አቶ ልደቱ አያሌው – በወቅታዊ የአገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ

“ኢትዮጵያ ውስጥ የብዙኃን አስተሳሰብ ተጨፍልቋል”

ባለፉት 4 ወራት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ተቃውሞና ግጭት እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ
አካባቢዎች የተከሰቱ ብጥብጦችን አስመልክቶ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው፤ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሚከተለውን ትንታኔ ሰጥተዋል

ዘንድሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለምን ተቃውሞና ግጭቶች የበዙ ይመስልዎታል?
የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመርን አንስቶ፣ ስርአቱ እንደ ስርአት ያለው አቅጣጫ ልዩነት ላይ የሚያተኩር ስለሆነ፣ በሂደት የህዝብን ትስስርና አብሮ የመኖር ሁኔታ እየሸረሸረ፣ ግጭቶችን እንደሚያባብስ ስንገልፅ ነበር፡፡ በአንፃሩ ኢህአዴግ የያዝኩት መንገድ ይበልጥ የህዝቡን አንድነት የሚያጠናክር ነው የሚል አቋም ላለፉት 25 አመታት ይዞ ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት የሰላም ኮንፈረንስ ሲያካሂድ ነው የኖረው፡፡ ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ አልታየም፡፡ አሁን ደግሞ በመጠኑም ሆነ በይዘቱ አቅጣጫውን የቀየረ አስቸጋሪ ሁኔታ በሀገሪቱ እየተፈጠረ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ከአሁን በፊት ግጭት ብቅ ይላል፤ ብዙም ሳይታይ ይዳፈናል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ብቅ ይላል፡፡ አሁን ግን ቀጣይ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በብዙ አካባቢዎች እያየን ነው፡፡ ኢህአዴግ በአጠቃላይ በህዝቦች አንድነት ላይ ሳይሆን ለልዩነት ትኩረት ሰጥቶ የሚያራምደው ፕሮፓጋንዳ፣በሂደት ውጤቱ ምን እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ በቀጥታ ከፌደራል ስርአት አደረጃጀቱ ጋር ይያያዛል፤ቋንቋና ብሄርን መሰረት አድርገው ከተደራጁ ፓርቲዎች አጠቃላይ ሁኔታም ጋር ይገናኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ችግሮቹ ለምን እየተባባሱ መጡ?
አንዱና ዋናው ጉዳይ ህብረተሰቡ በሰላማዊ መንገድ ሃሳቡን የሚገልፅበት እድል እየጠበበ መምጣቱ ነው፡፡ ስርአቱ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የበላይነት ብቻ የሚመራ መሆኑና የህብረተሰቡ አስተሳሰብና ጥቅሞች የሚወከሉበት ም/ቤት ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፓርላማ መጥፋቱ ሌላው ነው፡፡ ኢህአዴግ ስለ ዲሞክራሲ ሲያወራ ትርጉም የሌለው የታይታ ዲሞክራሲ እንደሆነ፣ የተለያዩ ሃሳቦችም ተቀባይነት እንደሌላቸው ህብረተሰቡ እየተረዳ ነው የመጣው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀበሌ እስከ ፓርላማ ም/ቤቶች ጥርግርግ ብለው መውጣታቸው ህዝቡ ብሶቱን የሚተነፍስበት መድረክ አሳጥቶታል። ህዝቡ መድረኩን ሲያጣ ሊከተል የሚችለው አማራጭ አመፅንና ተቃውሞን ነው፡፡
ቀደም ሲል ይሄ አልታየም፤ ምክንያቱም ቢያንስ በርከት ያሉ ፕሬሶች ነበሩ፡፡ ተቃዋሚዎች በፓርላማ ነበሩ፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ክርክሮች ይካሄዱ ነበር፡፡ ህዝባዊ ስብሰባዎችም ይደረጋሉ። በአጠቃላይ የተለያዩ የህብረተሰቡ ቅራኔዎችና ሃሳቦች የሚስተናገዱበት እድል ነበረ፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ወደ አመፅና ግጭት የመሄድ እድሉ እምብዛም ነበር፡፡ አሁን በሂደት ይሄ እየጠፋና መድረኩ እየጠበበ በመምጣቱና ፍፁማዊ የአንድ ፓርቲ የበላይነት በመንገሱ ለአመፅና ግጭቶች በር ከፍቷል፡፡ መንግስት ሰላማዊ ትግልንም ፈርቶ፣ የትጥቅ ትግልንም ፈርቶ መኖር አይችልም፡፡ አንዱን መምረጥ አለበት፡፡ የፖለቲካና የአመለካከት ልዩነት የሚስተናገድበት መድረክ ከሌለ፣ አመፅና የትጥቅ ትግል ምቹ መደላድል እያገኘ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት፡፡ የተፈጠረው ችግርም የዚህ ሁሉ መግለጫ ነው፡፡
አመፅና ግጭቶቹ የመብት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የብሄር አክራሪነት የታከለባቸው ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ህብረተሰቡ በታሪኩ አብሮ የኖረ ህብረተሰብ ነው፡፡ በልዩነት የመኖሩን ያህል ብዙ የአንድነት መገለጫ የሆኑ እሴቶች አሉት፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ግን ሲሰበክ የኖረው ልዩነቱ ነው እንጂ አንድነቱ አልነበረም፡፡ በዚህ ህብረተሰቡ “እኛና እነሱ” የሚል አመለካከት እንዲያዳብር ነው የተደረገው። ይሄ ሂደት ወደ ጠባብነትና ዘረኝነት የሚያመራ አደጋ እንደሚፈጥር ግልፅ ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ይሄን ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ሃገራዊ ራዕይ ሳይሆን አካባቢያዊ ሁኔታን ነው፡፡ እኛ ብሎ “እነሱ” የሚባሉትን የሚጠላ ኃይል ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡ በኔ ሀብት ማንም ሊጠቀም አይገባም ብሎ የሚያምን ህብረተሰብ ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡
ጤናማ ያልሆነ ጥላቻ የታከለበት ፉክክር ነው እየዳበረ የመጣው፡፡ ስርአቱምኮ የጠባብነት ችግር እንዳለበት ይናገራል፡፡ ግን ይሄን የጠባብነት አመለካከት ወደዚህ ደረጃ ያጎለበተው ማን ሆነና ነው ዛሬ እሱ ወቃሽ የሆነው? አሁን እያጨድን ያለነው የዚህን ፍሬ ነው፡፡፡ ይሄ ሀገር ወዴት እየሄደ ነው ተብሎ ተገምግሞ መሰረታዊ ማሻሻያ መወሰድ ካልተቻለ አደገኛ ነው፡፡ በተሃድሶ ላይ በር የዘጋ ስርአት አመፅና አብዮት ነው የሚያስተናግደው፣ ይሄ በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዱን ባጠበበ ቁጥር ሊያስተናግድ የሚገደደው አመፅና አብዮት ነው፡፡
ኢህአዴግ ያለፈውን ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ሲል አደጋው ሊታየው ይገባ ነበር።  ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የብዙሃን አስተሳሰብ ተጨፍልቋል፡፡ አንድ አስተሳሰብ ብቻ የህብረተሰቡን ህይወት እየወሰነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ የብዙሃን አስተሳሰብና ፓርቲ ስርአት አስፍነናል ማለት በህዝብ ላይ መቀለድ ነው፡፡ ኢህአዴግ በሌሎች ላይ ጣት መቀሰሩ የትም አያደርሰውም፤ ራሱን ነው መመርመር ያለበት፡፡ ተቀናቃኙም ሃይል ቢሆን አመፅና ግጭት ይህቺን ሀገር ወዴት ሊወስዳት እንደሚችል ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፡፡ ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ መከተል ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ብጥብጥ ኢትዮጵያን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስዳት ይችላል፡፡
