲ ፎርትን

ከዊሊያም ዴቪድሰን ጋር የታሰረችው ጄሲ ፎርትን በትዊተር ገጿ፤ “በኢትዮጵያ ዘገባ ሳቀርብ አዳሬን ታስሬ ነበር” በማለት የምስራቅ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማህበር ያወጣውን መግለጫ አካታለች።

የምስራቅ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማህበር በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ዙሪያ የሚታዩ ጥሰቶች ክፉኛ እንዳሳሰቡት አስታውቋል። በኢትዮጵያ ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች እንዲሁ በዘፈቀደ ለአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር እየዋሉ፤ ስራቸውን እንዳይሰሩ ሆን ተብሎ ይደረጋል፤ አሰራሩም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን ይጥሳል ብሏል ማህበሩ። ኢልያ ግሪንደርፍ የድርጅቱ የቦርድ ሃላፊ ናቸው።

“ጋዜጠኞችን ማሰር የሚጠቅማቸው አይደለም። አነጋጋሪና ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ (ለምሳሌ እንደ ኦሮሚያ ተቃውሞዎች ያሉ) ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳያቀርቡ ማስቆም የሚያመጣው ፋይዳ የለም። በጣም የሚያሳስበንና ድምጻችንን እንድናሰማ የሚያስገድደን ሁኔታ አለ። የኢትዮጵያ መንግስት ከለት ወደለት በመገናኛ ብዙሃና ላይ የሚያከናውነውን አፈና እያጠናከረ ሲሄድ ተመልክተናል። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ ባለሃብቶችን በመሳብ ላይ ትገኛለች። በአፍሪካ ሁለተኛው ትልቅ የህዝብ ብዛት ወዳላት ሀገር የምጣኔ ሀብቱን እድገት ተከትሎ፤ በስፋት ወደ ኢትዮጵያ ስራ ለመስራት የንግዱ ማህበረሰብ በመትመም ላይ የገኛል። የሚይድጉ ሀገሮች እንደ ዩናይትድስ ስቴይትስ፣ ብርታንያና አውስትራሊያ የመሳሰሉ አይነት የመብትና የአሰራር ደረጃ መኖር እንዳለበት እናምናለን።” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። ከፍተኛ የመንግስቱን ባለስልጣናት ለማግነት ሞክረን አልተሳካልንም።

ሔኖክ ሰማእግዜርና ሳሌም ሰለሞን ጉዳዩን ተከታትለው ያቀረቡትን ዘገባ ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/03/08/5d14b506-a792-4ace-9e71-77ed4e21f3c5.mp3?download=1

የምስራቅ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማህበር

10 Comments on “በኦሮሚያ ዘገባ ለማቅረብ የተንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር ውለው ተለቀቁ:: (VOA)”

  1. Those Old VOA journalists should go and the generation should replace them they don’t fit the present time Ethiopia except few
    They are too old .

  2. The problem we had
    is completely reversed.
    Long live EPRDF
    God bless Ethiopia.
    And may God bless
    the United States of America!

  3. Reply
    Hero Hero Hero!!!!!!!!!!
    አንዶም አብርሃ says:

    March 8, 2016 at 12:09 pm

    ዳግም አደዎ ዘመቻ ቁጥር 4 መመሪያ።
    አዳም አና ሔዎን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሲፈጠሩም ሆነ ነፍሳቸውን ካወቁ በኋላ በቋንቋ እንዲግባቡ እንጂ ዘረኝነት ለመገለጫ አልተጠቀሙበትም። ሰለዚህ ዛሬም ቋንቋን መሰረት ያረገ አፍቃሪዎች ከአሁን በኋላ ቦታ የላቸም። ኢትዮጵያ የምትፈልገው ከአሁን በኋላ በአንድ አይን ሁሉንም የሚያስተዳድር ብቻ ነው። ለአላማችን ድል ላይ ለመድረስ ተያይዘን ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምስራቅ ፣ ምእራብ በአገር ውስጥ እና ውጭ አንድላይ ተነሱ። ለኢሕአዴግ ሰላማዊ ጥሪ አርገን ስልጣኑን ለማሰረከብ ፍቃደኛ አይደለም፣ ይባስ ብሎ ሕዝባችንን በየ አቅጣጫው መግደሉን ቀጥለዎል። በኢትዮጵያ ህዝብ በላይነት በአጭር ጊዜ በሁሉም የተቀናጀ የትግል ማእበል
    ይጀምራል። የተቀናጀ ትግሉ በተዎራድ በቁጥር 3 መሰረት ደ/ር ብርሐኑ እስከ ሽግግር ድረስ መሪ እና ጀነራል ከማል አዛዥ ሆነው ከትግራይ ነፃ አዊጭዎች ጋር በመሆን በኢትዮጵያውያን ዳግም አደዎ ወኔ ማእበሉን ከህዝቡ ጋር በያሉበት በቆረጣ ውጊያ 1000 የአደዎ ዛራፈዎችን ነጥለን፣የትግራይን ህዝብ እንዴት እንደአተለሉት ከዘረፉት $50 ቢሊዬን ጋር ለስላዊ ፍርድ እናቀርቧቸወለን።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!!
    ተራማጅ የኦሮሞ መሪዎች ከ አምቦ ጫካ ጽ/ት የትጥቅ ሰንሰለት ንኡስ። ይድረስ ለቆራጥ ጀግኖች መሪዎቻችን። አባቶቻችን በቁመና ሙቱ አላሉም ለ ነፃነት እንጂ የእነሱ ደም ይወቅሰሀል የመጨረሻው የተያይዞ ጥሪ ከአገር ውስጥ። ግልባጭ ይድረስ የግልኝነት ሆድ ያሸነፈችሁ ወይም በ140 ካሬ መሬት እራሳችሁን ሸጣችሁ፣ ተረት ተረት በየቦታው የምትፀፍ ሄዳችሁ የሞላው ካድሬዎች የመጫረሻው ምእራፍ ላይ ደርሳችሀል። የ እውነት ትግል እና የውሽት የሆድ ፍቅር ፍም መስለው ተፈጠዎል??? ጊዜ አለው ሁሉም በቃ ሕዝባችን አንድ ኢትዮጵያ ብሎ ተነስቷል

    http://www.elfign.com/2016/03/shimelis-tadesse-yeneta-art-club.html

  4. “… ሰለ እስልምና ብዙ መናገር የጀመርኩት…እኔ ባለሁበት 99/100 ሙሲሊም ነው ስለዚህ ማንም ሰዉ ደፍሮ ቀና አይልም በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው…”ጁሐር መሐመድ።አቤት ጭብጨባ አቤት ንግግር አቤት።VOA እዉነት ሐቀኛ ዘጋቢ ከሆናችሁ በምዕራብ ሐረርጌ አርበረከቴ፣ሐብሮ፣ ቦኬ፣ዳሮ ለቡ ወረዳዎች ይህ የጁሐር አባባል መፈፀሙን አረጋግጣችሁ ትመጡ ነበር እናንተ ግን ይህን ማድረግ አትፈልጉም።እወቁ የክርስቲያኑ ደም ግን ስላሴ ደጅ ይጮሃል።።።

  5. Esat byankelafa geleba gobegnew medre banda hula gezew tekrboal yetare geze selhone anferdbachum

  6. The journalist whom I hate from VOA
    Solomon Abata is attention seeker , naïve ,
    and boastful .
    Tizeta Belachew she is too old .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*