ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ሆናለች::ለሕዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በክልሉ ሰፍረዋል::
ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ሆናለች::ለሕዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በክልሉ ሰፍረዋል::
#Ethiopia #Oromoprotests #EPRDF #OromiaIsWarZone #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው የሕዝብ ጭቆና በቃኝ ንቅናቄ ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ እስከ ምሽቱ ድረስ የቀጠለ ሲሆን ሕጻናት አዛውንት ወጣት ሳይለዩ የሚገድሉ እና የሚያፍሱ የአግኣዚ ሰው በላ ወታደሮች ጭፍጨፋቸውን ቀጥለዋል::ባልተተገበረ ሕገመንግስት ከለላነት አምባገነን ተግባራትን የሚፈጽመው የወያኔው ማፊያ ገዳይ አገዛዝ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመግደል እና በማቁሰል ላይ ይገኛል:: እምቢ ለነጻነቴ እምቢ ለመብቴ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ትግላቸውን ከበፊቱ በበለጠ አጠናክረው ቀጥለዋል::
በደንቢ ዶሎ ለሰላማዊው ሕዝቡ የአይሮፕላን መጣያ ዙ23 የጦርነት ነጋሪት የሚጎስመው አገዛዝ በሕዝብ ላይ ጠምዶ እየተንቀሳቀሰ ሲገኝ በየአከባቢው እንዲሁ ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ ወታደራዊ ካሚዮኖች ተሰማርተዋል::የመብቱን ጥያቄ ይዞ አደባባይ የወጣን ሕዝብ በጥይት መግደል ወንጀል መሆኑ ሲታወቅ ማንም ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ የሕወሓት መሪዎች ሊያውቁ ይገባል::ተቃውሞ በዛሬው እለት ከወለጋ እስከ ሃረርጌ ጉጂ ከሸዋ እስክ ኢሊባቦር ተስፋፍቶ ቀጥሏል::ወያኔ እንደለመደው በሚዲያዎቹ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ የሚገኝ ሲሆን ታማኝነት ያሌላቸ እጅግ አሳፋሪ ሃሰቶችን በሕዝብ ላይ እየረጨ ይገኛል::ድል ለጭቁን ሕዝቦች!!! #ምንሊክሳልሳዊ