መንግስት ችግሩን እያስተናገደ ያለበት ሁኔታ ያዋጣል ብለው ያስባሉ?
እንግዲህ ችግሩን ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያየሁ እየፈታሁ ነው ይላል፡፡ በኛ ግምገማ ግን መንግስት በቀጥታ ከጉዳዩ ባለቤት ጋር ሲወያይ አይደለም የምናየው፤ የራሱን ካድሬዎች እየሰበሰበ ነው እያወያየ ያለው፡፡ የራሱን ካድሬዎች ያወያያል፤ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ይቀረፃል፤ ያ ለህዝብ ይቀርባል፡፡ ይሄ መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር አይሄድም፡፡ ህዝቡ የመንግስት ሚዲያዎችን በዚህ የተነሳ ማየት አይፈለግም፤ ሌሎች የውጭ አማራጮችን ይሻል። 25 ዓመት ሙሉ በሚዲያዎች እየተሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ፣ ስርአቱን በህዝብ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ አድርጎታል፡፡ ህዝብና መንግስትን ሆድና ጀርባ አድርጎታል፡፡ አሁን መንግስትን የሚያምን ህዝብ  የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ነው አመፅና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች ካለፈው ጊዜ በተሻለ እድል እያገኙ የመጡት፡፡
ባለፉት 4 ወራት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካቶች ህይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡ እልባቱ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?
በዚህ ጉዳይ ብዙ ድርድር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ እነ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሶርያ… አሁን ያሉበት ችግር ውስጥ የገቡት ተሃድሶ ማካሄድ አቅቷቸው ነው፡፡ ስርአቶቹ ቆም ብለው ራሳቸውን ገምግመው፣ ተሃድሶ ማድረግ አቅቷቸው ነው አብዮት ተቀስቅሶ ለራሳቸውም ለህዝባቸውም የማይጠቅም ሁኔታ ውስጥ የገቡት፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ቆም ብሎ ተሃድሶ የማያደርግ ከሆነ፣ እነሱ የደረሰባቸው እጣ ፈንታ በሱም ላይ የማይደርስበት ምክንያት የለም፡፡ ችግሩ ግን በመንግስት ላይ ደርሶ የሚቆም አይደለም፡፡ ለሀገርና ለህዝብ የሚተርፍ ነው፡፡ በተለይ በሀገሪቱ ባለው የፖለቲካ ቅራኔና የልዩነት ስፋት እንዲሁም ሲሰብክ ከኖረው የጠባብነት አስተሳሰብ አንፃር፣ በግብፅና በሊቢያ የተፈጠረው አይነት እዚህ ቢያጋጥም፣ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚከት ነው የሚሆነው፡፡ ችግሩ ቢከሰት የአደጋው ተጠቂ የሚሆነው መንግስት ብቻ ነው ብሎ ማሰብ ተገቢ አይሆንም፡፡ መንግስት ይሄን አደጋ በሚገባ ተገንዝቦ ራሱን ለተሃድሶ ዝግጁ ማድረግ አለበት፡፡
ለተሃድሶ ዝግጁ መሆን አለበት ሲሉ ምን ማለት ነው?
ለዚህ ሀገር የታይታ ሳይሆን እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲመጣ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ የህብረተሰቡ የተለያዩ አመለካከቶች የሚወከሉበት መድረክ መፍጠር መቻል አለበት፣ ፓርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው፣ ልዩነታቸውንና ሃሳባቸውን የሚያራምዱበት ሁኔታ መኖር ይገባዋል፡፡ በየ5 ዓመቱ የሚካሄዱ ምርጫዎችም ይሄን የህብረተሰቡን የሀሳብ ልዩነት የሚያስተናግዱ መሆን አለባቸው፤ ለታይታ ብቻ መሆን የለባቸውም፡፡ ግጭቱን በሃይል ለተወሰነ ጊዜ ማስቆም ይቻል ይሆናል፤ በዘላቂነት ግን ማስቆም አይቻልም፡፡ ዘላቂው መፍትሄ ከተፈለገ፣ ሃቀኛ የሆነ ተሃድሶ መምጣት አለበት፡፡
ሰሞኑን የታክሲ ሾፌሮች አዲሱን የመንገድ ደህንነት ደንብ በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡፡ አድማው ተገቢ ነው ይላሉ?
የታክሲ ሹፌሮች ህይወታቸው የተመሰረተበት ስራ ስለሆነ ህጉ ሊያመጣባቸው የሚችለው ችግር ሊያሳስባቸው ይችላል፡፡ ሲያሳስባቸው ተቃውሞአቸውን ማቅረብ መብታቸው ነው፡፡ ይህን ማንም ሰው መቃወም ያለበት አይመስለኝም፡፡ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት በሰላማዊ መንገድ ነው። ስራ ማቆም አንድ የሰላማዊ ተቃውሞ መንገድ ነው። ታክሲዎች ሲቆሙ ዞሮ ዞሮ ህብረተሰቡ ይጎዳል፡፡ ስለዚህ ሹፌሮችና መንግስት ተወያይተው መፍትሄ ማበጀት አለባቸው፡፡ ግን በአጠቃላይ በኦሮሚያም ሆነ በአማራ ክልል ወይም በሌሎች አካባቢዎች የሚነሱት ተቃውሞዎች መነሻ ምክንያቶች ይኑራቸው እንጂ ጥያቄዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተከሰተውም ይሄ ነው፡፡ አንዳንድ ጥያቄዎች መነሻ እንጂ ዋነኛ ጥያቄዎች አይደሉም። በኦሮሚያ ያለው የማስተር ፕላን ጥያቄ ብቻ ነው ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል፤ስረ መሰረቱን በደንብ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ለነዚህ ሁሉ የሀገሪቱ ችግሮች ምንድነው መፍትሄው ይላሉ ትሄ ያበጁለታል?
ህዝብና መንግስት እየተራራቁ እንደሆነ መንግስት ተገንዝቦ፣ ህዝቡ በአግባቡ ብሶቱንና ተቃውሞውን የሚያሰማበት መድረክ መፍቀድ አለበት፡፡ በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሚካሄዱ ምርጫዎች እድል የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡ አንዱ መፍትሄ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዱን ማስፋት ነው፡፡ የብዙሃን ፓርቲ አሰራር ሰፍኖ ልዩነት፣ ብሶት፣ ተቃውሞ… የሚደመጥበት መድረክ ያስፈልጋል፣ አሁን ግን ይሄ የለም፤ የአንድ ፓርቲ ብቸኛ የበላይነትና ቁጥጥር ያለበት ሀገር ነው፡፡
ሁለተኛው ህገ-መንግስታችንን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የፌደራል አደረጃጀቱን በተመለከተ አደረጃጀቱ 25 ዓመት ውስጥ አንድነታችን እያጠናከረ መጣ ወይ? በህብረተሰቦች ዘንድ መተማመንን መፈቃቀርን ነው ወይ ያመጣው? የሚለውን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ መሻሻል ካለበት መሻሻል አለበት፡፡ አሁን የሚደረገው ወታደራዊ እርምጃ ለጊዜው ችግሩን ሊያስታግሰው ይችላል ግን ያዳፍነዋል እንጂ አያጠፋውም፤መልሶ መፈንዳቱ አይቀርም፡፡

