አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠበት

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠበት

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በሽብር ተጠርጥሮ ላለፉት ሁለት ወራት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጥቶበታል፡፡
ዛሬ የካቲት 15/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ለ3ኛ ጊዜ የቀረበው ዮናታን ተስፋየ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ በዚህም በቀጣይ መጋቢት 13/2008 ዓ.ም ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
እስካሁን የተከሳሽነት ቃሉን እንዳልሰጠ ለችሎት የገለጸው ዮናታን በእስር በሚገኝበት ማዕከላዊ ከጠበቃው ጋር እንዲነጋገር እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከታሰረ ጊዜ ጀምሮ አንድም ቀን ጠበቃውን አግኝቶ ለማነጋገር እንዳልቻለ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁንም ከጠበቃው ጋር ሳይመካከር ቃሉን ለመስጠት እንደማይፈልግ ለችሎት አስረድቷል፡፡
የአቶ ዮናታንን ችሎት ለመከታተል በስፍራው የተገኙ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ጋዜጠኞችና የዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ ተወካዮች ችሎቱ በዝግ በመታየቱ ችሎቱን መከታተል አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

Negere Ethiopia's photo.

4 Comments on “አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠበት”

  1. [email protected] said it was better before weyanes.hhhhh you want the ortodox time.no more ethiopia is ortodox and ethiopia is over.all the habesha are the killer from minelik era up to weyane.bye bye,ethiopia is almost dead.RIP emye ethiopia.yes oromia is for oromo.

  2. ለመሆኑ ወያኔ አሳቡ ምንድን ነው?
    እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን ማዳከም ነው! እውነትም አዳክመዋታል ወደብ አልባም ሆናለች ወደብም አሉ ወያኔዎች ሸቀጥ ጥቅም የሌለው ነው ሸቀጥም እንደሚጠቅምና ሃብት መሆኑን ማሰቢያቸው አቁሞል
    ጎንደርንና ወሎን ግዛት ማጥበብ ለምን ተፈለገ?
    ባድሜን ለሻቢያ ተሰጠ ቆራን ለሱዳን ተሰጠ
    አሁን ደግሞ ጋምቤላን ለደቡብ ሱዳን ለመስጠት ዝግጅት አላቸው ለምን?

    ሳተናው አሊ
    ከኢትዮጵያ

  3. ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ከሆንክ ሽብርተኛ ትባላለህ በዘመነ ወያኔ። አይ ወያኔ/ ገ/ዳቢሎስ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*