25 Comments on “አቶ ልደቱ አያሌው – በወቅታዊ የአገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ”

  1. Ato Lidetu (Kihdetu)!You are again thinking coming back to politics! I know you have benefitted a lot as an amateur politician? You have also satisfied your ego by playing the biggest role in disintegrating the opposition and making sure that it will never revive again. You are shameless for daring to give public interviews and lament on the current regime that you should be grateful for allowing you to amass wealth. I am sure, tomorrow, you will be a politician-turned investor.

    I get sick when I hear your ugly voice and picture.

  2. @ kumneger,

    i think you are talking about Qinijit or CUDP.

    If so my suspicion is Berhanu Nega is the guy who played the most destructive role at the most critical time, during the protests against vote riging.

    You sure know what Berhanu did during a negotiation.

    But i think the CIA was behind Berhanu and it was the CIA that was the main responsible for the failure of the negotiations and also the failure of the Qinijit revolution.

    The CIA, based in the USA embassy in Addis Abeba, was of course monitoring all communications in Addis Abeba and beyond.

    You perhaps know about a top secret map from August 13 2010 G.C. published by Edward Snowden where people can see where the CIA – NSA spy centers are located. Addis Abeba is among the listed cities.

    The embassy spy centre network (updated)

    Over 80 US Embassies around the world conceal joint NSA-CIA “Special Collection Service” (SCS) radio and electronic surveillance equipment. The images here show some of the more prominent sites in Europe, South America and the Middle East.  All feature rooftop sheds or structures concealing mobile phone, wifi and radio surveillance antennae and equipment to “collect” communications from city centres and government districts.

    CIA & NSA have a base in Addis Abeba, the USA embassy. Can you find the city on the map ?

    Of course those monitored include the public, opposition and civil society, and that for decades, also during Haile Selassie era.

    https://en.wikipedia.org/wiki/Special_Collection_Service

    Note: i could not post a link to the duncancampbell dot org site where the info above is posted.

  3. Lets look at the Ethiopian situation,

    USA/CIA were behind:

    1. the so-called Ethiopian Students Movement,

    2. overthrow of Haile Selassie,

    3. overthrow of Derg,

    4. separation of Eritrea,

    5. landlocking of Ethiopia,

    6. introduction of tribalism and killils in Ethiopia as initial steps to dismantle Ethiopia, and

    7. the failure of the Qinijit revolution in relation to the 2005 elections.

    https://www.youtube.com/#/watch?v=sSx8yLOHSUs

    In the above video you can see how the USA or the CIA masterminded and facilitated the transfer of power from Derg to Woyane from ca. 1989 G.C. to 1991 G.C.. We can see the standard operating procedure of the USA state department (= CIA) in regime change situations, here using the Ukrainian example.

    The youtube video shows the telephone conversation between USA under secretary of state for Europe, Victoria Nuland, and the USA ambassador to Ukraine Pyatt, intercepted by the Russian spy agency in February 2014 G.C..

    ” THE TREACHEROUS TREATMENT OF EPDA BY THE CIA, AS TOLD BY COMMODORE TASEW 

    Shortly before the end of the EPLF-TPLF war against the derg with certainly over 500 000 Ethiopians dead if not a million, the CIA was preparing the EPLF-TPLF for the take over of power in Ethiopia. It is as a chapter of this strategy that the CIA decides to treat treacherously its own creation the EPDA which it had used as an instrument until it was no more useful and had to be thrown away. The story of the last days of the EPDA in Khartoum is told us by Commodore Tasew who was the President of the EPDA with a determined stand to serve the cause of Ethiopian unity to the end. As such Commodore Tasew was an element to be liquidated by the CIA and its proxy agents the EPLF-TPLF as well as by the loyalist Wing in EPDA in the service of the CIA led by Dereje Deresa. This is how the story was told by Commodore Tasew; “ yeetiopia andenet teztana tegel, 1998” p.190 

    “ America’ s anti-Ethiopian unity policy had become clear to us beyond any doubt when the US had started to identify itself closely with the EPLF and TPLF and had decided to hand over power in Ethiopia from the Derg to the EPLF-TPLF. It was also then that the CIA had come out openly to block the forces of Ethiopian unity and serve the cause of Ethiopian dismemberment. 

    This had become clear at the Toronto Conference which was held from Hamle 12 to Hamle 15 (July 1990) with the object of creating a democratic united front of forces committed to Ethiopian unity for the formation of a transitional government to replace the expiring Derg. And as this objective was contrary to the US strategy to replace the Derg by EPLF-TPLF those loyal to the CIA had done everything to sabotage and disrupt the Conference before it achieves its objectives. I was one of the persons responsible in organising the Toronto Conference with the objective of achieving o the unity of pro-unity forces and, as President of EPDA,I was preparing to lead the EPDA delegation to Toronto when I was told to go urgently to Khartoum (Sudan) where I was told my service was needed urgently. Replacing me to lead the EPDA delegation to Toronto was assigned Dereje Deressa, EPDA secretary General. It was only upon arrival in Khartoum tht I understood the CIA mischief to avoid my presence at Toronto. At this point CIA was engaged in bringing together forces that will form the entourage of EPLF-TPLF and follow them applauding to the power pedestal in Addis Ababa so as to give them the appearance of popular support while alienating pro-unity forces and individuals. ” “

  4. አቶ ልደቱ;
    የወያኔ አስተዳደር በጥገና ለውጥ ይሻሻላል እያልከን ነው::ባጭሩ ወያኔ የሚከተሉትን በደሎች በሃገር ላይ የፈጼም ድርጅት ነው::
    1.ወያኔ በማንም ሃገር የሌለ የዘር ፌደራሊዝም ብሎ ኢትዮጵያን እንደ ፋሽሽት ጥኣልያን በጎሳ ከፋፍሎል
    2.የውሽት ታሪክ በህዝብ መካከል በመንዛት ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ጤላት እንዲሆኑና እራሳቸው ደማቸውን አፍስሰው የመሰረቱትን ሃገራቸውን እንዲጤሉ አድርጎዋል::
    3.ወያኔ በፈጥረው የዘር ፖለቲካ ምክንያት “ኢትዮጵያውያ” የሚለው የሃገር ስም በክልል ስም እንዲለወጥ ኣዽርጎዋል::ኢትዮጵያን ሃገራቸውን እንዲጤሉና እንዲረሱ በወያኔ ከፍተኝኣ ዘመቻ ተደርጎዋል::
    4.ከሻብያ ጎን ተሰልፎ ኢትዮጵያን ወግት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጎዋል::
    5.ወያኔ ሃገሪቱን ከተቆጥኣጤረ ጀምሮ ሃገረቱን የለአንዳች ተቆጥኣጥኣሪ ዘርፎዋል::ለዚህም ግልጽ ማስረጃው ከ25 አመታት
    በፊት ባዶ እግራቸውን ኢትዮጵያን የወረሩ ወያኔዎች በአሁኑ ግዘእ ባለትላልቅ ፎቅ:ቤቶች;ባለሆቴሎች; ባለፋብሪካዎች;አስመጭእና ላኪዎች;የብዙ መኪና ባለቤቶች;የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቁልፍ ቦታውች ባለስልጥኣኖች ወዘተ ሆነዋል::ብዙሃኑ ህዝብ ግን ስደተኝኣ: ረሃብተኝኣ: ስራአጥ: ሆኑዋል::ባጥቃላይ ኢትዮጵያ የልመና ሃገር ሆናለች::
    ስለዚህ ይህ ዘረኝኣ ድርጅት መጥፋት እንጂ በመንም አይነት ሊሻሻል አይችልም::በሌብነት የበሰበሰ ድርጅት መፍረስ እንጂ መዳኝኣ የለውም::

  5. Aye Ledetu andum tetyake man honena yehzben tegel kegedlut andu ante nehe gezew yerake mesleh gezew kerbowal

  6. My point of view regarding racist Weyane and the real PanAfricanist Adeyola!

    She is my inspiration!

    Dear Adeyola,
    In the first place, what made me surprise is the deepest, very adequate knowledge and sympathy that you have about Ethiopia and Ethiopians. Your clarification capacity regarding the real scenario in the country that has been going on since 1991!
    Secondly, your great commitment to be voice for voiceless Ethiopians and you proved to be real panAfricanist practically in the beginning of 21st century!
    Thirdly, your concern and day to day follow up about the evil activity of the racist Weyane conducting against the people and nation, and well known regime with rampant corruption in Ethiopian history that the country faced for the last 25 years in unprecedented way!!!

    Furthermore, your observation, the way you gather information, the way you organize, and analyze the information itself, how you develop it to tangible evidence then at last how you provide to the audience is really very professional. The points you stated, clarified and the reality you revealed out to the face of international community and to the world arena beyond the struggle and sacrifice paid by our compatriots every where at home and in abroad, what you have provided is more than 100% true!!!

    Therefore, Ade keep it up please.

    The peace, security and the sovereignty of our motherland the entity of the people and the Horn of Africa regionally and Africa as a continent is in jeopardized in relation to tribalist Weyane.
    1. This regime is a terrorist at state level since 1991!
    2. It’s a threat at regional level/ IGAD member countries!
    One of its attribution in here is, inculcating, transmitting, and transforming tribalism, ethnicity, and a toxic clan politics to the neighbor countries in Eastern Africa. This is for nothing, but not to be cursed alone at international political arena! Also, to divide and rule and in visa-vis to stay on power as much as they want!

    Example:

    – Djibouti:
    It’s a matter of Issa and Gadabuursi Somali clans on power while high Afar population is living there and alienated from political power. The government is using its weak military leverage to keep the power at the hands of Somali tribe and particularly on the fistful of clans of Issa and Gadabuursi!

    Ismael Omar Guelleh president of Djibouti, in office since 1999.
    Guelleh was first elected as president in 1999 as the handpicked successor to his uncle Hassan Gouled Aptidon who had ruled Djibouti since independence in1977.
    President Ismael Omar Guelleh from Somali tribe and Issa clan has been characterized as dictator and his rule has been considered by some human rights groups.
    The First Lady of Djibouti, Kadra Mahmoud Haid also from Gadabuursi sub clan of Somali. She has a decisive role in string and monopolizing the economical activities of the country while the president is controlling the whole activities of the politics and this is exactly the same as what the racist Meles Zenawi was doing, and his wife, blind minded Azeb Gola; as she was a free rider to monopolize resources every where in the country!

    You know what is going on:

    – Somalia:
    In Somalia what Weyane has been doing is what any body can imagine the level of their intervention by ignoring international law and violating the sovereignty of Somalia, and how much they tried to impose clan based federalism structure of government, how they creat conflict between different clans. If they want they assist one clan today, but tomorrow they easily change their mind and supply weapons to the other clan and this way they play games in human life. They escalate the conflict in to violence intentionally!
    They do fight Alshabab through AMISOM, but it is puzzle. In most of their military operations they defeated Alshabab, but they retreat deliberately by leaving the place they controlled with the innocent Ethiopian troops life and sacrifice. In here, their target is money and they don’t care for the life of Ethiopian army, they don’t have a clear resolution to their objectives and their military leader ship failed to demonstrate it’s purpose properly in front of the international community.
    They pretend and act as if they are working to bring peace regionally and they contribute their part to maintain the international peace and security, but it’s totally fake and this is their significant attempt to cheat the world!

    – South Sudan:
    In S. Sudan the armed conflict launched between Dinka the tribe of President Salva Kiir Mayardit a South Sudanese politician who has been President of South Sudan since its independence July 9 2011 and Nuer the tribe of Dr Rick Macher who was Vice President after the independence of the nation until the new conflict occurred in December 15, 2013 is still unsolved. Every stakeholders know what kind of interest that the Weyane has explicitly exhibited!

    – Kenya:
    In Kenya it’s a matter of Kikuyu, Luhya, and Luo issue. Ethnicity issues are there implicitly.
    Uhuru Kenyatta the current president of Kenya is the son of Jomo Kenyatta who was the first president of Kenya December 12, 1964- August 22, 1978 from Kikuyu tribe came to power in 9, April 2013. The Vice President William Ruto Kalenjin ethnic group and he used his tribe to come to power!
    The Kenyan government is trying to benchmark what the Weyane is doing against it’s own people mercilessly and the country, and how in a day to day activities the conspiracy theories they apply to protect their power and to stay on chair safely until doomsday comes!

    – Sudan:
    Darfurian and Blue Nile issue and the struggle is there, even though declined in today’s Sudan. Weyane was supplying the blue Nile fighters officially and assisting with armed man power when they quarreled with Sudan government in connection with exe Egyptian President Hosni Mubarak assassination attempt Monday 27, June 1995 by Muslim extremists after he welcomed warmly by Weyane officials at Bole international airport and while he was on the way to Hilton Hotel AddisAbaba and when reached exactly at Bole Woreda 17 b/n the corridor of Kebele 23 and 20 which is to the right hand side means Kebele 23 region at specific area today opposite of DH Gada Tower or Friend ship building.
    The assassination attempt had conducted by the extremist group members who came from Sudan months ago and before the incident due date. Strangely enough, president Mubarak survived from the assassination attempt when gunmen ambushed his motorcade as he arrived in Addis Ababa, Ethiopia, for a summit of African leaders for the then OAU Summit today’s AUC on the above specific place. Since that time on president Mubarak never and ever returned to AddisAbaba until he toppled from the power by public uprising in Feb. 11, 2011. But, Marshal Abdel Fatah el-Sisi is doing it and came to Ethiopia for official visit more than two times after became president of Egypt June 9, 2014.

    So, two decades ago when Sudanese government refused to hand over the mastermind of the extremists who led the team, the attack and at last able to escape alive from the Ethiopian territory via Gondar by bus and he was the only one who escaped among the group members.
    As a result of this real story, the Weyane officials and the then militant intelligence inexperienced personnels were so crazy and got mad. That was the reason behind why Weyane was officially assisted the Blue Nile fighters by the time and now it’s a different story and turned in to secret and in underground way. This is the fact that related to strategical agreement and mutual benefit with Sudan government they reached!

    Although, Weyane is not in a position to assist officially the Blue Nile fighters for a positive Tit for Tat issue to both governments advantage/ don’t touch me I don’t touch you, and don’t throw the stone to me and I don’t throw the stone to you is the reality, but I know that some militant personnels of Blue Nile fighters moving secretly but freely in Addis Ababa and they do have strong relation with Weyane nominal Generals specially, with Samora Yenus today too!

    – Eritrea:
    It is the only country that has close door policy and applying against the tribalist Weyane regime. In relation to this, any person or groups considered as enemy of the regime are fled to Eritrea, and this country is the only nation that give fortification to freedom fighters and considered as safe heaven to any individuals or groups stand against the regime!
    The tribalist Weyane never has access to enter the Eritrean territory and snatch human life in the contemporary Horn Africa as they do in other neighboring countries in the horn many many times.

    In Eritrea tribalism is not an agenda at state level, but rather nationalism is the clear attribution of the government! I don’t mean democracy is flourishing in Eritrea but one thing we are sure 100% is, that there is no segregation between the People of Eritrea!
    On the other hand, in Ethiopia segregation between people in every aspect and ranking the citizens 1-7 is very normal because ruling elites never feel Shame and they don’t know even the term itself!

    3. Hippocratic at continent level!
    This is because, they do talk a lot about unity of Africa, they do run here and there, but this is totally pretending and they didn’t have that socialization. They engage every where without invitation, they abuse and use the UN and AU peacekeeping mission to generate income for their own sake and personal pocket!
    They do talk a lot about unity of Africa and regional integration politically, socially and economically while they don’t have legitimacy and legacy at home, and while they are working day and night to segregate the people at home and labeling their own people based on ethnicity and they issue ID card saying Amhara, Oromo, Tigre, Sidama, Somali, Gurage, Afar, Argoba,……, which is the replica of Hutu and Tutsi of Rwanda even though the Rwandan government eliminated that story because they knew that doesn’t worse and un functional!

    4. Cheater at international level!

    The tribalist Weyane government is also well known as the most cheating government at international level and this is in connection with election!
    They do talk a lot about democracy and they pretend as if, they work for democracy by only conducting periodical election every 5 years on May, and by letting plenty of paralyzed and nominal parties to talk only when election comes every 5 years but no democracy in substance at all because no rotation of power. This is just pretending and cheating the international community to collect fund from the western and to fill their personal pocket!
    With regard to democracy and rotation of power: These are inseparable and great attributions for the prevalence of democracy in a given country! This tribalist dictatorial regime; leave alone between parties in the country, no rotation of power between their own party colleagues unless death comes and take them one by one as it happened to their evil mastermind Meles Zenawi!
    They done need to leave the power peacefully rather, they yearn guns and bayonet to be toppled from the power!

    Our Dislike to the current regime of Ethiopia is not only because of it’s fascist, tribalist, totalitarian, authoritarian, tyrannical, selfishness, greedy, dictatorial and brutality behavior, but what pulls up our hate and put it in the climax, additionally what forced us to struggle and resist is the stance and the action of the regime against the sovereignty of the nation and the entity of the people in a very very unprecedented way in the 3000 years history of the country!!!

    Thank u for what you did and you are doing for us!

    The veneration that I have for you is in the climax no one pull it because no one reach it!

    SOURCES:

    Different types of questions require different sources of information. Information sources may be observations, people, speeches, or statements, documents, pictures, organizations, websites, etc. They may be primary sources, secondary sources, tertiary sources and so on.
    Information is the way to evidence and it’s the first instance of evidence! Information should be investigated properly to bring out the truth using technical and tactical issues by emphasizing neutrality!
    Therefore, my sources are based on the above facts:

    – Politics in the horn course manual.
    – Comparative Politics course manual.
    – Current affairs in the horn.
    – Education, and experience based knowledge.
    – Personal notes taken by the producer on timely manner and attempting to answer the 8 golden questions as much as possible to make the point clear and complete the information to the readers.
    – using perception power of the reality by the producer and tried do not step up on reality but followed the principle of holding the truth gently and with proud to move on!

    Prepared by: Seifeared Amdetsion

    Date: 5 March 2016

    AddisAbaba

    ETHIOPIA

    Footnote:
    read it solely and watch the video attentively!

  7. እይ ልደቱ የሚስማህ የለም አርፈህ ሆቴልህን ገንባ ፓልቲካውን ተወው ግዜህ አልፎብሃል ድሮስ ከወሎ ጎረቤት ይሻላል ባዶ ቤት ይባል የለ
    ዛሬ አማራን ክልል የሚመሩት የአንተው አገር ስዎች በእውቀታቸው ሳይሆን በአድር ባይነታቸው ተመርጠው የተቀመጡ መሆናቸውን እናውቃለን የተወለዱበት የወሎ መሪት ወደ ትግራይ ሲካለል ምንም ያላሉ ሆድ አደሮች ናቸው

  8. ቅንጅት አደረጃጀት ቀይሮ ሊመለሥ ይሆን? ማንያራገበውን እሳት በቆሎ ይጠብሣል።

  9. Seifeared Amdetsion appears to be shabia or shabia-lover, that is why he is lauding Eritrea as non-ethnic while Eritrea itself is trying to tribalize Ethiopian politics.
    It was also Eritrea that brought TPLF to Ethiopia. Eritrean cadres have been also working hard for decades to spread tribalism in Ethiopia using the internet as we can see on this site.
    Eritrea, like TPLF, is a ferenji worshipper with slave mentality.

  10. @Kuma Koricho,

    You have the right to hate an individual who committed him self for what he was thinking “right” or who had a very shroud personality, however you absolutely made it wrong when you generalized that all ethnics groups of this guy are “ridicules and can never be good neighborhoods” as you said it. This is where you made it wrong. This time the other world is talking about exploring water on Mars, you and your likes, talk about this rubbish.

  11. NYHETER
    idag 14:00
    Man hittad i container på Arlanda
    En levande man har hittats i en container på ett flygplan på Arlanda.
    Planet ska ha kommit från Etiopien.
    – Han var gömd i en tryckutjämnad fraktcontainer, så det fanns syre där inne, säger Carina Skagerlind på polisen.

    አንድ የ27 ዓመት ወጣት ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተጫነ ኮንቴይነር ውስጥ ተደብቆ ዛሬ ጥዋት March 6 ቀን ስቶክሆልም ስዊድን በህይወት ደርሶ ጥገኝነት ጠይቋል፡፡
    ይሄም ልጅ እንግዲህ የወያኔን ግፍና በደል፤ የነልደቱ አድርባይነትና ውሸት አንገፍግፎት ራሱን ነፃ ያወጣ ምስኪን ሀበሻ መሆኑ ነው፡፡

  12. Mr. Ledetu, the undercover Woyane agent must be scared to death that his masters the Meles/Sebhat led mafia group are near to their end. Mr. Ledetu, Make sure you have a legitimate Bank credit record evidences and proof of valid paper works for all your wealth for future reference. I’m just saying.

  13. Ledetu ( wirdetu- Keletu etc.) you are a living a living death as your friend Demeke Mekonen you both are traitors.

  14. This is the ugly side of our Ethiopian politics. At least we have to respect of this person’s a right to express his opinion. Then, if you look at what he said is whether it’s from his heart or not, he told the Ethiopian regime, what the truth on the ground is. That’s what the regime has to understand what’s going on at the grass root level instead of collecting the data from its useless and corrupted cadres. One thing this regime will never learn from its past experience is that, the public has spoken clearly its concerns but do not take this as a good bonus and correct its mistakes. Rather, waiting the rubbish information from the so called its own media outlets and cadres. Learn how the cadres information led you to your downfall of the 2005 election.
    So, based on this, I don’t need to blame someone always for what’s is happening in the past. Even though he did, time and events will teach him and could be changed.
    Therefore, let’s not mixed up things together.
    If we are going to judge this person, let’s focus not on the past but we have to see what’s is his suggestion to the solution of our country.
    Otherwise, it would be a long and exhaustive time we have to go to reach future we see our country will be.
    Let’s respect each other please.

  15. There will be no such a good thing expectation from the Sebhat/Meles gangs as the same is true to that a bird can never be hatched from a snake’s egg. Therefore; once a Banda always an Askari, the same applies to Ledetu as he is a Banda. What he is saying is just an old and expired tactic to mislead public then spare the dying his Banda mafia group bosses.

  16. Ante mindneh sew yemttechew what’s your contribution? I need answer new weys mawrat lmad honobih everyday talk wend lij aydeleh ende EPRDF LEFTO NEW EZIH YEDERESEW DO SOMETHING MAN OR SHUT UP UNTIL SOMETHING COME ANTE HEMOTIH FESWAL ATREBAM WENE BIS ENDE SET EVERYDAY TALKING WERADA

  17. አቶ ልደቱ አርቆ አሳቢና የሚመጣውን አደጋ ቀድሞ መተንበይ የሚችል ብሩህ አይምሮ ያለው ፖለቲከኛ ነው። የቅንጅትን አባላት እኮ እስራትና የፓርቲ መመታት እንደሚመጣ ቀድሞ ነግሯቸው ነበር ግን አልሰሙትም።

  18. Dear Kuma Qorcho, are you TPLF Cadere?.you are right to insult Ledetu Ayalew,but you can not insult all Wollo people. Do you know about wollo people social and political culture. It is the best people and The muslem and christian people live together without any differentiation.people are hero.Actually each and every ethnic people will have a bad guy like Ledetu. EXAMPLE, Mr. Wodewoson Kebede from Gojam he is still TPLF member and killed Amhara peole,even he do not want to be a member of the socalled BEHADIN. Do you remember the guy who received money from TPLF to kill our hero Angargachew who is from Gondar.We can call many people every ethenic and region,but they are different from people. please do not insult wollo people. I know your name is a fake.may be your are TPLF OR HODAM AMARA OR Hodam Oromo.

  19. @ Tenes Tatek Tsena Tewaga
    @ Seifeared Amdetsion

    ” This is just pretending and cheating the international community to collect fund from the western and to fill their personal pocket! ”

    Saying “cheating the international community” , i think the satanic ferenjis are meant here, is naive at best (that means we are assuming ignorance about the satanic nature of ferenjis) or a foolish attempt to mislead readers at worst.

    The reality is the satanic ferenjis in Washington DC, London, Berlin and elsewhere know very well what their puppet TPLF is doing. The satanic ferenjis have their ferenji and Ethiopian spies in Addis Abeba and Ethiopia, and they monitor TPLF’s communications 24/7 or 24 hours in 365 days. The satanic ferenjis are not being “cheated” by TPLF, but they want to play the innocent because they dont want to be held accountable for the horrible crimes they have been committing against Ethiopians the last 25 years as the supporters of TPLF.

    We can see on the map below that CIA & NSA have a spy center in Addis Abeba, in the USA embassy. They monitor the government, the general public, the opposition and the civil society in Ethiopia.
    https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/8/8c/SCSGlobalPresence.png

  20. ከእባቦች የዕርግብ እንቁላል፤…

    ዛሬም ከእባቦች የዕርግብን እንቁላል፤
    በአስተዳደር አሁን ኑ እናግኝ ይላል።
    በወቸገሉ ልብላው ልሳኑ ተቃኝቶ፤
    የሥልጣን ጅማቱን ከጅቦች አግኝቶ፤
    ድል እንደይማይጣልን ከርሱን እየሞላ፤
    ወኔ አሰልቦ ስንቱን ሰው አስቀላ።
    ልደቱ፤
    የክህደቱ።
    ሃያ አምስት  ዓመታት ባንዳ ሆነህ ነበር፤
    ልብ በለው ታሪክን ተደብቆም አይቀር።
    ሕዝብ የረሳው መሰለህ፤
    ልቡን በደም አቁስለህ።
    ጉንጭህን የሞላው:-ሁለት ሙዳ ሥጋ፤
    የሙታን መሆኑን በፍጹም አትዘንጋ።
    ወፈርኩ ብለህ አታስብ፤
    ደም አለው የግፍ ስብ።
    እናም በበደል ስሌት ቆንጥረህ የምትጽፈውም፤
    ሥልጣንን ለመመንተፍ ነው፤
    ሕዝብን አታለህ ያውም።
    ባንዳዬ ስማኝ:-ሁሉም በመክዳት ያውቅሃል፤
    ይልቅ ይቅርታ ልትጠይቅ ሕዝቡ ጊዜን ሰጥቶሃል።
    ስለዚህ ብዙ አትጻፍ ማንነትህን ታሪክ መዝግቧል፤
    በኢትዮጵያውያን ጭፍጨፋ;-
    ጉጅሌው ባንተ ክህደት ጠግቧል።
    ስለዚህ ሆዶ “አስተዳደር ነው” የምትለውም፤
    ሥልጣኑን እንዲሰጡህ ነው:-
    ሕዝብ ልታታልል ያውም።
    አይ ልደቱ፤
    አለ በክህደቱ።
    ዛሬም ከእባቦች የዕርግብ እንቁላል፤
    በአስተዳደር አሁን ኑ እናግኝ ይላል።
    ባንዳዬ ስማኝ በክህደትህ ሁሉም ያውቅሃል፤
    ገብቶሃል? ? ?…
    ይልቅ …….
    ይቅርታ ጠይቅ !!!!!!
    ያኔ ስንቴ ከድተሃል?????
    ሕዝቡ ጊዜ ሰጥቶሃል።
    የትኛው ሐቅ ይሻልሃል? ? ?…..
    ዛሬም በደም መሃል  ቆመሃል????…..
    የደም ጩኸት ይሰማሃል???….
    ዋይ ዋይ ይላል ደም ይበላል።
    አንተ ግና ከጉጅሌ ወግነህ፤
    እናውቃለን አንተማ ነህ።
    ምን ያህል ብር በላህበት፣በደም ጉርሻ ጠቅልለህ፤
    ስንቴ ደማ ልብህ ውስጡን፣ ሕሊናህን አምግለህ።
    አይበቃህም አልታየህም፣የሙታን ጣዕር አይሰማህም? ? ?…….
    እንደው ቢቀር ባዶ እጆች ሲገደሉም አያምህም????…
    ተው አታስብ አትራብም፤የደም ፍትፍት ብላ ቀጥል፤
    በምላስህ እንደኖርከው:-
    ሞትክን እየው በቁም ስቅል።
    እናም ይልቅ …….
    ይቅርታ ጠይቅ !!!!!!

  21. “Ke wallo gorebet yishala bado bet ” This is wat u said.But i say ..I know why u hate them.i think that ther oromo blood musr disturbing u.But sorry,i love wallo.i love ras Ali,i love Itege menen his grand daughter,l love iyasu the son of Ras Ali,i love Workit the most, (as any oromo couragess waman),the prominent warrior Who beat yohanis and released minilik from prison.And mMinilik the same night hit the road none stop running much faster than Abebe Bikila to Anko’s ber where he started paying the favor she has done for him by his lebensraum dream accompanied by oromo blood I wish she could return him back where she found him.U know the rest.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*